‌ ‌ ‌ ‌ ‌ ‌ ‌ ‌ ‌ ‌ ‌ ‌ ‌ ‌ ‌ ‌ ‌ ‌ 
All In blog by MCPS Superintendent Dr. Jack R. Smith

español | 中文 | français | tiếng Việt | 한국어 | አማርኛ

ሁሉም በአንድነት፦ ወረርሽኙ፣ ባጀት፣ እና የወደፊት ሁኔታ

የበጀት ዓመት-Fiscal Year (FY) 2021 የሥራ ማስኬጃ ባጀት ንድፈሃሳብ ዲሴምበር 18/2019 በይፋ ባቀረብኩበት ወቅት፣ እንደው ከሦስት ወራት በኋላ፣ በኮቪድ-COVID-19 ወረርሽኝ ምክንያት ማርች 16/2020 የሜሪላንድ ትምህርት ቤቶች ህንፃዎች ለተማሪዎች ዝግ እንደሚሆኑ ለማወቅ የምችልበት ምንም መንገድ አልነበረም። ሜይ 6፣ የስቴት ትምህርት ቤቶች ሱፐርኢንተንደንት ኬረን ሳልሞን-State Superintendent of Schools Karen Salmon ስለትምህርት ዓመቱ ቀሪ ጊዜ የትምህርት ቤት ህንጻዎች ዝግ መሆን እንዳለባቸው መግለጫ ሰጥተዋል። በአምስት ወራት ውስጥ ብቻ ነገሮች በከባድ ሁኔታ ተለዋውጠዋል።

ላለፉት ሁለት ወራት፣ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ሠራተኞች ኦንላይን የትምህርት መልመጃዎች-ተሞክሮዎች እና ሌሎች በርካታ አገልግሎቶች ለተማሪዎች እና ለቤተሰቦቻቸው ሲሰጡ ቆይተዋል። ይህም ከመምህራኖቻችን፣ ከአስተዳዳሪዎች እና ከድጋፍ ሰጪ ባልደረቦቻችን እጅግ በርካታ የእቅድ ዝግጅቶችን እና ጥረቶችን ጠይቋል።

ወደዚህኛው የትምህርት ዓመት መገባደጃ እየተቃረብን ሳለ እንኳ፣ ሦስትዮሽ ለሠመር እና ለሚቀጥለው ዓመት እቅድ በማዘጋጀት ብዙ ሥራ ላይ የተጠመድን ሲሆን፦ ምንም እንኳ ባለፉት ጊዜያት ከነበሩን አሠራሮች በተለየ መልኩ የተቀነባበረ ሊሆን ቢችልም ለተማሪዎች በኦንላይን ብቻ ትምህርት እንሰጣለን፣ ኦንላይን እና በአካል የተዳቀለ ሲስተም ይኖረናል፣ ወይም በአካል ተገኝቶ ወደመማር  እንመለስ ይሆናል። የጊዜው አጠቃቀም እንዴት በተለየ ሁኔታ ሊሆን እንደሚችል እያየን ነው። ለምሳሌ፦ ስለ ሠመር ትምህርት፣ ስለ ቅዳሜ ትምህርት፣ እና ሌሎች ከትምህርት ሠዓት በኋላ አማራጮችን እያየን ነው። እነዚህ በሙሉ በ FY 2021 በጀት ላይ ትልቅ ማስተካከያዎችን ማድረግ ይፈልጋሉ።
በተለያየ መንገድ የትምህርት ተሞክሮዎችን የሚያንፀባርቅ የባጀት ማስተካከል እና በመጪው ዓመት የተማሪዎችን እና ሠራተኞችን ደህንነት ከመጠበቅ አኳያ፣ የኮቪድ-COVID-19 ኢኮኖሚያዊ ተጽእኖ ማለት መጀመሪያ ከጠየቅነው የባጀት መጠን ይልቅ እጅግ ያነሰ ፈንድ ይኖረናል ማለት ነው።

የ MCPS የባጀት ምንጭ በመሠረታዊነት ከሁለት አካላት—የአካባቢ የመንግሥት አስተዳደር እና ከሜሪላንድ ስቴት ሲሆን (በጣም ጥቂት ፐርሰንት ከፌደራል መንግሥት እና ከሌሎች ምንጮች ይመጣል)። ሁለቱም የአካባቢ እና የስቴት አካላት በገቢዎቻቸው ላይ ከፍተኛ ማነስ እያጋጠማቸው ሲሆን፣ የአካባቢ የመንግሥት አስተዳደር በዚህ ወቅት ለትምህርት ቤቶቻችን ሲስተም ባሰቡት መጠን ፈንድ ለመስጠት አልቻሉም።

በዚህ ምክንያት፣ ሜይ 14፣ ስለ MCPS Fscal Year የሥራ ማስኬጃ ባጀት - MCPS Fscal Year operating budget at Maintenance of Effort የሞንትጎመሪ ካውንቲ ካውንስል የመጀመሪያ ስምምነት አድርጓል (Maintenance of Effort is a state law established in 1984 that requires every local government to spend at least as much per student as it did the previous year to receive additional state aid for education) ጥረትን ማገዝ የሚባለው እያንዳንዱ የአካባቢ መንግሥት አስተዳደር ለአንድ ተማሪ በፊተኛው ዓመት ላይ ያወጣውን ያክል የባጀት ስሌት ከስቴት የሚሰጥ የትምህርት ድጋፍ ለማድረግ በ1984 የተመሠረተ ህግ ነው። ስለ ፈንድ መቀነስ ከስቴት የሰማነው ምንም ነገር ባይኖርም፣ ኤፕሪል ላይ፣ የሜሪላንድ በጅሮንድ ፒተር ፍራንቾት-Maryland Comptroller Peter Franchot ሰኔ 30 የሚጠናቀቀው የዚህ ዓመት፣ የስቴት በጀት 15 ፐርሰንት እጥረት ሊኖር እንደሚችል አሳይተዋል።
በ "CARES Act" ድንጋጌ መሠረት ጥቂት የፌደራል ፈንድ ሊኖር ቢችልም፣ በዚህ አስቸጋሪ ወቅት የተማሪዎቻችንን ፍላጎት ለማሟላት መደረግ ያለባቸውን ለውጦች ለመሸፈን በቂ አይሆንም።

ይህ ማለት በአጭር ጊዜ ውስጥ፣ ለሚቀጥለው የባጀት ዓመት (FY 2021) አሁን ባለው የካውንቲው ገቢ ካቀረብነው የባጀት እቅድ $44 ሚሊዮን መቀነስ እንዳለብን ሲሆን፣ በሌላ በኩል ደግሞ የወቅቱን ሁኔታ ለመቋቋም ባጀቱ መጨመር እንዳለበት ነው። ይህንን ታዲያ እንዴት ነው የምናደርገው?

የመጀመሪያው እና ዋነኛው ነገር፤ ስለ ልቀት እና ሚዛናዊነት ያለንን ቁርጠኝነት መጠበቅ አለብን። "All Means All" የተሰኘውን መርኅ ሁልጊዜ እያስታወስን የእያንዳንዱን ተማሪ ፍላጎት ፊትለፊት በማድረግ ሥራችንን ማከናወን ይኖርብናል። የእኛ ቦርድ ፕሬዚደንት ሼብራ ኢቫንስ-Board President Shebra Evans ለካውንቲ ካውንስል ሜይ 7 እንደተናገሩት፣ “This unprecedented international health emergency, and its significant impact on our local community, economy and resources, does require us to refocus and reprioritize our work to prevent learning loss and new disparities in academic outcomes between student groups.” ይህ ታይቶም ተሰምቶም የማይታወቅ አይነት ዓለም አቀፍ የጤና ቀውስ በአካባቢያችን ማህበረሰብ፣ በኢኮኖሚ እና በሪሶርሶች ላይ ያስከተለው ተጽእኖ በተማሪዎች መካከል አዲስ ልዩነቶችን እንዳያሰፋ ትኩረታችንን እና በሥራዎቻችን ላይ ቅደም ተከተል የምንሰጣቸውን ነገሮች እንደገና እንድናጤን ያደርገናል።

በተጨማሪ፦ ለአካባቢያችን የትምህርት ስትራቴጂ እና ቅድሚያ የሚሰጣቸው ነገሮች ድጋፍ መስጠት የስቴት ትምህርት ቦርድ - State Board of Education’s Maryland Together: Maryland’s Recovery Plan for Education እና የ Governor’s Maryland Strong Roadmap to Recovery የትኩረት አቅጣጫ ነው።

እነዚህን ዋና ዋና እሴቶች እና እቅዶች ታሳቢ በማድረግ የ FY 2021 ባጀታችንን እንደገና በመከለስ ላይ እንገኛለን። ተማሪዎች ወደ መማሪያ ክፍሎቻቸው መቼ በአካል ለመመለስ እንደሚችሉ ስለማናውቅ፣ በተለይ በሦስት ዋና ዋና ሥራዎች ላይ ትኩረት በመስጠት እየሠራን እንገኛለኝ።

በ 2020-21 የትምህርት ዓመት ለተማሪዎች የትምህርት ጊዜ እና ለከሪኩለም ለውጦች የበለጠ ጊዜ መሰጠት አለበት።
 በዚህ ሠመር እና በሚቀጥለው ዓመት ለተማሪዎች ብዙ የመማሪያ ጊዜ መስጠት ይኖርብናል፣ በተለይም በዚህ ስፕሪንግ ወቅት በከፍተኛ ደረጃ የትምህርት ጊዜ ለባከነባቸው ተማሪዎች። እንዲሁም ደግሞ፣ ከሪኩለማችን መቀየር አለበት። ለምሣሌ፦ እንደዚህ አይነት የጤና ቀውስ በሚከሰትበት ወቅት ተማሪዎች እንዴት አካላዊ ደህንነታቸውን መጠበቅ እንዳለባቸው እንዲያውቁ ለማስተማር የምንፈልገውን ማንፀባረቅ አለበት። ከሪኩለሙ በቨርቹወል የትምህርት አሰጣጥ መድረኮችም ቢሆን ሁሉንም ይዘት በትክክል በሚሠራ አይነት የተጻፈ-የተዘጋጀ መሆን አለበት። አስፈላጊ ሲሆን ተማሪዎች እቤታቸው ለመጠቀም እንዲችሉ የማስተማሪያ ቁሳቁሶች-ማቴሪያሎች መሰጠት አለባቸው።

በሁሉም የሥራ ዘርፎቻችን ሙያን ማደበር ለሁሉም ሠራተኞች አስፈላጊ ነው
በአካዳሚ ይዘት፣ መምህራን ተገቢ የሆነ ኦንላይን የማስተማር ክህሎት እንዲኖራቸው ያስፈልጋል። ተማሪዎችም እንደዚሁ ማህበራዊ-ስሜታዊ/ስነልቡናዊ ድጋፍ በይበልጥ ያስፈልጋቸዋል። የትምህርት ምህዳሩ የተለየ ስለሚሆን፣ ከአስተማሪ እና ከጓደኞች የሚሰጠውን ድጋፍ ለመቀበል የእያንዳንዱ ተማሪ ችሎታም እንደዚሁ የተለየ ነው። በዚህ ወረርሽኝ ወቅት ከተማሪዎቻችን አንዳንዶቹ በግል ህይወታቸው ከፍተኛ ጉዳቶችም ስላጋጠማቸው፣ በዚህ ወቅት መርዳትና መደገፍ አለብን። በብዙ አቅጣጫ፣ እያንዳንዱ ተማሪ የአደጋ ስጋት ተደቅኖበ(ባ)ታል። እያንዳንዱ የእኛ፡ሥራ ዘርፍ የተለየ ነው። የአውቶቡስ አሽከርካሪዎች ተማሪዎችን እንዴት በደህና ሁኔታ ማጓጓዝ እንዳለባቸው ማወቅ አለባቸው። የምግብ አገልግሎት ሠራተኞች በአዲስ አይነት የአሠራር ዘዬ መሥራት ይኖርባቸዋል። ለህንፃ አገልግሎት ሠራተኞች አዲስ የደህንነት እና የንፅሕና አያያዝ አሠራር ይኖራል። ይህ አዲሱ የጤና ሁኔታ ሥራችንን በሙሉ የሚነካ ስለሆነ ዝርዝሩ ይቀጥላል።

በመጨረሻም፦ የቴክኖሎጂ ሲስተማችን በከፍተኛ ደረጃ መዳበር አለበት
እያንዳንዱ ተማሪ ዲቫይሶችን እና አገናኝ መረቦችን ማግኘት አለበ(ባ)ት። እያንዳንዱ መምህር(ት) ሲስተሞችን እና ፕላትፎርሞችን በትክክል መጠቀም መቻል አለበ(ባ)ት። ሠራተኞች በሙሉ ከማርች 16 በፊት ይሠሩ ከነበረው ሁኔታ በተለየ መንገድ ይሠራሉ።

እጅግ በጣም አስፈላጊ የሚሆነው፣ ይህን የአዲስ ሁኔታ-ዓለምን ስንቃኝ የእያንዳንዱን ተማሪ እና ሠራተኛን ፍላጎት ግምት ውስጥ ማስገባት አለብን። ከባድ የጤና መቃወስ ያለባቸውን ግለሰቦችን እና እንግሊዝኛ የመጀመሪያ ቋንቋቸው ያልሆነ ተማሪዎችን እንዲሁም ልዩ አይነት የትምህርት ሁኔታ የሚያስፈልጋቸውን ለመርዳት እቅድ ሊኖረን ይገባል።
የ MCPS ሠራተኞች በትምህርት ሲስተማችን በእነዚህ ጉዳዮች ላይ በግልም ሆነ ከሌሎች ባልደረቦቻቸው ጋር፣ ከማህበረሰብ አባሎች ጋር፣ እና በስቴት እና በሀገር ደረጃ ከሚገኙ ባልደረቦች ጋር ተግተው እየሠሩ ናቸው። በጠቅላላ ተማሪዎቻችንን ፍላጎቶቻቸውን ባያሟላም የሚደግፍ መፍትሔ ለማግኘት የጋራ የአእምሮ ብስለት፣ ችሎታንና ጥረትን አስተባብሮ መሥራት ይጠይቃል።

ይህ ዓለምአቀፋዊ ወረርሽኝ በምንሠራቸው ነገሮች ሁሉ ላይ ለአሁን እና ምናልባትም ለመጪዎቹ ዓመታት የምናደርጋቸው ነገሮች ላይ በሙሉ ተጽእኖ አሳድሯል። መልካሙን እየተመኘን፣ ኮቪድ-COVID-19 በኢኮኖሚያችን ላይ ያስከተለውን ጫና ግምት ውስጥ በማስገባት፣ ወደፊት ለማይታወቅ ያህል ጊዜ ሊያጋጥመን ስለሚችል ለባጀት አስተማማኝ አለመሆን መዘጋጀት ይኖርብናል። አሁን የምናከናውነው ነገር የመጪውን ዓመት ብሎም የቀጣዮቹን ዓመታት ደረጃ ይወስናል። አስፈሪ ነው? አንዳንድ ጊዜ። አስፈላጊ ነው? ያለጥርጥር። አንድ እርግጠኛ የሆንኩበት ነገር ቢኖር—በዚህ ላይ ለመሥራት የምፈልግበት ሌላ ሥፍራ የለም። በዚህ ሁላችንም አብረን ስለሆንን በጋራ ለተማሪዎቻችን ጤነኛ እና ደህንነቱ አስተማማኝ በሆነ አካባቢ ምርጥ የትምህርት እድሎችን ለመስጠት የሚያስችሉንን መንገዶች ለማግኘት እንችላለን።

 
Montgomery County Public Schools

View as a Web Page

Montgomery County Public Schools
850 Hungerford Drive, Rockville, MD, 20850
Call: 240-740-3000 | Spanish Hotline: 240-740-2845