boy in mask on bus

የተከበራችሁ ወላጆች፣ ተማሪዎች እና ሠራተኞች

ፌብሩወሪ 23 በተደረገው የትምህርት ቦርድ ስብሰባ ላይ፣ የ MCPS ሠራተኞች ወደ ትምህርት ቤት ስለመመለስ እቅድ በርካታ መረጃዎችን አካፍለውናል። ስለ እቅዱ ማወቅ ያለባችሁ አምስት ነግሮችን እነሆ:

 1. የጊዜ ማእቀፉ እና የሚመለሱት ተማሪዎች ቡድኖች ለውጥ የለውም። ቦርዱ ማርች 23 ባደረገው ስብሰባ ክለሳ ስለማድረግ እና የመመለሻውን ጊዜ በሚመለከት ለማፋጠን ውይይት አድርጓል። የጊዜ ሠሌዳውን እና የሚመለሱ ቡድኖች/የሚመለሱባቸውን ቀኖች በሚመለከት የት እንዳለን ከዚህ በታች ያሉትን ምስሎች ይመልከቱ:

  timeline

  የሚመለሱ ተማሪዎች

  ልዩ ትምህርት (March 1)
  የሙያ እና የቴክኒክ ትምህርት(March 1)
  • በአእምሮ ዘገምተኝነት የተጠቁ K-12 Autism K-12 Program
  • የሚራዘም ፕሮግራም
  • የትምህርት ቤት ማህበረሰብን-መሠረት ያደረጉ ፕሮግራሞች
  • ልዩ ት/ቤቶች
  • አውቶሞቲቭ
  • ኮንስትራክሽን
  • የውበት ሙያ ትምህርት/Cosmetology
  • የጤና እንክብካቤ ሙያዎች
  • የምግብ ቤት ማኔጅመንት

  ፈረቃ I
  ቡድን 1.1 (ማርች 15)
  ቡድን 1.2 (ኤፕሪል 6)
  • የልዩ ትምህርት ፕሮግራሞች Specific Special Education Programs
  • የልዩ ሙያ እና የቴክኒክ ትምህርት (CTE) ፕሮግራሞች
  • ከምዋእለ ህጻናት እስከ 3ኛ (K-3) ክፍሎች
  • አማራጭ የትምህርት ፕሮግራሞች
  • CREA
  • METS
  • ልዩ የስፔሻል ኢጁኬሽን ፕሮግራሞች Specific Special Education Programs
  • ከ 4ኛ - 5ኛ ክፍሎች
  • ቅድመ መዋዕለ ህፃናት Prekindergarten
  • 6ኛ ክፍል
  • 12ኛ ክፍል
  ፈረቃ II
  ቡድን 2.1 (ኤፕሪል 19)
  ቡድን 2.2 (ኤፕሪል 26)
  • 8ኛ ክፍል
  • 9ኛ ክፍል
  • 11ኛ ክፍል
  • 7ኛ ክፍል
  • 10ኛ ክፍል

  ትምህርት ቤቶች ዝርዝር እቅዶችን ከቤተሰቦች ጋር በኢሜይል እና በወላጅ/ማህበረሰብ ስብሰባዎች ላይ ማስተላለፍ ጀምረዋል። የመረጡትን ለማስታወስ ካልቻሉ ወይም ለውጥ ማድረግ የሚፈልጉ ከሆነ፣ የመጨረሻው ቀን ፌብሩወሪ 26 ነው። ከቨርቹወል - በአካል ለመቀየር የሚፈልጉ ከሆነ፣ የእርስዎ ትምህርት ቤት አሁን በቂ ቦታ ከሌለው በተጠባባቂ ዝርዝር ያቆያል።

 2. ጤንነት/ደህንነት ለእኛ የቅድሚያ ትኩረታችን ነው። የራስ ጤንነት መከላከያ ቁሳቁሶችን (ጭምብሎች (masks)፣ ሳኒታይዘሮች (sanitizer)፣ የእጅ ጓንቶች (gloves)፣ ወዘተ/etc) ለመግዛት MCPS ከ$15 ሚሊዮን በላይ ወጪ አድርጓል። እንዲሁም HVAC እና የሴፍቲ መገልገያዎች ላይ ከፍተኛ ለውጦችና ማሻሻያዎች ተደርገዋል። ይህም በት/ቤቶች ውስጥ የተሻሉ የአየር ማጣሪያዎችን መተካት እና መግጠምን ይጨምራል (65,000 የአየር ማጣሪያዎች ተቀይረዋል፣ እና ባሉት ሲስተሞች ላይ ተጨማሪ ለማድረግ 5,000 የአየር ማጣሪያዎች ተገጥመዋል)። የሚከተሉትን እርምጃዎች በመውሰድ አብረን እየሠራን በመተጋገዝ የኮቪድ-19 ስርጭትን መቀነስ እንችላለን:

  • የፊት ጭምብሎችን መጠቀም/መልበስ
  • አካላዊ ርቀት መጠበቅ
  • ዘወትር እጅ መታጠብ እና ሳኒታይዘር መጠቀም
  • የ/ቤት እና የመማሪያ ክፍሎችን ንጽህና መጠበቅ
  • ሣምታዊ የጤንነት ማረጋገጫ
  • ለሠራተኞች ክትባት ለመስጠት ከስቴት እና ከካውንቲ ኃላፊዎች ጋር መሥራት
  • በህንጻዎች ውስጥ በቂ የአየር ዝውውር/እና የውሃ ሲስተም በትክክል እንዲሠራ ማድረግ
  • የኮቪድ-19 ምርመራ ፕሮቶኮሎችን መተግበር
  • ክትትል ማድረግ
 3. ለተማሪዎች እና ለሠራተኞች የኮቪድ-19 ምርመራ በነፃ ይሰጣል። የኮቪድ-19 ምርመራ በየትምህርት ቤቱ የሚሰጥ ሲሆን ከማርች 15 ጀምሮ ይደረጋል። ሠራተኞች እና ተማሪዎች አፍንጫ በመጎርጎር የሚደረገውን ምርመራ ራሳቸው ያደርጉታል፣ በት/ቤት ፖዚቲቭ ኬዝ ከተገኘ ለቤተሰቦች ይገለጻል። የግዴታ ስለማይሆን—ሠራተኞች እና ተማሪዎች ካልፈለጉ መተው ይችላሉ። በእኛ በኩል ስለሚደረገው የኮቪድ-19 ምርመራ ፕሮግራም ይበልጥ መረጃ በፍጥነት ይሰጣል። ተማሪዎች እና ሠራተኞች በየሣምንቱ የጤንነት ማረጋገጫ ቅጽ እንዲሞሉ ይጠየቃሉ። ቅጹ በሁሉም ቋንቋዎች የሚገኝ ሲሆን ሊንኩ በፍጥነት ለቤተሰቦች ይላክላቸዋል። በመማሪያ ክፍል ውስጥ/ወይም በትምህርት ቤት ፖዚቲቭ ኬዝ ከተገኘ ከትትል በማድረግ MCPS ከካውንቲው የጤና ባለሙያዎች ጋር በቅርበት ይሠራል። ተማሪዎቻችን እና ሠራተኞቻችን በኮቪድ ከተያዘ(ች) ግለሰብ ጋር ከተገናኙ ራሳቸውን እንዲያገሉ (ኳራንቲን) ይፈለጋል።

  በት/ቤት ስለሚደረግ የኮቪድ-19 ምርመራ ይህንን አጭር ቪድኦ ይመልከቱ
 4. ተማሪዎች ከአስተማሪዎች ጋር በየቀኑ እየተገናኙ ይሠራሉ። የተማሪዎችን ፍላጎት ለማሳካት (በአካል እና ቨርቹወል ተማሪዎች) ትምህርት ቤቶች ቅይጥ የማስተማር ስልቶችን እየተጠቀሙ ተማሪዎች ትምህርት እና ድጋፍ ለማግኘት በየቀኑ ከአስተማሪዎቻቸው ጋር እና ከሌሎች የት/ቤት ሠራተኞች ጋር ይሣተፋሉ። በርካታ ተማሪዎች ሲመለሱ የትምህርት ቤት አቀራረብ ሊቀየር ይችላል። ለሁሉም ተማሪዎች የዳበረ ቨርቹወል ትምህርት ለመስጠት MCPS ማሻሻያዎችን በማድረግ ይቀጥላል። ይኼኛው ለሠራተኞች ይበልጥ ሙያ ማዳበርን፣ የተማሪን ደህንነት መንከባከብ እና ለተማሪ አመቺ የጊዜ ሠሌዳ መስጠትን ያካትታል።

 5. ሁሉም ምግቦች ይሰጣሉ። MCPS ቁርስ፣ ምሣ እና የእራት ምግቦችን በትምህርት ቤቶች እና የምግብ ማከፋፈያ ጣቢያዎች ላይ ለሁሉም ተማሪዎች በነጻ ይሰጣል። ተማሪዎች በትምህርት ቤት ግቢ ውስጥ የመማሪያ ክፍሎች እና ካፍቴሪያን የመሣሰሉ ሰፋፊ ቦታዎች ላይ አካላዊ ርቀት ኖሯቸው አግባብነት ያለው የተራራቀ የአቀማመጥ ስርአት እስከጠበቁ ድረስ በተለያዩ ቦታዎች እንዲመገቡ ይፈቀድላቸዋል።


ወደፊት ምን ይጠብቀናል?

ጤናማ የሆነ በአካል የት/ቤት ተሞክሮ ሞዴል ምን እንደሚመስል ለማየት ከፈለጉ እባክዎ ይህንን ቪድኦ ይመልከቱ. ይህንን ቪድኦ ይመልከቱ። በዚህ ምሽት ቀደም ብሎ የተካሄደውን ቨርቹወል የማህበረሰብ ውይይት እዚህ. መመልከት ይችላሉ። ወደ ት/ቤት ስለመመለስ እቅድ ከወላጆች፣ ከተማሪዎች እና ከሠራተኞች ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች የ MCPS ኃላፊዎች መልስ ሰጥተዋል። ወደ ት/ቤት ስለመመለስ እቅድ ተጨማሪ መረጃ በ MCPS የማገገም እቅድ በይነመረብ ላይ ይገኛል:
https://www.montgomeryschoolsmd.org/reopening/


ተጨማሪ ሪሶርሶችEmail us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools