Community Update

December 17, 2021

ለተከበራችሁ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ማህበረሰብ፦

የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ፣ ከተማሪዎቻችን እና ከሰራተኞቻችን ብዙ ነገሮች ተጠይቀዋል። እንደ ተቋም ይህን ወረርሽኝ በመጋፈጥ ላደረጋችሁት ነገር ሁሉ እናመሰግናለን። በማህበረሰባችን ሁሉም ሰዎች ባደረጉት ጥረት በሳምንት ለአምስት ቀናት በአካል ወደ መማር ለመመለስ ችለናል።

ነገር ግን አሁንም አደጋው ከፍተኛ ነው። በሞንትጎመሪ ካውንቲ እና በብዙ የሀገሪቱ አካባቢዎችም የኮቪድ-19 ሁኔታ እየጨመረ ነው። ሆኖም በሜሪላንድ ውስጥ ከአብዛኛዎቹ ሌሎች የትምህርት ስርአት ተቋማት ይልቅ በእኛ ተማሪዎች ላይ የተከሰተው የወረርሽኝ መጠን ዝቅተኛ ነው። በእርግጥ ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ በ MCPS ተማሪዎች እና በሰራተኞች መካከል የኮቪድ-19 ተጠቂዎች ቁጥር እየጨመረ መሆኑን ተመልክተናል።

በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ትምህርት ቤቶች እና መገልገያዎች የሁሉንም ተማሪዎች እና ሰራተኞች ጤንነትና ደህንነት ለማረጋገጥ MCPS ከሞንትጎመሪ ካውንቲ የጤና እና ሰብአዊ አገልግሎት (DHHS) ጋር በቅርበት መስራቱን ቀጥሏል። ከ DHHS በተላለፈው ወቅታዊ መመሪያ መሰረት የሚከተሉት እርምጃዎች ተግባራዊ ይደረጋሉ፦

 1. በአካል የሚሰጡ ትምህርቶች በሙሉ፣ ከትምህርት ቀናት ውጪ የሚከናወኑ አትሌቲክስ ያልሆኑ ከቀለም ትምህርት ተጨማሪ አክቲቪቲዎች ከሰኞ ዲሴምበር 20 ጀምሮ እስከ ዓርብ ጃኑወሪ 7 ድረስ እንዲወገዱ ተደርጓል። ማህበረሰብ የት/ቤት ህንጻዎችን መጠቀም እና የዴይኬር ፕሮግራሞች በተያዘካቸው የጊዜ ሠሌዳ መሠረት መቀጠል ይችላሉ።
 2. ሁሉም የዊንተር ስፖርቶች ላይ የሚሳተፉ ተማሪ-አትሌቶች ክትባት የወሰዱ ስለሆነ የአትሌቲክስ ልምምዶች እና ጨዋታዎች በታቀደላቸው መሰረት ሊቀጥሉ ይችላሉ። በዊንተር እረፍት ወቅት (ከዲሴምበር 23 እስከ ጃኑወሪ 2) የሚካሄዱ ጨዋታዎች በሙሉ ተሠርዝዋል።ከሰኞ ዲሰምበር 20 ጀምሮ በምርጫ የሚደረጉ ልምምዶች ይፈቀዳሉ። አንድ ቡድን ሶስት ወይም ከዚያ በላይ የኮቪድ-19 ክስተት ካለ፣ ሁሉም የቡድኑ እንቅስቃሴዎች ለ14 ቀናት መቋረጥ አለባቸው። ለአትሌቲክስ ውድድሮች ሁሉም ተመልካቾች ሁል ጊዜ ጭምብል ማድረግ አለባቸው እና የዝግጅቱ ትኬቶች በተገኘው ቦታ መጠን የተገደቡ ይሆናሉ።
 3. የሁሉንም ተማሪዎች እና ሰራተኞች ደህንነት ከምንጠብቅባቸው ምርጥ መንገዶች አንዱ በትምህርት ቤቶች ውስጥ የዘፈቀደ የኮቪድ-19 የማጣሪያ ምርመራ ማድረግ ነው። ይህ በአሁኑ ጊዜ በሁሉም 209 ትምህርት ቤቶች ውስጥ የሚከናወን ሲሆን ጃኑወሪ ላይ የኮቪድ-19 የማጣሪያ ምርመራ መጠን እንጨምራለን ። ለወላጆች/አሳዳጊዎች ተማሪዎቻቸው በኮቪድ-19 የማጣሪያ ምርመራ ፕሮግራም ላይ እንዲሳተፉ ፍቃድ መስጠት አስፈላጊ ነው።
 4. ከሜሪላንድ የጤና ጥበቃ ዲፓርትመንት በተገለጸው መሠረት፤ በትምህርት ቤት ውስጥ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ የመሠራጨት ስጋት መኖሩን በ DHHS ከተረጋገጠ፣ክትባት ላልወስዱ ተማሪዎች ስለ ንክኪ ተቀንሶ የነበረው የኳራንቲን አማራጭ ሁኔታ በስራ ላይ አይውሉም።

ስለ በሽታው የስርጭት ሁኔታዎችን ለመከታተል MCPS ከ DHHS ጋር በቅርበት መስራቱን ይቀጥላል።ከዊንተር እረፍት በፊት ተጨማሪ ወቅታዊ መረጃ ለማህበረሰቡ ይላካል። የወረርሽኝ ሁኔታው መባባስ የሚቀጥል ከሆነ፣ DHHS ተጨማሪ የመከላከል እርምጃዎችን በማካተት የ MCPS ን መመሪያ ያሻሽላል። በትምህርት ዓመቱ ሲደረግ እንደነበረው በአከባቢ እና የስቴት የመንግስት ባለስልጣናት ውሳኔ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ብቻ፥ MCPS ትምህርት ቤቶችን በመዝጋት ወደ ቨርቹወል መማር - ማስተማር ይሸጋገራል።

ሁላችንም ነቅተን መጠበቅ አለብን! እርስዎ እንደተጋለጡ ወይም የኮቪድ-19 ምልክቶች እያጋጠመዎት እንደሆነ ከተጠራጠሩ፣እባክዎ የኮቪድ-19 ምርመራ ያድርጉ። ይህ ወረርሽኙን የመከላከል ወሳኝ አካል ነው፣ነገር ግን ወረርሽኙን ለመከላከል ምርመራ ማድረግ ብቻውን በቂ አይደለም።

ማድረግ የሚችሉት እነዚህ ናቸው፡-

 • ክትባት ይውሰዱ። የኮቪድ-19 ክትባቱ ደህንነቱ የተጠበቀ ነው፥ 5 ዓመት እድሜ እና ከዚያ በላይ ለሆኑ ሰዎች ሁሉ ይሰጣል።
 • ብቁ ከሆኑ ቡስተር ክትባት "booster shot" ይውሰዱ በበቂ ሁኔታ ወረርሽኙን ለመቋቋም እንደሚችሉ ለማረጋገጥ 16 ዓመት እና ከዚያ በላይ ለሆኑ ሰዎች ሁሉ "booster shot" ይሰጣል።
 • በ MCPS ህንፃ ውስጥ ወይም በህዝባዊ ሕንፃዎች ውስጥ በሚሆኑበት ጊዜ በአፍንጫዎ እና በአፍዎ ላይ የፊት መሸፈኛ ጭምብል ያድርጉ።
 • ከመመገብዎ በፊትና በኋላ አይንዎን፣ አፍንጫህን ወይም አፍዎን ከመንካትዎ በፊት እና በኋላ እጅዎን አዘውትረው ይታጠቡ።
 • ለምርመራ አዎ ይበሉ በ MCPS ትምህርት ቤቶች ላሉ የዘፈቀደ እና ፈጣን የኮቪድ-19 የማጣሪያ ምርመራ ፕሮግራሞች ፍቃድ ይስጡ። ይህ የወረርሽኝ ሁኔታዎችን ለመለየት እና በኳራንቲን የሚገለሉ ተማሪዎችን ቁጥር ለመቀነስ ወሳኝ ነው።
 • ከሰዎች ጋር ሲሆኑ ከቤት ውጭ ይዝናኑ።ቤት ውስጥ ከሌሎች ጋር ከተገናኙ፣ የተጨናነቁ እና በቂ አየር የሌላቸውን ቦታዎች ያስወግዱ። ከበሽታ ቁጥጥር እና መከላከል ማእከል ተጨማሪ ምክሮችን ይመልከቱ
 • ለመጓዝ እቅድ አለዎት? እንዴት በደህና ማድረግ እንደሚችሉ CDC ምን እንደሚመክር ይወቁ።

ብዙዎቻችን የወረርሽኙ ድካም እየተሰማን ነው። እስካሁን ረጅም መንገድ ተጉዘናል። ነገር ግን የማህበረሰባችንን ደህንነት ለመጠበቅ የረዱትን የመከላከል ባህሪያትን መለማመዳችንን መቀጠል ወሳኝ ነው።

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS)

ጠቃሚ መረጃዎችEmail us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools