ውድ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ ማህበረሰብ

አርብ በማጉሩደር ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት (Magruder High School) የተፈፀመው የመሣርያ ጥቃት መላውን የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ማህበረሰቦችን አስደንግጧል።በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ የተጎዳውን ተማሪ ከነቤተሰቡ እና የመግሩደር ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ማህበረሰብን እባክዎ በህሊናዎ ያስቧቸው። ምንም እንኳን እንደዚህ አይነት ድርጊቶች እምብዛም የሚከሰቱ ባይሆኑም እያንዳንዳችን - በልጆቻችን፣ በሰራተኞቻችን፣ በቤተሰቦቻችን እና በጓደኞቻችን ላይ ሊያስከትል የሚችለውን ተፅእኖ እንገነዘባለን። ለእንደዚህ አይነት ሁኔታዎች ግለሰቦች በተለያየ መንገድ አፀፋ-ምላሽ ይሰጣሉ። ሀዘን፣ቅሬታ፣ አቅመ ቢስነት፣ ጭንቀት እና ቁጣ ሊሰማን ይችላል። በእንደዚህ አይነት የሚሰማዎት ስሜት ምንም ቢሆን ሊፈጠር የሚችል ነው።

በሚቀጥሉት ቀናት በመግሩደር ለሚገኙ ተማሪዎች እና በሁሉም ትምህርት ቤቶቻችን የምክር አገልግሎቶችን (ካውንስሊንግ) ጨምሮ ማህበራዊ እና ስሜታዊ ድጋፎች ይሰጣሉ። በትምህርት ቤቶቻችን ውስጥ ያለ ማንኛውም የሚታመን ጎልማሳ ተማሪዎች ይህንን ክስተት ለመቋቋም ወይም ሊያጋጥሟቸው ስለሚችሉ ማናቸውም ጉዳዮች ለመወያየት ከተገቢው ሪሶርስ ጋር ሊያገኛቸው ዝግጁ ነው። ተጨማሪ ሪሶርሶች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል።ይህ ክስተት ለእናንተም ለወላጆች፣ ልጆቻችሁን ለማዳመጥ የመነጋገር እድል የሚከፍት ይሆናል። መጥፎ ነገሮች በሚከሰቱበት ጊዜም እንኳ ወላጆች፣ መምህራን፣ የትምህርት ቤት ሰራተኞች እና የአካባቢ ፖሊስን ጨምሮ ብዙ ሰዎች ደህንነታቸውን ለመጠበቅ እየሰሩ መሆናቸውን አረጋግጡላቸው። አንድ ነገር ካወቁ፣ ካዩ፣ ወይም ከተጠራጠሩ ለሚታመን አዋቂ ሰው መናገር እንዳለባቸው እባክዎን ያስታውሱአቸው።

ሠላም እና ደህንነት ቀዳሚ ተግባራችን እንደሆነ ይቀጥላል። ለሞንትጎመሪ ካውንቲ ፖሊስ ዲፓርትመንት ድጋፍ እና እንዲሁም ሌሎች የአካባቢ ፖሊስ ኤጀንሲዎች በማህበረሰባችን ውስጥ እያደጉ ያሉ የአመፅ ድርጊቶችን በመፋለም ስለሚያደርጉት እርዳታ እናመሰግናለን። እነዚህ አዝማሚያዎች ወረርሽኙ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ በመላ አገሪቱ እያየናቸው ያሉትን ክስተቶች የሚያንፀባርቁ ናቸው። የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፖሊስ ዲፓርትመንት ከትምህርት ቤቶቻችን ጋር በቅርበት እየሠራ ይገኛል። በማግሩደር 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በደረሰው ከባድ ችግር መነሻነት፥ የፖሊስ ዲፓርትመንት ቀሪውን ወር የበእያንዳንዱ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት እና በሁሉም የትምህርት ቤት ማህበረሰቦች መካከል ፖሊስ ክትትል ለማድረግ ወስኗል።

በሚቀጥሉት ወራት፣ የ MCPS አመራር ከካውንቲያችን ባለስልጣናት፣ ከማህበረሰብ አጋሮች እና በት/ቤት ከሚገኙ ሰራተኞች ጋር በመተባበር፡-

  • ሁሉንም የትምህርት ቤት ደህንነት እና ሠላም የማስጠበቅ ተሞክሮዎችን አጠቃላይ ግምገማ ማድረግ፣
  • በትምህርት ቤት ግቢ ውስጥ የፖሊስ መገኘትን በተመለከተ በቀጣይነት የነበሩትን ስጋቶች መፍታት፣
  • በትምህርት ቤት የሚገኙ የደህንነት ሰራተኞችን እና የአደጋ ጊዜ ምላሽ ሂደቶችን መገምገም፣
  • ለሰራተኞች የተሻሻለ የደህንነት አጠባበቅ ስልጠና ተግባራዊ ማድረግ፣
  • ለተማሪዎች እና ለሰራተኞች ማህበራዊ-ስሜታዊ ድጋፍ መስጠት፣ እና
  • ስለ ቀጣይ ጥረታችን በፍጥነት እና በግልፅ መነጋገር በትኩረት የምናከናውናቸው ናቸው።

 

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ ለሁሉም ተማሪዎች ደህንነቱ የተጠበቀ እና ምቹ የትምህርት አካባቢ እንዲሆን በምናደርገው ጥረት ለሚያደርጉት ያላሰለሰ ድጋፍ እናመሰግናለን።

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ
Montgomery County Public Schools 

ጠቃሚ መረጃዎች፦

  • የአሜሪካ የሳይኮሎጂስቶች ማህበር (American Psychological Association)፦ ስሜታዊ ቀውስ ሲያጋጥም እንዴት መርዳት እንደሚቻል
    www.apa.org/helpcenter
  • ብሔራዊ የትምህርት ቤት ሳይኮሎጂስቶች ማህበር (National Association of School Psychologists)፡ የትምህርት ቤት ደህንነት እና ቀውስ

https://www.nasponline.org/resources-and-publications/resources/school-safety-and-crisis

ከ MCPS

ድጋፍ ለመጠየቅ ጠቃሚ የስልክ መስመሮች

  • የሞንትጎመሪ ካውንቲ የቀውስ ሁኔታ ክፍት መስመር = Montgomery County Crisis Hotline: 301-738-2255
  • ሜሪላንድ የትምህርት ቤቶች ደህንነት = Maryland Safe Schools Tip Line: 833-MD-B-SAFE
  • የሞንትጎመሪ ካውንቲ የቀውስ ሁኔታ ማዕከል = Montgomery County Crisis Center: 240-777-4000
  • የሠራተኛ ድጋፍ ፕሮግራም = Employee Assistance Program (EAP): (240) 401-6498 (For MCPS Employees)


Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools