ስለ ተማሪ ደህንነት እና የደህንነት ሁኔታን በሚመለከት ከጊዚያዊ ሱፐርኢንተንደንት የተላለፈ መልእክት

ውድ ወላጆች፣ ተማሪዎች እና የማህበረሰብ አባላት

ዛሬ የምፅፈው በትምህርት ቤታችን ግቢ ውስጥ ስለተከሰቱት ከባድ ክስተቶች እና የተማሪዎቻችንን እና የሰራተኞቻችንን ደህንነት ለማረጋገጥ እየወሰድን ስላለው እርምጃ ለመግለጽ ነው።

በቅርብ ሳምንታት ውስጥ፣ በትምህርት ቤት ግቢ ውስጥ ጥቂቶቹ የጦር መሳሪያ ያካተቱትን ጨምሮ በርካታ ከባድ ክስተቶች ነበሩ። በትምህርት ቤት ግቢ ውስጥ ማንኛውንም አይነት የጦር መሳሪያ እንደማንታገስ ግልጽ ማድረግ እፈልጋለሁ። በትምህርት ቤት፣ በትምህርት ቤት ንብረት ላይ ወይም ትምህርት ቤት በሚያካሄዳቸው የተለያዩ ዝግጅቶች ላይ የጦር መሳሪያ ይዞ የተገኘ(ች) ማንኛውንም ሰው ወደ ፖሊስ እናስተላልፋለን። ከ MCPS የስነምግባር ህጋችን ጋር በማጣጣም ተማሪዎች ከት/ቤት ከባድ የዲሲፕሊን እርምጃ ይወሰድባቸዋል።

ተማሪዎች በትምህርት ቤት ስኬታማ ለመሆን ደህንነት ሊሰማቸው ይገባል። በ MCPS የተማሪዎች ስነምግባር ህግ መሰረት ተማሪዎቻችንን የደህንነት ስጋት እንዲሰማቸው የሚያደርግ ማንኛውም ባህሪ በፍጥነት እርምጃ ያስወስዳል። ከተማሪዎች ስለሚጠበቅ ባህሪ እና የዲሲፕሊን እርምጃዎች ጥያቄዎች ካሉዎት፣ እባክዎ ስለ መብቶች እና ሀላፊነቶች የተማሪ የስነምግባር መመሪያ ይመልከቱ ወይም የትምህርት ቤትዎን አስተዳደር ያነጋግሩ። እባክዎ ከተማሪዎ ስለሚጠበቅ መልካም ስነምግባር እና ውጤቶች በቂ ግንዛቤ እንዳለው/እንዳላት ያረጋግጡ።

እርስዎ ወይም ተማሪዎ መሳሪያ የያዘ ሰው እንዳለ ካወቃችሁ ወይም በትምህርት ቤት እራሳቸውን ወይም ሌሎችን ለመጉዳት እያሰቡ ከሆነ፣ እባክዎ ወዲያውኑ ለትምህርት ቤት አስተዳደር፣ ለአካባቢ ፖሊስ ወይም የሜሪላንድ የትምህርት ቤቶች ደህንነት ክፍል በ 833-632-7233 (24/7 ክፍት ነው) ይግለጹ።

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የተማሪዎቻችንን እና የሰራተኞቻችንን ደህንነት ለማረጋገጥ ፖሊሲዎች፣ ልምዶች እና ደንቦች አሉት፣ እንዲሁም የሰለጠኑ አስተዳዳሪዎች እና የደህንነት ሠራተኞች ሁኔታዎችን ለማርገብ/ለመቆጣጠር ዝግጁ ናቸው። ለድንገተኛ አደጋዎች ምላሽ ለመስጠት ከሞንትጎመሪ ካውንቲ ፖሊስ ዲፓርትመንት እና ከሌሎች የአካባቢ ፖሊስ ኤጀንሲዎች ጋር የተደረጉ ስምምነቶችን ሠንደናል። ካውንስለሮች/አማካሪዎች እና ሌሎች የአእምሮ ጤና ባለሙያዎች ማንኛውንም ሁኔታ ተከትሎ የሚሻክሩ ግንኙነቶችን ለመጠገን እና ለማደስ ዝግጁ ናቸው። ማስተማር እና መማር ዋናው ጉዳያችን ቢሆንም፣ ደህንነት እጅግ ቅድሚያ የምንሰጠው ተግባራችን ነው።

ባለፉት ሳምንታት ያየናቸው ከባድ ክስተቶች መንስኤው ምን እንደሆነ ለመናገር አስቸጋሪ ቢሆንም አንዳንድ ተማሪዎቻችን ማህበራዊ እና ስሜታዊ ትግል እንዳለባቸው እናውቃለን። በወረርሽኙ ምክንያት ስለ ማህበራዊ ኢፍትሃዊነት ስጋት እና ሌሎች ምክንያቶች፣ብዙ ተማሪዎቻችን እና ቤተሰቦቻቸው የሚያጋጥሟቸው ጉልህ ግለሰባዊ ተግዳሮች ለሁሉም ሰው በጣም አስቸጋሪ ጊዜ ሆኖ ቆይቷል። የተማሪ ደህንነት ስለ አእምሮ ጤንነት የግንዛቤ ሳምንት ላይ የተማሪ ደህንነት አይነተኛ ትኩረታችን ነው። በዚህ ሳምንት ስለሚከናወኑ ተግባራት እና ስለሚጋሩት ግብአቶች መረጃ ለማግኘት እባክዎ የ MCPS ስለ አእምሮ ጤንነት ግንዛቤ ማስጨበጫ ሳምንት ድረ-ገጽን ይጎብኙ። እርስዎ የሚያውቁ(ቋ)ት እየታገለ(ች) ያለ(ች) ተማሪ ካለ(ች)፣ እባክዎን በትምህርት ቤቱ ውስጥ የሆነ ሰው እንዲያነጋግር/እንድታነጋግር ያድርጉ ወይም በሞንትጎመሪ ካውንቲ አስቸኳይ የስልክ መስመር 301-738-2255 ይደውሉ

የተማሪዎቻችንን ደህንነት እና ጤንነት መጠበቅ በትምህርት ቤቶቻችን፣ በቤተሰቦች እና በማህበረሰባችን መካከል የሚደረግ የትብብር ጥረት ነው። አብረን በመስራት ተማሪዎቻችን ደህንነት እንዲሰማቸው፣ፋይዳ ያላቸው እና ለመማር እና ለማደግ ዝግጁ መሆናቸውን ማረጋገጥ እንችላለን።

ከአክብሮት ጋር

Dr. Monifa B. McKnight
Interim Superintendent, Montgomery County Public Schools
ሞኒፋ ቢ. ማክነይት (ዶ/ር)
ተጠባባቂ የትምህርት ቤቶች ሱፐርኢንተንደንት

 

የ MCPS ሪሶርሶች/መርጃዎች፡-



Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools