ሐሙስ፣ ማርች 31 መታወቅ ያለባቸው ነገሮች እነሆ!

ለሐሙስ፣ መጋቢት 31 መታወቅ ያለባቸው ቁልፍ ነገሮችን እነሆ! ስለ ስፕሪንግ ዕረፍት አስፈላጊ የኮቪድ-19 ማሳሰቢያዎችን፣ የመዋዕለ ሕፃናት ምዝገባ አሁን ክፍት መሆኑን፣ ስለመጪዎቹ የማህበረሰብ ተሳትፎ ዝግጅቶች እና ሌሎችንም ያካትታል።

 1. የስፕሪንግ ዕረፍት ሰኞ፣ ኤፕሪል 11 ይጀምራል

ኮቪድ-19 አሁንም ከእኛ ጋር ስላለ በጥንቃቄ ራስዎን ይጠብቁ።
ከቤተሰብ እና ከጓደኞች ጋር ብዙ ጊዜ ለማሳለፍ፣ አንዳንዶቻችን በአንዳንድ ፕሮግራሞች ምክንያት ልንጓዝ ወይም ልንሰባሰብ ሁላችንም የስፕሪንግ ዕረፍትን በጉጉት እንጠባበቃለን። ከስፕሪንግ እረፍት በኋላ ኤፕሪል 19 በሰላም ወደ ትምህርት ቤት ለመመለስ ለምን በስፕሪንግ እረፍት ጊዜ ከኮቪድ-19 በሠላም የሚጠበቁበትን ዝርዝር አያዘጋጁም? የበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማእከል (CDC) እራስዎን ከኮቪድ-19 ለመከላከል በስፕሪንግ ዕረፍት ወቅት ማድረግ የሚችሏቸውን የሚከተሉትን ማሳሰቢያዎች እንዲተገብሩ ይመክራል።

 • ክትባት ይውሰዱ እና ስለ ኮቪድ-19 ክትባት ወቅታዊ መረጃ ያግኙ፣ ብቁ ከሆኑ booster ክትባት ይውሰዱ።
 • በተለይም ሕዝብ በሚሰበሰብባቸው ቦታዎች ወይም ለበሽታ የመጋለጥ እድል ካለብዎት ጭምብል ይጠቀሙ።
 • ከሌሎች ሰዎች የስድስት ጫማ ርቀት ይጠብቁ።
 • በደንብ ነፋሻ ያልሆኑ ቦታዎችን እና መጨናነቅ የበዛበት ቦታዎችን ያስወግዱ።
 • ወደ ሌሎች እንዳይዛመት ይመረመሩ።
 • እጅዎን አዘውትረው ይታጠቡ።
 • ሲያስልዎት እና ሲያስነጥስዎት አፍና አፍንጫዎትን ይሸፍኑ።
 • ማጽዳት እና የተዋስ/ጀርም መከላከያ ይጠቀሙ
 • ጤንነትዎን በየቀኑ ይቆጣጠሩ።
 • ከታመሙ፣ የለይቶ ማቆያ እና የኳራንቲን ምክሮችን ይከተሉ።
 • በሚጓዙበት ጊዜ ጥንቃቄዎችን ያድርጉ።

ማህበረሰባችን ጤናማ ሆኖ እንዲቆይ ራሳችንን መጠበቅ የሁላችንም ሃላፊነት ነው።

 1. ማሳሰቢያ፡ ኮቪድ-19 ወደ ቤት የሚወሰዱ ፈጣን መመርመርያዎች

 • ሰኞ፣ ኤፕሪል 18፣ ቤተሰቦች የሁሉም የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች ወላጆች ከ MCPS በተሰጧቸው ፈጣን ወደ ቤት የሚወስዱ የምርመራ ኪቶች በመጠቀም እንዲመረመሩ እና ፖዚቲቭ/በሽታ ከተገኘባቸው ኦንላይን ቅፅ በመሙላት እንዲያሳውቁን እንጠይቃለን። የምርመራው ውጤት ፖዚቲቭ ከሆነ፣ ቤት ይቆዩ እና ራስን የማግለለና የኳራንቲን መመሪያዎችን ይከተሉ። ልጅዎ የኮቪድ-19 ምልክት ካለበ(ባ)ት ወይም ከታመመ(ች)፣ ቤት መቆየት አለበ(ባ)ት። ወደ ቤት የሚወሰዱ የመመርመርያ ዕቃዎችን ለሚቀበሉ ሰራተኞችም መመሪያው ተመሣሳይ  ነው። ወደ ትምህርት ቤት ከመመለሳችን አንድ ቀን በፊት ኤፕሪል 18 ይመርመሩ እና ማንኛውንም ፖዚቲቭ ሁኔታ ሪፖርት ያድርጉ።

ማሳሰቢያ፡ የኮቪድ-19 ምልክቶች ሳል፣ የጉሮሮ መቁሰል፣ የሙቀት መጠን 100.4 ወይም ከዚያ በላይ የሆነ ትኩሳት፣ ተቅማጥ፣ ማስታወክ፣ ጣዕም ወይም ሽታ ማጣት እና የመተንፈስ ችግር ናቸው። ይህን ጠቃሚ የተማሪ የጤንነት ማረጋገጫ ዝርዝር ይጠቀሙ።
ስርጭት፡-
MCPS የኮቪድ-19 ፈጣን የቤት መመርመሪያ ቁሳቁሶችን እስከ ኤፕሪል 6 ድረስ ያሰራጫል። የልጅዎን ቦርሳ ይመልከቱ።

የኮቪድ-19 መመርመሪያ ኪት አጠቃቀም መመሪያዎች፦
ቪዲዮ፡ የኮቪድ-19 ፈጣን መመርመሪያ መሣሪያ አጠቃቀም መመሪያ
በዚህ ድረገጽ ላይ የበለጠ ግንዛቤ ያግኙ፤ በራሪ ወረቀቶች ላይ ያለውን መመሪያ ያንብቡ።
እንግሊዘኛ / እስፓኒሽ / 中文 / ፈረንሳይኛ / ፖርቺጊዝ / ቻይንኛ / tiếng ቪትናም / አማርኛ 
(ማሳሰቢያ፡ እነዚህ ከአፍንጫ ፈሳሽ በመውሰድ የሚከናወኑ ፈጣን መመርመርያዎች ናቸው፤ እባክዎን በመሳሪያዎቹ ውስጥ የተካተቱትን መመሪያዎች ይከተሉ።)

  • በትምህርት ቤት ምርመራ እንዲደረግ መስማማትዎን ይግለጹ

MCPS በት/ቤት ውስጥ የኮቪድ-19 ምልክቶችን ለሚያሳዩ ተማሪዎች እና ለሌሎችም በዘፈቀደ ፈጣን ምርመራ ያደርጋል። ወላጆች ለዚህ ምርመራ ፈቃድ መስጠት አለባቸው ይህን ቅጽ በመሙላት። ስለ ት/ቤት የኮቪድ-19 ምርመራ የበለጠ ግንዛቤ ያግኙ

  • ክትባቶች፡ 5 ዓመት እና ከዚያ በላይ እድሜ ያላቸው ግለሰቦች የኮቪድ-19 ክትባት ለመውሰድ ብቁ ናቸው። ነፃ፣ደህንነቱ የተጠበቀ፣ እና የተዘጋጀ ነው። MCPS በየሳምንቱ መጨረሻ የክትባት ክሊኒኮችን ያካሄዳል። ተጨማሪ ግንዛቤ ያግኙ.

 

 1. ለ 2022-2023 የትምህርት ዘመን የመዋዕለ ሕፃናት ምዝገባ አሁን ተከፍቷል።

ለ 2022-2023 የትምህርት ዓመት ልጆቻቸውን በ MCPS መዋእለ ህጻናት እንዲማሩ ማስመዝገብ ለሚፈልጉ ወላጆች ምዝገባ ተጀምሯል። በሴፕቴምበር 1፣ 2022 ልጆች የ 5 ዓመት ዕድሜ መሆን አለባቸው። ማመልከቻን ለመሙላት፣ ስለ ብቁነት መመሪያዎችን ለመመልከት፣ ለምዝገባ ወይም ስለ አስፈላጊ ሰነዶች ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት 240-740-4006 ይደውሉ ወይም MCPS የመዋዕለ ሕፃናት ምዝገባ ድረገጽ ይጎብኙ።

 1. የማህበረሰብ ተሳትፎ ኦፊሰር 2.0 እቅድ በቅርቡ ይወጣል

አዲሱ የማህበረሰብ ተሳትፎ ኦፊሰር (ዋና ስራ አስፈፃሚ) ፕሮግራም ሁሉንም ተማሪዎች እና ሰራተኞች የሚጠቅም ደህንነቱ የተጠበቀ፣አካታች እና አወንታዊ የትምህርት አካባቢን ለማረጋገጥ የተነደፈ አዲስ አቀራረብ ነው። በፕሮግራሙ ላይ ስለ MCPD እና ስለ MCPS መካከል ስለሚደረግ ትብብር የማሻሻያ እቅድ የተደረገ ሲሆን ከብዙ የትኩረት ቡድኖች፣ ከተማሪዎች፣ ከሰራተኞች፣ ከወላጆች እና ከበርካታ የማህበረሰብ ባለድርሻ አካላት የተሰበሰበ ጉልህ የሆነ የማህበረሰብ ግብአቶችን ያካትታል። የፕላኑ አዘጋጆች ከትምህርት ቦርድ እና ከሞንትጎመሪ ካውንቲ ካውንስል ጋር በተደረጉ የህዝብ ስብሰባዎች የእቅዱን ይዘት በተለያዩ ጊዜያት አቅርበዋል። በተከታታይ አስተያየቶችንና ግብረመልሶችን ለመሰብሰብ እና የዳሰሳ ጥናት ለማካሄድ ቀጣይ ዕድሎች ይኖራሉ።

 1. ተማሪዎቻችንን ማስቀደም፡ የማህበረሰብ ውይይቶች ለኤፕሪል፣ ሜይ ተቀናብረዋል።

ለሶስት የማህበረሰብ ውይይቶች ጊዜያዊ የበላይ ተቆጣጣሪ ዶ/ር ሞኒፋ ቢ.ማክኒትን ተቀላቀሉ፣ ሁሉም አንድ ላይ አሁን፡ ተማሪዎቻችንን በማስቀደም ለኤፕሪል እና ሜይ ተቀናብሯል። እነዚህ ዝግጅቶች ቤተሰቦችን፣ ተማሪዎችን፣ ሰራተኞችን እና ማህበረሰቡን በአንድ ላይ የሚያሰባስቡ ሲሆን MCPS ተማሪዎቹን እንዴት በተሻለ ሁኔታ ማገልገል እንደሚችል ስለ ዲስትሪክቱ ጥንካሬዎች፣ ቅድሚያ ትኩረት ስለሚሰጥባቸው ጉዳዮች እና እድሎችን በተመለከተ ውይይት ያደርጋሉ።
ዝግጅቶቹ የሚከናወኑት፦

  • ረቡዕ፣ ኤፕሪል 20፣ 7 p.m., Gaithersburg High School cafeteria, 101 Education Boulevard, Gaithersburg
  • ረቡዕ፣ ኤፕሪል 27, 7:30 p.m., Walter Johnson High School cafeteria, 6400 Rock Spring Dr., Bethesda
  • ቅዳሜ፣ ሜይ 7, 11 a.m., Paint Branch High School cafeteria, 14121 Old Columbia Pike, Burtonsville

ለመሣተፍ እንዲመዘገቡ እናበረታታለን።Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools