MCPS የሳምንቱ ወቅታዊ መረጃ — መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ አርማ

አበይት ጉዳዮች

ኤፕሪል 23, 2026

 
English / español / 中文 / français / Português / 한국어 / tiếng Việt / አማርኛ/Amharic
 
  ስለ MCPS ያለዎትን ልምድ መስማት እንፈልጋለን!

MCPS እስከ ሜይ 10 ድረስ ክፍት በሆነው አመታዊ የዳሰሳ ጥናታችን ልምዶቻችሁን እና አመለካከቶቻችሁን እንድታካፍሉን ቤተሰቦችን እና ተማሪዎችን ይጋብዛል።

ቀደም ሲል ይሄ "የትምህርት ቤት ድባብ እና ባህል ጥናት" ተብሎ ይጠራ ነበር፣ ነገር ግን ምንም ስለ አየር ሁኔታ የሚመለከት አይደለም። በትምህርት ቤቶቻችን ውስጥ ስላለዎት ልምድ እና እንዴት ማሻሻል እንደምንችል ግብረመልስ ለማግኘት ነው። ተጨማሪ ይወቁ እና የዳሰሳ ጥናቱን ሞልተው ይመልሱ። 

ቤተሰቦች፦ የዳሰሳ ጥናቱን ሞልተው ይመልሱ
ተማሪዎች፦ የዳሰሳ ጥናቱን ሞልታችሁ መልሱ። ዘንድሮ *አዲስ ነገር*፦ የተማሪ መታወቂያ ቁጥር መሙላት አያስፈልግም! 

 
  የፍላወር ሂል ፋይን የዓመቱ የብሔራዊ እውቅና ያገኘ ርዕሰ መምህር ተብሎ ተሰይሟል

በጌትስበርግ በሚገኘው የፍላወር ሂል አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር የሆኑት ዶ/ር ጆሽ ፊኔ በሜሪላንድ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህራን ማህበር የዓመቱ ብሔራዊ አክብሮት ያላቸው ርዕሰ መምህር ሆነው ተመርጠዋል።

በ 2025፣ ፊኔ የዋሽንግተን ፖስት የአመቱ ምርጥ ርዕሰ መምህር ተብለው ተሰይመዋል፣ ለሰራተኞቻቸው እና ለተማሪዎቻቸው ምቹ የሆነ የትምህርት አካባቢ ለመፍጠር ካላቸው የዕለት ተዕለት ፍላጎታቸው ባሻገር በመሥራታቸው እውቅና አግኝተዋል፣ እንዲሁም በአካዳሚክ ልቀትን፣ አዎንታዊ የሰው ልጅ ግንኙነቶችን እና የማህበረሰብ ተደራሽነትን በማሳደግ ረገድ ከ MCPS የተበረከተውን የማርክ ማን ኤክሴልሽን እና ሃርሞኒ ሽልማት አሸንፈዋል።

 
  ልዑል ዳዊት የቦርዱ ቀጣይ የተማሪ አባል ሆነው ተመርጠዋል

በኖርዝዉድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 10ኛ ክፍል ተማሪ የሆኑት ልዑል ዳዊት ለ 2026-2027 የትምህርት አመት የትምህርት ቦርድ (SMOB) ተማሪ አባል ሆነው ተመርጠዋል። የአቶ ዳዊት የቦርድ አባልነት አገልግሎት ዘመን የሚጀምረው ጁላይ 1, 2026 ነው። ዳዊት በጁን ወር የሚመረቀውን የሞንትጎመሪ ብሌር ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ የሆነውን አኑቫ ማሉን ይተካሉ። 49ኛ ተማሪ የቦርድ አባል ይሆናል። እዚህ ይበልጥ ያንብቡ።
 

 
  2026-2027 የቀን መቁጠሪያ/ካለንደር አማራጮች የዳሰሳ ጥናቱን ይሙሉ!

2026–2027 የትምህርት ቤት የቀን መቁጠሪያ/ካለንደር ለመቅረጽ ያግዙ! የሜሪላንድ ስቴት የትምህርት ቦርድ ትምህርት ቤቶች እስከ ጁን 19, 2027 ድረስ እንዲያጠናቅቁ ባወጣው መስፈርት መሰረት፣ MCPS ኦገስት መጀመሪያ ላይ ት/ቤት መጀመር፣ የዊንተር እና/ወይም የስፕሪንግ (ጸደይ) የእረፍት ቀናት ላይ ማስተካከያ ማድረግ፣ ወይም የሃይማኖታዊ ክብረ በዓላትን ቀናትን መርጦ እንደ ትምህርት ማካካሻ ቀናት መጠቀም በመሳሰሉ አማራጮች ላይ አስተያየትዎን እንዲሰጡን እንፈልጋለን። እርስዎ የሚሰጡን አስተያየት በጣም አስፈላጊ ነው። የዳሰሳ ጥናቱን ዛሬውኑ ይሙሉ!

 
  ልጅዎ በጸደይ ወቅት በሚካሄደው የትምህርት ግምገማዎች ላይ እንዲሳካ ለመርዳት — ቤተሰቦች ምን ማድረግ እንደሚችሉ፦

ወደ ትምህርት ዓመቱ ማጠቃለያ እየተቃረብን ስለሆነ፣ ተማሪዎች በሜሪላንድ አጠቃላይ የትምህርት ግምገማ ፕሮግራም (MCAP) ላይ በጥቅም ላይ የዋሉትን የፈተና ይዘቶች እና የትምህርት መርጃ መሳሪያዎችን አጠቃቀም ለማወቅ በክፍል ውስጥ የልምምድ/የመልመጃ ጥያቄዎችን ሲሠሩና ሲለማመዱ ቆይተዋል። እነዚህ የዓመቱ መጨረሻ የትምህርት ግምገማዎች ተማሪዎች የሚያውቁትን ያህል፣ የሚገነዘቡትን፣ እና የሙሉ ዓመት ትምህርት ከጨረሱ በኋላ ማድረግ የሚችሉትን ለመመዘን/ለመለካት የታለሙ ናቸው።

የስቴት ፈተና ኤፕሪል 28 ይጀምራል፣ እና እስከ ሜይ ድረስ ይቀጥላል፣ ይህም ተማሪዎች ፈተና ከመጀመሩ በፊት መማር ያለባቸውን እንዲያጠናቅቁ ተጨማሪ ጊዜ ይሰጣቸዋል። የፈተና ቀናት እየተቃረቡ ሲሄዱ፣ ትናንሽ የዕለት ተዕለት ተግባራት ተማሪዎች በራስ የመተማመን እና ዝግጁነት እንዲሰማቸው በማድረግ ረገድ ትልቅ ለውጥ ሊያመጡ እንደሚችሉ ያስታውሱ።

  • ከእያንዳንዱ የፈተና ቀን በፊት ልጅዎ ጥሩ የሌሊት እንቅልፍ ማግኘቱ(ቷ)ን ያረጋግጡ።
  • ጤነኛ ቁርስ ይስጡ(ጧ)ት።
  • ልጅዎ ትምህርት ቤት በሰዓቱ እንዲደርስ/እንድትደርስ እና ፈተና ለመሥራት ዝግጁ እንዲሆን/እንድትሆን ያግዙ(ዟ)ት።
  • ስለሚሰጠው ፈተና አዎንታዊ አስተሳሰብ እንዲኖረው/እንዲኖራት ያበረታቱ - ልጅዎ የተቻላቸውን ሁሉ እንዲሞክር/እንድትሞክር እና የተማረ(ች)ውን ስልቶች እንዲጠቀም/እንድትጠቀም ያስታውሱ(ሷ)ት።

ተማሪዎች በተሳካ ሁኔታ ለመፈተን ምን ማወቅ እንዳለባቸው የሚያስታውሱ ጠቃሚ አንድ ገጽ የመረጃ ጽሑፍ እነሆ።

ቤተሰቦች የጊዜ ሰሌዳዎችንና ወቅታዊ መረጃዎችን በሚመለከት በቀጥታ ከልጆቻቸው ትምህርት ቤት ይሰማሉ።

ዓመቱን በጋራ — ጠንክረን እንጨርሰው።

Watch in English | Spanish | French | Chinese | Vietnamese | አማርኛ/Amharic | Korean | Portuguese

 
  በጁላይ ወር በትክክለኛው መንገድ ለመቀጠል — ለሠመር ትምህርት ቤት ያስመዝግቡ

ለሠመር ትምህርት ቤት ምዝገባ ክፍት ነው! MCPS በእነዚህ ስድስት ቦታዎች — አርጋይል፣ ኢስተርን፣ ፎረስት ኦክ፣ ፍራንሲስ ስኮት ኪይ፣ ጁሊየስ ዌስት እና ሮኪ ሂል — የሂሳብ እና የሊተርሲ ችሎታን ለማጎልበት በኢግናይት መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አካዳሚ ትምሕርት ይሰጣል። ነፃ የትራንስፖርት አገልግሎት ይኖራል፤ የትምህርት ሠዓት ካበቃ በኋላ ለሚሰጥ የእንክብካቤ አገልግሎት ክፍያ ይኖራል። ምዝገባ የሚፈጸመው ParentVueላይ ነው። MCPS በአካል እና ቨርቹዋል የሠመር ትምህርት ፕሮግራም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ይሰጣል። የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ለመመዝገብ ከካውንስለሮቻቸው ጋር መነጋገር አለባቸው። 

ተጨማሪ መረጃ

 
  ቤተሰቦች ለአስፈላጊ የድጋፍ አገልግሎት አዲስ የሪሶርስ መመሪያ

MCPS የልዩ ድጋፍ አገልግሎቶች ክፍል ለቤተሰቦች የማህበረሰብ ሪሶርስ መመሪያ አዘጋጅቷል። መመሪያው በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የትምህርት ቤት እና የማህበረሰብ ሪሶርሶችን/መገልገያዎችን ዝርዝር ያካትታል፤ ከእነዚህም ውስጥ የጤና አጠባበቅ እና የአእምሮ ጤና አገልግሎቶች ተደራሽነት፤ በምግብ፣ በልብስ፣ በቤት ዕቃዎች፣ በመኖሪያ ቤት እና በመገልገያዎች ስለሚደረግ ድጋፍ፤ የወጣቶች ልማት እና ካውንስሊንግ፤ የቤት ውስጥ ጥቃት፤ የሥራ ግብረ ኃይል፤ ትምህርት እና የቴክኖሎጂ፤ ዓለም አቀፍ ቤተሰቦች እና ሌሎችንም ያካትታል።

 
  2026 የተማሪዎች ምረቃ መርሃ ግብር አሁን ተዘጋጅቷል

የዘንድሮው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የምረቃ ሥነ-ሥርዓቶች ከሐሙስ፣ ሜይ 28 እስከ ጁን 12 ይካሄዳሉ። አብዛኛዎቹ የምረቃ ፕሮግራሞች የሚካሄዱት በባልቲሞር ካውንቲ፣ ሜሪላንድ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ነው።

የእያንዳንዱ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የምረቃ ፕሮግራም ላይ ተናጋሪዎች፣ ቀናት፣ ቦታዎች እና ሰዓቶች

 
  ስለ ልዩ ትምህርት ምን አዲስ ነገር አለ? ሜይ 6 ዌቢናር ላይ ያገኛሉ

የልዩ ድጋፍ አገልግሎቶች ክፍል ረቡዕ፣ ሜይ 6 ከቀኑ 6-7:30 p.m. ለቤተሰቦች ዌቢናር ፕሮግራም ያካሂዳል፣ ይህም በልዩ ትምህርት አገልግሎቶች፣ በሠራተኞች አደረጃጀት እና በድጋፍ አሰጣጥ ዙርያ ምን አዲስ ነገር እንዳለ— እና ለምን አስፈላጊ እንደሆነ — መሰጠት ባለበት አፅንኦት ላይ ያተኩራል። MCPS የልዩ ትምህርት መሪዎች ይህ ለትምህርት ቤቶች እና ለመማሪያ ክፍሎች ምን ማለት እንደሆነ አውድ ይሰጣል። ክፍለ ጊዜው በቨርቹዋል የሚካሄድ ሲሆን ከጥያቄዎችና መልሶች ጋር በአጭር አቀራረብ ይከናወናል። የዙም ሊንክ እዚህ ይገኛል

እንዲሁም ቅዳሜ፣ ሜይ 9 ከጠዋቱ a.m.- 1 p.m. ፔይንት ብራንች ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሚካሄደውን የልዩ ትምህርት የቤተሰብ ሪሶርስ አውደ ርዕይ እንዳያመልጥዎ። እዚህ ይበልጥ ያንብቡ

 
  ማሳሰቢያ
 
  ለተማሪዎች የተዘጋጁ እድሎች
  • ጨዋታ ቀያሪ የጸደይ/የስፕሪንግ ኮንፈረንስ፡ ቅዳሜ፣ ኤፕሪል 25 በሞንትጎመሪ ኮሌጅ፣ ጀርመንታውን ካምፓስ ይካሄዳል። ይህ ኮንፈረንስ 4ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ላሉ አፍሪካን አሜሪካንስ እና አናሳ ቁጥር ያላቸው ማህበረሰብ ወንድ ተማሪዎች ክፍት ሲሆን ማህበራዊ-ስሜታዊ ደህንነት እና በራስ መተማመንን ለመገንባት የተዘጋጀ ነው።
  • ሮክቪል የሳይንስ ቀን፡- እሁድ፣ ኤፕሪል 26 በሮክቪል ካምፓስ፣ ሞንትጎመሪ ኮሌጅ ከ 120 በላይ ኤግዚቢቶች በሚታዩበት የሞንትጎመሪ ካውንቲ ትልቁ STEM ፌስቲቫል ላይ ለመሳተፍ እቅድ ያዙ።
  • Montgomery Can Code፡ ይህ ነፃ ሳምንት የሚቆይ የሠመር ካምፕ 6ኛ፣ 7ኛ፣ እና 8ኛ ክፍል ለሚማሩ MCPS ተማሪዎች ክፍት ነው።
    እዚህ የበለጠ መረጃ ማግኘት ይችላሉ፦ : English / español / 中文 / français / Português / 한국어 / tiếng Việt / አማርኛ
  • ዓመታዊ የሥራ ፈላጊዎች ቃለ መጠይቅ ቀን፡ ማክሰኞ፣ ሜይ 19 ከጠዋቱ 10 a.m.-2 p.m. ይካሄዳል። ከተመረቁ በኋላ ወዲያውኑ ሥራ ለመጀመር ለሚፈልጉ ሲንየር ተማሪዎች ክፍት ነው።
  • ስለ ደህንነት የሚቀነቀንበት ቀን፦ በዚህ ነፃ ዝግጅት ላይ ስለ እግረኞች ደህንነት፣ ወደ ትምህርት ቤት የሚወስዱ አስተማማኝ መንገዶች እና እይታን ስለሚጋርዱ ሁኔታዎች/ቪዥን ዜሮ ፕሮግራም ቅዳሜ፣ ሜይ 9 ከጠዋቱ 11 a.m. እስከ 3 p.m. ድረስ ሮክቪል በሚገኘው ካርቨር የትምህርት አገልግሎት ማዕከል ዝግጅት ይካሄዳል። አድራሻ፦ Carver Educational Services Center, 850 Hungerford Drive in Rockville
  • KID ሙዚየም ለተማሪዎች የሠመር ካምፖችን እና ነፃ ኢንቬስት ዘ ፊውቸር ኤክስፖ እድሎችን ይሰጣል። የሠመር ካምፖች ከጁን 22–ኦገስት ድረስ ከመዋዕለ ሕፃናት እስከ 8ኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች ይሰጣል። 21, 9 a.m.-4 p.m. ኢንቬስት ዘ ፊውቸር ኤክስፖ እሁድ፣ ሜይ 31 ከጠዋቱ 10 a.m.-2p.m. በዚህ አድራሻ፦3 Bethesda Metro Center ይካሄዳል። ይመዝገቡ/Register። 
 
  የዜና አምድ
 
  ከእኛ ጋር ግንኙነትዎን ይቀጥሉ
 

በመካሄድ ላይ ያሉ ክፍት ምዝገባዎች

 

MCPS የበለጠ መረጃ ያግኙ

Facebook X.com Instagram Youtube Flickr Linkedin
በዚህ አድራሻ ኢሜል ያድርጉልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ Montgomery County Public Schools
©1995–2026 Montgomery County Public Schools