ዓርብ፣ ማርች 4 መታወቅ ያለባቸው ነገሮች

ስለ ማስክ አጠቃቀም መመሪያ፣ ስለ ኮቪድ-19 ዳሽቦርድ፣ ስለ ኮቪድ-19 መመርመሪያ ኪቶች እና በመጪው 2022-2025 የበጀት ኣመት FY 2022-2025 የስትራቴጂክ ዕቅድ ድረ ገጽ ላይ መረጃን የሚያካትቱ ስድስት ነገሮች አርብ፣ ማርች 4፣ 2022 መታወቅ ያለባቸው ርእሰ ጉዳዮች።

 1. ስለ ማስክ አጠቃቀም ፖሊሲ በቅርቡ ውሳኔ እንደሚሰጥ ይጠበቃል

በቅርብ ጊዜ በተላለፈው ህዝባዊ መግለጫ፣ የትምህርት ቦርድ ለሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ ወደ “ጭምብል አጠቃቀም አማራጭ ፖሊሲ" ለመሸጋገር ድምጽ ሊሰጥ እንደሚችል ተገልጿል። ይህ ውሳኔ ከተሰጠ፤ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) በትምህርት ቤቶች እና ቢሮዎች ውስጥ የጭንብል አጠቃቀምን ወደ አማራጭ ስለመቀየር መመሪያ እና ድጋፍ ለቤተሰቦች ይገለጻል። የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ማህበረሰባችን የሌሎችን የጭንብል አጠቃቀም ምርጫ እንዲያከብር እንጠብቃለን። ይህንን የማህበረሰብ መልእክት ያንብቡ

 1. የኮቪድ-19 ዳሽቦርድ ተሻሽሏል

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) በይነመረብ የኮቪድ-19 ዳሽቦርድ ተሻሽሎ ቀርቧል። ከኮቪድ-19 ክዋኔዎች አማካሪ ቡድን ጋር በመተባበር የባለድርሻ አካላት ግብረመልስ መካተቱን ለማረጋገጥ ዳሽቦርዱ አሁን የሚከተሉትን ያካትታል፦

 • ባለፉት 10 ቀናት ውስጥ ከተማሪዎች እና ከሰራተኞች ለትምህርት ቤት ሪፖርት የተደረጉትን ፖዚቲቭ ሁኔታዎች፣ በየትምህርት ቤቱ የተማሪዎች እና የሰራተኞች ብዛት፣ እና ላለፉት 10 ቀናት በኮቪድ-19 ተጠቂ የሆነውን የህዝብ ብዛት በመቶኛ።
 • በጠቅላላ ዲስትሪክቱ ውስጥ ባለፉት 10 ቀናት አጠቃላይ የፖዚቲቭ ሁኔታዎች
 • አጠቃላይ የኳራንቲን ብዛት
 • ከኦገስት 31፣ 2021 ጀምሮ አጠቃላይ የበሽታው ስርጭት እና የለይቶ ማቆያዎች ብዛት
 • ዳሽቦርዱ በየቀኑ ወቅታዊ መረጃ ይኖረዋል።
 • የኮቪድ-19 ፈጣን የቤት ውስጥ መመርመሪያ ኪት እየተሰራጨ ነው።

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክስ ስኩልስ (MCPS) ፈጣን የኮቪድ-19 መመርመሪያ ኪቶችን ለሁሉም ተማሪዎች እና ሰራተኞች በየሶስት ሳምንቱ እስከ ማርች ድረስ ማሰራጨቱን ይቀጥላል። እነዚህን መሳሪያዎች መጠቀም የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት ለሚደረጉት ጥረቶች ወሳኝ ሚና አላቸው።
ቪዲዮ፡ የኮቪድ-19 ፈጣን መመርመሪያ መሣሪያ አጠቃቀም መመሪያ
በዚህ ድረገጽ <አገናኝ/LINK> ላይ የበለጠ ለማወቅ በራሪ ወረቀቶችን ያንብቡ።
እንግሊዘኛ / እስፓኒሽ / 中文 / ፈረንሳይኛ / ፖርቺጊዝ / ቻይንኛ / tiếng ቪትናም / አማርኛ 

(ማሳሰቢያ፦ እነዚህ ከአፍንጫ ፈሳሽ (አፍንጫ) በመውሰድ የሚከናወኑ ፈጣን መመርመሪያዎች ናቸው፡ እባክዎ ከመጠቀምዎ በፊት በመሳሪያዎቹ ውስጥ የተካተቱትን መመሪያዎች ያንብቡ)

 • በሚቀጥለው ሳምንት የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ስትራቴጂክ እቅድ ድረ ገጽ ይፋ ይደረጋል

አዲሱ ሳምንት የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የ 2022-2025 ስትራቴጂክ እቅድ ሶስት ዋና የትኩረት አቅጣጫዎችን ያሳያል፡-

 • አካዴሚያዊ ልቀት
 • ደህንነት እና የቤተሰብ ድጋፍ
 • ሙያ እና የሥራ ልቀት

ይህ በቦርድ የፀደቀው እቅድ ተማሪዎችን በትምህርታቸው ለመደገፍ ወሳኝ በሆኑ የትኩረት አቅጣጫዎች የመማር ማስተማር ሂደትን ይመራል።
ፖስተሮች
እንግሊዘኛ / እስፓኒሽ / 中文 / ፈረንሳይኛ / ፖርቺጊዝ / ቻይንኛ / tiếng ቪትናም / አማርኛ

 • በትምህርት ቤት የኮቪድ-19 ምርመራ ማድረግ አስፈላጊቱ ይቀጥላል

የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት በትምህርት ቤት የኮቪድ-19 ምርመራ ማድረግ ጠቃሚ ዘዴ ነው። MCPS በት/ቤት ውስጥ በዘፈቀደ እና ምልክቶች ለሚታይባቸው ተማሪዎች ፈጣን የኮቪድ ምርመራ ያደርጋል። ወላጆች ለዚህ ምርመራ ይህን ቅጽ በመሙላት ፈቃድ መስጠት አለባቸው። ስለ ኮቪድ-19 ትምህርት ቤት ውስጥ ስለ ምርመራ የበለጠ ይወቁ።
በሲልቨር ስፕሪንግ አፓርትመንት ሕንፃ ፍንዳታ ለተጎዱ ቤተሰቦች ድጋፍ
በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ የምንገኝ ሁላችንም ሐሙስ ማለዳ በሲልቨር ስፕሪንግ አፓርትመንት ሕንፃ በደረሰው ፍንዳታ ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸው ቤተሰቦች ደህንነት በጣም ያሳስበናል። ከዚህ ክስተት እንዲያገግሙ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ሰራተኞች እርዳታ ከሚያስፈልጋቸው ቤተሰቦች ጋር ይሰራሉ። በእሳቱ የተጎዱ ቤተሰቦችን መርዳት ከፈለጉ፣ እባክዎን Making Home Possible የሚሰጡትን ድጋፍ ያስገቡ።
በሚቀጥሉት ቀናት ተጨማሪ መረጃዎችን እናጋራለን።Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools