ሐሙስ ሜይ 19 ወቅ ያለብዎት ጉዳዮች

ሀሙስ ሜይ 19 ማወቅ ያለብዎት አምስት ጉዳዮችን እነሆ!
ስለ ኮቪድ-19፣ ስለመጪው የአእምሮ ጤና አውደ ርእይ፣ ኦንላይን የአእምሮ ጤና እና ደህንነት ሪሶርሶች እና ስለ እውቅና ሽልማት አሰጣጥ ማሳሰቢያዎችን ያካትታል።

  1. የኮቪድ-19 ኬዝ ጨምረዋል።

በሽታ መቆጣጠሪያና መከላከያ ማእከል (CDC) እና በሞንትጎመሪ ካውንቲ የጤና ጥበቃ እና ሰብአዊ አገልግሎቶች ዳሽቦርድ ላይ እንደተዘገበው የኮቪድ-19 ፖዚቲቭ ሁኔታዎች ጨምረዋል።ረቡዕ፣ ሜይ 18 በካውንቲው 100,000 ነዋሪዎች መካከል ከ 364 በላይ የኮቪድ ህሙማን ነበሩ፣ ይህም ማህበረሰባችንን “በመለስተኛ” የአደጋ ምድብ ውስጥ አስገብቶታል። የጤና ጥበቃና የሰብአዊ አገልግሎት ዲፓርትመንት ከማህበረሰቡ ውጭ በሚሆኑበት ጊዜ ጭምብል/ማስክ እንዲጠቀሙ፣ በሚችሉበት ጊዜ አካላዊ ርቀት እንዲጠብቁ፣ እጅዎን ደጋግመው እንዲታጠቡ እና ክትባት እና ቡስተር እንዲወስዱ ያበረታታል። እነዚህን ቀላል ነገሮች ማድረግ ጤንነትዎን ለመጠበቅ ይረዳዎታል።

  1. ሶስት ወይም ከዚያ በላይ ፖዚቲቭ ኬዞች/በበሽታው የተያዙ ሰዎች ባሉባቸው ቦታዎች ጭምብል መጠቀም አስፈላጊ ነው።

ከሞንትጎመሪ ካውንቲ የጤና ጥበቃና የሰብአዊ አገልግሎት መምሪያ ምክሮች ጋር በማሳለጥ ሁሉም ሰራተኞች እና ተማሪዎች በትምህርት ቤቶች እና በቢሮዎች ውስጥ በቤት ውስጥ እያሉ ጭምብል እንዲጠቀሙ በጥብቅ ይመከራል። በሲስተማችን ጭንብል መጠቀም እንደ አማራጭ ቢሆንም፣እየጨመረ ያለውን የኮቪድ ወረርሽኝ ለመከላከል ለተወሰኑ ክፍሎች፣ ወይም ትምህርት ቤቶች ስርጭቱን ለመቀነስ ለተወሰነ ጊዜ እንደገና ጭምብል መጠቀም ሊያስፈልግ ይችላል። ግባችን ተማሪዎችን፣ ሰራተኞቻችንን እና ማህበረሰባችንን ጤንነታቸው እንዲጠበቅ ማድረግ እና በአካል የሚሰጡ ትምህርቶች እንዲቀጥሉ ማስቻል ነው።
ስለ ጭንብል አጠቃቀም ምክርን ያካተተ ስለበሽታው መዛመት/ፖዚቲቭ ሁኔታዎችን የሚገልጽ ደብዳቤ እንደ አስፈላጊነቱ ወደ ቤት ይላካል። MCPS በተጨማሪ ወደ ቤት የሚወሰዱ ፈጣን መመርመሪያዎችን እና ጭንብል የኮቪድ ተጽእኖ ወዳለባቸው ትምህርት ቤቶች እያሠራጨ ነው። የኮቪድ-19 ክትባቶችንና ቡስተሮችን ያልወሰዱ ተማሪዎች እና ሰራተኞች ከ CDC፣ ከሜሪላንድ የጤና ጥበቃ ዲፓርትመንት፣ እና ከሞንትጎመሪ ካውንቲ የጤና ጥበቃና የሰብአዊ አገልግሎት ዲፓርትመንት በተላለፈ መመሪያ መሠረት ኳራንቲን ማድረግ ሊያስፈልጋቸው ይችላል።
ማሳሰቢያ፦ ማንኛውንም ፖዚቲቭ የኮቪድ-19 ሁኔታ በዚህ አገናኝ/ሊንክ ሪፖርት ያድርጉ።

  1. የአእምሮ ጤና አውደ ርእይ ለሜይ 31 ተዘጋጅቷል።

MCPS በሴኔካ ቫሊ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ማክሰኞ፣ ሜይ 31 ከሰዓት በኋላ 6፡15–8፡30 p.m. ለቤተሰቦች እና ለተማሪዎች ስለ አእምሮ ጤንነት የውይይት መድረክን እያዘጋጀ ነው። ዝግጅቱ ወላጆች ስለ አእምሮ ጤንነትና ሪሶርሶች እና የትምህርት ቤቶች ዲስትሪክት ለተማሪዎች ስለሚሰጣቸው አገልግሎቶች ይበልጥ እንዲያውቁ እድል ይሰጣል። ራስን የማጥፋት ጠቋሚ ምልክቶች እና ራስን ማጥፋት ስለመከላከል፣ በተማሪዎች ላይ ጭንቀት እና ድብርት፣ ፍትኃዊ የመልሶ ማቋቋም፣ በአስጨናቂ ሁኔታ ምክንያት የሚደርስ ጉዳት እና በአእምሮ ላይ ያለው ተጽእኖ፣ የዲያሌክቲካል ባህሪ ሕክምና፣ ጥንቃቄ እና ማሰላሰልን ጨምሮ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የመርጃ/ሪሶርስ አውደ ርዕይ እና ልዩ ልዩ ክፍለ ጊዜዎች ይኖራሉ።
የሴኔካ ቫሊ ት/ቤት አድራሻ፦ Seneca Valley is located at 19401 Crystal Rock Drive in Germantown
እዚህ የበለጠ ግንዛቤ ያግኙ፦
እዚህ ይመዝገቡ/RSVP here።

  1. የአእምሮ ጤንነት እና ደህንነት መርጃዎችን በኦንላይን ያግኙ

mental healthMCPS ከ160,000 ለሚበልጡ ተማሪዎቹ እና 24,000 ሰራተኞቹ አካላዊ፣ ማህበራዊ እና ስነ-ልቦናዊ ደህንነት ቁርጠኛ ነው። በ MCPS ዋናው ደረገጽ ላይ ለተማሪዎች፣ ለሰራተኞች እና ለቤተሰቦች ጠቃሚ የዲስትሪክት አቀፍ መረጃ እና የማህበረሰብ ሪሶርሶችን ማግኘት ይችላሉ።
በ MCPS ውስጥ የአእምሮ ጤንነትን እና ደህንነትን ስራ ለመደገፍ ስለሚደረጉ ኢንቨስትመንቶች እንዲሁም ጠቃሚ የስራ መደቦችን የበለጠ ይወቁ።
MCPS ዋናው የበይነመረብ ገጽ
MCPS የበይነመረብ ዳሰሳ
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) Mental Health and Wellness Resources by School

  1. የአርጊሌ መለስተኛ ደረጃ ት/ቤት ርእሰመምህር (Argyle Middle School Principal) የሜሪላንድ የአመቱ ምርጥ ርእሰ መምህርነት አሸናፊ ሆነዋል

ጄምስ አልሪች፣ የአርገይል መካከለኛ ደረጃ ትምህት ቤት ርዕሰ መምህር (James Allrich, principal of Argyle Middle School)፣ የሜሪላንድ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ርእሰመምህራን ማህበር (MASSP) የ 2023 ምርጥ ርእሰመምህርነት ስያሜ አግኝተዋል። MASSP ለተማሪዎች ከፍተኛ ጥራት ያለው የመማር እድሎችን በመስጠት እና ለሙያው አርአያነት ያላቸውን አስተዋጾ በማሳየት ረገድ የተሳካላቸው የሜሪላንድ መካከለኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርእሰ መምህራንን እውቅና ይሰጣል።

እያንዳንዳቸው 50ዎቹ ግዛቶች፣ ዲስትሪክት ኦቭ ኮሎምቢያ፣ የዩኤስ ስቴት ዲፓርትመንት የውጭ አገር ትምህርት ቤቶች ቢሮ እና የመከላከያ ትምህርት አክቲቪቲ ተቋሞቻቸውን ለመወከል አንድ የመካከለኛ ደረጃ ወይም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ይመርጣሉ። ከነዚህ የስቴት አሸናፊዎች ሶስት የመጨረሻ እጩዎች የአመቱ ምርጥ ብሄራዊ ሽልማት ተፎካካሪዎች ሆነው ተሰይመዋል።

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ
Montgomery County Public Schools Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools