MCPS የሳምንቱ ወቅታዊ መረጃ — መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ አርማ

አበይት ጉዳዮች

ኤፕሪል 16, 2026

 
English / español / 中文 / français / Português / 한국어 / tiếng Việt / አማርኛ/Amharic
 

በመጨረሻም የትምህርት ዓመቱ አራተኛ ሩብ ዓመት ላይ ደርሰናል። ለተማሪዎችና ለቤተሰቦች አስደሳችና አስፈላጊ ጊዜ ነው።

ለማስታወስ ያህል፣ የሶስተኛው የማርክ መስጫ ጊዜ የሚያበቃው ኤፕሪል 14 ላይ ነው፣ ነገር ግን የውጤት ሪፖርት እስከ ኤፕሪል 20 ድረስ ይዘገያል። የሪፖርት ካርዶች ኤፕሪል 24 ParentVue ላይ ይገኛሉ፤ የወረቀት ቅጂዎች እስከ ኤፕሪል 30 ድረስ ይሰራጫሉ።

 
  ለሞቃታማ ቀናት መዘጋጀት

MCPS በትምህርት ቤቶቻችን ውስጥ ከሙቀት ወደ አየር ማቀዝቀዣ ወቅታዊ ለውጥ ማድረግ ጀምሯል። ምክንያቱም እነዚህ ትላልቅ የቢዝነስ ሥርዓቶች በመሆናቸው፣ ሂደቱ - አራት ሳምንታት ያህል - ጊዜ ይወስዳል እና በእያንዳንዱ ትምህርት ቤት መከናወን አለበት።

ይህንን ሽግግር የጀመርነው ኤፕሪል 7 ሲሆን ይህ የሆነው ከቅርብ ጊዜው ሞቃታማ የአየር ሁኔታ ምክንያት ከወትሮው ቀደም ብሎ ነው። ከመኖሪያ ቤቶች በተለየ ሁኔታ፣ ሲስተሞቻችን በየቀኑ የሙቀት መጠን መለዋወጥ ሲከሰት መቀያየር አይቻልም። እያንዳንዱ ሕንፃ ከመስመር ውጭ ተዘግቶ፣ ውሃው እንዲፈስ፣ እንዲስተካከል፣ እና የማቀዝቀዣ ሁኔታው እንደገና ተስተካክሎ እንዲጀመር መደረግ አለበት።

ልዩ ፍላጎት ላላቸው ተማሪዎች የሚያገለግሉ ትምህርት ቤቶችና ፕሮግራሞች ቅድሚያ የሚሰጣቸው ሲሆን፣ በእነዚያ ትምህርት ቤቶች ላይ ማንኛውንም ተጽዕኖ ለመቀነስ በቅርበት ክትትል ይደረግባቸዋል። ይህንን አስፈላጊ ሽግግር እስከምናጠናቅቅ ለምታሳዩት ትዕግስት እናመሰግናለን፤ እንዲሁም የትምህርት ቤቶቻቸውን ማስተካከያ ጊዜ በተመለከተ ለርእሰ መምህራን ማሳወቃችንን እንቀጥላለን።

 
  2026–2027 የትምህርት ቤት ቀን መቁጠሪያ/ካለንደር ማስተካከያ ጠረጴዛ ላይ ስለሆነ፤ በእናንተ በኩል ምን እንደምታስቡ ንገሩን/አስተያየት ስጡን!

የትምህርት ቦርድ ዛሬ (ኤፕሪል 16) ባካሄደው የሥራ ክፍለ ጊዜ 2026-2027 የትምህርት ዓመት የት/ቤት ቀን መቁጠሪያ ላይ የቀረቡ ማሻሻያዎችን ተወያይቷል። የሜሪላንድ ስቴት የትምህርት ቦርድ የሕዝብ ትምህርት ቤቶች የትምህርት አመታቸውን እስከ ጁን 18, 2027 ድረስ እንዲያጠናቅቁ ባወጣው ደንብ ምክንያት፣ ቦርዱ የትምህርት ቤቶችን የቀን መቁጠሪያ ማሻሻል ያስፈልገዋል። ለውጦች የሚከተሉትን ሊነኩ ይችላሉ፦- የሃይማኖት ክብረበዓላት ቀኖችን፣ የክረምት/ዊንተር እና/ወይም የጸደይ/የስፕሪንግ ዕረፍት ቀናትን ማሳጠር፣ ወይም ምናልባትም የትምህርት ዓመቱን በኦገስት ወር መጀመሪያ ላይ እንዲጀምሩ ማድረግ ይችላል።

MCPS በእነዚህ ለውጦች ላይ የማህበረሰቡን አስተያየት መስማት ይፈልጋል። እባክዎ ይህንን የዳሰሳ ጥናት ይሙሉና በሚቀጥለው ዓመት የትምህርት ቤት የቀን መቁጠሪያ ላይ ለውጦችን ለማድረግ ምርጫዎን ያሳውቁን።  

ቦርዱ ኤፕሪል 30 በሚካሄደው የሥራ ስብሰባ የመጨረሻ ውሳኔ ይሰጣል። 

 
  ለጸደይ/ለስፕሪንግ የትምሕርት መመዘኛዎች/ግምገማዎች መዘጋጀት፡ ቤተሰቦች በቤት ውስጥ እንዴት መርዳት እንደሚችሉ

አሁን በአራተኛው ሩብ ዓመት ላይ ስለሆንን፣ ተማሪዎች በክፍል ውስጥ የሜሪላንድ አጠቃላይ የትምሕርት ግምገማ ፕሮግራም (MCAP) ጥቅም ላይ ከሚውሉት የትምህርት ይዘቶች እና መሳሪያዎች ጋር ለመተዋወቅ በክፍል ውስጥ የልምምድ ጥያቄዎችን መልመጃዎች እየሠሩ ሲሆን ይህም ተማሪዎች የሚያውቁትን፣ የቀሰሙትን፣ እና የሙሉ ዓመት ትምህርት ከጨረሱ በኋላ ምን ማድረግ እንደሚችሉ የሚለኩ የዓመቱ የመጨረሻ ግምገማዎች አካል ነው።

ቤተሰቦች ተማሪዎቻቸውን በቤት ውስጥ በሚከተሉት ሁኔታዎች መርዳት ይችላሉ፦

  • ልጅዎ ጥያቄ ሲመልስ/ስትመልስ ሀሳቡን እንዲያብራራ/እንድታብራራ መጠየቅ።
  • በጥንቃቄ ማንበብ፣ ማስረጃ መጠቀም፣ እና ስራቸውን መፈተሽ የመሳሰሉ ስልቶችን መተግበር። 
  • ልጅዎ ሁሉንም በአንድ ጊዜ ከማከናወን ይልቅ በየቀኑ ትንሽ በትንሽ ልምምድ እንዲያደርግ/እንድታደርግ ማበረታታት።
  • ስህተቶች የመማር አካል እንደሆኑ እና አእምሮ እንዲዳብር የሚረዱ መሆኑን እንዲያውቅ/እንድታውቅ ልጅዎን ማሳሰብ።
  • ልጅዎ ተረጋግቶ(ታ) መሥራት፣ በጥንቃቄ ማንበብ እና የሠራ(ች)ውን ስራ እንዲፈትሽ/እንድትፈትሽ መርዳት።

እንዲሁም ቀደም ሲል በፈተና መርሃ ግብሩ ላይ ስለሚደረጉ ለውጦች እና ተማሪዎ ለመጪዎቹ የትምህርት ምዘናዎች/ግምገማዎች እንዲዘጋጅ/እንድትጋጅ እንዴት መርዳት እንደሚችሉ ለቤተሰቦች መረጃዎችን አጋርተናል

 
  ለ 2026–2027 የትምህርት አመት የታቀደ የትምህርት ቤት ምግብ የዋጋ ጭማሪ

የትምህርት ቦርድ ዛሬ (ኤፕሪል 16) ባካሄደው የሥራ ክፍለ ጊዜ የቀረበለትን ሃሳብ በማድመጥ 2026-2027 የትምህርት አመት ላይ የትምህርት ቤት የምግብ ዋጋ በ 30 ሳንቲም መጨመር በሚቻልበት ሀሳብ ላይ ተወያይቷል። ከዚህ በፊት የትምህርት ቤት የምግብ ዋጋ የተጨመረው 2015 የበጀት ዓመት ላይ ነበር። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ በምግብ እና በሠራተኛ ጉልበት ወጪዎች ላይ ከፍተኛ ጭማሪ ታይቷል። MCPS በአካባቢው ከሚገኙት የትምህርት ቤት ዲስትሪክቶች ጋር ሲነጻጸር ዝቅተኛ የትምህርት ቤት ምግብ ዋጋ አለው። 

ቦርዱ ኤፕሪል 30 በሚካሄደው የሥራ ስብሰባ የመጨረሻ ውሳኔ ይሰጣል። 

በፓወር ፖይንት የቀረበውን ይመልከቱ.

 
  የትምህርት ቦርድ ወቅታዊ መረጃ፦ MCPS የትምህርት ቤቶች ደህንነት

ዛሬ ቀደም ብሎ (ኤፕሪል 16)፣ የትምህርት ቦርድ MCPS ትምህርት ቤቶች ውስጥ ስለሚደረጉ የደህንነት ጥበቃ ጥረቶች ወቅታዊ መረጃዎችን አድምጧል። የት/ቤት ሰራተኞች ስለ ስልጠና፣ ስለ ትምህርት ቤት ደህንነት ኦዲት እና በቴክኖሎጂ አማካኝነት የደህንነት ጥበቃን ስለማጠናከርና መሻሻል እንዲሁም ስለ ቀጣይ ተግዳሮቶች የሚያሳዩ መረጃዎችን አጋርተዋል። በቅርቡ በተካሄደ የተማሪዎች፣ የሰራተኞች፣ እና የቤተሰብ የዳሰሳ ጥናት በተገኘ አስተያየት በት/ቤቶች ደህንነት ጥረቶች ዙሪያ የበለጠ የሚታይ እና ግንኙነት መኖር አስፈላጊ መሆኑን በጉልህ ተመልክቷል። እዚህ ይበልጥ ያንብቡ

 

“Senior Assassins” Game: ቅድሚያ ስለ ደህንነት ማሳሰቢያ

በዚህ የጸደይ/ስፕሪንግ ወቅት ሲንየሮች ወሳኝ የስኬት ጊዜያቸውን ሲያከብሩ፣ ቤተሰቦችን ስለ “Senior Assassins” Game. ጋር የተያያዙ አደጋዎች ለማስታወስ እንፈልጋለን። ይህ እንቅስቃሴ ለመዝናኛ የታሰበ ቢሆንም፣ ብዙውን ጊዜ የውሃ ሽጉጦችን እና ማህበራዊ ሚዲያዎችን የሚያካትት በመሆኑ፣ በግድየለሽነት መንዳት፣ ደንብ/ህግ መጣስ እና ሕዝብ በሚበዛባቸው ቦታዎች ላይ አስደንጋጭ ሁኔታዎችን የመሳሰሉ አደገኛ ባህሪያት ጋር የተያያዘ ነው።

በአሻንጉሊት የውሃ ሽጉጦች እንኳን እንደ እውነተኛ የጦር መሳሪያዎች ሊታለሉ ይችላሉ፣ ይህም ከባድ መዘዞችን ያስከትላል። በዚህ አይነት ጨዋታ እንዳይሳተፉ አጥብቀን እናበረታታለን እንዲሁም ቤተሰቦች ከተማሪዎቻቸው ጋር ደህንነቱ የተጠበቀ እና ኃላፊነት የተሞላበት ምርጫዎችን እንዲያደርጉ እናበረታታለን። ለሁሉም ተማሪዎች የትምህርት አመቱ አዎንታዊ እና ደህንነቱ የተጠበቀ እንዲሆን ተባብረን እንስራ።

 
  የቅርብ ጊዜ EdTalk፡በትምህርት ዘርፍ የሴቶች መሪነት

EdTalk በቅርብ ጊዜ መግለጫ ላይ፣ የትምህርት ቦርድ (BOE) ፕሬዝዳንት ግሬስ ሪቪዬራ-ኦቨን ከአሜሪካ የማህበረሰብ ኮሌጆች ማህበር ፕሬዝዳንት እና ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ዴሪዮን ፖላርድ እና የትምህርት ቦርድ አባል ከሆኑት ካርላ ሲልቬስትሬ ጋር ውይይት ያደርጋሉ። በትምህርት ረገድ የሴቶች መሪዎች ያላቸውን ጠቀሜታ እና የሚያመጡትን ግንዛቤ፣ እንዲሁም ወጣት ሴቶችን የመምከር አስፈላጊነት እና ሴቶች በትምህርት አመራር ውስጥ ያበረከቱትን ጉልህ እድገት እና አስተዋፅዖዎች ይወያያሉ። እዚህ ይመልከቱ.

 
  ወጣቶቻችንን ለመደገፍ እና ደህንነቱ የተጠበቀ ማህበረሰብ ለመገንባት ኤፕሪል 18 ላይ ይቀላቀሉን

የሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የአእምሮ ጤና እና የአደንዛዥ ዕፅ አጠቃቀም መከላከል የቤተሰብ መድረክ ቅዳሜ፣ ኤፕሪል 18 ከቀኑ 1–4 p.m. በሞንትጎመሪ ብሌር ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ ይካሄዳል። አድራሻ፦ Montgomery Blair High School, 51 University Blvd. East in Silver Spring. ይህ ዝግጅት ነፃ እና ለተማሪዎች፣ ለቤተሰቦች፣ ለሠራተኞች፣ እና ለማህበረሰብ አባላት ክፍት ነው። የሚሳተፉ ተማሪዎች 3 የተማሪ አገልግሎት ትምህርት ሰዓት ማግኘት ይችላሉ። አውደጥናቱ የሚካሄደው በእንግሊዝኛ እና በስፓንሽኛ ቋንቋዎች ነው። ተጨማሪ ግንዛቤ ይውሰዱ

 
  ለመጨረሻ ጊዜ ያገለገሉ መኪናዎች እና የኮምፒውተሮች ሽያጭ ሜይ 9 ይጠናቀቃል።

ያገለገሉ መኪኖችና የኮምፒውተሮች የትምህርት ዓመቱ የመጨረሻ ሽያጭ ቅዳሜ፣ ሜይ 9 ከጠዋቱ 9–11 a.m. ሲልቨር ስፕሪንግ በሚገኘው ቶማስ ኤዲሰን ሁለተኛ ደረጃ የቴክኖሎጂ ትምህርት ቤት ይካሄዳል። አድራሻ፦ Thomas Edison High School of Technology, 12501 Dalewood Drive in Silver Spring የሞንትጎመሪ ካውንቲ ተማሪዎች የአውቶሞቲቭ ትሬድስ ፋውንዴሽን (ATF) እና የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፋውንዴሽን (ITF) ለክፍል እና ለላብራቶሪ ትምሕርታቸው የተጠቀሙባቸውን ያገለገሉ መኪኖችን እና ኮምፒውተሮችን ይሸጣሉ። ተጨማሪ መረጃ እዚህ ይለጠፋል።

 
  ስለ ልዩ ትምህርት አገልግሎቶች/Special Ed Services፣ የሰው ኃይል እና ድጋፍ የቅርብ ጊዜ መረጃ ማግኘትዎን ያረጋግጡ።

የልዩ ድጋፍ አገልግሎቶች ክፍል ረቡዕ፣ ሜይ 6 ከቀኑ 6-7:30 p.m. ለቤተሰቦች ዌቢናር ፕሮግራም ያካሂዳል፣ ይህም በልዩ ትምህርት አገልግሎቶች፣ በሠራተኞች አደረጃጀት እና በድጋፍ አሰጣጥ ዙርያ ምን አዲስ ነገር እንዳለ— እና ለምን አስፈላጊ እንደሆነ — መሰጠት ባለበት አፅንኦት ላይ ያተኩራል። MCPS የልዩ ትምህርት መሪዎች ይህ ለትምህርት ቤቶች እና ለመማሪያ ክፍሎች ምን ማለት እንደሆነ አውድ ይሰጣል። ክፍለ ጊዜው በቨርቹዋል የሚካሄድ ሲሆን ከጥያቄዎችና መልሶች ጋር በአጭር አቀራረብ ይከናወናል። የዙም ሊንክ እዚህ ይገኛል።

የልዩ ትምህርት ቤተሰቦችን የሚመለከት ሁለት ተጨማሪ ዝግጅቶች አሉ -- ይኼውም ኤፕሪል 23 የሚካሄደው ወርሃዊ SECAC ስብሰባ እና ሜይ 9 የሚካሄደው የልዩ ትምህርት የቤተሰብ መገልገያ/ሪሶርስ ትርኢት ነው። እዚህ ይበልጥ ያንብቡ

 
  ሜይ 16 በጌትስበርግ እንገናኝ፡ ለሁሉም ዕድሜ የሚሆን የመጽሐፍት ፌስቲቫል ይካሄዳል።

የጌትስበርግ የመጽሐፍት ፌስቲቫል፣ የመጻሕፍት፣ የደራሲዎች፣ እና የስነ-ጽሑፍ ብቃት ክብረ በዓል፣ ቅዳሜ፣ ሜይ 16 ከጠዋቱ 10 a.m. to 6 p.m. ጌትስበርግ በሚገኘው ቦኽረር ፓርክ ይካሄዳል። አድራሻ፦ Bohrer Park, 506 S. Frederick Avenue in Gaithersburg. በፌስቲቫሉ ላይ የበርካታ ደራሲዎች ስብስብ እና በሁሉም እድሜ ለሚገኙ ህጻናት ተስማሚ የሆኑ እንቅስቃሴዎች ይቀባሉ። ልጆች የማንበብ፣ የመጻፍ፣ እና የትወና ፍላጎታቸውን ለማሳደግ የሚጠቅሟቸው ፕሮግራሞች፣ አውደ ጥናቶች፣ እና እንቅስቃሴዎች ይኖራሉ። ከ100 በላይ ደራሲያን እና ሥዕላዊ መግለጫዎች እንደሚቀርቡ ታቅዷል፤ ከእነዚህም ውስጥ የአሁንና የቀድሞ የሞንትጎምሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) አስተማሪዎች ይገኙበታል። መግቢያ እና መኪና ማቆሚያ በነፃ ነው።

 
  ለመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የሠመር ኮድ መስጫ ካምፕ በነፃ ትምህርት ይሰጣል።"Free Summer Coding Camp"

ሞንትጎመሪ ካን ኮድ የሠመር ካምፕ "Montgomery Can Code’s summer camp" ለሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) 6ኛ፣7ኛ፣ እና 8ኛ ክፍል ተማሪዎች ለአንድ ሳምንት የሚካሄድ ካምፕ ነው። በካምፑ ውስጥ የሚቆዩ ተሳታፊዎች ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ መተግበሪያዎችን ለመፍጠር ፕሮፌሽናል አልሚዎች በሚጠቀሙት ለመረዳት ቀላል በሆነው አፕል ስዊፍት ኮድ ማድረግን ይማራሉ። በጁላይ ወር በሞንትጎመሪ ኮሌጅ ሁለት በአካል የሚደረጉ ስብሰባዎች ይካሄዳሉ፤ ሶስተኛ ሳምንት ላይ ደግሞ በቨርቹዋል ይካሄዳል።

Learn more: English / español / 中文 / français / Português / 한국어 / tiếng Việt / አማርኛ

 
  ማሳሰቢያ
 
  ወደ ተግባር መስፈንጠር/Spring Into Action

4ኛ እስከ 12ኛ ክፍል የሚገኙ ወንድ ተማሪዎች ቅዳሜ፣ ኤፕሪል 25 ከጠዋቱ 8 a.m. እስከ እኩለ ቀን ድረስ በሞንትጎመሪ ኮሌጅ፣ ጀርመንታውን ካምፓስ ውስጥ በሚካሄደው 2026 የጸደይ/ስፕሪንግ ጨዋታ ቀያሪ የወጣት ወንዶች ኮንፈረንስ ላይ እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል። ምዝገባ ሰኞ፣ ኤፕሪል 20 ይዘጋል። ይመዝገቡ/Register. ለአፍሪካን-አሜሪካን እና ለማይኖሪቲ ተማሪዎች የተዘጋጀ ኮንፈረንስ ስለ ማህበራዊ-ስሜታዊ ደህንነት እና በራስ መተማመንን ለመገንባት የተነደፈ ነው።

ለተማሪዎች ሌሎች እድሎች፦

  • 11ኛው አመታዊ G.L.O.W. (ዓለማችንን እየመሩ ያሉ ልጃገረዶች) የሙያ ጉባኤ፡ ከ 8ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያሉ ሴት ተማሪዎች ቅዳሜ፣ ኤፕሪል 18 በሚካሄደው የሙሉ ቀን ኮንፈረንስ ላይ ፓነሎችን፣ አውደ ጥናቶችን እና ኔትወርኪንግን እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል።
  • NAACP የወጣቶች ስብሰባ: ቅዳሜ፣ ኤፕሪል 18 10 a.m.-2 p.m. , በሪቻርድ ሞንትጎሞሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት/Richard Montgomery High School. ይህ ነፃ ዝግጅት ለሁሉም ተማሪዎች ክፍት ሲሆን ስለ አመራር ክህሎት አውደ ጥናቶችን፣ የተማሪዎች የፓናል ውይይቶችን እና ሀሳብን የማንፀባረቅ እና የማቀንቀን ዘመቻ እድሎችን ይሰጣል። ምሳ፣ ትራንስፖርት፣ እና SSL የአገልግሎት ሰዓት ይሰጣል።
  • ዓመታዊ የሥራ ፈላጊዎች ቃለ መጠይቅ ቀን፡ ማክሰኞ፣ ሜይ 19 ከጠዋቱ 10 a.m.-2 p.m. ይካሄዳል። ከተመረቁ በኋላ ወዲያውኑ ሥራ ለመጀመር ለሚፈልጉ ሲንየር ተማሪዎች ክፍት ነው።
  • ስለ ደህንነት የሚቀነቀንበት ቀን፦ በዚህ ነፃ ዝግጅት ላይ ስለ እግረኞች ደህንነት፣ ወደ ትምህርት ቤት የሚወስዱ አስተማማኝ መንገዶች እና እይታን ስለሚጋርዱ ሁኔታዎች/ቪዥን ዜሮ ፕሮግራም ቅዳሜ፣ ሜይ 9 ከጠዋቱ 11 a.m. እስከ 3 p.m. ድረስ ሮክቪል በሚገኘው ካርቨር የትምህርት አገልግሎት ማዕከል ዝግጅት ይካሄዳል። አድራሻ፦ Carver Educational Services Center, 850 Hungerford Drive in Rockville
 
  በዜና ገጾቻችን ላይ የቅርብ ጊዜ ዘገባዎችን ይመልከቱ
 
  ከእኛ ጋር ግንኙነትዎን ይቀጥሉ
 

በመካሄድ ላይ ያሉ ክፍት ምዝገባዎች

 

MCPS የበለጠ መረጃ ያግኙ

Facebook X.com Instagram Youtube Flickr Linkedin
በዚህ አድራሻ ኢሜል ያድርጉልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ Montgomery County Public Schools
©1995–2026 Montgomery County Public Schools