ሐሙስ፣ ኤፕሪል 7 ግንዛቤ የሚሹ ጉዳዮች

ሐሙስ፣ ኤፕሪል 7 መታወቅ ያለባቸው ቁልፍ ጉዳዮችን እነሆ! በስፕሪንግ ዕረፍት ስለ ኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጥንቃቈ፣ ስለመጪው የማህበረሰብ ውይይት ተሳትፎ፣ እና ሌሎችም አስፈላጊ ማሳሰቢያዎችን ያካትታሉ።

 1. የስፕሪንግ ዕረፍት የሚቀጥለው ሳምንት ነው!

በእረፍት ጊዜዎ ይደሰቱ ነገር ግን በጥንቃቄ ራስዎን ይጠብቁ
ምንም እንኳን በሞንትጎመሪ ካውንቲ ውስጥ ፖዚቲቭ የኮቪድ-19 መጠን ዝቅተኛ ቢሆንም፣ በዚሁ እንዲቀጥል እና ኤፕሪል 19 ከኮቪድ-19 ተጽእኖ ነፃ ሆኖ ወደ ትምህርት ቤት ለመመለስ፣ በንቃት ጥንቃቄ ማድረግ አለብን። በስፕሪንግ እረፍት ጊዜ እርስዎ ከኮቪድ-19 ነጻ ለመሆን ማድረግ ያለብዎትን ጥንቃቄ ዝርዝር ያስታውሱ? የበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማዕከል (CDC) ኮቪድ-19 ለመከላከል በስፕሪንግ ዕረፍት ማከናወን የሚችሏቸውን ቀላል ነገሮች ዝርዝር ይመክራል። የማህበረሰባችንን ጤንነት መጠበቅ የሁላችንም ሃላፊነት ነው።

ለተማሪዎች እና ለሰራተኞች ማሳሰቢያ፦ ከ MCPS በተሰጠው የኮቪድ-19 ቤት- መመርመርያ ሰኞ፣ ኤፕሪል 18 ምርመራ ይውሰዱ
rapid testing kit

 • ሰኞ፣ ኤፕሪል 18፣ የስፕሪንግ እረፍት ከመግባቱ የመጀመሪያው የትምህርት ቀን በፊት፣ ቤተሰቦች ከ MCPS የተሰጠውን ፈጣን ከቤት መመርመርያ ኪት በመጠቀም ሁሉንም የ MCPS ተማሪዎች እንዲመረመሩ እና ፖዚቲቭ ሁኔታዎችን ወደ እኛ ሪፖርት እንዲያደርጉ እንጠይቃለን። ኦንላይን በሚሞላ ቅጽ የምርመራው ውጤቱ ፖዚቲቭ ከሆነ፣ ቤት ይቆዩ እና ራስን የማግለለና የኳራንቲን መመሪያዎችን ይከተሉ። ልጅዎ የኮቪድ-19 ምልክት ካለበ(ባ)ት ወይም ከታመመ(ች)፣ ቤት መቆየት አለበ(ባ)ት። ወደ ቤት የሚወሰዱ መመርመሪያዎችን ለተቀበሉ ሰራተኞችም መመሪያው ተመሣሣይ ነው። ወደ ትምህርት ቤት ከመመለሳችን አንድ ቀን በፊት ኤፕሪል 18 ምርመራ በማድረግ ማንኛውንም ፖዚቲቭ ሁኔታ ሪፖርት ያድርጉ። ማሳሰቢያ፡ የኮቪድ-19 ምልክቶች ሳል፣ የጉሮሮ መቁሰል፣ የሙቀት መጠን 100.4 ወይም ከዚያ በላይ የሆነ ትኩሳት፣ ተቅማጥ፣ ማስታወክ፣ ጣዕም ወይም ሽታ ማጣት እና የመተንፈስ ችግር ናቸው። ይህን ጠቃሚ የተማሪ የጤንነት ማረጋገጫ ዝርዝር ይጠቀሙ።

  ስርጭት፡-
  MCPS የኮቪድ-19 ፈጣን የቤት መመርመሪያ ቁሳቁሶችን እስከ ኤፕሪል 6 ድረስ አሰራጭቷል። የልጅዎን ቦርሳ ይመልከቱ።

  የኮቪድ-19 መመርመሪያ ኪት አጠቃቀም መመሪያዎች፦
  ቪዲዮ፡ የኮቪድ-19 ፈጣን መመርመሪያ መሣሪያ አጠቃቀም መመሪያ
  በዚህ ድረገጽ ላይ የበለጠ ግንዛቤ ያግኙ፤ በራሪ ወረቀቶች ላይ ያለውን መመሪያ ያንብቡ።
  እንግሊዘኛ / እስፓኒሽ / 中文 / ፈረንሳይኛ / ፖርቺጊዝ / ቻይንኛ / tiếng ቪትናም / አማርኛ
  (ማሳሰቢያ፡ እነዚህ ከአፍንጫ ፈሳሽ በመውሰድ የሚከናወኑ ፈጣን መመርመርያዎች ናቸው፤ እባክዎን በመሳሪያዎቹ ውስጥ የተካተቱትን መመሪያዎች ይከተሉ።)

 1. ክትባቱን ይውሰዱ፡ በማኅበረሰባችን ውስጥ የሚሰራጨውን የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ለመቆጣጠር ክትባት መውሰድ አስፈላጊ ነው።

5 ዓመት እና ከዚያ በላይ እድሜ ያላቸው ግለሰቦች የኮቪድ-19 ክትባት መውሰድ ይችላሉ። ክትባቱ ደህንነቱ የተጠበቀ እና በነፃ የሚሰጥ ነው። MCPS ቅዳሜ፣ ኤፕሪል 9 የክትባት ክሊኒኮችን ያስተናግዳል። እንዲሁም የሞንትጎመሪ ካውንቲ የጤና እና የሰብአዊ አገልግሎት ዲፓርትመንት በስፕሪንግ ዕረፍት ጊዜ የክትባት አገልግሎት ይሰጣል። በ MCPS ድረገጽ እና DHHS ድረገጽ ላይ የበለጠ ግንዛቤ ያግኙ።

 1. በስፕሪንግ ዕረፍት ጊዜ ከ MCPS የተሰጠህ(ሽ)ን ኮምፒውተር ወደ ቤት መውሰድ አለብህ(ሽ)

እንደተለመደው፣በማንኛውም የእረፍት ጊዜ ዓርብ ትምህርት ቤቶች ለእረፍት ከመዘጋታቸው በፊት፣ ተማሪዎች እና ሰራተኞች የሚጠቀሙባቸውን የትምህርት መሳሪያዎቻቸውን ወደ ቤታቸው እንዲወስዱ ት/ቤቶች ያሳስባሉ። የቻርጀር ገመዱን ጭምር ወደ ቤት እንዲያመጣ/እንድታመጣ ልጅዎን ያስታውሱ።

 1. አዲስ የማህበረሰብ ተሳትፎ ኦፊሰር እቅድ በቅርቡ ይወጣል

አዲሱ የማህበረሰብ ተሳትፎ ኦፊሰር (ዋና ስራ አስፈፃሚ) ፕሮግራም ስምምነት በቅርቡ ይፈረማል ተብሎ ይጠበቃል። ከስፕሪንግ ዕረፍት በኋላ ሲዘጋጅ፣ የማህበረሰብ መልእክት እንልካለን ጋዜጣዊ መግለጫም እንሰጣለን። ይህ አዲስ ስምምነት ሁሉንም ተማሪዎች እና ሰራተኞች የሚጠቅም ደህንነቱ የተጠበቀ፣አካታች እና ምቹ የትምህርት አካባቢን ለማረጋገጥ የተነደፈ አዲስ አቀራረብን የሚገልጽ ነው።

 1. "ተማሪዎቻችንን ማስቀደም" በሚል ርእስ የማህበረሰብ ውይይቶች በኤፕሪል፣እና ሜይ ወራት ይካሄዳሉ።

በጊዜያዊ ሱፐርኢንተንደንት ዶ/ር ሞኒፋ ቢ.ማክኒትን (Dr. Monifa B. McKnight) አማካይነት የሚካሄዱ ሶስት የማህበረሰብ ውይይቶች ላይ ይሳተፉ፦ ተማሪዎቻችንን ለማስቀደም አሁን ሁላችንም አንድ ላይ እንሁን! ኤፕሪል እና ሜይ ላይ የማህበረሰብ ውይይቶች ይደረጋሉ። በእነዚህ ዝግጅቶች ላይ ቤተሰቦች፣ ተማሪዎች፣ ሰራተኞች እና የማህበረሰብ አባላት MCPS እንዴት ተማሪዎቹን በተሻለ ሁኔታ ማገልገል እንደሚችል እና ስለ ዲስትሪክቱ ጥንካሬዎች ቅድሚያ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች እና ስላሉት እድሎች ይወያያሉ።
ዝግጅቶቹ የሚከናወኑት፦

 • ረቡዕ፣ ኤፕሪል 20፣ 7 p.m., Gaithersburg High School cafeteria, 101 Education Boulevard, Gaithersburg
 • እሮብ፣ ኤፕሪል 27፣ 19፡30 p.m., Walter Johnson High School cafeteria, 6400 Rock Spring Drive, Bethesda
 • ቅዳሜ፣ ሜይ 7, 11 a.m., Paint Branch High School cafeteria, 14121 Old Columbia Pike, Burtonsville

እነዚህ ውይይቶች በተከታታይ ከሚደረጉ የተሳትፎ ክንውኖች የመጀመርያዎቹ ሲሆኑ ወደፊትም ቨርቹወል በሚደረጉ ውይይቶች ላይ የመሳተፍ እድሎች ይኖራሉ። RSVP ለመሣተፍ እንዲመዘገቡ እናበረታታለን። የተወሰነ የ MCPS አውቶቡስ መጓጓዣ ይቀርባል። በጌትስርበርግ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት (Gaithersburg High School) ለሚደረገው የመጀመሪያው ፕሮግራም የ MCPS አውቶቡስ ዝግጅቱ ከመጀመሩ በፊት እና በኋላ "Gaithersburg High stopping at Montgomery Village Middle, Roberto Clemente Middle and Clarksburg High School መካከል ይመላለሳል።Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools