የሞንትጎመሪ ካውንቲ የሕዝብ ትምህርት ቤቶች
 

English / español / 中文 / français / Português / 한국어 / tiếng Việt / አማርኛ/Amharic

 

የክረምት ወቅት ተቃርቧል፤ እኛ ዝግጁ ነን፣ እናንተስ?

ለተከበራችሁ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ማህበረሰብ 

የዓመቱ የክረምት ወቅት ሊገባ ተቃርቧል! በመጸው ወቅት እየረገፉ ባሉ ቅጠሎች ተደስተን ሳናበቃ፣ የክረምት ቀዝቃዛ የአየር ሁኔታ በራችንን ያንኳኳል። የክረምቱ የአየር ሁኔታ አካባቢያችን ላይ ተፅእኖ በሚፈጥርበት ጊዜ ጠዋት በማለዳ ከሚደረገው የበረዶ ክምችት ግምገማ አንስቶ እስከ ቀትር ድረስ የሚደረጉ የትምሕርት ቤቶች የሥራ መርኃግብር ማስተካከያዎች ላይ ምን መጠበቅ እንዳለባችሁ እንድታውቁ እንደምናደርግ ማረጋገጥ እንፈልጋለን።

MCPS የቀለም ኮድ አጠቃቀም መግለጫ

የክረምት ከባድ አውሎ ነፋስ፣ ውሽንፍር ሲከሰት መረጃ በፍጥነት እንደሚያስፈልጋችሁ እናውቃለን። ከአየር ሁኔታ ጋር የተያያዙ መረጃዎችን ለተማሪዎች፣ ለቤተሰቦች፣ እና ለሰራተኞች ለማድረስ የቀለም ኮድ መግለጫ ስርዓት እንጠቀማለን።

  • ኮድ አረንጓዴ ቀለም ማለት፦ መደበኛ ሥራዎች ይካሄዳሉ ማለት ነው
  • ኮድ ቢጫ ቀለም ማለት፦ ትምህርት ቤቶች ዘግይተው ይከፈታሉ ማለት ነው።
  • ኮድ ሠማያዊ ቀለም ማለት፦ተማሪዎች ከመደበኛው ሠዓት ቀደም ብሎ ይሰናበታሉ ማለት ነው።
  • ኮድ ብርቱካን ቀለም ማለት፦ ትምህርት ቤቶች ዝግ ይሆናሉ/ ቢሮዎች ክፍት ናቸው ማለት ነው።
  • ኮድ ቀይ ቀለም ማለት፦ የትምህርት ስርዓቱ በሙሉ ዝግ ይሆናል ማለት ነው።
  • ኮድ ሐምራዊ ቀለም ማለት፦ በኦንላይን/ቨርቹዋል ትምሕርት የሚሰጥበት ቀን ማለት ነው።

እያንዳንዱ የቀለም ኮድ ለእርስዎ እና ለቤተሰብዎ ምን ማለት እንደሆነ ለመረዳት፣ ውሳኔዎች እንዴት እንደሚወሰኑ ለማወቅ፣ እንዲሁም ለክረምት የአየር ሁኔታ ዝግጅት ለማድረግ፤ Weather One-Pager/የአየር ሁኔታ መረጃ ገጻችንን እና የትምህርት ቤቶች ሥራ ሁኔታ መግለጫ እና የቀለም ኮዶች/Operating Status & Color Codes ድረ-ገጻችንን እንድትመለከቱ እናበረታታለን።

MCPS የወቅታዊ መረጃ ሲስተም

በይፋዊ የመገናኛ ብዙሃን አውደመረቦቻችን ላይ ወቅታዊ መረጃዎችን ማግኘት ትችላላችሁ። 

  • ድረገጽ፦ MCPS ዋናው ድረ ገጽ እና በእያንዳንዱ ትምህርት ቤት ድረ-ገጽ ላይ ተመልከቱ።
  • ParentSquare፦ላይ ኢሜሎችን እና የጽሑፍ መልዕክቶችን ተከታተሉ።
  • ቴክስት/ኢሜል (Text/Email)፦ Alert MCPS/Alerta Montgomeryላይ መልእክቶችን ለማግኘት ተመዝገቡ።
  • ማሕበራዊ ሚድያ፦ Follow MCPS on X (ENG/SPAN)፣ Facebook (ENG/SPAN) እና Instagram (ENG/SPAN) ላይ ይከታተሉን።
  • ስልክ፦ AskMCPS በስልክ ቁጥር 240-740-3000 ይደውሉ።

World Premiere: Snow Day Trailer

ትንሽ ለመዝናናት! ለክረምት የአየር ሁኔታ መዘጋጀት ስትጀምሩ፣ ስለ በረዶ ቀናት የተዘጋጀውን ማስተዋወቂያ ቪዲዮችን ተመልከቱ። 

ተቀነጫጭቦ የቀረበ ማስተዋወቂያ ተመልከቱ

በዚህ የክረምት ወቅት፣ መላው የትምህርት ቤት ማህበረሰባችን ደህንነቱ የተጠበቀ፣ መረጃ ያለው፣ እና እርስ በርስ እንዲገናኝ ስለምታደርጉት ድጋፍ እናመሰግናለን!

 

በዚህ አድራሻ ኢሜል አድርጉልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org