አበይት ጉዳዮች
ሜይ 07, 2026
|
|
|
ሀሳብዎን ሊያጋሩን የቀሩት … ሦስት ቀናት ብቻ ናቸው! |
|
አትዘግዩ — ከእርስዎ መስማት እንፈልጋለን። ለዳሰሳ ጥናቱ ምላሽ ለመስጠት ሶስት ቀናት ብቻ ቀርተዋል፤ ከ 10 ደቂቃ ባነሰ ጊዜ ውስጥ ሞልተው መመለስ ይችላሉ! ዲስትሪክቱ ከትምህርትና ከማህበረሰብ ጋር ያሉ ግንኙነቶችን በሚመለከቱ ጉዳዮች አጠቃላይ ስለ ትምህርት ቤቶች እና የቢሮ ሁኔታ ምን ያህል ጥሩ እየተሰራ እንዳለ እና ምን ማሻሻል እንደሚያስፈልግ ሀሳብዎን ያካፍሉን። ከእርስዎ የምናገኘው አስተያየት/ግብዓት አስፈላጊ ነው።
ይህ አስፈላጊ ዓመታዊ የዳሰሳ ጥናት እስከ ሜይ 10 ድረስ ክፍት ነው። ተጨማሪ ይወቁ እና የዳሰሳ ጥናቱን ሞልተው ይመልሱ።
ቤተሰቦች፦ የዳሰሳ ጥናቱን ሞልተው ይመልሱ።
ተማሪዎች፦ የዳሰሳ ጥናቱን ሞልታችሁ መልሱ። የተማሪ መታወቂያ ቁጥር አያስፈልግም!
|
|
|
|
|
|
ምናልባት አምልጥዎት ከሆነ… |
|
በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ፣ MCPS እና የትምህርት ቦርድ ትላንት ምሽት 2026 የትምህርት ልህቀት ሥነ ሥርዓት ላይ ለትምህርት አስደናቂ አስተዋጽኦ ያበረከቱትን አክብሮት ሰጥተዋል። በዝግጅቱ ወቅት፣ 22 ግለሰቦች እና ድርጅቶች ለሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች ስኬት ላሳዩት ቁርጠኝነት እውቅና ተሰጥቷቸዋል፣ ዲስትሪክቱ MCPS የትምህርት አመት 2026–2027 የአመቱ ምርጥ መምህር ተብሎ ተሰይሟል። ተጨማሪ ያንብቡ እንዲሁም ፎቶዎችን ይመልከቱ። የምሽቱን ፕሮግራም ቪዲዮይመልከቱ።
|
|
|
|
|
|
ይህን ታላቅ ስራ ይቀጥሉ! |
|
የሜሪላንድ አጠቃላይ የግምገማ ፕሮግራም (MCAP) የስቴት ፈተና እየተካሄደ ሲሆን፣ ተማሪዎቻችን ጽናት እና ትኩረት በማሳየታቸው በጣም እንኮራለን።
ፈተና እየተሰጠ ባለበት ወቅት፣ወላጆች በቤት ውስጥ የሚያደርጉት ድጋፍ አሁንም አስፈላጊ ነው፡
- ተማሪዎች መደበኛ የእንቅልፍ ሠዓት ይኑራቸው።
- በፈተና ወቅት አዎንታዊ አስተሳሰብ እንዲኖራቸው እና ጥረት እንዲያደርጉ ያበረታቱ።
- ልጅዎ ጊዜ መውሰድ እና በተረጋጋ ሁኔታ የፈተና ስራውን የመፈተሽ ስልቶችን እንዲጠቀም/እንድትጠቀም ያስታውሱ(ሷ)ት።
|
|
|
|
|
|
ከግማሽ በላይ የሚሆኑ የሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ትምህርት ቤቶች አሁን የሜሪላንድ ግሪን ትምህርት ቤቶች መሆናቸው ተረጋግጧል። |
|
MCPS ስለ አካባቢ ጥበቃ እና እንክብካቤ ትምህርት 10 ተጨማሪ ትምህርት ቤቶች በትምህርት አመት 2026 የሜሪላንድ ግሪን ትምህርት ቤቶችን ታዋቂነት ስያሜ በማግኘታቸው የዲስትሪክቱ አጠቃላይ ድምር 123 የተረጋገጡ የግሪን ትምህርት ቤቶች በመሆናቸው ወደ አስደናቂ ደረጃ አድርሶታል። ይህ ስኬት 58 በመቶ የሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ትምህርት ቤቶች ይህንን እውቅና እንዳገኙ ያሳያል፣ ይህም በሞንትጎመሪ ካውንቲ የአየር ንብረት ጥበቃ እና እንክብካቤ እቅድ ከተቀመጠው 50 በመቶ ግብ የሚበልጥ ነው።
አዲስ እውቅና የተሰጣቸው ትምህርት ቤቶች እነዚህን የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ያካትታሉ፡ ቤል ፕሪ፣ በርተንስቪል፣ ክሎፐር ሚል፣ ኦክ ቪው፣ ዶ/ር ሳሊ ኬ. ራይድ፣ ስቶንጌት፣ ትዊንብሩክ እና ዋተርስ ላንዲንግ። ፓይንት ብራንች እና ዋትኪንስ ሚል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችም ይህንን እውቅና አግኝተዋል። እዚህ ይበልጥ ያንብቡ.
|
|
|
|
|
|
ቤተሰቦችንና ሪሶርሶችን አንድ ላይ የሚያገናኝ የልዩ ትምህርት አውደ ርዕይ |
|
የልዩ ትምህርት የቤተሰብ ሪሶርስ አውደ ርዕይ ቅዳሜ፣ ሜይ 9 ከጠዋቱ 10 a.m.- 1 p.m. በፔይንት ብራንች ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ይካሄዳል። ይህ ነፃ ዝግጅት ቤተሰቦችን፣ አስተማሪዎችን እና የማህበረሰብ ድርጅቶችን ልዩ ፍላጎት ያላቸውን ግለሰቦች ለመደገፍ ከልዩ ልዩ መገልገያዎች/ሪሶርሶች እና መረጃዎች ጋር ያገናኛል። ተሳታፊዎች መረጃ መሰብሰብ፣ ጥያቄዎችን መጠየቅ፣ እና ተመሳሳይ ተግዳሮቶች የሚያጋጥሟቸው ሁሉ ከባለሙያዎች እና ከሌሎች ቤተሰቦች ጋር መገናኘት እና ልምድ መቅሰም ይችላሉ።
|
|
|
|
|
|
መምህራኖቻችንን ማክበር! |
|
ትምህርት ቤቶቻችን የተገነቡት መምህራኖቻችን — እና ሁሉም የሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የሥራ ባልደረቦች — በየቀኑ ወደ ትምህርት ቤት በሚያመጡት ቁርጠኝነት፣ እውቀት፣ እና እንክብካቤ ላይ ነው። በዚህ ሳምንት፣ በተማሪዎቻችን ሕይወት ላይ ልዩ ለውጥ የሚያመጡትን አስተማሪዎች እውቅና የምንሰጥበት ብሔራዊ የመምህራን አድናቆት ሳምንት እናከብራለን። አድናቆታችንን ስንገልጽ ይቀላቀሉን — ቀላል ማስታወሻ ወይም የምስጋና መልክት በተማሪዎቻችን እና በቤተሰቦቻችን ላይ ያላቸውን ተጽእኖ በመገንዘብ ረገድ ትልቅ ሚና ሊጫወት ይችላል። እባክዎን ትንሽ ጊዜ ወስደው ከሱፐርኢንቴንደንት ቶማስ ቴይለር እና ከትምህርት ቦርድ ፕሬዝዳንት ግሬስ ሪቬራ-ኦቨን የተላከውን ልዩ መልእክት ይመልከቱ
|
|
|
|
|
|
የኤዥያን አሜሪካን የፓስፊክ ደሴት ተወላጆችን የቅርስ ወር መዘከር |
|
የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ አባል ጁሊ ያንግ እና የሞንትጎመሪ ካውንቲ ተማሪ የትምህርት ቦርድ አባል አኑቫ ማሉ፣ ባህላቸው ለተማሪዎች እና ለማህበረሰቡ የሚያደርጉትን አገልግሎት እንዴት እንደቀረፀው ግንዛቤ ያግኙ። ቪዲዮውን ይመልከቱ.
|
|
|
|
|
|
|
|
|
|
CPR ይማሩ፤ ሕይወት ያድኑ |
|
ሕይወት ለማዳን ዝግጁ ነዎት? ቅዳሜ፣ ጁን 6 በሞንትጎመሪ ብሌር ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከጠዋቱ 11 a.m.-1 p.m. ድረስ በሜድስታር ሄልዝ MedStarHealth 3ኛ አመታዊ ባይስታንደር CPR አውደ ጥናት ላይ በእጅ ብቻ የሚደረግ CPR እና AED እንዴት መጠቀም እንደሚችሉ ትምሕርት ይሰጣል።
ከሜድስታር ሄልዝ/MedStar Health እና ከማህበረሰብ አጋሮች የተውጣጡ ሀኪሞች ሕይወት አድን ክህሎቶችን ለማስተማር በቦታው ይገኛሉ። በተጨማሪም፣ ከዋሽንግተን ካፒታልስ ልዩ እንግዳ ይገኛል። ጓደኛዎን ይዘው ይምጡ፣ በማህበረሰብዎ ውስጥ ለውጥ ያድርጉ። ይመዝገቡ/Register.
ተጨማሪ መረጃ
|
|
|
|
|
|
ማሳሰቢያ |
|
|
|
|
|
|
|
ለልጆች ተፈላጊ የሆነ፡ የጎልፍ ተጫዋቾች ውድድር እና ስፖንሰሮች |
|
RICA Association, Inc. and the Kiwanis Club of Wheaton-Silver Spring ሰኞ፣ ጁን 8 ቀን 31ኛውን አመታዊ FORE የህፃናት የጎልፍ ውድድር ያስተናግዳሉ፣ ይህም በጆን ኤል. ጊልድነር ሪጅናል የህፃናት እና ታዳጊዎች ተማሪዎችን ተጠቃሚ ያደርጋል። በሞንትጎመሪ ካንትሪ ክለብ የሚካሄደው ይህ ውድድር የጎልፍ ተጫዋቾችን፣ አራት ሆነው እንደ አንድ ቡድን የሚጫወቱ እና ስፖንሰሮችን ይፈልጋል። ተጨማሪ ግንዛቤ ያግኙ።
|
|
|
|
|
|
ለተማሪዎች የተዘጋጁ እድሎች |
- *አዲስ* የሞንትጎመሪ የታሪክ ስነጥበብ ኤግዚቢሽን፡- የካውንቲው 250ኛ ዓመት የምስረታ በዓል አካል እንደመሆኑ፣ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ተማሪዎች (8ኛ ክፍል እስከ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት) “MoCo at 250: Then and Now.” ስራቸውን እንዲያቀርቡ ተጋብዘዋል። የመጨረሻ ቀን፦ እሁድ፣ ኦገስት 2, 2026ነው።
- የሠመር ትምህርት ቤት ምዝገባ!፦ MCPS በስድስት ቦታዎች ላይ የሂሳብ እና የሊተርሲ ችሎታን የማዳበር ኮርስ በኢግኒት መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አካዳሚ ይሰጣል። ParentVue ላይ ይመዝገቡ። እንዲሁም በአካል የሚካሄድ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና ቨርቹዋል የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሠመር ትምህርት ቤት አለ። የተማሪዎችን በራስ መተማመን ለመገንባት እና የፈተና ወቅት ጭንቀትን ለመቀነስ የሚሰጠውን የኮሌጅ ድርሰት ጽሑፍ እና የፈተና ዝግጅት ይመልከቱ። ለመመዝገብ ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ካውንስለር ጋር ይነጋገሩ።
- የደህንነት ቀን፡ ቅዳሜ፣ ሜይ 9 ከጠዋቱ 11 a.m.-3 p.m. ሮክቪል በሚገኘው ካርቨር የትምህርት አገልግሎት ማዕከል ነፃ ዝግጅት ይካሄዳል።
አድራሻ፦ Carver Educational Services Center, 850 Hungerford Drive in Rockville. ስለ እግረኞች ደህንነት፣ ወደ ትምህርት ቤት የሚያደርሱ አስተማማኝ መንገዶች፣ እና ስለ ቪዥን ዜሮ ፕሮግራም ግንዛቤ ያገኛሉ።
- "Montgomery Can Code" ይህ ለሳምንት የሚቆይ የሠመር ካምፕ ነፃ ዝግጅት 6ኛ፣ 7ኛ፣ እና 8ኛ ክፍል ለሚማሩ MCPS ተማሪዎች ክፍት ነው። እዚህ የበለጠ መረጃ ማግኘት ይችላሉ፦ : English / español / 中文 / français / Português / 한국어 / tiếng Việt / አማርኛ
- ዓመታዊ የሥራ ፈላጊዎች ቃለ መጠይቅ ቀን፡ ማክሰኞ፣ ሜይ 19 ከጠዋቱ 10 a.m.-2 p.m. ይካሄዳል። ከተመረቁ በኋላ ወዲያውኑ ሥራ ለመጀመር ለሚፈልጉ ሲንየር ተማሪዎች ክፍት ነው።
- KID ሙዚየም ለተማሪዎች የሠመር ካምፖችን እና ነፃ ኢንቬስት ዘ ፊውቸር ኤክስፖ እድሎችን ይሰጣል። የሠመር ካምፖች ከጁን 22–ኦገስት ድረስ ከመዋዕለ ሕፃናት እስከ 8ኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች ይሰጣል። 21, 9 a.m.-4 p.m. ኢንቬስት ዘ ፊውቸር ኤክስፖ እሁድ፣ ሜይ 31 ከጠዋቱ 10 a.m.-2p.m. በዚህ አድራሻ፦3 Bethesda Metro Center ይካሄዳል። ይመዝገቡ/Register።
|
|
|
|
|
|
ከዜና ገጾቻችን ወቅታዊ መረጃ |
- ስለማስተማርዎ እናመሰግናለን!፡ሁለት የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህራን በዚህ ዓመት Shirley J. Lowrie “Thank You for Teaching” በማሸነፋቸው እያንዳንዳቸው $2,500 ዶላር ሽልማት አግኝተዋል — እነርሱም ቻርለስ ሲልበርማን/ Charles Silberman, P.E. የሮሊንግ ቴራስ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ፊዚካል ኢጁኬሽን መምህር እና በግሬት ሴኔካ ክሪክ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሁለተኛ ክፍል መምህር ጁሊ ሊፕስማን/Julee Lipsman ናቸው።
- MCPS ብሔራዊ የአካል ብቃት ማጎልመሻ ትምህርት እና የስፖርት ሳምንትን እንዴት እያከበረ እንዳለ ለማየት የዘገባ ገጹን ይመልከቱ።
|
|
|
|
|
|
ከእኛ ጋር ግንኙነትዎን ይቀጥሉ
|
|
|
|
|
|
|
|
|
|
|
|
|
|
በዚህ አድራሻ ኢሜል ያድርጉልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org
|
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ
|
|
©1995–2026 Montgomery County Public Schools
|
|