MCPS የሳምንቱ ወቅታዊ መረጃ — መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች
MCPS መለያ አርማ

የሠመር እትም

አበይት ጉዳዮች

ጁላይ 30, 2026

 
English / español / 中文 / français / Português / 한국어 / tiếng Việt / አማርኛ/Amharic
 
  በብሔራዊ የምሽት እለት ይቀላቀሉን! MCPS ጋር ማህበረሰቡን ያክብሩ

ማክሰኞ፣ ኦገስት 4 በሚካሄደው የብሔራዊ ምሽት መውጫ ቀን MCPS ይቀላቀሉ፦

  • Montgomery College, Germantown Campus, 20200 Observation Drive, Germantown, 5:30–8 p.m.
  • Mt. Calvary Baptist Church, 608 North Horners Lane, Rockville, 6–8 p.m.

ብሔራዊ ውጪ የማምሸት ፕሮግራም ለማህበረሰብ አጋሮች እውቅና እና አክብሮት ይሠጣል፣ እና የመኖሪያ ሰፈሮች የበለጠ ደህንነታቸው የተጠበቀ እና ሳቢ የመኖሪያ አካባቢ እንዲሆኑ ለማድረግ ወዳጅነትን ያጠናክራል። ዝግጅቶቹ ዝናብ ወይም ብራ ቢሆንም ይካሄዳሉ፣ ምግብ የሚያከፋፍሉ ተሽከርካሪዎች ይኖራሉ፣ በአካባቢው ሻጮችን እና ለሁሉም ዕድሜ አስደሳች እና አዝናኝ እንቅስቃሴዎችን ያካትታሉ። የሞንትጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ ትምህርት ቤቶች (MCPS) ሰራተኞችን ለማግኘት፣ መገልገያ ቁሳቁሶችን ለመውሰድ እና ከእኛ ጋር ለማክበር ከጠረጴዛዎቻችን አንዱን ይጎብኙ። 

 
  የትምህርት ዓመቱን ለመቀበል አመቺ የሠመር ወቅት እነሆ!
  • በሠመር ትምህርት ቤት ከእኛ ጋር ለቆያችሁ ሁሉ፣ ስለ ብርቱ ስራችሁና ትጋታችሁ ሁሉ እናመሰግናለን። የሠመር ትምህርት ቤት የመጨረሻ ቀን ሐሙስ፣ ኦገስት 6 ነው። በሠመር ትምህርት ቤት ምረቃ ወቅት ያከናወኗቸውን ስኬቶች ሁሉ ኦገስት 12 ከጠዋቱ 10 a.m. ላይ በፔይንት ብራንች ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እናከብራለን። 
  • ወደ ሙአለህፃናት፣ 6ኛ፣ እና 9ኛ ክፍል ለሚገቡ፣ ለሞንትጎሞሪ ካውንቲ የህዝብ ት/ቤቶች (MCPS) አዲስ ለሆኑ እና በመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ወደ 3ኛ ክፍል ለሚገቡ የትምህርት ቤቶች የመጀመሪያ ቀን ሰኞ፣ ኦገስት 24 ነው። የሽግግር ቀን ተማሪዎች ከአዳዲስ የትምህርት ቤት አካባቢዎች፣ ከዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎች እና ከሚጠበቁባቸው ነገሮች ጋር እንዲተዋወቁ በመርዳት ላይ ያተኮረ በመሆኑ በትምህርት ቤቶች ውስጥ ቢውሉም የክፍል ትምህርት-የማይሰጥበት ቀን ነው። ማክሰኞ፣ ኦገስት 25 ላይ የትምህርት ቤቶች የመጀመሪያ ቀን ከመጀመሩ በፊት ርዕሰ መምህራንን፣ የት/ቤት ሕንፃዎች እና ከክፍል ጓደኞቻቸው ጋር ይገናኛሉ።
 
  በዚህ ዓመት አዲስ የገቡ ተማሪ ከሆኑ —ለሁሉም ተማሪዎች ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው ደወል ክፍል ውስጥ የእጅ ስልክ መጠቀም አይፈቀድም።

MCPS በዚህ የትምህርት አመት ተማሪዎች በክፍል ውስጥ ትምሕርታቸው ላይ ትኩረት እንዲሰጡ እና እርስ በርስ እንዲገናኙ የሚያግዝ አዲስ የሞባይል ስልክ ደንብ ተግባራዊ ያደርጋል። በትምህርት ቀን ከመጀመሪያው ደወል እስከ መጨረሻው ከት/ቤት የሚለቀቁበት ደወል እስኪደወል ድረስ — ሁሉም የግል ሞባይል ስልኮችና ተንቀሳቃሽ የኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎች (በምክንያት ከሚፈቀድላቸው ጥቂቶች በስተቀር) በሁሉም የትምሕርት ክፍሎች በእጃቸው ይዘው እንዳይቀመጡ ይደረጋል። ይህ እርምጃ ተማሪዎች በትምሕርት ክፍል ላይ የሚያሳዩትን መስተጓጎል እንደሚቀንስ እና በመማር ላይ እንዲያተኩሩ እንደሚያግዝ ይጠበቃል። በሚቀጥለው ሣምንት ተጨማሪ መረጃ እናጋራለን

 
  የመረጃ መመሪያ ቤተሰቦችን ከአስፈላጊ የድጋፍ አገልግሎቶች ጋር ያገናኛል

MCPS የልዩ ድጋፍ አገልግሎቶች ክፍል ለቤተሰቦች የማህበረሰብ ሪሶርስ መመሪያ አዘጋጅቷል። መመሪያው በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የትምህርት ቤት እና የማህበረሰብ ሪሶርሶችን/መገልገያዎችን ዝርዝር ያካትታል፤ ከእነዚህም ውስጥ የጤና አጠባበቅ እና የአእምሮ ጤና አገልግሎቶች ተደራሽነት፤ በምግብ፣ በልብስ፣ በቤት ዕቃዎች፣ በመኖሪያ ቤት እና በመገልገያዎች ስለሚደረግ ድጋፍ፤ የወጣቶች ልማት እና ካውንስሊንግ፤ የቤት ውስጥ ጥቃት፤ የሥራ ግብረ ኃይል፤ ትምህርት እና የቴክኖሎጂ፤ ዓለም አቀፍ ቤተሰቦች እና ሌሎችንም ያካትታል።

በሚከተሉት ቋንቋዎች መመሪያውን ያንብቡ፦ English | Spanish | French | Chinese | Vietnamese | አማርኛ/Amharic | Korean | Portuguese.

 

 
  ወደ ትምህርት ቤት የመመለሻ ትርኢት ላይ እንገናኝ!

በጥቂት ሳምንታት ውስጥ ወደ ትምህርት ቤት እንመለሳለን! የመጀመሪያው ደወል ከመደወሉ በፊት፣ የሞንትጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ ት/ቤቶች (MCPS) ባዘጋጃቸው ስድስት ሪጅናል ወደ ት/ቤት የመመለሻ ትርኢቶች ላይ ይቀላቀሉን።

ትምህርት ቤት መመዝገብ ከፈለጉ፣ አስፈላጊ የሆኑ ክትባቶችን ወይም የጤና ምርመራዎችን ማግኘት ከፈለጉ፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ፣ የቴክኖሎጂ ድጋፍ ማግኘት፣ ስለ ትምህርት ቤት ምግቦች መረጃ ማግኘት፣ ስለ ትምህርት ቤት መተግበሪያዎች ማወቅ፣ የትምህርት ቤት አቅርቦቶችን መውሰድ፣ የጊዜ ሰሌዳዎችን መመልከት፣ ስለ ክፍያዎች ወይም IEP አገልግሎቶች ጥያቄዎችን መጠየቅ ወይም የማህበረሰብ መገልገያዎችን ማግኘት ቢያስፈልግዎት፣ የሚፈልጉትን ሰዎች እና አገልግሎቶች ሁሉንም በአንድ ቦታ ያገኛሉ። ከትምህርት ቤትዎ ቡድን፣ እና ከማህበረሰብ አጋሮች ጋር መገናኘት እና ለቤተሰብ ተስማሚ በሆኑ እንቅስቃሴዎች መደሰት ይችላሉ።

ከዝርዝሩ ላይ ትምህርት ቤትዎን ያግኙ እና በሪጅን ወደ ትምህርት ቤት የመመለስ ትርኢት ላይ ይቀላቀሉን!

 
  የተማሪዎ ክትባቶች ወቅታዊ መሆናቸውን ያረጋግጡ

በሜሪላንድ ሕግ መሠረት፥ በሁሉም የሕዝብ ትምህርት ቤቶች የሚማሩ ተማሪዎች በተረጋገጠ የሕክምና ሁኔታ ወይም በሃይማኖት ምክንያት ክትባት እንዳይወስዱ የተፈቀደላቸው ካልሆኑ በስተቀር ሁሉም ልጆች/ተማሪዎች በልጅነታቸው የተወሰኑ ክትባቶችን እንዲወስዱ ይደነግጋል።

የሜሪላንድን የክትባት መስፈርቶችን ያላሟሉ ተማሪዎች አስፈላጊውን ክትባት እስኪያገኙ ወይም ተገቢ የሆነ ሰነድ እስኪያቀርቡ ድረስ ትምህርት ቤት እንዲከታተሉ አይፈቀድላቸውም። የጤና እንክብካቤ ከሚሰጥዎት ጋር ወይም ከአካባቢው የጤና ክሊኒክ ጋር ቀጠሮ ይያዙ፣ ወይም በኦገስት እና ሴፕተምበር ወር ነጻ የክትባት ክሊኒክ ይጎብኙ፣ ከሞንትጎመሪ ካውንቲ የጤና እና ሰብአዊ አገልግሎት መምሪያ (DHHS) አገልግሎት ይሰጣል።

ትምህርት ቤት ለመማር ስለሚያስፈልጉ ክትባቶች ይወቁ።

ስለ ልጆች ክትባቶች በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎች። 

 
  የቅዳሜ ትምህርት ቤት/Saturday School ምዝገባ ክፍት ነው

George B. Thomas Sr. Learning Academy, Inc. እና የቅዳሜ ትምህርት ቤት/Saturday School በመባል የሚታወቀው ት/ቤት ለ 2026–2027 የትምህርት አመት ምዝገባ ክፍት ነው። የቅዳሜ ትምህርት ቤት ከመዋእለ ህጻናት እስከ 12ኛ ክፍል የሂሳብ እና የእንግሊዝኛ/ቋንቋ ስነጥበብ የትምህርት ድጋፍ ፕሮግራሞችን ይሰጣል። በአካል እና ቨርቹዋል አማራጮች አሉት።

የቅዳሜ ትምህርት ቤት የመክፈቻ ጊዜ ሴፕቴምበር 19 ነው። የመጀመሪያው የማጠናከሪያ ትምህርት የሚጀመረው ሴፕቴምበር 26 ነው። ሥርዓተ ትምህርቱ ከሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ሥርአተ ትምህርት ጋር የተጣጣመ ከመሆኑም በላይ የሚያስተምሩት በሙያቸው የተመሰከረላቸው አስተማሪዎች ናቸው።

ከአስር አመታት በኋላ፣ የቅዳሜ ትምህርት ቤት በዚህ አመት ክፍያ ይጨምራል። ለነፃ እና የቅናሽ ዋጋ ምግብ (FARMS) ብቁ ለሆኑ ቤተሰቦች እስከ ማክሰኞ፣ ሴፕቴምበር 1 ድረስ ዓመታዊ ክፍያ $85 እና $40 ዶላር ይሆናል። ከሴፕቴምበር 1 በኋላ፣ FARMS ብቁ ለሆኑ ቤተሰቦች ክፍያው ወደ $100 እና $50 ይጨምራል። በጊዜ ቀደም ብለው ይመዝገቡ! ለአጠቃላይ መረጃ 301-287-8980 ይደውሉ።

ምዝገባ እና ተጨማሪ መረጃ

 
  ለሠመር ተይዟል፡ ሁለት ቋንቋ ተናጋሪ ሊተርሲ ይቀጥላል

MCPS ተመራቂዎች ከ 50 በላይ ቋንቋዎችን በመጠቀም የሜሪላንድ ሁለት ቋንቋ የመናገር ብቃት ማህተም "Maryland Seal of Biliteracy" ማግኘታቸውን ያውቃሉ? ይህ እውቅና በእንግሊዝኛ እና ቢያንስ በአንድ ሌላ ቋንቋ ችሎታ ያላቸውን ተማሪዎች አክብሯል። በዚህ ሠመር ከሞንትጎመሪ ካውንቲ የህዝብ ቤተ-መጻሕፍት ስብስብ በ 10 ቋንቋዎች መጽሐፍትን፣ ቪዲዮዎችን፣ እና ዲጂታል መገልገያዎችን/ሪሶርሶችን በመቃኘት ወይም ለሠመር ወቅት በተዘጋጀው የዲጂታል መመሪያ ውስጥ ካሉት አስደሳች የቋንቋ እንቅስቃሴዎች አንዱን በመጠቀም እነዚያን የቋንቋ ክህሎቶች ማዳበር ይቀጥሉ። ይበልጥ ያንብቡ 

 
  ማሳሰቢያ
  • የፎል ወቅት ስፖርቶች በቅርቡ ይጀምራሉ —የአካል ብቃት ምርመራዎን ያድርጉ እና ይመዝገቡ፡የ2026–2027 የውድድር ወቅት የፎል አትሌቲክስ ምዝገባ አሁን በParentVue ላይ ይገኛል። የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች MCPS አትሌቲክስ ውስጥ ከመሳተፋቸው በፊት ዓመታዊ የአካል ብቃት ምርመራ ማድረግ አለባቸው። የመኸር ወቅት/ፎል አትሌቲክስ ቡድኖች ረቡዕ፣ ኦገስት 12 ላይ የማጣሪያ ልምምዶችን ሊጀምሩ ይችላሉ። የሞንትጎመሪ ካውንቲ ተንቀሳቃሽ የጤና ክሊኒክ ነፃ የስፖርት አካላዊ እንቅስቃሴዎችን ለመጨረሻ የሚሰጠው ቅዳሜ፣ ኦገስት 8 ይሆናል። ስለዚህ እና ስለ መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የአትሌቲክስ ጨዋታ ተጨማሪ መረጃ እዚህ ይገኛል
  • የመዋዕለ ህጻናት ምዝገባ፡ ተማሪዎ እስከ ማክሰኞ፣ ሴፕቴምበር 1፣ 2026 ድረስ 5 ዓመት ይሞላዋል/ይሞላታል? ለሙሉ ቀን የመዋእለ ህጻናት ፕሮግራም ያስመዝግቡ።
  • የቅድመ መዋዕለ ህጻናት/ሄድ ስታርት ምዝገባ፡ ተማሪዎ እስከ ማክሰኞ፣ ሴፕቴምበር 1, 2026 ድረስ 4 ዓመት ይሞላዋል/ይሞላታል? በአንዳንድ የሞንትጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ ትምሕርት ቤቶች (MCPS) እና በግል የቅድመ ትምህርት አገልግሎት ሰጪዎች በገቢ ሁኔታ ምክንያት ብቁ ለሚሆኑ ቤተሰቦች ቦታ አሁንም ይኖራል። ለመመዝገብ፣ ከሰኞ እስከ አርብ፣ ከጠዋቱ 9 a.m.-4 p.m. ሮክቪል የሚገኘውን፦ Pre-K/Head Start office at 4910 Macon Road in Rockville ይጎብኙ። የበለጠ መረጃ ለማግኘት፦ 240-740-4530 ይደውሉ። 
  • የMCPS የወላጅ አካዳሚ የሽግግር ሪሶርሶች: ተማሪዎ በዚህ ፎል ወቅት መዋዕለ ህጻናት፣ መለስተኛ ደረጃ ትምህርት ወይም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ይጀምራል/ትጀምራለች? የMCPS የወላጅ አካዳሚ የሽግግር ወርክሾፕ ቅጂዎች እና ፕረዘንቴሽኖች ቤተሰብዎ ለመጪው ዓመት በተግባራዊ ምክሮች፣ ሪሶርሶች እና መረጃዎች እንዲዘጋጁ ለመርዳት ዝግጁ ናቸው።
  • የተማሪ አገልግሎት ትምህርት፡በመንገድ ደህንነት ላይ ለሚደረገው ለዚህ የPSA ውድድር ጽሁፍ ያስገቡ እና 10 የSSL ሰዓቶችን ያግኙ። እና፣ በዚህ ወር ሌሎች SSL እድሎች መኖራቸውን መመልከት እንዳለብዎት እርግጠኛ ይሁኑ!
 

የቅርብ ጊዜ ዘገባዎችን በዜና ገጾቻችን ላይ ይመልከቱ

 
  ከእኛ ጋር ግንኙነትዎን ይቀጥሉ
 

በመካሄድ ላይ ያሉ ክፍት ምዝገባዎች

 

ከሞንትጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ ትምህርት ቤቶች (MCPS) የበለጠ መረጃ

Facebook X.com Instagram Youtube Flickr Linkedin
በዚህ አድራሻ ኢሜል ያድርጉልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ Montgomery County Public Schools
©1995–2026 Montgomery County Public Schools