Is this email not displaying correctly? View it in your browser Date: April 6, 2020

mcps logo

English | español | 中文 | français | tiếng Việt | 한국어 | አማርኛ


ለወላጆች እና ለሞግዚቶች ጠቃሚ መረጃ ስለ ተማሪ የማይገለፅ ግለ ሁኔታ እና ስለ ትምህርት ቀጣይነት

የተከበራችሁ ወላጆችና አሳዳጊዎች፣

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) በአካል ወይም ኦንላይንም ቢሆን፣ ለተማሪዎች እና ለሠራተኞች ደህንነቱ የተጠበቀ እና አመቺ የትምህርት አካባቢ ለመስጠት ቁርጠኛ ነው። በዚህ ሣምንት፣ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የትምህርት ቤት ህንፃዎች የተዘጉ ቢሆንም ተማሪዎች ትምህርታቸውን መቀጠል የሚያስችላቸውን የመጀመሪያ ምዕራፍ/phase one የትምህርት ቀጣይነት ፕላን ጀምረናል። እንደምታውቁት፣ ፕላኑ ተማሪዎች ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ እና ከጓደኞቻቸው-ከእኩዮቻቸው እና ከአስተማሪዎቻቸው ጋር መተባበር/መረዳዳት የሚያስችላቸው አውታረመረብን መሠረት ያደረገ መሣሪያዎችን- web-based tools ያካተተ ነው። እነዚህ አዳዲስ መሣሪያዎች/tools ለመማር አዳዲስ እድሎችን የሚሰጡ ቢሆንም ስለ ተማሪ የማይገለፅ የግል ገመና አሳሳቢነት ጥንቃቄ ጭምር ከግምት እናስገባለን። MCPS በኦንላይን አጠቃቀም የተማሪን ግላዊ ገመና ለመጠበቅ ያወጣቸው ፖሊሲዎች፣ የመጀመሪያ ስምምነቶች እና የዲጅታል ደህንነት ጥበቃ-መከላከል እርምጃዎችን የሚመለከት መረጃ ከዚህ በታች ይገኛል።

የተማሪ ግለሁኔታ ፖሊሲዎች እና ደንቦች-

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ስለ ኮምፒውተር ሲስተሞች አጠቃቀም እና አስተዳደር ጠንካራ ፖሊሲዎች እና ደንቦች አሉት። በ Regulation IGT-RA እንደተገለጸው፣ User Responsibilities for Computer Systems, Electronic Information, and Network Security/ስለኮምፒውተር ሲስተሞች፣ ስለ ኤሌክትሮኒክ መረጃ፣ እና ስለ ኔትዎርክ ደህንነት የተጠቃሚ ሃላፊነት ፣ ሳይፈቀድ ይፋ ማድረግ፣ በዝቅተኛ የእድሜ ክልል የሚገኙ ልጆችን የግል መረጃ መጠቀም እና ማሰራጨት ለማንኛውም ተጠቃሚ ሆን ብሎ እንዳይሳተፍ/እንዳትሳተፍ የተከለከለ ነው፤ እና ማንኛውም ከ MCPS ሲስተም ወይም ኢንተርኔት ጋር የተገናኘ ማቴሪያል ወይም መረጃ ከትምህርት ዓላማ ጋር ወጥነት ያለው መሆን አለበት። በዚህ ኦንላይን ትምህርት በሚከታተሉበት ወቅት፣ የ MCPS Student Code of Conduct፤ Regulation JFA-RA፣ Student Rights and ResponsibilitiesA Student’s Guide to Rights and Responsibilities in MCPS፤ እና ያሉት የትምህርት ቦርድ ፖሊሲዎች እና የ MCPS ደንቦች በጠቅላላ በተግባር መዋላቸው ይቀጥላል። የተማሪን ግላዊ ሁኔታ በአጽንኦት እንጠብቃለን፣ እናም ከእኛ የስነምግባር አሠራር ውጪ ይህንን ደንብ በሚጥስ-በምትጥስ ተማሪ ወይም ሠራተኛ ላይ የዲስፕሊን እርምጃ የመውሰድ መብት አለን።

በቪድኦ ስለሚደረጉ ኮንፈረንሶች ደህንነት ለመጠበቅ የ MCPS ጥረት

በቪድኦ ለሚደረጉ ኮንፈረንሶች እና ቀጥታ ለሚተላለፍ የማስተማር ተግባር የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ "Zoom platform" ይጠቀማል። የእርስዎ ልጅ በቀጥታ ስርጭት ትምህርት ላይ የሚሳተፍ-የምትሳተፍ ከሆነ(ች)፣ ያልታቀደ-ያልታሰበ ሦስተኛ ወገን የመመልከት ወይም ሪኮርድ የማድረግ ሁኔታ ይፈጠር ይሆናል። ተማሪዎች ኦንላይን ቪድኦ ኮንፈረንስ እየተከታተሉ ባሉበት ወቅት ተገቢ ያልሆነ ኦንላይን ባህርይ ለመለየት፣ የተማሪን ተጠቃሚ ስም፣ ትምህርት ቤት እና የትምህርት ቤቱን አድራሻ ጭምር MCPS የተጠቃሚ መረጃን ይሰበስባል። በእነዚህ መድረኮች-platforms ተደብቆ መጠቀም ስለማይቻል አግባብነት የሌለው ባህርይ በፍጥነት ይወገዳል። ለእነዚህ መረጃዎች ያለን ተደራሽነት በ MCPS አማካይነት ደህንነቱ የተጠበቀ እና ልክ እንደ መልካም ባህርይ-ቨርቹወል፣ በጨዋነት የመጠቀም ሁኔታን ለመጠበቅ ይረዳል። በተማሪዎች ላይ የሚወሰዱ የዲስፕሊን እርምጃዎች የሚያካትቱት፦ በዚህ ብቻ አይወሰንም፤ ወላጆችን ወይም ሞግዚቶችን በስልክ መጥራት፣ ልዩ ጥቅሞችን መከልከል፣ የተበላሸ/የጠፋ/የተሰበረ ነገርን መተካት፣ መታገድ፣ እና/ወይም መወገድ-ማስወጣት-መባረር፣ እና/ወይም በወንጀል ተጠያቂ-ተከሳሽ መሆን። (እነዚህን ደንቦችና መመሪያዎች ይመልከቱ፦ MCPS Regulation JFA-RA, Student Rights and Responsibilities; Regulation IGT-RA, User Responsibilities for Computer Systems, Electronic Information, and Network Security; and school discipline policies).

"Zoom Conferencing" በተመለከተ ስለ ግለሁኔታ ጠቃሚ መረጃ
Zoom ስለተማሪዎች የሚከተለውን መረጃ እንደሚሰበስብ እባክዎ ይገንዘቡ፦

  • ማንነትን ለመለየት የተለመደው አይነት የመረጃ አሰባሰብ፣ እንደ የተጠቃሚ ስም እና ሌላ ተመሣሣይ መለያዎች (ለምሳሌ፦ የተማሪ ኢ-ሜይል አድራሻ፣ የተማሪ መታወቂያ ቁጥር፣ የመጀመሪያ እና የመጨረሻ ስም)። አካውንት ለመፍጠር ይሄ መረጃ በ MCPS አማካይነት ለ Zoom ይሰጣል።
  • ተማሪው(ዋ) ስለሚጠቀምበት-ስለምትጠቀምበት ዲቫይስ፣ ኔትዎርክ እና የኢንተርኔት ግንኙነት መረጃ። ይህ መረጃ በ Zoom የሚሰበሰብበት ምክንያት የበይነመረብ ኮንፈረንስ-web conference ተጠቃሚነት ለመስጠት ነው።
  • ስለ ተማሪ የ "Zoom platform" መድረክ አጠቃቀም መረጃ፣ የተወሰዱ እርምጃዎችን ጨምሮ፣ ቀን እና ሠዓት፣ ድግግሞሽ፣ የቆየ(ች)በት ጊዜ፣ ብዛት፣ ጥራት፣ የኔትዎርክ ግንኙነት ሁኔታ እና ለመግባት ሲከፈት የትግበራ ሁኔታ መረጃ/performance information፣ logins, clicks, messages, contacts, content viewed and shared, calls, use of video and screen sharing, meetings, cloud recording and other feature usage information የመሣሰሉትን መረጃዎች ሁሉ ያጠቃልላል። Zoom ይህንን የሚሰበስበው የበይነመረብ ኮንፈረንስ መጠቀምን ለማስቻል ነው።
  • ሌላ መረጃ ተጠቃሚዎች—መምህራንን ጭምር፣ የትምህርት ቤት አስተዳዳሪዎች እና ተማሪዎች—የሚጭኑት/upload፣ የሚሰጡት ወይም Zoom በሚጠቀሙበት ጊዜ የሚፈጥሩት-የሚከፍቱት። ይህ መረጃ በ Zoom አማካይነት ይሰበሰባል።

በቤተሰብ የመማር መብቶች እና ግለሁኔታ ድንጋጌ-Family Education Rights and Privacy Act (FERPA) እና በሌሎች ህጎች ላይ የተደነገጉ የእርስዎ መብቶች
በ MCPS የሚጠበቁ በኤሌክትሮኒክ የሚደረጉ የተማሪ ሪኮርዶች እንደማናኛውም ሌሎች ሪኮርዶች፣ አያያዛቸው በ Family Education Rights and Privacy Act (FERPA)፣ ተፈጻሚ የሚደረጉ የፌደራል ደንቦች፣ እና የ Code of Maryland Regulations (COMAR) 13A.08.02.መሠረት ይሆናል። እነዚህ መብቶች ለወላጆች እና ለሞግዚቶች በሚተላለፈው ዓመታዊ የማጠቃለያ ሪፖርት ላይ ተገልጸዋል፣ በተጨማሪም በምዝገባ ወቅት የተገለጹ ናቸው። "Zoom platform" ለመጠቀም የማይፈልጉ ወላጆች የልጃቸውን አስተማሪ ወይም ርእሰመምህር ማነጋገር አለባቸው።

እንዲሁም የእርስዎን ተማሪ ግላዊ ገመና ለመጠበቅ "Zoom platform" ስለሚያደርገው ጥንቃቄ-ጥረት እዚህ መመልከት ይችላሉ። የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) በ "Zoom" እና በታወቁ የኢንዱስትሪ ሳይበርሰኩሪቲ ባለሙያዎች አማካይነት የታዘዙ ጠቅላላ ቴክኒካዊ ፖሊሲዎችን እና መቼቶችን/ቅንብሮችን/settings አካቷል።

የተማሪ እና የወላጅ/ሞግዚት ኃላፊነቶች
የተማሪን ግላዊ ገመና ከመጠበቅ አኳያ ተማሪዎች፣ ወላጆች እና ሞግዚቶችም እንደዚሁ ሚና መጫወት ይችላሉ። MCPS የኮምፒውተር እቃ/equipment፣ አገልግሎት እና የኔትዎርክ ተጠቃሚነትን ለተማሪዎች እና ለሠራተኞች የሚሰጠው ከ MCPS ተልእኮ ጋር ለሚጣጣሙ ዓላማዎች ብቻ ነው። ነገር ግን፣ የመልካም ስነምግባር ሃላፊነቱ የሚወድቀው የእኛን የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሪሶርሶችን-መገልገያዎችን በሚጠቀሙ ላይ ነው። ስለ ተማሪ ግለሁኔታ እና ክፍል መሰል ተቀባይነት ያለው ባህርይ አስፈላጊ የሆኑ ጥቂት ተቃሚ ህጎችን ከዚህ በታች ገልፀናል።

  • የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ የርቀት ትምህርት የሚከታተሉ/MCPS distance learning ወላጆች፣ ሞግዚቶች እና ተማሪዎች ኦንላይ ከሚማሩት ትምህርት የትኛውንም ያክል ክፍል በማንኛውም ሁኔታ ሪኮርድ ማድረግ፣ ማባዛት ወይም ማጋራት/ፖስት ማድረግ አይፈቀድም እና የተማሪን መረጃ ይፋ ከማድረግ መቆጠብ/ማስወገድ ይኖርባቸዋል።
  • መሰል/ቨርቹወል የትምህርት ክፍል ከመግባታቸው በፊት፣ ተማሪዎች በዚህ ህግ ላይ በተገለጸው መሠረት በአግባብ መልበስ አለባቸው MCPS Regulation JFA-RA፣Student Rights and Responsibilities/የተማሪ መብቶች እና ግዴታዎች-ኃላፊነቶች
  • ተማሪዎች ዙሪያውን ተገቢ የሆነ ሥፍራ መጠቀም አለባቸው (ይህ ማለት፦ ሌሎች የቤተሰብ አባላት በማይታዩበት ቦታ፣ እና አስከፊ-አናዳጅ-የሚያበሳጭ አይነት ፖስተሮች እና ሌሎች ነገሮች የሌሉበት ሥፍራ)
  • ተማሪዎች ፀጥታ ባለበት ሥፍራ መሆን አለባቸው፣ ወይም እየተሰጠ ያለውን ትምህርት እንዳያደናቅፍ የማይክሮፎን/microphones ድምፅ እንዳይሰማ ማድረግ ይኖርባቸዋል። በተጨማሪ፣ በማናቸውም የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ በይነመረብ መድረክ-MCPS web-based platform ላይ የቪድኦ ፈንክሽን መጠቀም የግዴታ አስፈላጊ ስለማይሆን፣ በጠቅላላ ተማሪዎች ወይም ሞግዚቶች የቪድኦ ፈንክሽኑን መዝጋት ይችላሉ።
  • ተማሪዎች ሁልጊዜም በመማሪያ ክፍል የሚደረገውን አይነት ሥነምግባር መከተል-መፈጸም-ማክበር አለባቸው።

ስለ እርስዎ ተማሪ ኦንላይን ግላዊ ሁኔታ ተጨማሪ ጥያቄዎች ወይም አሳሳቢ ሁኔታዎች ካሉዎት፣ እባክዎ ይህንን በይነመረብ ይጎብኙ እዚህ ወይም ከዚህ በታች ባለው ሊንክ ላይ የሚገኙትን ሪሶርሶች ይመልከቱ።

ተማሪዎችን እና መምህራንን በመሰል ሁኔታ/virtual way እንደገና ለመገናኘት የሚያስችል አዲስ እድል ደስታ ይሰማናል፣ እና የተማሪዎችን ደህንነት በመጠበቅ ረገድ የሚያደርጉትን ትብብር እናደንቃለን።