ለ 2016-2017


የትምህርት ዓመት ዓመታዊ ሪፖርት እንኳን ደህና መጡ።

የ 2017 ዓመታዊ ሪፖርት


መግቢያ

የተከበሩ አንባቢ፡-

በሞንጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ ስም፣ የ2017 ዓመታዊ ሪፖርት ለማህበረሰቡ ሳቀርብ ደስታ ይሰማኛል

የሞንጎመሪ ካውንቲ የህዝብ ት/ቤቶች (MCPS) ተልእኮ በትምህርት፣ ችግርን የመፍታት ፈጠራ፣ እና የማህበራዊ ስሜት ሙያ በኮሌጅ እና በሥራ ስኬታማ ለመሆን የሚያስችል እውቀት ለእያንዳንዱ/ዷ ተማሪ ማስጨበጥ ነው። በየዓመቱ፣ ለተማሪዎቹ ከባድ ኣካዴሚያዊ ትምህርት፤ ወደተለያዩ የመማር እድሎች መድረሻ፤ ሃይለኛ የትምህርት መገልገያዎች፤ ሰላማዊ የመማርያ ኣካባቢዎች፤ እና ሌላም ሌላም በማቅረብ/በመስጠት MCPS ተልእኮውን ለማራመድ ይሰራል። ለማህበረሰቡ የሚቀርበው ዓመታዊ ሪፖርት በ 2016–2017 የትምህርት ዓመት የተከናወኑ እጅግ አስፈላጊ ሥራዎችን አጭር የግንዛቤ ምስል ለመስጠት ያገለግላል።

በዚህ የማህበረሰብ ዘገባ የተካተቱት፡-

  • ከ 2016 – 2017 የትምህርት አመት ትኩረቶች
  • የMCPS የህዝብ ስብጥር ጥናቶች/demographics እይታ በጨረፍታ
  • የተማሪ አፈፃፀምና ምረቃ አሃዞች
  • ስለ ስራ ማስኬጃና የካፒታል በጀቶቻችን መረጃ
  • ሌላም፣ ሌላም
  • ተልእኮኣችንን ወደ ትምህርትና ተግባር ለመለወጥ ላገዙን ከ23,000 በላይ መምህራን፣ ኣስተዳዳሪዎች እና ሰራተኞች ምስጋና ይድረሳችሁ። ለአጋሮቻችን፣ ለወላጆች፣ እና ለማህበረሰቡ በጠቅላላ ስላደረጋችሁት ድጋፍ፣ ስለ አስተዋጽኦዋችሁ እና ስለተሳትፎአችሁ አመሰግናለሁ።

    በዚህ ሪፖርት ላይ በተገለጹት ውጤቶች ላይ እየገነባን ለሁሉም ተማሪዎች ታላቁን የህዝባዊ ትምህርት እንደምንሰጥ በማረጋገጥ ወደፊት ትጋታችንን እንቀጥላለን።

    ከኣክብሮት ጋር፣
    Michael A. Durso ማይክል ኤ. ዱርሶ
    የትምህርት ቦርድ ፕሬዚደንት

የ 2017 ዓመታዊ ሪፖርት


በጨረፍታ/በአጭሩ

ትልቁ በሜሪላንድ

17ትልቁበዩናይትድ ስቴትስ

ምዝገባ

በ MCPS የተመዘገቡ 161,546 ተማሪዎች


በዕድሜ፣ በፆታ ወይም በሌላ ያለው ስብጥር የቆጠራ መረጃ

MCPS ያለው ስብጥር፦ ነጮች/White 28.3%፣ ሂስፓኒክ/ላቲኖ-Hispanic/Latino 32.3%፣ ጥቁር ወይም አፍሪካዊ አሜሪካዊ/Black or African American 21.4%፣ ኤዥያ/Asian ፦14.4%,፣ ሁለት ወይም የበለጠ ዝርያ ያላቸው/Two or more races፦ ≤5.0%፣ አሜሪካዊ ህንድ ወይም አላስካ ተወላጅ/American Indian or Alaskan Native ≤5.0%፣ ሃዋይ ተወላጆች ወይም ሌላ የፓስፊክ ደሴት/Native Hawaiian or other Pacific Islander ≤5.0%


የምረቃ መጠን

MCPS አፈፃፀም 89.8% የምረቃ መጠን


የስኮላርሺፕ ገንዘቦች

የ MCPS 2017 ክፍል/ተመራቂዎች ከ $350 ሚሊዮን በላይ ለኮሌጆች ስኮላርሽፕ አግኝተዋል።


አገልግሎቶች በተማሪ ቡድን

የ MCPS አገልግሎቶች በተማሪ ቡድን፦ 17.5% እንግሊዝኛ ለሌላ ቋንቋ ተናጋሪዎች (ESOL)፣ 11.7% የልዩ ትምህርት አገልግሎት አግኝተዋል፣ 35.1% በነፃ እና ቅናሽ-ዋጋ ምግብ (FARMs) ተሳትፈዋል


የስራ ቴክኖሎጂን ያሟሉ

በMCPS የስራ ቴክኖሎጂን ያሟሉ

መጠን እና ብዛት/ Size & Population

የ MCPS ስፋት/Size 497 ስኩዌር ማይሎች እና Sq Miles & የህዝብ ብዛት/Population 1,000,017


ት/ቤቶች

MCPS 205 ት/ቤቶች


የሰራተኞች ብዛት፡- 23,347 (በጀት የተያዘላቸው)

የ MCPS በጀት የተያዘላቸው ሠራተኞች 23,347


የሥራ ግብረኃይል ስብጥር

የሥራ ግብረኃይል ስብጥር


መምህራን

MCPS መምህራን፦ 86.4 ፐርሰንት % መምህራን ማስትሬት ወይም ተመጣጣኝ ዲግሪ አላቸው።


መጓጓዣ/ትራንስፖርት

በMCPS የስራ ቴክኖሎጂን የሚያሟሉ


ምግቦች

በ 2016-2017 የትምህርት ዓመት 16 ሚሊዮን የምግብ አገልግሎት ተሰጥቷል

የ 2017 ዓመታዊ ሪፖርት


የትምህርት ስርአቱ ተቀዳሚ ትኩረቶች

ተልእኮ በኮሌጅና በስራ ስኬታማ ለመሆን እያንዳንዱ/ዷ ተማሪ ኣካዴሚያዊ፣ ፈጠራዊ ፕሮብሌም አፈታት፣ እና ማህበራዊ ስሜታዊ ክሂሎቶች ይኖረዋል/ይኖራታል።

ራእይ ለእያንዳንዱ እና ለማንኛውም ተማሪ ከፍተኛ/ምርጥ የሆነ ህዝባዊ ትምህርት እየሰጠን ለትምህርት እናነሳሳለን።

ዋነኛ ዓላማ ሁሉንም ተማሪዎች ለወደፊታቸው ብልጽግና ማዘጋጀት።

ዋነኛ እሴቶች ትምህርት፣ ዝምድናዎች፣ መከባበር፣ ልቀት፣ ርትኣዊነት።


የሞንጎመሪ ካውንቲ የህዝብ ት/ቤቶች ስልታዊ እቅድ/MCPS Strategic Plan

MCPS ስልታዊ እቅድ/Strategic Plan

MCPS በ 2017 በአዲስ ሱፐርኢንተንደንት ጃክ አር. ስሚዝ/superintendent, Jack R. Smith አመራር አዲስ ስልታዊ የትኩረት መርሃግብሮችን መተግበር ጀምሯል። እነዚህ ቀዳሚ የትኩረት አቅጣጫዎች ለበጀት ዓመት 2018 የ MCPS ስልታዊ እቅድ እንዲሆኑ ተገንብተዋል።

በተጨማሪ ይወቁ

የ2017 ዓመታዊ ሪፖርት


ፖሊሲ ማሻሻል

በእያንዳንዱ ዓመት የሞንጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ ትልቁ የሥራ ድርሻ፣ የዲስትሪክቱን የትምህርት ሥራ ሂደት ለመምራት የተለያዩ ፖሊሲዎችን ማዳበር፣ ክለሳ ማድረግ፣ ማሻሻል፣ ወይም መሻር/ማምከን ነው። እንደየአስፈላጊነቱ እየተሰበሰበ የቦርዱን ፖሊሲ ማዳበር ወይም ክለሳ ማድረግ የትምህርት ቦርድ የፖሊሲ ማኔጅመንት ኮሚቴ ኃላፊነት ነው። ኮሚቴው አግባብነት ካላቸው ሠራተኞች ጋር እየተሰበሰበ የፖሊሲ ረቂቅ በማዳበር (ወይም የፖሊሲ ክለሳዎችን በማድረግ) ለቦርዱ ውይይትና እርምጃ እንዲወሰድ ያቀርባል፡፡

በ 2016-2017 የትምህርት ዓመት በአጠቃላይ 41 የትምህርት ቦርድ ፖሊሲዎች እና የሞንጎመሪ ካውንቲ የህዝብ ት/ቤቶች (MCPS) ደንቦች እና መመሪያዎች ወይ ማሻሻያ ተደርጎባቸዋል፣ ክለሳ ተደርጓል፣ ወይም ተሰርዘዋል። አንዳንዶቹ ክለሳና ማሻሻያ የተደረገባቸው ቴክኒካዊ ስለሆኑ ጎልተዉ የሚታዩ አይደሉም።

የትምህርት ቦርድ 10 ፖሊሲዎችን ማሻሻያ አድርጓል፣ 4 ፖሊሲዎችን አምክኗል፣ እና 27 ደንቦች ላይ ግምገማ አድርጓል።

 የ MCPS የትምህርት ቦርድ

ግምገማ/ክለሳ የተደረገባቸው የትምህርት ቦርድ ፖሊሲዎች

የ2017 ዓመታዊ ሪፖርት


የተማሪ የአፈፃፀም አሃዞች


የትምህርት/የመማር ማዕቀፍ ማረጋገጫ፦

  • በ2016-17 የትምህርት አመት መጨረሻ ላይ የተገነባ የ MCPS መሰረተልማት፣ተማሪዎቻችን እየተማሩ እና በበቂ ሁኔታ እየተማሩ መሆናቸውን ለመወሰን በርካታ እርምጃዎችን (ማለትም፣ ክፍል፣ድስትርክት እና ውጫዊ) አካቷል።
  • ለንባብ/Literacy እና ለሂሳብ ለሁለቱም ያገኙትን ትምህርት በስኬታማነት መቅሰማቸውን ለማረጋገጥ ፈተና/ምርመራ ይደረጋል።
  • በ 2ኛ፣ 5ኛ፣ 8ኛ እና 11ኛ ክፍሎች ላይ ለቀጣዩ የክፍል ደረጃ ዝግጁነት መለኪያዎችን ያካትታል።
  • በ K (ሙዋዕለ ህፃናት)፣ 3ኛ፣ 6ኛ፣ 9ኛ፣ እና 12ኛ ክፍሎች ላይ ስኬታማ የሽግግር መለኪያዎችን ይጨምራል።
  • በሴኬታማነት ትምህርት ስለመቅሰም መሠረታዊ የዝግጁነት መረጃ በ2017 የበጀት ዓመት ዓመታዊ ሪፖርት ላይ ተገልጿል።

ስኬታማ ትምህርት የመቅሰም ማረጋገጫ፡-

  • አንድ/አንዲት ተማሪ ቢያንስ በሁለት ዓይነት የመማሪያ ክፍል መመዘኛዎች፣ በዲስትሪክት፣ እና ውጫዊ ስኬታማነቱ(ቷ)ን ያሳያል/ታሳያለች።

ቀጣይነት ያለው ሥራ

ሱፐርኢንተንደንቱ መደበኛ የሆነ ወቅታዊ የመማር ስኬታማነትን (ይኼውም፦ ዝግጁነትና ስኬታማ ሽግግር) መረጃ/ማረጋገጫ ለትምህርት ቦርድ ይሰጣል። ስለ ዝግጁነት መረጃ ሴፕቴምበር 25/2017 የቀረበ ሪፖርት እዚህይገኛል። የተማሪ ሽግግርን የሚመለከት ሪፖርት በ ፌብሯሪ፣ 2018 ለቦርዱ ይቀርባል።

(*ተለቅ ያለ ምስል ለማየት ጠቅ/ክሊክ ያድርጉ)


2017 ዓመታዊ ሪፖርት


የስራ ማስኬጃ በጀት

የገንዘብ ምንጮች

የገንዘብ ምንጮች

ወጪዎች

ወጪዎች በየፈርጁ

ለ2017 የበጀት ዓመት የትምህርት ቦርድ $2.46 ቢሊዮን የሥራ ማስኬጃ ባጀት አጽድቋል ጁን 14/2016 የሞንጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ የ$2.46 ቢሊዮን የሥራ ማስኬጃ በጀት እንዲጠየቅ ለበጀት ዓመት 2017 ወስኗል። ይኼ ከበጀት ዓመት 2016 በ $180,244,605 ጨምሯል/አድጓል። ይህ የወጪ መጠን መጨመሩ በስምንት ዓመት አስቸጋሪ የኤኮኖሚ ወቅት ጫና የነበረበትን የትምህርት ሥርዓቱን መሠረት አጠናክሯል፣ እናም በአፍሪካ-አሜሪካውያን፣ በላቲኖ፣ እና በኤኮኖሚ ዝቅተኛ ደረጃ ላይ ያሉ ተማሪዎችን የትምህርት ስኬታማነት ክፍተት ፈጣን የማጥበብ እርምጃ ለመውሰድ ረድቷል።

MCPS Budget 101 የሚለው ላይ ስለ ባጀት ሂደት፣የጊዜ ሰሌዳ እና ስለ ሌሎችም የበለጠ ለማወቅ ያንብቡ

ለበጀት ዓመት 2017 የበጀት ምንጮች የሞንጎመሪ ካውንቲ የሥራ ማስኬጃ ባጀት ቅኝት

የ 2017 ዓመታዊ ሪፖርት


የካፒታል ማሻሺያ በጀት

Montgomery County Public Schools የሜሪላንድ ከሁሉም የሰፋ የት/ቤት ስርኣት ብቻ ኣይደለም፣ በስቴት ውስጥና በሃገሪቱ ከዳር እስከዳር እጅጉን በፍጥነት በማደግ ላይ ካሉት የት/ቤት ዲስትሪክቶች በተጨማሪ ኣንዱ ነው። MCPS ከ2007 ጀምሮ በ23,801 ተማሪዎች በላይ ኣድጓል እናም በ2021 ከ10,000 በላይ ኣዳዲስ ተማሪዎች እንደሚጨምር ይጠብቃል። ይሀ ትርጉም ያዘለ የምዝገባ እድገት ለተጨማሪ የመማርያ ክፍል ቦታ ጭማሪ ከመጠን በላይ የሆን ጥያቄ እየፈጠረ ነው። ባለፉት አሥር ዓመታት ት/ቤት ከሚገቡ ተመዝጋቢዎች ብዛት ጋር ለማጣጣም MCPS ከ 1,200 የመማሪያ ክፍሎችን እና ከ 14,000 በላይ መቀመጫዎችን ጨምሯል። ነገር ግን ከእድገቱ ጋር ሊመጣጠን አልቻለም።

የጸደቀው የበጀት ዓመት 2017 የትምህርት ተቋማት/ መገልገያዎች/Facilities ማስተር ፕላን እና የበጀት ዓመት2017-2022 CIP ኖቬምበር 16/2015 በትምህርት ቦርድ ጸድቋል። ቦርዱ ለበጀት ዓመት 2017–2022 የጠየቀው ለ 10 የተጨማሪ መማሪያ ክፍሎች ማስፋፊያ ፕሮጀክቶች -6 በአንደኛ ደረጃ ት/ቤቶች እና 4 በሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች እና አንድ አዲስ የአንደኛ ደረጃ ት/ቤት ለክላርክስበርግ አካባቢ። የ CIP የበጀት ጥያቄ በመርሃ ግብሩ መሠረት የሚያካትታቸው ሌሎች ፕሮጀክቶች የት/ቤቶችን አቅም ግንባታ እና ካውንቲ አቀፍ መሠረተ ልማት ፕሮጀክቶችን ማሞቂያ፣ የአየር ማነፈሻ/Ventilation እና የአየር ማቀዝቀዣዎችን (HVAC) ለመተካት እና ሌሎች በርካታ የመሠረተ ልማት ፋላጎቶችን ያካትታል።

በካፒታል ማሻሺያዎች የሚከናወኑ የመዋዕለ ንዋይ ፍሰቶች በተማሪዎችና በወደፊቶቻቸው ላይ የሚደረጉ የመዋዕለ ንዋይ ፍሰቶች ናቸው። የምዝገባን እድገት ለመቋቋምና ተማሪዎች ሊማሩና ሊያድጉ የሚችሉባቸው ዘመናዊ፣ ሰላማዊ መማርያ ክፍሎች ለማቅረብ በትያትራዊ የመገልገያ ፍላጎቶችና በፋይናንሳዊ ሃቆች መካከል መፈፀም ያለበት ሚዛን ነው።

ትምህርት ቤት ዓይነት ስኩዌር ጫማ/Sq Ft
ሃሊ ወልስ መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት (Hallie Wells MS) ኣዲስ 150,089
ጁሊዩስ ዌስት መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት (Julius West MS) ተጨማሪ/ቀጣይ 35,394
ዊህትን ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት (Wheaton HS) እደሳ/ማስፋፋት 333,268
ዊሊያም ኤች. ፋርኩወኸር መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት (William H. Farquhar MS) እደሳ/ማስፋፋት 134,063
ውድ አክረስ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት (Wood Acres ES) ተጨማሪ/ቀጣይ 21,425
ድምር 674,239

በ 2015-2016 የትምህርት ዓመት የተጀመሩ እና ኦገስት 2016 ት/ቤት መጀመሪያ ላይ የተጠናቀቁ ፕሮጀክቶች፡፡

በ 2015-2016 የትምህርት ዓመት የተጀመሩ እና ኦገስት 2016 ትምህርት መጀመሪያ ላይ የተጠናቀቁ ፕሮጀክቶች፡፡

  • የ674,239 ጫማ-ካሬ አዲስ ት/ቤት ህንፃ ግንባታ ተጠናቋል።
  • በኦገስት 2016 ት/ቤት ሲከፈት አምስት (5) ከፍ ያሉ የት/ቤት ካፒታል ፕሮጀክቶች ተጠናቀዋል።
    • 1 አዲስ ት/ቤት – ሃሊ ዌልስ መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት (Hallie Wells Middle School)
    • 2 የእደሳ/ማስፋፋት ፕሮጀክቶች
      • ዊሊያም ኤች. ፋርኳር መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት (William H. Farquhar Middle School)
      • ዊህተን ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት (Wheaton High School)
  • 2 ተጨማሪ ፕሮጀክቶች
    • ጁሊየስ ዌስት መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት (Julius West Middle School)
    • ውድ አክረስ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት (Wood Acres Elementary School)
  • ስድስት (6) ከፍ ያሉ የካፒታል ፕሮጀክቶች የህንፃ ስራ በመካሄድ ላይ ነው።
  • የአስራዘጠኝ (19) ከፍ ያሉ የካፒታል ፕሮጀክቶች ፕላን/ንድፍ በመካሄድ ላይ ነው

የ2017 ዓመታዊ ሪፖርት


የሥራ ልቀት

የአውቶቡስ በጊዜ መድረስ

የሞንጎመሪ ካውንቲ ት/ቤት አውቶቡሶች በሞንጎመሪ ካውንቲ ውስጥ ከ200 በላይ ት/ቤቶች እና ልዩ ት/ቤቶች በሜሪላንድ፣ ቨርጅኒያ፣ እና ዋሽንግተን ዲሲ ተማሪዎችን ያጓጉዛሉ። አውቶቡሶቹ በካውንቲው ውስጥ ስድስት ስልታዊ በሆኑ የአውቶቡስ ጣቢያዎች ይቆማሉ። እያንዳንዱ የአውቶቡስ ጣቢያ የነዳጅ ማደያ፣ የጥገና እና እድሳት ጋራዥ፣ እና የቤቶች ማቆሚያ አስተዳደራዊ ቢሮዎች አሏቸው። አውቶቡሶቹ ለሰመር ትምህርት ቤቶች፣ ለመስክ ጉዞዎች እና ለማህበረሰብ እንቅስቃሴዎች/ዝግጅቶች ዓመቱን በሙሉ የመጓጓዣ አገልግሎት ይሰጣሉ። የእኛ በጊዜ የመድረስ መረጃ ተማሪዎች ትምህርት ከመጀመሩ በፊት በትክክለኛው ሠዓት የክፍል ትምህርት ለመከታተል ት/ቤት ለመድረስ እንዲችሉ ያለንን በጣም አስፈላጊ አላማችንን ያረጋግጣል።

ለመከላከል የሚቻል የአውቶቡስ አደጋዎች

በ MCPS የአደጋ ገምጋሚ ቦርድ እና በሜሪላንድ መመሪያዎች መሠረት ሁሉም የአውቶቢስ አደጋዎች ለመከላከል-የሚቻል/ለመከላከል-የማይቻል በሚል ይለያሉ። ስለ ደህንነት ስልጠና/safety training፣ ግምገማ፣ እና ዓመታዊ የአደጋን ብዛት ለመቀነስ በዓመት ለመከላከል የሚቻል አደጋ ከ45 በላይ እንዳይኖር ለመመጠን የመጓጓዣ/ትራንስፖርት መምሪያ ዒላማ አድርጓል/አስቀምጧል። ስለ ሁሉም ለመከላከል የሚቻሉ አደጋዎች፣ የአውቶቡስ አሽከርካሪው/ዋ የ MCPS ከአደጋ በኋላ የእድሳት ስልጠና መውሰድ እንዳለበ(ባ)ት ግዴታ ነው። እነዚህ ስልጠናዎች የሚካሄዱት በትምህርት ዓመት ውስጥ በየወሩ ነው።

ፖሊስ የሚይዛቸው ሞተረኞች

የትራፊክ ህጎችን በመጣስ የቆሙ አውቶቡሶችን አልፈው የሚሄዱ ሞተረኞችን የሚቀርጽ/ሪኮርድ የሚያደርግ የካሜራ ቴክኖሎጂ በት/ቤት አውቶቡሶች ላይ ተገጥመዋል። በት/ቤት አውቶቡሶች ካሜራ የተቀረጸውን ፊልም ማስረጃ መሠረት በማድረግ ህጉን ለተላለፉት ሞተረኞች የፖሊስ መጥሪያ ይሰጣቸዋል። ከ ኦክቶበር 2016 መግቢያ ጀምሮ ይበልጥ ህግ የሚጥሱትን ሪኮርድ ለማድረግ የሚያስችል ቴክኖሎጂ በስፋት ተግባራዊ ተደርጓል።

የምግብ እና አልሚ ምግብ አገልግሎቶች

ለተማሪዎቻችን የሚሰጡ የተለያዩ የልጆች የአልሚ ምግብ ፕሮግራሞች በዩናይትድ ስቴትስ የግብርና መምሪያ የተዘጋጁትን መስፈርቶች ያለፉ ናቸው። የተራበ ልጅ ለመማር እንደማይችል ስለምናውቅ የሞንጎመሪ ካውንቲ የህዝብ ት/ቤቶች (MCPS) ከፍተኛ-ጥራት ያላቸው አልሚ የሆኑ ምግቦች እና መክሰስ ለሁሉም ተማሪዎች ለማቅረብ ቁርጠኞች ነን።

FARMS ተቀባዮች

ለነፃ እና ለቅናሽ ዋጋ ምግብ አቅርቦት ብቁ የሆኑ ተማሪዎች (FARMS) ከመቼውም ጊዜ የበለጠ ጨምሯል። በዝቅተኛ ኢኮኖሚ ምክንያት የምግብ እጥረት የሚያጋጥማቸው/የምግብ ዋስትና የሌላቸው በርካታ ተማሪዎች ወደ እኛ የመምጣት ሁኔታ እንደቀጠለ ነው። የት/ቤት የምግብ ፕሮግራም እና የሰመር የምግብ አገልግሎት ፕሮግራም የተማሪዎቻችንን ጤንነት ለመጠበቅ አስፈላጊ የሆኑ አልሚ ምግቦችን ይሰጣል።

የሳምንት መጨረሻ ምግብ የማስያዝ ፕሮግራም

የምግብ እጥረት ያለባቸውን ተማሪዎች እና ቤተሰቦቻቸውን በሳምንት መጨረሻ ምግብ የማስያዝ አገልግሎቶች ይሰጣሉ። ፕሮግራሙን የሚያካሄዱ ሦስት አትራፊ-ያልሆኑ ሸሪኮች አሉ። ከ50 ፐርሰንት በላይ ለሆኑ ለFARMS አገልግሎቶች ብቃት ላላቸው በኤለመንተሪ ት/ቤቶች ለሚማሩ ተማሪዎች እነዚህ ሸሪኮች የሳምንት መ ጨረሻ የምግብ እርዳታ አገልግሎቶችን ለመስጠት የጋራ ግብ/ትልም አላቸው።

የታዘዙ የእድሳት ሥራዎች እና የተጠናቀቁ (እድሳት የተደረገላቸው)

መረጃው የሚያሳየው እድሳት/ጥገና እንዲደረግላቸው ት/ቤቶች የጠየቁትን እና በማእከል ጥቂት የመከላከያ እድሳት የተደረገላቸውን ነው። መረጃው ያስፈለገው የተጠየቀውን ያክል እና የተጠናቀቁትን ስራዎች፣ የቀረቡ ጥያቄዎች ብዛት፣ በተጠየቁት አስፈላጊ ሥራዎች እና በተጠናቀቁት ሥራዎች መካከል ያለው ክፍተት፣ እና ሥራዎቹን ለማጠናቀቅ የፈጀው ያክል ጊዜ።

ባጀት የተያዘላቸዉ ጥገና እና እድሳት ከተደረገላቸው አኳያ ሲታይ

መረጃው የሚያገለግለው የህንፃዎቹን የአገልግሎት እድሜ ለማራዘም ጥገና ለማድረግ እንዲቻል ባጀት ለመጠየቅ ድጋፍ ይሰጣል። መረጃው በተጨማሪ የሚጠቅመው ያረጁ ህንፃዎችን አገልግሎት ለመስጠት ካረጁ በኋላ ጥገና የማድረግ አስፈላጊነት ትንታኔ ለመስጠት ወይም ቅድሚያ የመከላከያ ጥገና መጨመር ይሻል እንደሆነ ለመረዳት ነው።

በእቅድ የተያዘ እና የተከናወነ የህንፃ ምርመራ

መረጃው/ዳታው የሚያመለክተው በአግባብ ቁጥጥር የተደረገላቸውን/የተጠናቀቀ እና እንደግብ የተያዘ ህንፃዎችን አሃዝ ነው። የህንፃዎቹ ቁጥጥር/ኢንስፔክሽን የሚዳስሰው ንጽህና እና የህንፃዎቹን አገልግሎት ሰጪነት እና የህንፃዎቹን የአገልግሎት ሠራተኞች ሥራ ነው። ሌሎች መገልገያዎች አንድ ጊዜ ቁጥጥር/ኢንስፔክሽን የሚደረግላቸው ሲሆን ት/ቤቶች በዓመት ሁለት ዙር ቁጥጥር/ኢንስፔክሽን ይደረግላቸዋል። ሥራዎችን በማጠናቀቅ ረገድ የአየር ሁኔታ፣ ሌላም የአስቸኳይ ጊዜ ምላሽ አጋጣሚዎች፣ እና የሠራተኛ እጥረቶች ተፅእኖ ያደርጋሉ።

የአካባቢ የህንፃ ምርመራ ቁጥጥር ውጤቶች

በህንፃ አገልግሎት ዙርያ የሚሠሩ ተቆጣጣሪዎች መደበኛ የሆነ የአካባቢ ቁጥጥር በማድረግ በፊደላት የጥራት ደረጃ ይሰጡታል። ለሁሉም ምርመራ/ኢንስፔክሽን ሲደረግ ኢላማ የሚደረገው "B" ወይም ከዚያ በላይ የሆነ ውጤት ነው።

ሃይል የሚያገኘው በSocrata ነው

የግሪንሃውስ ጋዝ ቅነሳ

MCPS የግሪንሃውስ ጋዝ ጭስ የመቀነስ ጥረቱን የሚቆጣጠረው በተለያዩ ዘላቂነት ባላቸው ፕሮግራሞች እና ኢንቨስትመንቶች አማካኝነት ነው። መረጃው እነዚህን የቅነሳ ዘይቤዎችን በስድስት ረድፍ ይከፋፍላቸዋል፤ ኃይል አሻሽሎ መጠቀም/energy retrofits፣ በንፋስ የሚሠራ ኃይል ግዢ፣ መላልሶ መጠቀም/recycling፣ ጠጣር የሚጣሉ ቆሻሻዎችን በመቀነስ/solid waste reductions፣ በት/ቤት የኃይል እና መላልሶ የመጠቀም ቅነሳ ፕሮግራም (SERT)፣ እና የኃይል አጠቃቀም ብኩንነት ቅነሳ/ማሻሻል በግንባታ ፕሮግራም በተካተተዉ መሰረት ነው። በ2016 የበጀት ዓመት የSERT ቅነሳ የሆነበት ምክንያት ለት/ቤቶች በተገበረው ሃይል የመቀነስ ስሌትን መሰረት በማድረግ ነው። ከ2003 ጀምሮ፣ MCPS የመካነ አትክልት/Greenhouse ጋዝ/ጢስ ፍልቀቶችን ከ70,000 ሜትሪክ ቶን በላይ በሆነ የካርቦን ዳዮክሳይድ ተመጣጣኝ ወይም MTCO2e ቀንሷል። ይህ ከ2003 ጀምሮ በMCPS በካርቦን የሚሠራ/carbon footprint 30 በመቶ ቅነሳን ይወክላል።

ወዳቂ ቆሻሻ ማመንጨት ከሚገባ/ተመዝጋቢ አኳያ

የሚገባ/ተመዝጋቢ እየጨመረ ቢሄድም በMCPS በተቃራኒው የወዳቂ ቆሻሻ ማመንጨት እየቀነሰ ሄዷል። የሚወዳድቁ ነገሮችን ዳግም ጥቅም ላይ እንዲውል/recycling እና የእነዚህን ጥረቶች አፈፃፀም ለመከታተል MCPS ትልቅ ቁርጠኝነት አድርጓል። Montgomery County አራት የቁሳቁስ ፈርጆች፡- ወረቀት/ካርቶን፣ ጠርሙሶች/ጣሳዎች፣ የጓሮ ቆሻሻ፣ እና የተጣለ ብረት እንደገና ስራ ላይ እንዲውሉ ይጠይቃል።

በአምስት ቀናት ውስጥ የተጠናቀቁ የስንቅና ትጥቅ/የሎጂስቲክስ ጥያቄዎች

የቁሳቁሶች ማኔጅመንት ክፍል (DMM) መጋዘን እና አስፈላጊ የሆኑ የመማሪያ መጻሕፍትን፣ የማስተማሪያ እቃዎችን፣ የመማሪያ ክፍል እና የጽ/ቤት-ቢሮ ቁሳቁሶችን፣ የሳይንስ ትምህርት መርጃዎችን፣ የቤት እቃዎች፣ የትምህርት መሣሪያዎች እና የቴስት/የፈተና ቁሳቁሶችን ለት/ቤቶች እና ለቢሮዎች የማሰራጨት አውታር ያስተዳድራል። ለ DMM የሚቀርቡ ጥያቄዎች የጊዜ ወሳኝነት ያላቸው መሆኑን ስለሚገነዘብ ጥያቄዎቹ በቀረቡ በአምስት የሥራ ቀናት ውስጥ ግብ የማድረስ-ምላሽ ለመስጠት ይተጋል።

የኮፒ ማድረጊያዎች ጥገና አገልግሎቶች

የማስተማሪያ እቃዎችን ለማሟላት የሚቀርቡ የት/ቤቶችን ፍላጎት ጥያቄዎችን ግብ ለመድረስ ምላሽ የምንሰጥበት መንገድ ለሁሉም መምህራን አስተማማኝ የሆኑ የኮፒ ማሽኖችን በእያንዳንዱ የትምህርት ቀን ለመጠቀም እንዲችሉ በመስጠት ነው። ስለ እድሳት/ጥገና ምላሽ የምንሰጥበትን የጊዜ እርዝመት እየተቆጣጠርንም ከርእሰመምህራን ጋራ ባለን የአገልግሎት ስምምነት መሠረት (ዒላማ ያደረገው በ48 ሠዓት ውስጥ ነው) ይህንን ግብ ለመድረስ የእኛ ዋነኛ የክንውን መለኪያችን ጥገና መቀነስ እና መከላከል የሚያስችል እድሳትን በመጨመር ነው።