MCPS የሳምንቱ ወቅታዊ መረጃ — መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ አርማ

አበይት ጉዳዮች

ኤፕሪል 30, 2026

 
English / español / 中文 / français / Português / 한국어 / tiếng Việt / አማርኛ/Amharic
 
  ስለ MCPS ያለዎትን ልምድ መስማት እንፈልጋለን!

አታንከባልሉት - ከእርስዎ መስማት እንፈልጋለን። ከ 10 ደቂቃ ባነሰ ጊዜ ውስጥ፣ እንደ ዲስትሪክት ጥሩ እየተሰራ ያለውን እና ከአካዳሚክ ባለሙያዎች ጋር ምን ማሻሻል እንዳለብን ሃሳብዎን ያጋሩን።

እና አጠቃላይ ከትምህርት ቤት እና ከቢሮዎች ጋር ስላለው የግንኙነት ሁኔታ እርስዎ የሚሰጡን አስተያየትና ግብአት ጠቃሚና አስፈላጊ ነው። ይህ አስፈላጊ ዓመታዊ የዳሰሳ ጥናት እስከ ሜይ 10 ድረስ ክፍት ነው።ተጨማሪ ይወቁ እና የዳሰሳ ጥናቱን ሞልተው ይመልሱ

ቤተሰቦች፦ የዳሰሳ ጥናቱን ሞልተው ይመልሱ
ተማሪዎች፦ የዳሰሳ ጥናቱን ሞልታችሁ መልሱ። ዘንድሮ *አዲስ ነገር*፦ የተማሪ መታወቂያ ቁጥር መሙላት አያስፈልግም! 

Watch in English | Spanish | French | Chinese | Vietnamese | አማርኛ/Amharic | Korean | Portuguese

 
  MCAP ፈተና በመካሄድ ላይ ነው፡ እስከ ሜይ ድረስ የተማሪዎችን ስኬት መደገፍ

የሜሪላንድ አጠቃላይ ግምገማ ፕሮግራም (MCAP) የስቴት ፈተና አሁን በመካሄድ ላይ ነው። ፈተና መስጠት የተጀመረው ኤፕሪል 28 ሲሆን እስከ ሜይ ድረስ ይቀጥላል። እነዚህ የዓመቱ መጨረሻ የትምህርት ግምገማዎች ተማሪዎች የሚያውቁትን ያህል፣ የሚገነዘቡትን፣ እና የሙሉ ዓመት ትምህርት ከጨረሱ በኋላ ማድረግ የሚችሉትን ለመመዘን/ለመለካት የታለሙ ናቸው። በትምህርቱ ወቅት በፈተና ክፍለ ጊዜዎች ተማሪዎችን ትኩረት እንዲያደርጉ፣ ችግር/ፕሮብሌም መፍታት እና በራስ መተማመን እንዲኖራቸው ለማስቻል የሚከተሉትን ስልቶች ይማራሉ እና ይበረታታሉ። ይበልጥ ያንብቡ።

 
  ቦርዱ ከማህበረሰብ የተሰጡትን ግብዓቶች ግምት ውስጥ በማስገባት ተሻሽሎ የቀረበውን የትምህርት ዓመት 2026–2027 የትምህርት ቤት የቀን መቁጠሪያ/ካላንደር አጽድቋል።

ሐሙስ፣ ኤፕሪል 30 የትምህርት ቦርድ ከቤተሰቦች እና ከሰራተኞች በተገኘው ወጥ እና ሰፊ አስተያየቶች ላይ በመመሥረት የትምህርት ዓመት 2026–2027 የተሻሻለ የቀን መቁጠሪያ/ካላንደር አጽድቋል። የማህበረሰብ ፍላጎትን ለማሰባሰብ በተደረገው የዳሰሳ ጥናት ከ 30,000 በላይ ምላሾች ተሰጥተዋል። ቤተሰቦችና ሰራተኞች በተቻለ መጠን የተረጋጋ የትምህርት ቀናትን መጠበቅ እንደሚያስፈልግ መርጠዋል፤ ይህም የትምህርት ዓመቱን በኦገስት ወር መጀመሪያ ላይ አለመጀመርን እና የክረምት/ዊንተር እና የጸደይ/የስፕሪንግ እረፍት ጊዜያትን እንደታቀደው መጠበቅን ያካትታል። ትምህርት ቤቶች የሚጀምሩበት ቀን ማክሰኞ፣ ኦገስት 25, 2026 ይሆናል። ይበልጥ ያንብቡ። የተማሪዎች የሽግግር ቀን ሰኞ፣ ኦገስት 24, 2026 እንደሆነ ይቀጥላል።

 
 
  የትምህርት ጉዞዎን ያቀጣጥሉ - ለሠመር ትምህርት ቤት ይመዝገቡ

ለሠመር ትምህርት ቤት ምዝገባ ክፍት ነው! MCPS በኢግናይት መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አካዳሚ አማካኝነት በስድስት ማዕከሎች ላይ የሂሳብ እና የሊተርሲ ችሎታን የማዳበር ፕሮግራም ይሰጣል። ነፃ የትራንስፖርት አገልግሎት ይኖራል፤ የትምህርት ሠዓት ካበቃ በኋላ ለሚሰጥ የእንክብካቤ አገልግሎት ክፍያ ይኖራል። ምዝገባ የሚካሄደው ParentVueላይ ነው።

MCPS በአካል እና ቨርቹዋል የሠመር ትምህርት ፕሮግራም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ይሰጣል። በዚህ ሠመር፣ የተማሪዎችን በራስ መተማመን በመገንባት እና የፈተና ውጥረትን በመቀነስ ላይ በማተኮር በምርጫ የሚሰጥ አዲስ — የኮሌጅ ድርሰት ስነጽሑፍ እና የፈተና ዝግጅት ይመልከቱ። ይህ ኮርስ ከጁላይ 7-21 ወይም ከጁላይ 23 እስከ ኦገስት፤ ከሰኞ እስከ ሐሙስ ከጠዋቱ 8 a.m.–2:30 p.m.,ይካሄዳል። 6. የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ለመመዝገብ ከካውንስለሮቻቸው ጋር መነጋገር አለባቸው።

ተጨማሪ መረጃ

 
  የአንደኛ ክፍል አስተማሪ የአመቱ ኮከብ አስተማሪ በመባል ተሰይማለች

አሁን አምስተኛ ዓመቷን በማስተማር ላይ የምትገኘው ኬይላ ጃክሰን/Kayla Jackson የመጨረሻዎቹን አራት ዓመታት በመዋእለ ህጻናት በማስተማር ካሳለፈች በኋላ አንደኛ ክፍል በማስተማር የመጀመሪያ ዓመቷ ላይ ትገኛለች። በሥራ ጅማሬዋ ላይ እጅግ በጣም ጥሩ አስተማሪ የሆነችው በሞንትጎመሪ ኖልስ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የምትገኘው መምህርት በተማሪዎች ስኬት ላይ በማተኮር የተሞላች፣ እንዲሁም ተማሪዎች የራሳቸውን የትምህርት እድገት የሚከታተሉበትን ሥርዓት ታስተምራለች፣ ተማሪዎች ለራሳቸው ያወጡትን ግብ እንዲያሳኩ ታበረታታቸዋለች። ጃክሰን የዘንድሮው የሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) አንፀባራቂ ኮከብ የአመቱ ምርጥ መምህርት ሆናለች። ይበልጥ ያንብቡ።

 
  MCPS የፆታ ማንነት መመሪያ አሻሽሏል።

ከሜሪላንድ ሕግ ጋር በሚስማማ መልኩ፣ MCPS በጾታ፣ በጾታዊ ዝንባሌ እና በጾታ ማንነት ላይ የተመሠረተ ጉልበተኝነትን፣ ትንኮሳን፣ ማስፈራራትን እና መድልዎን ይከለክላል። በቅርብ ጊዜ በተደረጉ የሕግ ማሻሻያዎች ምክንያት፣ MCPS ከኤፕሪል 27, 2026 ጀምሮ ተግባራዊ የሆነ የፆታ ማንነት መመሪያ አሻሽሏል። እነዚህ ማሻሻያዎች በወላጅ መብቶች ላይ የበለጠ ትኩረት የሚሰጡ አዳዲስ የሕግ ድንጋጌዎችን ያንፀባርቃሉ። በተሻሻለው ማዕቀፍ መሠረት፣ አንድ ወላጅ ወይም አሳዳጊ ስለልጃቸው የፆታ ማንነት ሁኔታ መረጃ በተለይ ከጠየቁ ወይም ይፋ ማድረግ አስፈላጊ ከሆነ፣ የትምህርት ቤት ሰራተኞች የተጠየቀውን መረጃ የማሳወቅ/ይፋ የማድረግ ግዴታ አለባቸው። ይበልጥ ያንብቡ።

 
  ትልቅ መድረክ እየተዘጋጀ ነው

በቅርቡ ይጀመራል፡ የተማሪዎች ምረቃ ፕሮግራሞች! የዘንድሮው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የምረቃ ሥነ-ሥርዓቶች ከሐሙስ፣ ሜይ 28 እስከ አርብ፣ ጁን 12 ድረስ ይካሄዳሉ። አብዛኛዎቹ የምረቃ ፕሮግራሞች የሚካሄዱት በባልቲሞር ካውንቲ፣ ሜሪላንድ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ነው።

የእያንዳንዱ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የምረቃ ፕሮግራም ላይ ተናጋሪዎች፣ ቀናት፣ ቦታዎች እና ሰዓቶች

 
  ስለ ልዩ ትምህርት ምን አዲስ ነገር አለ? ሜይ 6 ዌቢናር ላይ ያገኛሉ

የልዩ ድጋፍ አገልግሎቶች ክፍል ረቡዕ፣ ሜይ 6 ከቀኑ 6-7:30 p.m. ለቤተሰቦች ዌቢናር ፕሮግራም ያካሂዳል፣ ይህም በልዩ ትምህርት አገልግሎቶች፣ በሠራተኞች አደረጃጀት እና በድጋፍ አሰጣጥ ዙርያ ምን አዲስ ነገር እንዳለ— እና ለምን አስፈላጊ እንደሆነ — መሰጠት ባለበት አፅንኦት ላይ ያተኩራል። MCPS የልዩ ትምህርት መሪዎች ይህ ለትምህርት ቤቶች እና ለመማሪያ ክፍሎች ምን ማለት እንደሆነ አውድ ይሰጣል። ክፍለ ጊዜው በቨርቹዋል የሚካሄድ ሲሆን ከጥያቄዎችና መልሶች ጋር በአጭር አቀራረብ ይከናወናል። የዙም ሊንክ እዚህ ይገኛል

 
  ግብዓቶችን/ሪሶርሶችን ይቃኙ፡ ልዩ Ed አውደ ርዕይ ሜይ 9 ይካሄዳል

ቅዳሜ፣ ሜይ 9 ከጠዋቱ 10 a.m.- 1 p.m. በፔይንት ብራንች ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በሚካሄደው የልዩ ትምህርት የቤተሰብ መገልገያ/ሪሶርስ አውደ ርዕይ ላይ ለመገኘት እቅድ ይያዙ። ይህ ነፃ ዝግጅት ቤተሰቦችን፣ አስተማሪዎችን እና የማህበረሰብ ድርጅቶችን ልዩ ፍላጎት ያላቸውን ግለሰቦች ለመደገፍ ከልዩ ልዩ መገልገያዎች/ሪሶርሶች እና መረጃዎች ጋር ያገናኛል። ተሳታፊዎች መረጃ መሰብሰብ፣ ጥያቄዎችን መጠየቅ፣ እና ተመሳሳይ ተግዳሮቶች የሚያጋጥሟቸው ሁሉ ከባለሙያዎች እና ከሌሎች ቤተሰቦች ጋር መገናኘት እና ልምድ መቅሰም ይችላሉ።

 
  ሥራ እየፈለጉ ነው? የአውቶቡስ አሽከርካሪዎችን እና የአውቶቡስ ረዳት ሰራተኞችን እየቀጠርን ነው!

MCPS ማክሰኞ፣ ሜይ 12 ከጠዋቱ 10:30 a.m.-12:30 p.m. ለአውቶቡስ አሽከርካሪዎችና የአውቶቡስ ረዳት ሠራተኞች የሥራ ቅጥር አውደ ርዕይ አዘጋጅቷል። የሥራ አውደርዕይ የሚካሄደው ሮክቪል በሚገኘው የትራንስፖርት አገልግሎት ዲቪዥን በሚከተለው አድራሻ ነው፦ Division of Transportation Services, 16651 Crabbs Branch Way in Rockville. ይበልጥ ያንብቡ።

MCPS ኤፕሪል 28 የትምህርት ቤት አውቶቡስ አሽከርካሪዎችን የማመስገን ቀን አክብሯል። ስለ አንዳንድ አሽከርካሪዎቻችን የበለጠ ይወቁ 

 
  ለልጆች ተፈላጊ የሆነ፡ የጎልፍ ተጫዋቾች ውድድር እና ስፖንሰሮች

RICA Association, Inc. and the Kiwanis Club of Wheaton-Silver Spring ሰኞ፣ ጁን 8 ቀን 31ኛውን አመታዊ FORE የህፃናት የጎልፍ ውድድር ያስተናግዳሉ፣ ይህም በጆን ኤል. ጊልድነር ሪጅናል የህፃናት እና ታዳጊዎች ተማሪዎችን ተጠቃሚ ያደርጋል። በሞንትጎመሪ ካንትሪ ክለብ የሚካሄደው ይህ ውድድር የጎልፍ ተጫዋቾችን፣ አራት ሆነው እንደ አንድ ቡድን የሚጫወቱ እና ስፖንሰሮችን ይፈልጋል። ተጨማሪ ግንዛቤ ያግኙ።

 
  ማሳሰቢያ
 
  ለተማሪዎች የተዘጋጁ እድሎች
  • Montgomery Can Code፡ ይህ ነፃ ሳምንት የሚቆይ የሠመር ካምፕ 6ኛ፣ 7ኛ፣ እና 8ኛ ክፍል ለሚማሩ MCPS ተማሪዎች ክፍት ነው።
    እዚህ የበለጠ መረጃ ማግኘት ይችላሉ፦ : English / español / 中文 / français / Português / 한국어 / tiếng Việt / አማርኛ
  • ዓመታዊ የሥራ ፈላጊዎች ቃለ መጠይቅ ቀን፡ ማክሰኞ፣ ሜይ 19 ከጠዋቱ 10 a.m.-2 p.m. ይካሄዳል። ከተመረቁ በኋላ ወዲያውኑ ሥራ ለመጀመር ለሚፈልጉ ሲንየር ተማሪዎች ክፍት ነው።
  • ስለ ደህንነት የሚቀነቀንበት ቀን፦ በዚህ ነፃ ዝግጅት ላይ ስለ እግረኞች ደህንነት፣ ወደ ትምህርት ቤት የሚወስዱ አስተማማኝ መንገዶች እና እይታን ስለሚጋርዱ ሁኔታዎች/ቪዥን ዜሮ ፕሮግራም ቅዳሜ፣ ሜይ 9 ከጠዋቱ 11 a.m. እስከ 3 p.m. ድረስ ሮክቪል በሚገኘው ካርቨር የትምህርት አገልግሎት ማዕከል ዝግጅት ይካሄዳል። አድራሻ፦ Carver Educational Services Center, 850 Hungerford Drive in Rockville
  • KID ሙዚየም ለተማሪዎች የሠመር ካምፖችን እና ነፃ ኢንቬስት ዘ ፊውቸር ኤክስፖ እድሎችን ይሰጣል። የሠመር ካምፖች ከጁን 22–ኦገስት ድረስ ከመዋዕለ ሕፃናት እስከ 8ኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች ይሰጣል። 21, 9 a.m.-4 p.m. ኢንቬስት ዘ ፊውቸር ኤክስፖ እሁድ፣ ሜይ 31 ከጠዋቱ 10 a.m.-2p.m. በዚህ አድራሻ፦3 Bethesda Metro Center ይካሄዳል። ይመዝገቡ/Register። 
 
  ከእኛ ጋር ግንኙነትዎን ይቀጥሉ
 

በመካሄድ ላይ ያሉ ክፍት ምዝገባዎች

 

MCPS የበለጠ መረጃ ያግኙ

Facebook X.com Instagram Youtube Flickr Linkedin
በዚህ አድራሻ ኢሜል ያድርጉልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ Montgomery County Public Schools
©1995–2026 Montgomery County Public Schools