Is this email not displaying correctly? View it in your browser Date: Sept. 24, 2020


mcps logo

English | español |  中文 | français | tiếng Việt | 한국어| አማርኛ | Português


የተወደዳችሁ ወላጆች፣ ሞግዚቶች፣ ተማሪዎች እና ሰራተኞች

ዛሬ (ሴፕተምበር 24)፣ የስቴት ትምህርት ቤቶች ሱፐርኢንተንደት ኬረን ሳልመን (Karen Salmon) በጠቅላላ በስቴት ትምህርት ቤቶች መካከል ስለሚካሄድ አትሌቲክስ ከሜሪላንድ የትምህርት ዲፓርትመንት የተላለፈ ወቅታዊ መመሪያ አጋርተዋል። የዚህ መመሪያ፣ ስያሜው በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መካከል የመጠባበቂያ ወቅት የአትሌቲክስ አማራጮች (Interscholastic Athletic Contingency Season Options) ፣ የተሰኘ ሲሆን ስለ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አትሌቲክስ ለትምህርት ቤት ዲስትሪክቶች ሁለት አማራጮችን ይገልጻል።

የመጀመሪያው አማራጭ የትምህርት ቤት ዲስትሪክቶች በሁለት ሴሚስተር እቅድ ላይ የተነደፈውን የወቅቱን ማእቀፍ የሁለት ሴሚስተር እቅድ-Two Semester Plan ከሜሪላንድ የሁለተኛ ደረጃ የህዝብ ትምህርት ቤቶች አትሌቲክስ ማህበር "Maryland Public Secondary Schools Athletic Association (MPSSAA)" ሴፕተምበር 11/2020 የተሰጠውን እቅድ እንዲከተሉ ይፈቅዳል። የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) አትሌቲክስ ፕሮግራም በዚህ ወቅት በመጀመሪያው ሴሚስተር ጭምር ይህንን እቅድ በ R.A.I.S.E. Reimagined የቨርቹወል አትሌቲክስ ማእቀፍ መሠረት ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ በማድረግ እየሠራበት ይገኛል። በተጨማሪ፣ የኮቪድ-19 የ MCPS አትሌቲክስ ግብረኃይል ለህብረተሰብ ጤንነት የማያሰጋ ሁኔታ ሲረጋገጥ እና ሁኔታው የ MCPS የሥራ እንቅስቃሴዎችን በማይገታበት ጊዜ በጤናማ ሁኔታ በአካል ወደሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ስለመመለስ እያቀደ ቆይቷል። እነዚህ እንቅስቃሴዎች፣ ልምምድ እና የብቃት ስልጠናዎችን የሚያካትቱ እንደመሆናቸው፣ በሁለተኛ ሴሚስተር በአካል ውድድር ይካሄዳል ተብሎ የታለመው ወቅት ከመጀመሩ በፊት በመጀመሪያው ሴሚስተር ላይ ይፈቀዳሉ። ከሁለቱ ሴሚስተር እቅድ ውስጥ የሁለተኛው ሴሚስተር አማራጭ በዊንተር፣ በፎል እና በስፕሪንግ የሚካሄዱ አጫጭር የስፖርት ወቅቶች ናቸው።

በዛሬው ቀን የተገለጸው ሁለተኛው አማራጭ፣ የአካባቢ የትምህርት ሥርዓቶቹ (local school systems) የአትሌቲክስ፣ ውድድሮችን፣ የፎል ስፖርት ወቅት ኦክቶበር 7/2020 የሚጀመረውን የስፖርት ወቅት ጭምር በአካል የትግባራ እንቅስቃሴ እንደሚደረግ ይፈቅዳል። በዚህኛው አማራጭ ላይ የትምህርት ቤት መዋቅሮች የህብረተሰብ ጤና ሁኔታዎችን በማጤን በአካል የሚካሄዱ ስፖርታዊ ክንውኖች የአካባቢ የጤና ጥበቃ መመሪያን ተከትሎ ለጤና በማያሰጋ ሁኔታ በቂ ጊዜ አግኝተው በአካል ወደ ማካሄድ እንደሚመለሱ አማራጭ ይሰጣል። ሁለተኛው አማራጭ በተጨማሪ፤ በዊንተር እና በስፕሪንግ ወቅቶች በመደበኛ አሠራር ስለሚጀመሩባቸው ቀኖች መጠነኛ መዘግየት እንደሚኖር ያካተተ ነው። በተጨማሪ፣ የሁለተኛው አማራጭ ረዘም ያለ ወቅት ሆኖ አሁን ባለው እቅድ በሁለት ሴሚስተር መካከል ያለውን የወቅቶች መደራረብ ያስወግዳል።

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) እነዚህን ሁለት አማራጮች በተለያየ አቅጣጫ ለመገምገም ከሞንትጎመሪ ካውንቲ የጤና እና ሰብአዊ አገልግሎት ዲፓርትመንት ጋር በቅርበት ይሠራል። በዚህ ጊዜ፣ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) በ R.A.I.S.E. Reimagined ላይ እንደተገለጸው፣ የተማሪዎችን፣ የሥራ ባልደረቦችን እና የባለድርሻ አካላትን ጤንነት እና ደህንነት ለማረጋገጥ ስለ ቨርቹወል አትሌቲክስ ማእቀፍ በተዘጋጀው እቅድ ይቀጥላል። ስለ MCPS አትሌቲክስ የጤንነት ሁኔታን በሚመለከት አስተማማኝነት ያለው እቅድ በሚጠናቀቅበት ጊዜ፣ ከከሪኩለም ተጨማሪ እንቅስቃሴዎች፣ የስነጥበባት ፕሮግራሞች እና እንቅስቃሴዎች ጭምር ታሳቢ ይደረጋሉ። የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) በአትሌቲክስ እና ከከሪኩለም ተጨማሪ እንቅስቃሴዎች ላይ የተማሪ ተሳትፎ አስፈላጊ መሆኑን በመገንዘብ እነዚህን እንቅስቃሴዎች በአካል ወደማከናወን ለመመለስ ቁርጠኛ ነው። የበለጠ መረጃ እና ወቅታዊ መግለጫዎችን ወደፊት በቅርቡ እናጋራለን።

Montgomery County Public Schools