‌ ‌ ‌ ‌ ‌ ‌ ‌ ‌ ‌ ‌ ‌ ‌ ‌ ‌ ‌ ‌ ‌ ‌ 
All In blog by MCPS Superintendent Dr. Jack R. Smith

español | 中文 | français | tiếng Việt | 한국어 | አማርኛ

ሁሉም በአንድነት፦ የስፔሻል ኢጁኬሽን ተማሪዎች ለርቀት ትምህርት የሚያስፈልጋቸውን ማሟላት

ጄን ካርልሰን - Jean Carlson፣ ስለ “ቻይነት፣ ታጋሽነት፣ ፅኑነት፣ እና ተስፋ” ስላስተላለፍሽው መልእክት አመሰግናለሁ። አንቺ ከተማሪዎችሽ ጋር ያደረግሽውን ውይይት ኢ-ሜይልሽን ስመለከት ፊቴን ፈገግ አሰኝቶኛል። ይህንን ለሌሎችም እንዳካፍል ስለፈቀድሽልኝ አመሰግንሻለሁ፣ እንደዚሁም ለተማሪዎች ስለምታደርጊላቸው መልካም ነገሮች ሁሉ አመሰግንሻለሁ።

ከ "Jean Carlson" ኢ-ሜይል፦

"ሁላችንም እንደሆንነው፣ እኔ በዚህ ወቅት የተማሪዎቼን ስሜታዊ-ስነልቦናዊ ደህንነት በመደገፍ እና እነዚህ ወጣት ተማሪዎች በተቻላቸው መጠን በትምህርት ቤት ሥራቸው ላይ ትኩረታቸውን እንዲቀጥሉ የመምከርና የማበረታታትን ሚዛን ለመጠበቅ ጥረት አደርጋለሁ-እታገላለሁ። ባለፈው ሣምንት፣ ለብቻ የሚሠራ የቤት ሥራ እንዲሠሩ እና ሠርተው የጨረሱትን ማስረከብ አስፈላጊ እንደሆነ እያስረዳሁ እያለ፣ አንድ ተማሪ ደወለና "ነገር ግን አሁን ትምህርት ቤት እስከዓመቱ መጨረሻ ተዘግቷል -But now school is closed until the end of the year" በማለት ተናገረ።

ይህ ሃሳብ ህንፃዎች እንዴት እንደተዘጉና ትምህርት እንደቀጠለ የክፍል ውይይት አስነሣ ህንፃዎች ተዘግተዋል- ነገር ግን እኛ እስካሁን እየተማርን እና እያደግን (እኛን በሚመለከት) ለአምስተኛ ክፍል እየተዘጋጀን ነው። በአጭሩ፣ ትምህርት እስካሁን ክፍት ነው! በመጨረሻም፣ ልጁ በለሆሳስ ድምፅ ደግሞ በመናገር "ቢሆንም ግን እነርሱ ትምህርት ቤት ተዘግቷል ብለዋል አለ- but they said school is closed."

ይህ ንግግር መልእክቱ በትክክል ምን እንደሚል ከ MCPS ድረ-ገጽ ላይ ወደ ማጣራት አመራኝ። "... all Maryland schools are to remain closed for the rest of the school year."   የሜሪላንድ ትምህርት ቤቶች በጠቅላላ ለቀሪው የትምህርት ዓመት ዝግ ናቸው።

ለአንዳንዶች ይሄ ግልፅ የሆነ መልእክት ነው፤ ለሌሎች ምናልባት የትርጉም ጉዳይ ይሆናል "just semantics"፣ ለሌሎች ደግሞ ማምለጫ ቀዳዳ ሊሆን ይችላል፣ ነገር ግን ይህ መግለጫ የሚለው "ትምህርት ቤት ዝግ ነው፣" የበረዶ ቀን እንደሚባለው ነው።

እነዚህ ነገሮች ሁሉ አንድ መጠየቅ ወደምፈልገው ነጥብ ያመጡኛል፤ ይኼውም፦ መልክቱን-ኮሙሚኬሽኑን ትምህርት ቤት ተዘግቷል ከማለት ይልቅ የትምህርት ቤት ህንፃዎች ተዘግተዋል፣ ነገር ግን ትምህርቱ እስካሁን እነደቀጠለ ነው!!?/"school is closed," to (something like) "School buildings are closed, but SCHOOL IS STILL ON!!?”

የእኔ መነሻ ሃሳብ ግልጽነት ያለው ቃል ይበልጥ ግልጽ የሆነ መልእክት ያስተላልፋል ለማለት ነው። የሆነ ሆኖ፣ በእኔ ተማሪ ንግግር ላይ እንደገለጽኩት፣ መልእክቱን በድጋሚ ግልፅ አድርጎ በማስቀመጥ ጥቅም እንዳለው ተገንዝቤአለሁ። መከበር ያለበትን ምክንያት መነጋገር-ኮሙኒኬት ማድረግ እድል ነው! የፅኑነት መልእክት ነው። የትምህርት ቤት ህንፃዎች የተዘጉ ቢሆንም፣ ትምህርት እስካሁን እንደቀጠለ ነው። ምንም እንኳ ከጓደኞቻችን ጋር በአውቶቡስ ወደ ትምህርት ቤት ባንሄድም፣ በመጫወቻ ሜዳ ላይ ባንሯሯጥም እና ከክፍል ጓደኞቻችን ጋር በትምህርት ቤት ህንጻ መተላለፊያዎች ላይ ባንመላለስም ቅሉ እስካሁን ድረስ ትምህርት እየተማርን ነው። እስካሁን ትምህርት እየተማርን እና ወደፊት እየሄድን ነው! ኮሮና ቫይረስ እኛን ከትምህርታችን እንዲገታን አንፈቅድለትም !!!"

Jean Carlson
4th Grade Teacher

እና፣ የድረ-ገጽ መልእክቱን ቀይረናል!

ትምህርት እስካሁን ድረስ እየተካሄደ መሆኑን በግልጽ የሚያሳይ ምሣሌ በስፔሻል ኢጁኬሽን ፕሮግራም ከአምስት መምህራን ጋር ባደረግሁ ውይይት ላይ ይገኛል። እነዚህ አምስቶቹ ሃሳባቸውን ሲያጋሩ፣ ስለ ሥራዎቻቸው ስሜታቸውን እና የሥራ ባህርያቸውን ሲያካፍሉ፣ ድንገተኛ ሁኔታ በሥራቸው ላይ ያስከተለውን ለውጥ እና የተማሪዎቻቸውን ፍላጎት ለማሟላት እንዴት አይነት የፈጠራ ጥረቶቻቸውን እንደሚጠቀሙ በጣም ጥሩ ሃሳብ ያላቸው እና ተማሪን ማዕከል ያደረጉ ናቸው። ከመቼውም ጊዜ የበለጠ አሁን ከተማሪዎቻችን ጋር በየቀኑ ለምንሰራቸው ሥራዎች ሳይንስን፣ ስነጥበብን እና ቀና የሆነ ልብን የሚጠይቅ እጅግ ጠቃሚ የሆኑ ቁምነገሮችን ገልጸዋል።

Thank you Britanny Miller, Carrie Carlson, Jerry Turner, Kristin Secan and Susan Russell—the five of you, along with Jean Carlson—demonstrate that school is still on and that you bring infinite amounts of science, art and heart to the job.  ብሪታኒ ሚለር፣ ኬሪ ካርልሰን፣ ጄሪ ተርነር፣ ክርሲትን ሰካን፣ እና ሱዛን ረስል—አምስታችሁም፣ ከጄን ካርልሰን ጋር—እስካሁን ድረስ ትምህርት እንደቀጠለ እና ማብቂያ የሌለው የሳይንስ፣ የስነጥበብ እና ቅን ልብ በሥራችሁ ላይ በተግባር ስላሳያችሁ በጣም እናመሰግናለን።

blog-speced

 
Montgomery County Public Schools

View as a Web Page

Montgomery County Public Schools
850 Hungerford Drive, Rockville, MD, 20850
Call: 240-740-3000 | Spanish Hotline: 240-740-2845