ጁላይ 02, 2026
የዩናይትድ ስቴትስን 250ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ስናከብር እና የነጻነት ቀንን ስንዘክር፣ የዩናይትድ ስቴትስን 250ኛ ዓመት የምስረታ በዓል የሚያስታውስ እና የሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎችን የፈጠራ እና የአመለካከት ገጽታ የሚያንፀባርቅ በርካታ ድምጾችን፣ እና ስለ አንድ ሀገር ዜግነት” ይበልጥ ግንዛቤ ለማግኘት eBook ላይ ይቃኙ። ተማሪዎች በዘፈን፣ በግጥም፣ በስዕሎችና በዳንስ አማካኝነት አገራችንን በዚህ ደረጃ ለመቅረጽ የረዱትን ድምጾች፣ ልምዶች፣ እና ማህበረሰቦች አክብረዋል። eBook ይመልከቱ እና የተማሪዎቻችንን ታላቅ ተሰጥኦና ችሎታ ያድንቁ።
ከዚያም፣ በዚህ ቅዳሜና እሁድ በሞንትጎመሪ ካውንቲ ዙሪያ የነጻነት ቀን ዝግጅቶችን በማድረግ፣ ርችቶችን፣ ቀጥታ የሚቀርቡ የሙዚቃ ትርኢቶችን፣ እና ለቤተሰብ ተስማሚ የሆኑ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ በዓሉን ማክበር ይቀጥሉ። እዚህ እና እዚህ በመመልከት የበለጠ ይወቁ።
ለሠመር የተዘጋጀ ማለት የሠመር ወቅት ዕረፍት ጊዜዎን በአግባቡ ለመጠቀም የሚያስችልዎት መመሪያ ነው! በተለያዩ አዝናኝ እንቅስቃሴዎች የታጨቀ፣ የመማሪያ እድል እና ለቤተሰብ ጠቃሚ ግብዓቶች ያሉት ይህ ፕሮግራም በጥቂት ሳምንታት ውስጥ ትምህርት ከመጀመሩ በፊት የልጆችን አእምሮ ንቁ በማድረግ እንዲንቀሳቀሱ ለማድረግ የተነደፈ ነው።
ለዚህ ሳምንት በተለይ የቀረበ፦ ሂሳብ! የአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች የሂሳብ ክህሎታቸውን አእምሮን በማሠራት እንቆቅልሾችን በመፍታታት እና በማሳደግ፣ በማሻሻል፣ በሚቀጥለው ዓመት በሚደረገው ትምህርት ጥሩ ውጤት ማግኘት ይችላሉ። የመካከለኛ እና የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች IXL የክህሎት ማሻሻያ እቅድ ወይም በሥርዓተ ትምህርት ፓኬት በመጠቀም ጥልቅ የሒሳብ ስሌት ትምህርት መቅሰም እና የፕሮብሌም አፈታት ክህሎቶቻቸውን በማዳበር ላይ መስራት ይችላሉ።
ለመጀመር ተዘጋጅተዋል? ይበልጥ ያንብቡ።
አዲሱ ተማሪ የትምህርት ቦርድ አባል (SMOB) ልዑል ዳዊት ሰኞ፣ ጁላይ 6 ከቀኑ 4 p.m. ላይ ሹመቱን ሲረከብ ይመልከቱ። ቦርዱ በኖርዝውድ ሁለተኛ ደረጃ ት// ቤት ተማሪ የሆነውን ልዑል ዳዊትን ለ 2026–2027 የትምህርት አመት 49ኛው ተማሪ የትምህርት ቦርድ አባል - SMOB አድርጎ በይፋ ይሾማል። ላዑል የሚተካው ከሞንትጎመሪ ብሌር ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመራቂ የሆነችውን ተማሪ የትምህርት ቦርድ አባል - SMOB አኑቫ ማሉን ነው። በተጨማሪም ቦርዱ ማሉ ላበረከተችው አስደናቂ አስተዋጽኦ እና አመራር በሥነ ሥርዓቱ ላይ እውቅና ይሰጣል።
MCPS አርብ ጁላይ 17 ከጠዋቱ 10 a.m.- 1 p.m. ድረስ ለአውቶቡስ ሾፌሮች የስራ አውደ ርዕይ ያዘጋጃል። የሥራ አውደ ርዕዩ የሚካሄደው በሼዲ ግሮቭ ትራንስፖርት ዴፖ ሲሆን አድራሻው የሚከተለው ነው፦ Shady Grove Transportation Depot, 16651 Crabbs Branch Way in Rockville ፍላጎት ያላቸው ተወዳዳሪዎች በራሪ ወረቀቱ ላይ ያለውን QR ኮድ እንዲቃኙ እና MCPS Careers ድረ ገጽ ላይ መገለጫ እንዲሞሉ ይጠየቃሉ። ለተጨማሪ መረጃ 240-740-6080 ይደውሉ፤ ወይም ኢሜል ይላኩ። ተጨማሪ ግንዛቤ ያግኙ
የመኸር/ፎል የስፖርት ማጣሪያ ምዝገባ ParentVue ሰኞ፣ ጁላይ 13 እኩለ ቀን ላይ ይከፈታል። የመኸር/ፎል አትሌቲክስ ቡድኖች ረቡዕ፣ ኦገስት 12 ላይ የማጣሪያ ልምምዳቸውን ሊጀምሩ ይችላሉ። ተማሪዎች ለሠመር ማጣሪያ ልምምድ የተመዘገቡ ከሆነ፣ ለመሳተፍ ብቁ ለመሆን በመኸር/ፎል ስፖርት ላይ መመዝገብ አለባቸው። ለተለየ መረጃ በአካባቢዎ ትምህርት ቤት የሚገኘውን አሰልጣኝ ያነጋግሩ።
ተጨማሪ መረጃ ይፈልጋሉ? ስለ ምዝገባ፣ ስለ ብቁነት መስፈርቶች፣ የማጣሪያ ጊዜዎች እና አስፈላጊ ቀናትን ዝርዝሮች ለማግኘት የትምህርት ቤትዎን የአትሌቲክስ ዳይሬክተር ያነጋግሩ።
ስቴድዊክ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለመማሪያ ክፍሎች ድጋፍ $5,000 የገንዘብ ድጋፍ አግኝቷል፡ AdoptAClassroom ጋር ባለው ቀጣይነት ያለው አጋርነት፣ የበርሊንግተን መደብሮች በመላ አገሪቱ ያሉትን የመማሪያ ክፍሎች በገንዘብ ለመደገፍ እና አስፈላጊ የትምህርት ቤት አቅርቦቶችን ለማሟላት ይረዳል።
ይህን ድረገጽ ይጎብኙ፦ MCPS homepage
240-740-3000 ይደውሉ፦ ከሰኞ እስከ አርብ ጠዋት 7:30 a.m. እስከ 5 p.m. ሠራተኞች በእንግሊዝኛ እና በስፓንሽኛ ጥሪዎችን ስለሚቀበሉ በስልክ ቁጥር (240-740-2845) ይደውሉ።
የኢሜይል እና የጽሁፍ መልዕክቶችን እና MCPS የሚያቀርባቸውን ዘገባዎች ያንብቡ።
MCPS የማህበራዊ ሚድያ ገጾቻችንን ይከታተሉ፦ x.com/mcps / facebook.com/mcpsmd / instagram.com/mcps_md facebook.com/mcpsespanol / x.com/MCPSEspanol / instagram.com/mcpsenespanol
ኢሜሎች እና የጽሑፍ መልእክቶች/ማሳሰቢያዎች እንዲደርስዎት ይመዝገቡ፤ የእርስዎ ParentVue ወቅታዊ መሆኑን ያረጋግጡ
MCPS ኬብል ቻነሎችን ይከታተሉ፦ Comcast 34 (1071 HD)፣ Verizon 36 ወይም RCN 89
የገቢያቸው ሁኔታ ብቁ ለሚያደርጋቸው ቤተሰቦች የቅድመ መዋዕለ ሕፃናት እና ሄድ ስታርት ምዝገባ ክፍት ነው
የትምህርት ቤቶች ቀን መቁጠርያ/ካለንዳር
የወላጆች መገልገያ/ሪሶርስ ገጽ
ዘገባዎች፤የመረጃ ገፅ/Noticas en Español
የቅርብ ጊዜ ፎቶግራፎች ክምችት ይመልከቱ
MCPS TV ቪዲዮ
MCPS TV español