አበይት ጉዳዮች
ኤፕሪል 09, 2026
|
|
|
ስለ ጸደይ/ስፕሪንግ የትምህርት ምዘና ለመዘጋጀት፡ ቤተሰቦች ማወቅ ያለባቸው ነገሮች |
|
የትምህርት ቤት የመጨረሻ ሳምንታት - በጣም አስፈላጊ ናቸው።
የሜሪላንድ አጠቃላይ የግምገማ ፕሮግራምን (MCAP) ጨምሮ የዓመቱ የመጨረሻ ግምገማዎች፣ ተማሪዎች የሚያውቁትን፣ የሚረዱትን እና የሙሉ ዓመት ትምህርት ከጨረሱ በኋላ ማድረግ የሚችሉትን ይመዝናል። እነዚህ ውጤቶች የተማሪዎችን የትምህርት እድገት ለመለካት፣ የተማሩትን ትምህርት ለማስገንዘብ እና በሜሪላንድ የትምህርት ቤት ሪፖርት ካርድ ላይ የእያንዳንዱን ትምህርት ቤት አፈፃፀም ለማጎልበት ይረዳሉ። ቤተሰቦች እንዴት መርዳት ይችላሉ? ይበልጥ ያንብቡ።
|
|
|
|
|
|
ከገጾች እስከ ቦታዎች፡ ስላነበቡ እናመሰግናለን! |
|
በጸደይ/ስፕሪንግ እረፍት የምንባብ ፈተናች ላይ የተሳተፋችሁትን ሁሉ እናመሰግናለን። ከቤት ውስጥ ካሉ ምቹ ማዕዘኖች እስከ ጉዞ ላይ ያሉ ጀብዱዎች፣ የማንበብ ፍቅር በየትኛውም ቦታ ሊከሰት እንደሚችል አሳይታችሁናል። ንባብ ምናባዊ አስተሳሰብን ብቻ አያንፀባርቅም - የአንጎል እድገትን ያጠናክራል፣ ትኩረትን ያሻሽላል እና የቃላት አጠቃቀምን ይገነባል። ገጾችን ማገላበጥ ይቀጥሉ፣ እና ኢንስታግራም፣ ፌስቡክ እና X ላይ #MCPSCaughtYouReading በመጠቀም የንባብ ጊዜዎችዎን ከእኛ ጋር ይጋሩ።
እና፣ ቅዳሜ፣ ሜይ16 በጌትስበርግ በሚካሄደው የመጽሐፍት ፌስቲቫልላይ ለመገኘት ቀኑን ያስታውሱ።
|
|
|
|
|
|
ቆጠራ ተጀምሯል! የሱፐርኢንቴንደንት ሸፍል ቅዳሜ ነው |
|
በቅርቡ እንገናኛለን! ሱፐርኢንቴንደንት ሽፍል ቅዳሜ፣ ኤፕሪል 11 ቦኸረር ፓርክ ጠዋት 8 a.m. ላይ ይጀምራል። የውድድሩ ሰዓት ከጠዋቱ 9 a.m. ይጀመራል። ዛሬ ጠዋት MCPS የትምህርት ፋውንዴሽንን ዳይን ዊዝ ዲኔ ካምቢቲ ዘመቻ ለመደገፍ የሚደረገው የማህበረሰብ እንቅስቃሴ የተማሪዎችን የምግብ ዕዳ ለማስወገድ ይረዳል።
|
|
|
|
|
|
የትምህርት ቦርድ የማህበረሰብ መሪዎችን፣ እና የኮሙኒኬሽን ባለሙያዎችን ወደ አማካሪ ኮሚቴው እንዲቀላቀሉ ይፈልጋል |
|
የሞንትጎመሪ ካውንቲ የማህበረሰብ መሪዎች እና በመገናኛ እና በተሳትፎ ልምድ ያላቸው ባለሙያዎች የትምህርት ቦርድ የኮሙኒኬሽን እና የማህበረሰብ ተሳትፎ አማካሪ ኮሚቴ አባል ለመሆን እንዲያመለክቱ ተጋብዘዋል፣ ይህም በቦርዱ እና በማህበረሰቡ መካከል ያለውን ትብብር ለማጠናከር የተነደፈ ቁልፍ ተነሳሽነት ነው።
ይህ ኮሚቴ የማህበረሰቡን ትስስር በማጠናከር፣ ግልጽነትን በማሻሻል፣ እና በጣም አስፈላጊ በሆኑ የቦርዱ ተነሳሽነቶች ዙሪያ ትርጉም ያለው ተሳትፎን በመምራት ረገድ ወሳኝ ሚና ይጫወታል። የኮሚቴ አባላት የዲስትሪክቱን የግንኙነት ስልቶች ለማጠናከር እና ለማጎልበት እንዲሁም ትምህርት ቤቶቻችንን እና ማህበረሰቦቻችንን በሚመለከቱ ወሳኝ ጉዳዮች ላይ ሁሉም ድምጾች እንዲሰሙ ለማድረግ ይረዳሉ።
እስከ አርብ፣ ሜይ 1 ድረስ ያመልክቱ።
|
|
|
|
|
|
ስለ ልዩ ትምህርት አገልግሎቶች፣ የሰው ኃይል እና ድጋፍ ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት ይቀላቀሉን |
|
የልዩ ድጋፍ አገልግሎቶች ክፍል ረቡዕ፣ ሜይ 6 ከቀኑ 6-7:30 p.m. ለቤተሰቦች ዌቢናር ፕሮግራም ያካሂዳል፣ ይህም በልዩ ትምህርት አገልግሎቶች፣ በሠራተኞች አደረጃጀት እና በድጋፍ አሰጣጥ ዙርያ ምን አዲስ ነገር እንዳለ— እና ለምን አስፈላጊ እንደሆነ — መሰጠት ባለበት አፅንኦት ላይ ያተኩራል። MCPS የልዩ ትምህርት መሪዎች ይህ ለትምህርት ቤቶች እና ለመማሪያ ክፍሎች ምን ማለት እንደሆነ አውድ ይሰጣል። ክፍለ ጊዜው በቨርቹዋል የሚካሄድ ሲሆን ከጥያቄዎችና መልሶች ጋር በአጭር አቀራረብ ይከናወናል። የዙም ሊንክ እዚህ ይገኛል።
የልዩ ትምህርት ቤተሰቦችን የሚመለከት ሁለት ተጨማሪ ዝግጅቶች አሉ -- ይኼውም ኤፕሪል 23 የሚካሄደው ወርሃዊ SECAC ስብሰባ እና ሜይ 9 የሚካሄደው የልዩ ትምህርት የቤተሰብ መገልገያ/ሪሶርስ ትርኢት ነው። እዚህ ይበልጥ ያንብቡ.
|
|
|
|
|
|
ማሳሰቢያ፡ ኤፕሪል 15 ተማሪዎች ቀደም ብሎ የሚለቀቁበት ቀን ነው |
|
አሁን ረቡዕ፣ ኤፕሪል 15 ተማሪዎች ቀደም ብሎ የሚለቀቁበት ቀን ነው። ይህ ከመጥፎ የአየር ሁኔታ የትምህርት ማካካሻ ቀናት አንዱ ነው። ሦስተኛው የማርክ መስጫ ጊዜ የሚያበቃው ኤፕሪል 14 ላይ ሲሆን፣ የውጤት ሪፖርት የሚደረገው እስከ ኤፕሪል 20 ድረስ ይዘገያል። የሪፖርት ካርዶች ኤፕሪል 24 ParentVue ላይ ይገኛሉ፤ የወረቀት ቅጂዎች እስከ ኤፕሪል 30 ድረስ ይሰራጫሉ።
|
|
|
|
|
|
መብራቶች፣ ካሜራ… ትወና! |
|
ኢንተርሚሽን ጊዜው አብቅቷል፣ እና ተውኔት እና የአርት ስነጥበብ ወደ መድረክ ተመልሷል! የሥነ ጥበብ ትርኢት ላይ ለመታደም ይምጡ፣ በጸደይ/ስፕሪንግ የሙዚቃ ትርኢት ይደሰቱ ወይም የዳንስ ትርኢቶችን መጥተው ይመልከቱ። ተማሪዎቻችን ኪነጥበብን በቀጥታ ሲተውኑ መላውን ቤተሰብ ይዘው በመምጣት ይደግፉ። በአቅራቢያዎ ያለ ዝግጅት ለማግኘት የስነጥበብ ቀን መቁጠሪያ/Fine Arts calendar ይቃኙ - ለሁሉም ሰው የሚመች ነገር ይኖራል!
|
|
|
|
|
|
ወጣቶቻችንን ለመደገፍ እና ደህንነቱ የተጠበቀ ማህበረሰብ ለመገንባት ኤፕሪል 18 ላይ ይቀላቀሉን |
|
የሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የአእምሮ ጤና እና የአደንዛዥ ዕፅ አጠቃቀም መከላከል የቤተሰብ መድረክ ቅዳሜ፣ ኤፕሪል 18 ከቀኑ 1–4 p.m. በሞንትጎመሪ ብሌር ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ ይካሄዳል። አድራሻ፦ Montgomery Blair High School, 51 University Blvd. East in Silver Spring. ይህ ዝግጅት ነፃ እና ለተማሪዎች፣ ለቤተሰቦች፣ ለሠራተኞች፣ እና ለማህበረሰብ አባላት ክፍት ነው። የሚሳተፉ ተማሪዎች 3 የተማሪ አገልግሎት ትምህርት ሰዓት ማግኘት ይችላሉ። አውደጥናቱ የሚካሄደው በእንግሊዝኛ እና በስፓንሽኛ ቋንቋዎች ነው። ተጨማሪ ግንዛቤ ይውሰዱ
|
|
|
|
|
|
ለሲንየሮች የተዘጋጀ እድል፡ አመታዊ የሥራ ቃለ መጠይቅ ቀን - ሜይ 19 ይደረጋል። |
|
ከተመረቁ በኋላ የሙሉ ጊዜ ሥራ፣ የሥራ ተለማማጅ መሆን ወይም የሙያ ሥራ ይፈልጋሉ? በዓመታዊ የሥራ ቃለመጠይቅ ቀን MCPS እና Career Council, Inc. ይቀላቀሉ።
- መቼ፦ ማክሰኞ፣ ሜይ 19 (በትምህርት ቀን)
- የት፦ Rockville Sportsplex (60 Southlawn Court, Rockville)
- ምን፦ ለመግቢያ ደረጃ ቦታዎች፣ ለሥራ ተለማማጅነት እና ለሙያ ሥራ እድሎች ከአካባቢው ኩባንያዎች ጋር የሚደረጉ ቃለመጠይቆች ይኖራሉ።
እንዴት መመዝገብ እንደሚቻል፦
- እስከ አርብ፣ ኤፕሪል 24 ድረስ የኮሌጅ እና የስራ አሳሽ (CCN) ይመልከቱ።
- የፈቃድ ወረቀት ይውሰዱ እና የጉግል ምዝገባ ቅጽ ይሙሉ።
- ረዙሜ ይጫኑ/ያቅርቡ እርዳታ ይፈልጋሉ? ስለ ሪዙሜ ድጋፍ ለማግኘት ከፈለጉ CCN፣ የትምህርት ቤት ካውንስለር፣ አስተማሪ ወይም ወላጅ/አሳዳጊ ይጠይቁ!
|
|
|
|
|
|
ፈጠራ ላይ እናተኩር፣ MCPS! |
|
የመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በሞንትጎመሪ ካውንቲ የትራንስፖርት ዲፓርትመንት ‘Paint the Plow’ ውድድር ላይ እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል፤ ይህም ለትምህርት ቤታቸው የገንዘብ ሽልማቶችን የማሸነፍ እድል ለማግኘት በረዶ የማጽዳት ሥራ እና ማስጌጥ ላይ ለመሳተፍ ነው። የበረዶ ማጽዳት ሥራ የበረዶ ክምችት ባለበት ወቅት በሪጅኑ በሙሉ ይሰማራሉ። ተጨማሪ ግንዛቤ ያግኙ።
የሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች እና ሰራተኞች በሙሉ 2026 የዘላቂነት እና የሥነ ስርዓት ተገዢነት ቡድን ፖስተር ውድድር ላይ እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል። ይህ ውድድር ከኢነርጂ ቁጠባ፣ ከቆሻሻ ቅነሳ እና ኃላፊነት የተሞላበት መልሶ ጥቅም ላይ ማዋል ጋር የተያያዙ ዘላቂ እርምጃዎችን ግንዛቤን ይጨምራል። የመጨረሻ ቀን፡ ሰኞ፣ ኤፕሪል 13ነው። ተጨማሪ ግንዛቤ ያግኙ።
|
|
|
|
|
|
ተጋብዘዋል! በዋትኪንስ ሚል STUNT ሚዲያ ቀን ይቀላቀሉን |
|
ቤተሰቦች ሰኞ፣ ኤፕሪል 13፣ ከቀኑ 6 p.m. ላይ በዋትኪንስ ሚል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በሚገኘው STUNT የሚዲያ ቀን እንዲገኙ ተጋብዘዋል። ይህ ዝግጅት ወላጆችን፣ አትሌቲክስ እና ሚዲያዎችን STUNT ወደ MCPS ለመቀበል እና የፓይለት ወቅቲን በመምራት ላይ ያሉትን 13 ትምህርት ቤቶች እውቅና ለመስጠት አንድ ላይ ያገናኛሉ። STUNT የተነደፈው ከተለምዶአዊ የአበረታችነት አጨዋወት የተገኘ እና ፊት ለፊት ውድድር ላይ ቦታ ላይ ለመገኘት በቴክኒካዊ ክህሎት፣ ትወና እና ትክክለኛነት ላይ ያተኮረ ነው። በአገሪቱ ውስጥ በፍጥነት ከሚያድጉ የሴቶች ስፖርቶች አንዱ ነው። የስፖርትን አወቃቀር፣ ደንቦች፣ እና ይዘት የሚያሳይ STUNT ዝግጅት የቀጥታ ትርኢት ይኖራል። ዋትኪንስ ሚል አድራሻ፦ Watkins Mill is located at 10301 Apple Ridge Road in Gaithersburg.
|
|
|
|
|
|
ማሳሰቢያ |
|
|
|
|
|
|
|
ወደ ተግባር መስፈንጠር/Spring Into Action |
|
4ኛ እስከ 12ኛ ክፍል የሚገኙ ወንድ ተማሪዎች ቅዳሜ፣ ኤፕሪል 25 ከጠዋቱ 8 a.m. እስከ እኩለ ቀን ድረስ በሞንትጎመሪ ኮሌጅ፣ ጀርመንታውን ካምፓስ ውስጥ በሚካሄደው 2026 የጸደይ/ስፕሪንግ ጨዋታ ቀያሪ የወጣት ወንዶች ኮንፈረንስ ላይ እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል። ምዝገባ ሰኞ፣ ኤፕሪል 20 ይዘጋል። ይመዝገቡ/Register. ለአፍሪካን-አሜሪካን እና ለማይኖሪቲ ተማሪዎች የተዘጋጀ ኮንፈረንስ ስለ ማህበራዊ-ስሜታዊ ደህንነት እና በራስ መተማመንን ለመገንባት የተነደፈ ነው።
ለተማሪዎች ሌሎች እድሎች፦
- የሞንትጎመሪ ካውንቲ የጥቁሮች ትምህርት ቤት አስተማሪዎች ጥምረት ለዓመታዊው የተከበሩ የአፍሪካን አሜሪካን ምሁራን ሽልማት ማመልከቻዎችን እየተቀበለ ነው። ሽልማቶቹ ድህረ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ለመከታተል ለሚፈልጉ የሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተመራቂዎች ክፍት ናቸው። ማመልከቻ መቅረብ ያለበት አርብ፣ ኤፕሪል 10 ነው።ያመልክቱ
- የማህበራዊ ፍትህ ትርኢት፡- የወንጀል ፍትህ ማሻሻያ፣ በሴቶች መብቶች፣ በአካባቢ ፍትህ፣ እና የዘረኝነት ፍትህ ዙሪያ ከባለሙያ ተናጋሪዎች እና ድርጅቶች ጋር ይገናኙ። SSL ሰዓቶች ይሰጣሉ። ቅዳሜ፣ ኤፕሪል 11 ከጠዋቱ 10:30 a.m. እስከ 1 p.m. ፣ በዋልት ዊትማን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት/Walt Whitman High School. Feria de Justicia Social LASJ
- ስለ እግረኞች ደህንነት የኪነጥበብ/አርት ውድድር፡ ከመዋእለ ህጻናት እስከ 5ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች የእግረኞችን ደህንነት መጠበቅን በሚመለከት የኪነጥበብ/አርት ስራዎችን በማዘጋጀት እንዲወዳደሩ ይበረታታሉ። የመጨረሻው ቀን ዓርብ፣ ኤፕሪል 17 ነው።
- 11ኛው አመታዊ G.L.O.W. (ዓለማችንን እየመሩ ያሉ ልጃገረዶች) የሙያ ጉባኤ፡- 8ኛ እስከ 12ኛ ክፍል የሚገኙ ሴት ተማሪዎች ቅዳሜ፣ ኤፕሪል 18 በሚካሄደው በዚህ የሙሉ ቀን ኮንፈረንስ ላይ ፓነሎችን፣ አውደ ጥናቶችን እና ኔትወርኪንግን ላይ እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል። እስከ አርብ፣ ኤፕሪል 10 ድረስ የሚመዘገቡ ተማሪዎች swag bag እና professional blazer ያገኛሉ።
- NAACP የወጣቶች ስብሰባ: ቅዳሜ፣ ኤፕሪል 18 10 a.m.-2 p.m. , በሪቻርድ ሞንትጎሞሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት/Richard Montgomery High School. ይህ ነፃ ዝግጅት ለሁሉም ተማሪዎች ክፍት ሲሆን ስለ አመራር ክህሎት አውደ ጥናቶችን፣ የተማሪዎች የፓናል ውይይቶችን እና ሀሳብን የማንፀባረቅ እና የማቀንቀን ዘመቻ እድሎችን ይሰጣል። ምሳ፣ ትራንስፖርት፣ እና SSL የአገልግሎት ሰዓት ይሰጣል።
- ለምርጫ ውድድር ዘመቻ ሰራተኞች ይፈለጋሉ፦ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች 2026 የስቴት ፕራይመሪ ምርጫ ውድድር በምርጫ ሰራተኛነት ማገልገል ይችላሉ። ተማሪዎች ለሰሩበት ለእያንዳንዱ ሙሉ ቀን እስከ $250 ወይም እስከ 25 የSSL ሰዓታት ማግኘት ይችላሉ። አመልካቾች የአሜሪካ ዜጎች፣ የሜሪላንድ ነዋሪዎች፣ ቢያንስ 16 ዓመት የሞላቸው እና ድምጽ ለመስጠት የተመዘገቡ መሆን አለባቸው። ሁለት ቋንቋ የሚናገሩ ተማሪዎች እንዲያመለክቱ ይበረታታሉ።
- ስለ ደህንነት የሚቀነቀንበት ቀን፦ በዚህ ነፃ ዝግጅት ላይ ስለ እግረኞች ደህንነት፣ ወደ ትምህርት ቤት የሚወስዱ አስተማማኝ መንገዶች እና እይታን ስለሚጋርዱ ሁኔታዎች/ቪዥን ዜሮ ፕሮግራም ቅዳሜ፣ ሜይ 9 ከጠዋቱ 11 a.m. እስከ 3 p.m. ድረስ ሮክቪል በሚገኘው ካርቨር የትምህርት አገልግሎት ማዕከል ዝግጅት ይካሄዳል። አድራሻ፦ Carver Educational Services Center, 850 Hungerford Drive in Rockville
|
|
|
|
|
|
ከዜና ገፆቻችን |
|
|
|
|
|
|
|
ከእኛ ጋር ግንኙነትዎን ይቀጥሉ
|
|
|
|
|
|
|
|
|
|
|
|
|
|
በዚህ አድራሻ ኢሜል ያድርጉልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org
|
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ
|
|
©1995–2026 Montgomery County Public Schools
|
|