MCPS የሳምንቱ ወቅታዊ መረጃ — መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች
MCPS Logo

አበይት ጉዳዮች

ኦክቶበር 08, 2026

 
English / español / 中文 / français / Português / 한국어 / tiếng Việt / አማርኛ/Amharic
 
  የትምህርት ቦርድ ስለ ትምህርት ቤት መዘጋት እና ማጣመር ጥናት ወቅታዊ መረጃ እያገኘ ነው

ሐሙስ፣ ኦክቶበር 8፣ MCPS የአንደኛ እና የመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን የመዝጋት እና የማዋሃድ/ማጣመር ጥናትን በተመለከተ ለትምህርት ቦርዱ ማብራሪያ ሰጥቷል፤ ይህም የዚህን ሥራ አስፈላጊነት ምክንያቶች እንደገና ስለመገምገም፣ ውሳኔዎች እንዴት እንደሚወሰኑ እና ምክረ-ሀሳብ ከመዘጋጀቱ በፊት ማህበረሰቡ እንዴት መሳተፍ እንደሚችል ማብራሪያዎችን ያካትታል። ይበልጥ ያንብቡ።

 
  በመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ፕሮግራም የሚደረጉ ለውጦች በአንድ ዓመት እንዲዘገዩ ተደርጓል

MCPS ለመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የትምህርት መርሃ ግብር ሊደረጉ የታቀዱ ማናቸውንም ለውጦች እስከ 2027-2028 የትምህርት አመት ድረስ ያዘገያል። ይህም ለግምገማ፣ ለውይይት እና 2028-2029 የትምህርት አመት ላይ ስለሚደረገው ተግባራዊ አፈጻጸም ተጨማሪ ጊዜ ለመስጠት ታስቦ ነው። በውይይት ላይ ካሉት ሀሳቦች መካከል 60 ደቂቃ ዋና ትምህርቶች እና በመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ይበልጥ ወጥ የሆነ የምርጫ ትምህርት አቅርቦት ይገኙበታል። በዚህ የትምህርት አመት ምንም ዓይነት ለውጦች አይተገበሩም። ይበልጥ ያንብቡ።

 

ቦርዱ ለሕዝብ አስተያየት የቀረበን የትምህርት ቤት የቀን መቁጠሪያ/ካለንደር ሀሳብ መስጫ ጊዜውን አራዝሟል።

የትምሕርት ቦርዱ ኦክቶበር 8 ቀን 2027–2028 እና 2028–2029 የትምህርት ዘመናት የቀረቡትን የትምህርት ቤት የቀን መቁጠሪያ/ካለንደር ረቂቆች በሚመለከት ገለጻ ያዳመጠ ሲሆን፣ እነዚህን ሀሳቦች ለህዝብ አስተያየትና ግብረ-መልስ እንዲቀርቡ ወስኗል። የውይይቱ ዋና ገጽታ የሁለት ዓመት የቀን መቁጠሪያ/ካለንደር አሰራርን የሚመለከት ሲሆን፣ ይህም ቤተሰቦች እና ሰራተኞች ዋና ዋና ቀኖችን አስቀድመው በመወሰን ለወደፊት የተሻለ ዕቅድ እንዲያወጡ ለማስቻል ታስቦ የተዘጋጀ ነው።
በዚህ አሰራር መሰረት፣ ቦርዱ የቀጣዩን የትምህርት ዘመን የቀን መቁጠሪያ/ካለንደር የሚያጸድቅ ሲሆን፣ በተመሳሳይ ጊዜም ለቀጣዩ ዓመት እንደ ትምህርት መጀመሪያና መጨረሻ ቀናት እንዲሁም የክረምትና የጸደይ የዕረፍት ጊዜያት የመሳሰሉ ዋና ዋና ቀናትን በጊዜያዊነት ይወስናል። ማህበረሰቡ በቀረቡት የቀን መቁጠሪያዎች/ካለንደሮች ላይ አስተያየት የመስጠት ዕድል ይኖረዋል፤ የመጨረሻው ውሳኔ የሚሰጠው ደግሞ በቦርዱ መደበኛ የሥራ ስብሰባ ላይ፣ ማለትም ሐሙስ፣ ኖቬምበር 19 ይሆናል።

የቀረበውን ቪዲዮ እዚህ ይመልከቱ።

ስላይዶችን ይመልከቱ።

 

 
  MCPS በሥርዓተ-ትምህርት ቀን ኦክቶበር 19 ልጅዎ ምን እየተማረ(ች) እንደሆነ ይቃኙ።

MCPS «ስርዓተ-ትምህርት የሚመለከቱበት ቀን» (Curriculum Preview Day) እያዘጋጀ ነው። ይህ ዝግጅት ቤተሰቦች የማስተማሪያ ቁሳቁሶችን እንዲመለከቱ፣ ተማሪዎች ስለሚማሯቸው ትምህርቶች ተጨማሪ መረጃ እንዲያገኙ እና በቤት ውስጥ የመማር ሂደትን ለመደገፍ የሚረዱ ግብዓቶችን እንዲያውቁ ለማስቻል የተዘጋጀ ጠቃሚ ዕድል ነው። ይህ ዝግጅት ለሁሉም MCPS ትምህርት ዓይነቶች፣ ከመዋዕለ-ህጻናት እስከ 12ኛ ክፍል (K–12 ) ላሉ ቤተሰቦች ክፍት ነው። ሰኞ፣ ኦክቶበር 19፣ ከጠዋቱ 11 a.m.-1 p.m. ወይም ከሠዓት በኋላ 5-7 p.m. ባለው ጊዜ ውስጥ በካርቨር የትምህርት አገልግሎት ማዕከል (Carver Educational Services Center) ካፌቴሪያ በሚደረጉት ስብሰባዎች ላይ ይሳተፉ። ቤተሰቦች MCPS የትምሕርት ስራ ባለሙያዎች ጋር መገናኘት፣ ጥያቄዎችን መጠየቅ፣ የትምህርት መርጃ ቁሳቁሶችን መመልከት እና የዲጂታል ትምህርት መርጃዎችን ድጋፍ ማግኘት ይችላሉ።

 
  መንገድዎን ይቃኙ፡ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሴንተር ፕሮግራሞችን ያስሱ

በስድስቱም ሪጅኖች የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የመኸር ወቅት ትርኢቶች እየተካሄዱ ሲሆን የስምንተኛ ክፍል ተማሪዎችን እና ቤተሰቦችን በህክምና ሳይንስ፣ በአለም አቀፍ ባካሎሬት፣ በሰብአዊነት እና ቋንቋዎች ትምሕርት፣ STEM፣ በአመራር እና የሕዝብ አገልግሎት እና በተውኔት እና የስነጥበባት ትምሕርቶች የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የማዕከል ፕሮግራሞች ጋር ያገናኛሉ።

የሴንተር ፕሮግራሞቹ በመላው ካውንቲው ለሚገኙ በርካታ ተማሪዎች የተሻለ ተደራሽነት ይሰጣሉ፤ እንዲሁም ውስን የመቀመጫዎችን ብዛት፣ እና አቅምን በማገናዘብ፣ የተጠባባቂዎችን ዝርዝር፣ የትራንስፖርት እና ጂኦግራፊያዊ አቀማመጥ የመሳሰሉ እንቅፋቶችን በመቀነስ፣ ተማሪዎች ከዝንባሌአቸው፣ ከፍላጎታቸውና ከግቦቻቸው ጋር የሚጣጣሙ ፕሮግራሞችን እንዲከታተሉ ያስችላቸዋል።

 
  ብሔራዊ የርዕሳነ መምህራን ወር፡ ከማሪቫሌ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ኦሊቪያ ቤይሊ ጋር የተደረገ ቃለ-መጠይቅ

ኦክቶበር ብሔራዊ የርእሰ መምህራን ወር ነው። በዚህ ወር በሙሉ፣ MCPS ትምህርት ቤቶቻችንን የሚመሩ እንዲሁም ተማሪዎችን፣ የትምህርት ቤት ሰራተኞችን እና ቤተሰቦችን በየቀኑ የሚደግፉ ቁርጠኛ መሪዎችን እውቅና ይሰጣል። ይህንን አገልግሎት ለማክበር፣ በመላው ካውንቲ የሚገኙ ጥቂት የትምህርት ቤት ርዕሳነ መምህራንን በማስተዋወቅ፤ ምን እንደሚያነሳሳቸው እና በትምህርት ቤት ማህበረሰባቸው ውስጥ ምን ዓይነት አዎንታዊ ተጽዕኖ ለመፍጠር እንደሚፈልጉ ለመረዳት እንሞክራለን። እነዚህ መሪዎች፣ ያላቸውን ከፍተኛ ፍላጎት እና አንዳንድ አስደሳች እውነታዎችን ማወቅ ይችላሉ። ከኦሊቪያ ቤይሊ ጋር የተደረገውን ቃለ-መጠይቅ ያንብቡ። 

 
  የሴንተር ፕሮግራሞች 101: EdTalk ላይ ዝርዝር መረጃ ማግኘት ይችላሉ።

"EdTalk" ላይ፣ አስተናጋጇ የትምህርት ቦርድ ፕሬዝዳንት ግሬስ ሪቬራ-ኦቨን (Grace Rivera-Oven) እንዲሁም እንግዶቻቸው ስለ አዲሶቹ MCPS የሴንተር ፕሮግራሞች (Center Programs) ሲወያዩ አብረው ይሳተፉ። በአካባቢያቸው ለሚገኙ የተለያዩ የአራት ዓመት የአካዳሚክ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የልዩ ትኩረት ፕሮግራሞች (Center Programs)፣ 8ኛ ክፍል ተማሪ ያላቸው ቤተሰቦች እንዴት ማመልከት እንደሚችሉ ይወቁ። EdTalk ይመልከቱ | Vea Educacion al Día

 
  ParentVue ከፍተኛ ጥቅም አለው

ParentVUE በደንብ እየተጠቀሙበት ነው? ይህ የተማሪዎን የትምህርት ቤት ቆይታ ሂደት ለመከታተል እና ከት/ቤቱ ጋር ለመገናኘት ከሚያስችሉዎት እጅግ ቀላል መንገዶች አንዱ ነው። ቤተሰቦች የልጆቻቸውን የትምህርት ውጤቶች እና የቤት ሥራዎችን ለመከታተል፣ ትምህርት ቤት መገኘታቸውን ለማረጋገጥ፣ የት/ቤት አውቶቡስ መጓጓዣ መረጃ ለማግኘት፣ የሪፖርት ካርዶችን እና የትምሕርት ውጤት ግምገማዎችን ለማግኘት፣ የኦንላይን ምዝገባዎችን ለመሙላት እና ከመምህራን ጋር በቀጥታ ለመገናኘት ይጠቅማቸዋል።

አዲሱን ParentVUE መተግበሪያ ማውረድዎን፣ የውጤት ማህደር/Gradebook እና የሚመርጡትን አቋራጭ እንደፍላጎትዎ ማስተካከል፣ እንዲሁም ParentVUE በየጊዜው መመልከትዎን ያረጋግጡ። በመተግበሪያው አማካኝነት በቀጥታ የወላጅ-መምህር ውይይቶችን ቀጠሮ ማስያዝ ይችላሉ። ያስታውሱ፦ እያንዳንዱ ወላጅ ወይም አሳዳጊ የራሱን ParentVUE አካውንት/account እና የይለፍ ቃል መጠቀም አለበት።

ይበልጥ ይወቁ፦ English / español / 中文 / français / Português / 한국어 / tiếng Việt / አማርኛ/Amharic

 
  የክረምት ስፖርት ምዝገባ ኦክቶበር 12 ይጀመራል

ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የክረምት ስፖርቶች ምዝገባ ParentVue ላይ፣ ሰኞ፣ ኦክቶበር 12 እኩለቀን (noon) ይጀመራል። የክረምት ስፖርቶች የሚከተሉትን ያካትታሉ፡ የወንዶችና የሴቶች የቅርጫት ኳስ፣ (bocce)፣ ቺርሊዲንግ (cheerleading)፣ የወንዶችና የሴቶች የቤት ውስጥ የሩጫ ውድድር (indoor track)፣ የወንዶችና የሴቶች ዋና ዳይቪንግ፣ እንዲሁም ትግል።

 ለወንዶችና ለሴቶች የመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የቅርጫት ኳስ ውድድር ምዝገባ የሚጀምረው ሰኞ፣ ኦክቶበር 26 ቀትር ላይ ነው።

የምዝገባ መስፈርቶች

ተማሪዎች በልምምድ ወይም በተወዳዳሪዎች ምርጫ ሂደት (tryouts) ከመሳተፋቸው በፊት፣ ወላጆች/አሳዳጊዎች MCPS የስፖርት እንቅስቃሴዎች የኦንላይን ምዝገባ ሂደት ሞልተው ማቅረብ አለባቸው። በምዝገባ ወቅት፣ ተማሪዎች እና ወላጆች/አሳዳጊዎች በምዝገባ ስርዓቱ ውስጥ የተካተቱትን እና አስፈላጊ የሆኑትን የአትሌቲክስ መረጃዎች እንዲመለከቱና እንዲያረጋግጡ ያስፈልጋል።

 
  የሙቀት መጠን ስለመጨመር፡ HVAC ሲስተም እየተቀየረ ነው

ለሚመጣው ቀዝቃዛ የአየር ሁኔታ ለመዘጋጀት፣ MCPS በሁሉም ትምህርት ቤቶች፣ ተቋማት፣ እና የቢሮ ህንጻዎች ውስጥ የአየር ማሞቂያና ማቀዝቀዣ ሲስተሙን ወደ ማሞቂያነት የመቀየር ሂደት ኦክቶበር 19 ይጀምራል። ይህ ሂደት ጊዜ የሚወስድ እና ውስብስብ ሊሆን ይችላል። ይህን ለማድረግ ልክ እንደ ማብሪያና ማጥፊያ መቀያየር ቀላል አይሆንም። የጥገና ሠራተኞች ቡድኖች የማሞቂያ ሲስተሞች በትክክል እና በአስተማማኝ ሁኔታ እየሰሩ መሆናቸውን ለማረጋገጥ፣ የህንጻዎችን ሲስተሞች ቀስ በቀስ ማስተካከል፣ መሳሪያዎችን መፈተሽ፣ እና አስፈላጊ ማስተካከያዎችን ማድረግ አለባቸው። ይህ የሽግግር ሂደት በመቶዎች በሚቆጠሩ ሕንፃዎች ውስጥ የሚከናወን በመሆኑ፣ ሂደቱ በሚካሄድበት ወቅት የሙቀት መጠኑ ከሕንፃ ወደ ሕንፃ — እንዲሁም ከአንድ ክፍል ወደ ሌላ ክፍል — ሊለያይ ይችላል።

ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት ይህንን HVAC የማስተካከል ሁኔታ (HVAC Changeover Status) ድረ-ገጽ ይከታተሉ።

 
  ከቼስፒክ ቤይ እስከ ካፌቴሪያዎ ትሪ ድረስ

በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ፣ የሜሪላንድ ስቴት የግብርና ሚንስትር ኬቨን አቲክስ ከትምህርት ቦርድ አባላት፣ ከትምህርት ቤቶች ሱፐርኢንተንደንት ቶማስ ቴይለር፣ ከምግብ እና የተመጣጠነ ምግብ አገልግሎት ክፍል ሠራተኞች እንዲሁም ከዶክተር ማርቲን ሉተር ኪንግ ጁኒየር ት/ቤት የሥራ ባልደረቦች ጋር ተገናኝተዋል። የመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎችና ሰራተኞች በአካባቢው የሚገኝ የምግብ አይነት የሆነውን 'ቼስፒክ ብሉ ካትፊሽ' (Chesapeake Blue Catfish) ያቀርባሉ። ይበልጥ ያንብቡ።.

 
  አሁን ያውቃሉ — ከእኛ ጋር የሚያደርጉትን ግንኙነት ይቀጥሉ

MCPS የሚልካቸውን ጠቃሚ መረጃዎች እንዳያመልጡዎት ማረጋገጥ ይፈልጋሉ?

ለወላጆች፣ ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች፣ እና ለሰራተኞች የተዘጋጀና ለዲስትሪክት ኮሙኒኬሽን/ ግንኙነት እና ለቀጥታ መልዕክት ልውውጥ የሚያገለግለውን ParentSquare ለማግኘት ይመዝገቡ። መተግበሪያውን ከ App Store ወይም ከ Google Play ያውርዱ፤ ከዚያም MCPS ላይ ባስመዘገቡት የስልክ ቁጥር ወይም የግል ኢሜይል አድራሻ ላይ ይክፈቱ። MCPS Facebook፣ Instagram እና X፣ ላይ መከታተል ይችላሉ፤ ወይም በዚህ በይነመረብ montgomeryschoolsmd.orgማግኘት ይችላሉ።

የበለጠ ለማወቅ፦ እንግሊዝኛ/English |ስፓንሽኛ/Spanish | አማርኛ/Amharic | Chinese | French | Korean | Portuguese | Vietnamese

 
  የአእምሮ ጤንነት አስፈላጊ ነው፡ ኖቬምበር 14 ከእኛ ጋር ለመቀላቀል ቀኑን ያስታውሱ።

የልዩ ድጋፍ አገልግሎት ክፍል እና የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቤት ሳይኮሎጂስቶች ማህበር በጋራ በመሆን፣ ከኖቬምበር 9 እስከ 14 ቀን 2026 ዓ.ም የአእምሮ ጤንነት ግንዛቤ ሳምንትን (MHAW) ያዘጋጃሉ። የአእምሮ ጤንነት እና ደህንነት ኤግዚቢሽን፤ ቅዳሜ፣ ኖቬምበር 14 ከጠዋቱ 10 a.m.-1 p.m. ሲልቨር ስፕሪንግ በሚከተለው አድራሻ ይካሄዳል፦ James Hubert Blake High School, 300 Norwood Road in Silver Spring. ይህ ነጻ ዝግጅት ለሰራተኞች፣ ለተማሪዎች፣ እና ለቤተሰቦች ክፍት ስለሆነ፤ ወርክሾፖችን፣ ስለ አእምሮ ጤንነት እና ደህንነት መረጃ የሚያጋሩ የማህበረሰብ አጋሮችን እንዲሁም ከተማሪዎች የሚቀርብ መድረክ ይኖረዋል። ተማሪዎች በኤግዚቢሽኑ ላይ በመሳተፍ አራት ሰዓት የማህበረሰብ አገልግሎት ትምህርት ክሬዲት ማግኘት ይችላሉ።የበለጠ ግንዛቤ ያግኙ።

 
  ሙዚቃው ይጫወት! የሰልፍ ትርኢት ባንድ ኦክቶበር 24 ይካሄዳል

በዘንድሮው የማርቺንግ ባንድ ትርኢት ላይ ቅዳሜ፣ ኦክቶበር 24 ከጠዋቱ 11፡30 a.m. ጀምሮ በአልበርት አንስታይን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አስራ ሶስት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ባንዶች ይሳተፋሉ። የመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሙዚቃ ቡድን ብሔራዊ መዝሙር ያቀርባል። ዝግጅቱ፣ ለሟቿ ዶሊ ፓርተን ክብር መታሰቢያነት በሁሉም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሙዚቃ ቡድኖች በሚቀርብ የጋራ ትርኢት ይጠናቀቃል።

ይህ ዝግጅት ነፃ እና ለህዝብ ክፍት ነው። በአስቸጋሪ የአየር ሁኔታ ምክንያት የሚደረጉ ለውጦች "Fine Arts X feed @MCPSArts" ላይ ይለጠፋሉ። ይበልጥ ያንብቡ።

 
  ማሳሰቢያ
  • የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሲንየር ተማሪዎች ያሏቸው ወላጆች፦ 2027-2028 ለተማሪዎች የፌዴራል የገንዘብ ድጋፍ (FAFSA) ማመልከቻ ቅጽ ሞልተው ለማቅረብ አሁን ክፍት ነው። ይህ ቅጽ ቤተሰቦች ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት በኋላ የሚሰጠውን ትምህርት ለማጠናቀቅ የሚያስችሉትን ድጎማዎች፣ ብድሮች እና "ስራ-እና-ትምህርት" (work-study) የገንዘብ ድጋፎችን እንዲያገኙ ያግዛል። አብዛኞቹ ተማሪዎች በቅጹ ላይ መሙላት ያለባቸውን ክፍል 12 ደቂቃ ወይም ከዚያ ባነሰ ጊዜ ውስጥ ሞልተው ቅጹን ካቀረቡ በኋላ ወዲያውኑ ውጤቱን ማየት ይችላሉ። ለእርዳታ፣ በትምህርት ቤትዎ የሚገኘውን የኮሌጅ እና የሙያ ናቪጌተር (College and Career Navigator - CCN) ያነጋግሩ።
  • ስለቶማስ ኤዲሰን የቴክኖሎጂ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ልዩ ዝግጅት፡ ዝግጅቱ ሐሙስ፣ ኦክቶበር 15 ከምሽቱ 6:30-8 p.m. ይካሄዳል። ይህ ዝግጅት ተማሪዎች እና ቤተሰቦቻቸው ትምህርት ቤቱን እንዲጎበኙ፣ 16 የትምህርት ፕሮግራሞችን እንዲመለከቱ፣ ከመምህራን ጋር እንዲገናኙ፣ እና ተማሪዎች እንዴት የኮሌጅ ክሬዲት (college credit) ማግኘት እንደሚችሉ የማወቅ እድል ይሰጣቸዋል። ቤተሰቦች ወደ ኤዲሰን (Edison) ለማመልከት ስላለው የጊዜ ሰሌዳና አሰራር መረጃ ያገኛሉ፤ እንዲሁም ስለ ኢንዱስትሪ ሠርተፊኬት (industry certification) እና እየሠሩ ስለመማር ያሉትን እድሎች ማወቅ ይችላሉ። የኤዲሰን ት/ቤት አድራሻ፦ 12501 Dalewood Drive in Silver Spring።
  • የሜሪ ሃዋርድ አገልግሎት ቀን፡ የላዝሮፕ ኢ. ስሚዝ የአካባቢ ጥበቃ ትምህርት ማዕከል (Lathrop E. Smith Environmental Education Center) ዓመታዊ የህብረተሰብ አገልግሎት ቀን ቅዳሜ፣ ኦክቶበር 24 ከጠዋቱ 8 a.m.-1 p.m. ይካሄዳል። የሚከናወኑት ተግባራት የአትክልት ቦታዎችንና የመዝናኛ ስፍራዎችን (pavilions) ማሳመር፣ የእግር ጉዞ መንገዶችን ማስተካከል እና የተለያዩ የግንባታ ሥራዎችን ያካትታሉ። ተማሪዎች የአገልግሎት ትምህርት ሰዓቶችን ማግኘት ይችላሉ፤ ነገር ግን ከአዋቂ ሰው ጋር መሆን አለባቸው። ይበልጥ ግንዛቤ ያግኙ እና RSVPይመዝገቡ። አድራሻ፦ The Smith Center is located at 5110 Meadowside Lane in Rockville.
 
  ከመማሪያ ክፍል ውጭ
  • *አዲስ* MoCo EmpowHER እና የሞንትጎመሪ ካውንቲ የሴቶች ኮሚሽን (Montgomery County Commission for Women)፤ ሰኞ፣ ኦክቶበር 12 ከምሽቱ 6-8 p.m. ሮክቪል በሚገኘው ካርቨር የትምህርት አገልግሎት ማዕከል ራስን ስለመከላከል የሚያሣይ ዝግጅት ያካሂዳሉ። አድራሻ፦ Carver Educational Services Center, 850 Hungerford Dr. in Rockville. ይህ መርሐ ግብር ለሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ክፍት ስለሆነ፣ ደህንነትን ለመጠበቅ የሚያስችሉ ተግባራዊ ስልቶችን የሚያስተምር በመሆኑ፤ ተማሪዎች በአደገኛ ሁኔታዎች ውስጥ በራስ መተማመንና ዝግጁ መሆን እንዳለባቸው ትምሕርት ይሰጣል። ይመዝገቡ/Register.
  • የቪዲዮ ውድድር፦ "ድምጽዎን ያሰሙ፣ ህይወትን ይታደጉ" - በታዳጊዎች ዘንድ እየተስፋፋ ስላለው ህገ-ወጥ ኦፒዮይድስ፣ ከመጠን በላይ ስለመውሰድ (overdose) እና ስለ ፌንታኒል (fentanyl) አደጋዎች ግንዛቤን የሚያሳድግ ኦሪጅናል የቪዲዮ ውድድር ያዘጋጁ። የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች 10 የተማሪ አገልግሎት/ SSL ሰዓቶች ማግኘት ይችላሉ። ቪዲዮዎችን በእንግሊዝኛ ወይም በስፓንሽኛ ማቅረብ ይቻላል። አንደኛ ለወጣ $5,000፣ ለሁለተኛ $3,000 እና ለሦስተኛ $1,000 ሽልማት ይሰጣል። የመጨረሻው ቀን ሰኞ፣ ኖቬምበር 30ነው።መወዳደሪያውን ያቅርቡ።
  • የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ የሆኑ የምርጫ ሰራተኞች ይፈለጋሉ፡ የሞንትጎመሪ ካውንቲ የምርጫ ቦርድ ለ 2026 የገቨርነር አጠቃላይ ምርጫ ሰራተኞችን ይፈልጋል። ተማሪዎች ለሰሩበት ለእያንዳንዱ ሙሉ ቀን እስከ $250 ወይም እስከ 25 የSSL ሰዓታት ማግኘት ይችላሉ። አመልካቾች የአሜሪካ ዜግነት ያላቸው፣ የሜሪላንድ ነዋሪዎች፣ ቢያንስ 16 ዓመት የሞላቸው እና ድምጽ ለመስጠት የተመዘገቡ መሆን አለባቸው። ስፓንሽኛ ወይም ሌላ ብዝሃ ቋንቋ ችሎታ ያላቸው ተማሪዎች አገልግሎት እንዲሰጡ ይበረታታሉ። የበለጠ መረጃ ለማግኘት SERVE አጭር የጽሑፍ መልእክት ይላኩ በመቀጠል MCPS ተማሪ ያልሆነ ኢሜል ወደ 77788 (ለምሳሌ፦: SERVE 123@email.com) ወይም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የምርጫ ሰራተኞች ፕሮግራም ድረ-ገጽ ይመልከቱ።. ማመልከቻ መቅረብ ያለበት የመጨረሻ ቀን፦ ማክሰኞ፣ ኦክቶበር 13 ነው።
  • Latina Legacy Conference፡ ይህ ለላቲኖ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የተዘጋጀ ዝግጅት፣ አርብ ኦክቶበር 30 ቀን ከጠዋቱ 10 a.m.-1 p.m. ሮክቪል በሚከተለው አድራሻ ይካሄዳል። አድራሻው፦ 15 W. Gude Drive in Rockville. ለመመዝገብ፣ ተማሪዎች እስከ ሐሙስ፣ ኦክቶበር 15 ድረስ ምክትል ርዕሰ መምህራቸውን ማነጋገር አለባቸው።
  • ለአሜሪካ ያለዎትን ራዕይ ያጋሩ፡ 5ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች ፕሬዚዳንታዊ ንግግር በመጻፍና በማቅረብ እስከ $1,000 ሽልማት ማግኘት ይችላሉ። "ንግግሩን" ተማሪዎች ፕሬዝዳንት ሆነው እንደተመረጡ በማሰብ የበዓለ ሲመት ንግግራቸውን 2-3 ደቂቃ በሚፈጅ ቪዲዮ እንደሚያቀርቡ ያበረታታል።ተጨማሪ ግንዛቤ ያግኙ መወዳደሪያው መቅረብ ያለበት የመጨረሻ ቀን፦ አርብ፣ ኦክቶበር 30ነው።
  • "Smokey Bear Poster" ፖስተር አዘጋጅቶ የማቅረብ ውድድር፦ 7ኛ ክፍል ለሚማሩ ተማሪዎች ክፍት ነው። የሜሪላንድ የደን ልማትና ጥበቃ አገልግሎት 120ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን ምክንያት በማድረግ፣ 7ኛ ክፍል ተማሪዎች የእሳት አደጋ መከላከል ወርን አስመልክቶ "Smokey Bear" የተሰኘ የፖስተር ውድድር አዘጋጅቷል። ተማሪዎች "የዱር ሰደድ እሳትን መከላከል የሚችሉት እርስዎ ብቻ ነዎት!"/“Only YOU can prevent wildfires!” የሚለውን ታዋቂ መልእክት መነሻ በማድረግ ኦሪጅናል የጥበብ ሥራ ፈጥረው እንዲወዳደሩ ተጠይቀዋል። የዱር ሰደድ እሳት ደህንነትን እና የደን ጥበቃን ለመዳሰስ የመጨረሻው ቀን፦ ሰኞ፣ ኖቬምበር 2ነው።የበለጠ ግንዛቤ ያግኙ።
  • Capital Weather ከመዋእለ ህጻናት እስከ 8ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎችን፣ ስለ አየር ሁኔታ፣ ስለ ወቅቶች፣ ስለ አየር ንብረት ወይም በተፈጥሮ ተመስጠው የፈጠሯቸው ኦርጅናል ስራዎችን ለልጆች የጥበብ ማሳያ ዝግጅት እንዲያቀርቡ ይጋብዛል።የበለጠ ግንዛቤ ያግኙ።
 
  ከዋክብትን መመልከት

በዚህ ሳምንት፣ ከኦክቶበር 4 እስከ 10 የሚከበረውንና ለሳይንስና ቴክኖሎጂ እንዲሁም የህዋ ምርምር በዓለም ዙሪያ የሰዎችን ሕይወት ለማሻሻል ለሚያበረክተው አስተዋጽኦ የተዘጋጀ ዓለም አቀፍ የሕዋ ምርምር ሳምንት ለማክበር ጥቂት ጊዜ ይውሰዱ።

 
  ከእኛ ጋር ግንኙነትዎን ይቀጥሉ
 

በመካሄድ ላይ ያሉ ክፍት ምዝገባዎች

 

ከሞንትጎሞሪ ካውንቲ የሕዝብ ትምህርት ቤቶች (MCPS) የበለጠ መረጃ

Facebook X.com Instagram Youtube Flickr Linkedin
በዚህ አድራሻ ኢሜል ያድርጉልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org
የሞንትጎመሪ ካውንቲ የሕዝብ ትምህርት ቤቶች
©1995–2026 Montgomery County Public Schools