የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ኮርሶች የውጤት አሠጣጥ ምርጫ
እስከ ጁን 12፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ኮርሶችን የሚወስዱ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች የመጨረሻውን ሴሚስተር ውጤት ለአራተኛ የማርክ መስጫ ክፍለጊዜ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የኦንላይን ፖርታል የሴሚስተር ኮርሶች በፊደል ወይም አልፏል-አልፋለች/ወይም አላጠናቀቀም-አላጠናቀቀችም (a letter grade or Pass/Incomplete) መርጠዋል። እነዚህ አማራጮች ጁን 23 በፖስታ በሚላክ ሪፖርት ካርድ ላይ ይንፀባረቃሉ። ተማሪዎች በፖርታል ምርጫ ለማድረግ ያልቻሉ ከሆነ፣ አስቀድሞ የተቀመጠ ተማሪን የሚጠቅም አማራጭ ተግባራዊ ይደረጋል እና ይህም በሪፖርት ካርድ ላይ ይገለጻል።
ኦንላይን ፖርታል ላይ ስለ ውጤት አሠጣጥ ምርጫ ለማድረግ ያልቻሉ ወይም ምርጫቸውን እንደገና ለማየት የሚፈልጉ ተማሪዎች፣ እባካችሁ ሪፖርት ካርዳችሁን አግኝታችሁ ከተመለከታችሁ በኋላ የትምህርት ቤታችሁን ካውንስለር አነጋግሩ። ተማሪዎች በመጪው ጊዜ ስለ ውጤት አሰጣጥ ምርጫቸውን እንደገና መመልከት ይችላሉ። የበለጠ መረጃ ለማግኘት ይህንን ቪድኦ ይመልከቱ።
የሜሪላንድ ስቴት ዲፓርትመንት በስቴት ሪፖርት ካርድ ስለተማሪ የወጪ ሁኔታ ይገለጻል
ከዚህ ዓመት ጀምሮ፣ በየዓመቱ በሚዘጋጁ የትምህርት ቤት ሪፖርት ካርዶች ለአንድ ተማሪ የሚወጣውን ወጪ መጠን መረጃ/ዳታ MSDE እየደመረ ያወጣል። ስቴቶች እነዚህን መረጃዎች መስጠት ያለባቸው የ Every Student Succeeds Act፣ ወይም የ ESSA—ሚዛናዊነት፣ ትክክለኛነት፣ ኃላፊነት እና ተጠያቂነት፣ እና ለህዝብ ትምህርት ቤት ተማሪዎች በጠቅላላ ምርጥ የሆነ ትምህርት የመስጠት ድንጋጌ አካል በመሆኑ ነው። በትምህርት ቤት ለአንድ ተማሪ የሚወጣውን የወጪ ደረጃ ተፅኖ የሚያደርጉ በርካታ ምክንያቶች ይኖራሉ። እነዚህ ምክንያቶች፥ በትምህርት ቤት የሚገኙ የተማሪዎች ቁጥር፣ የሚሰጡት ስፔሻል ኢጁኬሽን አገልግሎቶች፣ የትምህርት ቤት አመዳደብ፣ እንደ "Title I and Focus schools" የመሣሠሉትን፣ እና የሠራተኞች የልምድ ደረጃ—ለምሣሌ፣ በትምህርት ቤት ህንፃ ውስጥ ይበልጥ ያገለገሉ መምህራንን ከአዳዲስ መምህራን ጋር በማነፃጸር ይዘጋጃሉ። ይህ መረጃ-ኢንፎርሜሽን ከጁን 23 ጀምሮ ለህዝብ ይፋ ይደረጋል።
የሠመር ፕሮግራሞች
የ MCPS ተማሪዎች ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ክሬዲት ቨርቹወል የሠመር ትምህርት-Virtual Summer School የመመዝገቢያ ቀነ-ገደብ ጁላይ 3 ነው። የእርስዎን ልጅ የሠመር ትምህርት ለማዳበር የተለያዩ በርካታ የትምህርት ማበልጸጊያ ፕሮግራሞችን እና አውደጥናቶችን-ዎርክሾፓችን ለመስጠት MCPS ከበርካታ ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶች ጋር፣ ከቢዝነስ እና ከካውንቲ ኤጀንሲዎች ጋር ትብብር ማድረጋችንን ስንገልጽ ደስታ ይሰማናል። ያሉትን ፕሮግራሞች ዝርዝር ለማየት፣ እባክዎ የሠመር ፕሮግራሞችን ድረ-ገጽ ይጎብኙ። ፕሮግራሞቹ ግብ መተለምን ጨምሮ፣ ስለ ፋይናንስ ሊተረሲ፣ ሙዚቃ፣ ስነጥበብ-አርት፣ ዳንስ እና STEM በርካታ የተለያዩ አርእስቶችን ይሸፍናሉ።
"Waymaking Special Event" የተሰኘ ልዩ ዝግጅት ዘረኝነት በአእምሮ ጤንነት ላይ ስለሚኖረው ተፅኖ ውይይት ያካሄዳል
MCPS "Waymaking" የተሰኘ ልዩ የሆነ ቨርቹወል ሁነት፣ ዘረኝነት በአእምሮ ጤንነት ላይ ስለሚያሳድረው ተፅኖ ትኩረት የሚያደርግ ግልጽነት የተሞላበት-ውይይት ያካሄዳል። ውይይቶቹ ማክሰኞ፣ ጁን 30 እና ማክሰኞ፣ ጁላይ 7፣ ከ 6:30–8 p.m በሁለት ክፍሎች— በኦንላይን ይካሄዳሉ። ሁነቶቹ የሚስተናገዱት በ Dr. Christina Conolly, director of psychological services for MCPS, እና John Landesman, a coordinator in the Equity Initiatives Unit አማካይነት ይሆናል። ሁለቱ የመድረክ ውይይቶች ከሚያቀርቡት ማብራሪያዎች በተጨማሪ፣ የጥያቄ እና መልስ ክፍለጊዜዎች ይኖራቸዋል።
ጁን 30 የሚካሄደው ሁነት የአእምሮ ህመምን በሚመለከት ያሉትን የጤና-የህክምና ተደራሽነት ችግሮች እና መሰናክሎችን ይዳስሳል። ይህም ስለ ማህበራዊ ፍትሃዊነት እና ስለ አእምሮ ጤንነት ያለውን አመለካከት እና መጥፎ ስያሜ-stigma ውይይት ያካትታል።
የጁላይ 7 ውይይት ሰዎች እንዴት የአእምሮ ጤንነት ስጋቶችን ለመርዳት እንደሚችሉ እና የአእምሮ ጤንነት ነቀፌታን እንዴት ማስወገድ እንደሚቻል በውይይቱ ላይ ይተኮራል።
webinars እዚህ ይሳተፉ።
ስለ ቅድመ ምዋእለ ህፃናት-ሄድስታርት ምዝገባ Prekindergarten/Head Start Registration
ሴፕተምበር 1 ላይ ወይም ከዚያ ቀደም ሲል አራት ዓመት እድሜ የሚሞላው-የሚሞላት ልጅ አለዎት? ካለዎት፣ ለፎል 2020፣ ቅድመ ምዋእለ ህፃናት/ሄድስታርት ፕሮግራም-Prekindergarten/Head Start program ለማስመዝገብ ጊዜው አሁን ነው። ምዝገባውን በኦንላይን እና በሥልክ ለማስመዝገብ ይቻላል። በ MCPS ድረ-ገጽ ላይ ማመልከቻ እና ዳሰሳ-survey በመሙላት ማስመዝገብ ይጀምሩ። በዳሰሳው ላይ ኦንላይን ማመልከቻ መሙላት፣ ወይም በፖስታ የሚላክ የወረቀት ማመልከቻ ስለማግኘት፣ ወይም ማመልከቻ ለመሙላት እርዳታ ስለመጠየቅ መምረጥ ይችላሉ። በተጨማሪ፣ ወላጆች የማስመዝገብ እርዳታ ለማግኘት በስልክ ቁጥር፦ 240-740-5999 ደውለው ለመጠየቅ ይችላሉ።
የትምህርት ቤት ቤተመጻህፍት የሚድያ ፕሮግራሞች-School Library Media Programs
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) በሠመር ወቅት ተማሪዎች እና ወላጆች እንዲጠቀሙ ሁለት የቨርቹወል ስብስቦች የ eBook platforms-መድረኮችን አዘጋጅቷል። ሁለቱም ስብስቦች ተማሪዎች በ MCPS፣ የሞንትጎመሪ ካውንቲ የህዝብ ቤተመጻህፍት፣ trials፣ እና ነፃ ድረ-ገጾች የተለያዩ በርካታ መድረኮችን ኢንፎርሜሽን የያዙ ናቸው። እነዚህ ሁለት ስብስቦች በሠመር ወቅት እንዴት የ "e-content" ተደራሽነት እንደሚኖራቸው መረጃ ይሰጣሉ።
ኤሌሜንታሪ
ሁለተኛ ደረጃ
የሞንትጎመሪ ካውንቲ የሠመር ወቅት የሥራ ቅጥር ፕሮግራም ጀምሯል
በሞንትጎመሪ ካውንቲ ከ 16-23 ዓመት እድሜ ያላቸው ነዋሪዎች በአገልግሎት እና በማገገሚያ መካከል ሽግግር የሚፈጥር ፕሮግራም “COVID Corps” የተሰኘ የሠመር ሥራ እድል መስጠት ተጀምሯል። የ "COVID Corps" አባላት፣ በሞንትጎመሪ ካውንቲ የመዝናኛ ማእከላት ሠራተኞች አማካይነት ቁጥጥር እየተደረገ፣ በአጠቃላይ በካውንቲው ውስጥ የኮቪድ-19 (COVID-19) ወረርሽኝን ምላሽ በመስጠት ሥራ ላይ ይሠማራሉ። የሞንትጎመሪ ካውንቲ ለቁጥጥር፣ ለመምራት፣ እና ስልጠና ለመስጠት አዋቂ ሰዎችን እና አሠልጣኞችን ጭምር ማናቸውንም ለውጤት የሚያበቁ አስፈላጊ ነገሮችን ይሰጣል። ተጨማሪ መረጃ እዚህ ይገኛል።
|