
አበይት ጉዳዮች
ጁላይ 09, 2026
|
|
|
የሞንትጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ ትምህርት ቤቶች (MCPS) አዲሱን ተማሪ የቦርድ አባል፡ ልኡል ዳዊትን ይተዋወቁ |
|
የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ፣ በኖርዝውድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጁንየር ተማሪ የሆነውን ልኡል ዳዊትን፣የቦርዱ 49ኛ የተማሪዎች ተወካይ የቦርድ አባል (SMOB) ተደርጎ በይፋ ተሹሟል። በትምሕርት ቦርዱ ውስጥ የተማሪዎች ተወካይ እንደመሆኑ መጠን፣ ዳዊት በመላው ሞንትጎመሪ ካውንቲ የሚገኙ ከ 155,000 በላይ ተማሪዎችን ፍላጎትና አመለካከት ይወክላል። ይበልጥ ያንብቡ።
|
|
|
|
|
|
ሜሪላንድን የምትወክለውን ተማሪ ሎሬና ዉ/Lorena Wu ይተዋወቁ፡ |
|
በፑልስቪል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጁንየር ተማሪ የሆነችው ሎሬና ዉ (Lorena Wu)፣ በሜሪላንድ ገቨርነር ከተሰየመች በኋላ፣ ጁላይ 1 ቀን የትምሕርት አመት 2026-2027 የሜሪላንድ ተማሪዎችን በመወከል የቦርድ አባል (SMOB) በመሆን ቃለ መሃላ ፈጽማለች። ዌስ ሙር በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ። ይበልጥ ያንብቡ.
|
|
|
|
|
|
ወደ ትምህርት ቤት የመመለሻ ጊዜ አውደ ርዕይ ኦገስት 22 ይጀመራል፡ ለእርስዎ የሚስማማዎት ዝግጅት ይኖራል! |
|
MCPS የትምሕርት አመት 2026–2027 ለመጀመር ቅዳሜ፣ ኦገስት 22፣ ስድስት ሪጅናል "ወደ ትምህርት ቤት የመመለስ አውደ ርዕይ" (Back-to-School) ዝግጅቶችን ያካሄዳል። በእያንዳንዱ ዝግጅት ላይ ቤተሰቦች የሚያስፈልጋቸውን ነገሮች በቀላሉ የሚያገኙባቸው እና ጥያቄዎችን በመመለስ አስፈላጊውን ድጋፍ ሊሰጡ ከሚችሉ ባለሙያዎች ጋር በቀጥታ የሚገናኙባቸው የተደራጁ ቦታዎች ይኖራሉ። የማህበረሰብ ድርጅቶች፣ የመንግስት ተቋማት/ኤጀንሲዎች፣ እና ከትምህርት ሰዓት ውጪ አገልግሎት ሰጪዎችም ያሉትን ሪሶርሶች፣ የተለያዩ እድሎች፣ እና አገልግሎቶችን ለማስተዋወቅ በሥፍራው ይገኛሉ። ቀኑን ይበልጥ አስደሳች ለማድረግ፣ እያንዳንዱ ኤግዚቢሽን ለቤተሰብ ተስማሚ የሆኑ እንቅስቃሴዎችን፣ ስጦታዎችን እና አዝናኝ ነገሮችን ያካትታል። ስለ አስተናጋጅ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እና ዝግጅቶቹ ስለሚቀርቡባቸው ጊዜያትተጨማሪ ያንብቡ።
|
|
|
|
|
|
ከእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል በስተጀርባ የሚከናወን ሥራ |
|
የትምህርት ቤት መክፈቻ ቀን (ማክሰኞ፣ ኦገስት 25) ከመድረሱ በፊት ከሰባት ሳምንታት ያነሰ ጊዜ ብቻ የቀረ ሲሆን፣ ከዚያ በፊት ልንወጣቸው የሚገቡ በርካታ ተግባራትም አሉን። ከመማሪያ ክፍሎች ማጽዳትና አውቶቡሶችን ከማደስ ጀምሮ እስከ ሰራተኞችን ማሰልጠንና የጊዜ ሰሌዳዎችን ዕቅድ ማዘጋጀት ድረስ፣ MCPS ተማሪዎች ስለሚመለሱበት ጊዜ እየተዘጋጀ ነው። ይበልጥ ያንብቡ።
|
|
|
|
|
|
ለሠመር የተዘጋጀ፡ ሳይንስን እና ማህበራዊ ጥናቶችን ቅኝት ያድርጉ |
|
ለሠመር የተዘጋጀ ማለት የሠመር ወቅት ዕረፍት ጊዜዎን በአግባቡ ለመጠቀም የሚያስችልዎት መመሪያ ነው! በተለያዩ አዝናኝ እንቅስቃሴዎች የታጨቀ፣ የመማሪያ እድል እና ለቤተሰብ ጠቃሚ ግብዓቶች ያሉት ይህ ፕሮግራም በጥቂት ሳምንታት ውስጥ ትምህርት ከመጀመሩ በፊት የልጆችን አእምሮ ንቁ በማድረግ እንዲንቀሳቀሱ ለማድረግ የተነደፈ ነው። በዚህ ሳምንት፣ በሳይንስ እና በማህበራዊ ጥናት ላይ ትኩረት እናደርጋለን። ይበልጥ ያንብቡ።
|
|
|
|
|
|
በዚህ መኸር (ፎል) ወቅት በስፖርት እንቅስቃሴዎች ይሳተፉ፤ ሶስት የስፖርት ማዕከላት ነጻ የጤና ምርመራ ያደርጋሉ። |
|
ለከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመኸር (ፎል) ወቅት ስፖርቶች የማጣሪያ ውድድር (tryouts) ምዝገባ ሰኞ፣ ጁላይ 13 ቀን ከሰዓት በኋላ ParentVue ላይ ይከፈታል። የመኸር/ፎል አትሌቲክስ ቡድኖች ረቡዕ፣ ኦገስት 12 ላይ የማጣሪያ ልምምዳቸውን ሊጀምሩ ይችላሉ። ተማሪዎች ለሠመር ማጣሪያ ልምምድ የተመዘገቡ ከሆነ፣ ለመሳተፍ ብቁ ለመሆን በመኸር/ፎል ስፖርት ላይ መመዝገብ አለባቸው። ለመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት (Middle school) ስፖርት እንቅስቃሴዎች ምዝገባ ሰኞ፣ ኦገስት 10 ይከፈታል። 2026-2027 የትምህርት አመት አዲስ ለውጥ እንደመሆኑ፣ የስድስተኛ ክፍል ተማሪዎች በትምህርት ቤቶች መካከል በሚደረጉ የስፖርት ውድድሮች ላይ የመሳተፍ ብቃት ይኖራቸዋል። የሞንትጎመሪ ካውንቲ ሞባይል የጤና ክሊኒክ ተማሪዎች ከመኸር (ፎል) ወቅት በፊት የሚያስፈልጋቸውን የአትሌቲክስ አካላዊ ብቃት እንዲያጠናቅቁ በዚህ ሠመር ሶስት ነፃ የስፖርት አካል ምርመራ አገልግሎት ይሰጣሉ። ይበልጥ ያንብቡ።
|
|
|
|
|
|
"Drive for Supplies" ወደ ትምህርት ቤት ለመመለስ አስፈላጊ ቁሳቁሶችን ለቤተሰቦች ይሰጣል። |
|
ዓመታዊው የቁሳቁስ ማሰባሰብ ዝግጅት (Drive for Supplies) አርብ፣ ጁላይ 24፣ ከጠዋቱ 9 a.m.–2 p.m. በጌትስበርግ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ይካሄዳል። አድራሻ፦ Gaithersburg High School, 101 Education Blvd. ጌትስበርግ። ቤተሰቦች ለትምህርት ቤት የሚጠቅሙ ቁሳቁሶችን በነፃ ማግኘት ይችላሉ፣ እንዲሁም UpCounty Hub እና Rise-N-Shine Foundation የምግብ መያዣዎችን ለቤተሰቦች ያሰራጫሉ። በተጨማሪ SNAP ጥቅማጥቅሞችን ለማግኘት፣ ለነጻ እና በቅናሽ ዋጋ ለሚቀርቡ ምግቦች እንዲሁም ለሠመር የድጋፍ ፕሮግራሞች ለመመዝገብ እድሎች ይኖራሉ።
|
|
|
|
|
|
በቅድመ-መዋእለ ህጻናት እና በሄድ ስታርት ለማስመዝገብ አሁንም ጊዜ አለ |
|
ልጅዎ እስከ ማክሰኞ፣ ሴፕቴምበር 1, 2026 ድረስ 4 ዓመት ዕድሜ ይሆነዋል/ይሆናታል? ለትምህርት አመት 2026-2027 የቅድመ-መዋዕለ ሕፃናት እና የሄድ ስታርት ፕሮግራሞች ነፃ ምዝገባ ክፍት ነው። በአንዳንድ የሞንትጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ ትምሕርት ቤቶች (MCPS) እና በግል የቅድመ ትምህርት አገልግሎት ሰጪዎች በገቢ ሁኔታ ምክንያት ብቁ ለሚሆኑ ቤተሰቦች ቦታ አሁንም ይኖራል። ለመመዝገብ፦ ፣ ቤተሰቦች በሮክቪል የሚገኘውን Pre-K/Head Start office at 4910 Macon Road in Rockville ቢሮ ከሰኞ እስከ አርብ፣ ከጠዋቱ 9 a.m.-4 p.m. ድረስ መጎብኘት ይችላሉ።
ለተጨማሪ መረጃ፣ MCPS Pre-K/Head Start ድረ-ገጽ ይጎብኙ ወይም 240-740-4530 ይደውሉ።
|
|
|
|
|
|
ለውጥ አድርጉ — SSL ሰዓቶችን አግኙ |
|
አላማ ያለው እና የሚደሰቱበት የሠመር ወቅት ፕሮጀክት ይፈልጋሉ?
ደህንነቱ የተጠበቀ ዓለም አቀፍ የመንገድ ጉዞ ማህበር እና የሞንትጎመሪ ካውንቲ ሪጅናል የተማሪዎች አመራር ማህበር "The Association for Safe International Road Travel and the Montgomery County Regional Student Government Association" ስለ መንገድ ደህንነት እና በመንገድ ላይ እራስዎን እና የሌሎችን ደህንነት እንዴት መጠበቅ እንደሚችሉ ላይ ያተኮረ የህዝብ አገልግሎት ማስታወቂያ ውድድር ስፖንሰር እያደረጉ ነው። መስፈርቶቹን የሚያሟላ ጥራት ያለው PSA የሚያቀርቡ የመካከለኛ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች 10 የተማሪ አገልግሎት ትምህርት (SSL) ሰዓት ያገኛሉ እንዲሁም የአማዞን የስጦታ ካርድ የማሸነፍ እድል ይኖራቸዋል። ዝርዝር መረጃ እዚህ ያግኙ እና ማመልከቻ ያስገቡ። የመጨረሻ ቀነገደብ፦ እሁድ፣ ኦክቶበር 4 ከምሽቱ 11፡59 p.m.ነው።
ሌሎች በጁላይ ወር የሚገኙ SSL ዕድሎች ዝርዝር እዚህ አለ!
|
|
|
|
ማሳሰቢያ |
|
ለአውቶቡስ ሾፌሮች የስራ ኤግዚቢሽን፡ አርብ፣ ጁላይ 17፣ ከጠዋቱ 10 a.m.- 1 p.m. ይካሄዳል። የሥራ አውደ ርዕዩ የሚካሄደው በሼዲ ግሮቭ ትራንስፖርት ዴፖ ሲሆን አድራሻው የሚከተለው ነው፦ Shady Grove Transportation Depot, 16651 Crabbs Branch Way in Rockville ለተጨማሪ መረጃ 240-740-6080 ይደውሉ፤ ወይም ኢሜል ይላኩ።
|
|
|
|
|
|
ከጓሮ አትክልት እስከ አረንጓዴ አካባቢ የለውጥ አራማጅ ቡድኖች፡ የሞንትጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ ትምህርት ቤቶች (MCPS) ተማሪዎች ስለ ተፈጥሮ የአካባቢ ጥብቃ ተጽዕኖ ይፈጥራሉ |
|
በዚህ ዓመት ከግማሽ በላይ የሚሆኑት MCPS ትምህርት ቤቶች የሜሪላንድ ግሪን ትምህርት ቤት መሆን ምን ማለት እንደሆነ ማሳየት እንደቻሉ አውቀዋል? ከማህበረሰብ ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ኢንጂነሪንግ፣ ስነጥበብ እና ሂሳብ (STEAM) ምሽቶች ጀምሮ እስከ በተማሪዎች የተገነቡ ክፍሎች ድረስ፣ ትምህርት ቤቶች በተፈጥሮ አካባቢ ጥበቃና አያያዝ ላይ አዎንታዊ ተጽእኖ ለማሳደር እና ለመሳተፍ የፈጠራ መንገዶችን አመቻችተዋል። ተጨማሪ ይወቁ እና በተነሳሽነት ይሳተፉ።
|
|
|
|
|
|
ከእኛ ጋር ግንኙነትዎን ይቀጥሉ
|
|
|
|
|
|
|
|
|
|
|
|
|
|
በዚህ አድራሻ ኢሜል ያድርጉልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org
|
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ
|
|
©1995–2026 Montgomery County Public Schools
|
|