ሐሙስ፣ ጁን 16 ማወቅ ያለብዎት ጉዳዮች

ሐሙስ ሰኔ 16 ማወቅ ያለብዎት ስድስት ጉዳዮችን እነሆ! ስለ ትምህርት ቤት የመጨረሻ ቀን ማሳሰቢያ፣ "Juneteenth" ስለ ማክበር፣ የሠመር ምግብ፣ ስለ ኮቪድ-19 ማሳሰቢያ፣ ነጻ የክትባት ክሊኒኮችን እና ሌሎችንም ያካትታሉ።

 1. last day of schoolትምህርት ቤት የሚዘጋበት ቀን ነገ ጁን 17 ነው።
  አርብ ጁን 17 የ 2021-2022 የትምህርት አመት የመጨረሻው የትምህርት ቀን ሲሆን ተማሪዎች ቀደም ብሎ የሚለቀቅበት ቀን ነው። በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ለምንገኝ ሁላችን መልካም እረፍት እና ጤናማ የሠመር ጊዜ እንመኛለን! እባክዎ ከ MCPS ጋር የሚያደርጉትን «ግንኙነት ይቀጥሉ»። በሠመር ወቅት ስለሚቀጥለው የትምህርት ዓመት ማሳሰቢያዎችን እና መረጃዎችን እንልክልዎታለን። በሠመር ትምህርት፣በሠመር የምረቃ ፕሮግራሞች እና ቅዳሜ፣ ኦገስት 27 በዌስትፊልድ ዊተን የገበያ ማዕከል ለሚካሄደው MCPS Back-to-school Fair አውደ ርዕይ በማቀድና ዝግጅት በማድረግ እንጠመዳለን። እባክዎ የቀን መቁጠሪያዎ ላይ ምልክት ያድርጉ፤ ትርኢቱ የትምህርት አመቱን ለመጀመር ሁል ጊዜ አመቺ የሆነ መንገድ ነው!
 2. "Juneteenth" ክብረ በዓል
  በእርስ በርስ ጦርነት ማብቂያ ላይ ጋልቭስተን ቴክሳስ (Galveston, Texas) የተጀመረው "Juneteenth" ክብረ በዓል የዩናይትድ ስቴትስ ባርነት ማብቃቱን ይዘከራል። ቀኑ የጥቁር የነጻነት ቀን በመባልም ይታወቃል። የእለቱን አስፈላጊነት እንዲያሰላስሉ እናበረታታዎታለን፤ ስለዚህ የፌደራል በዓል የበለጠ ለማወቅ ከዚህ በታች አጋዥ ግብአቶችን አቅርበናል። ከ MCPS ዋና እሴቶች አንዱ ፍትሃዊነት መሆኑን ስለምናስታውስ "Juneteenth" ማክበር አስፈላጊ ነው። MCPS እያንዳንዱ እና ሁሉም ተማሪ አስፈላጊ በመሆኑ ውጤታቸው በዘር፣ በጎሳ ወይም በማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ ደረጃ መተንበይ የለባቸውም ብሎ ያምናል።

  ተጨማሪ ግንዛቤ ያግኙ:
  1. The Historical Legacy of Juneteenth
  2. ቪዲዮ ስለ- "Juneteenth" ታሪክ
 1. MCPS በተለያዩ ቦታዎች የሠመር ትምህርት ቤት ምሳ በነጻ ይሰጣል
  በበርካታ የሰመር ት/ቤት ወይም የመዝናኛ ፕሮግራሞች የሚገኙ ተማሪዎች የሞንትጎመሪ ካውንቲ የሰመር ምግብ ፕሮግራም ምግቦችን ያገኛሉ። መርሃግብሩ ተማሪዎች በሠመር ወራት የትምህርት ቤት ቁርስ እና ምሳ በማያገኙበት ጊዜ የተመጣጠነ ምግብ ማግኘታቸውን ያረጋግጣል። ነፃ ምግብ ከጁን 27 ጀምሮ በየሳምንቱ በካውንቲው ውስጥ በግምት 175 ጣቢያዎች ላይ ይቀርባል (የሚጀመርበት ቀን በየቦታው ይለያያል)። 18 እና ከዚያ በታች ያሉ ልጆች ሁሉም እና የአካል እና የአዕምሮ እክል ያለባቸው እስከ 21 አመት የሆኑ ወጣቶች ምግብ መቀበል ይችላሉ። ለእግር ጉዞ ቅርብ ከሆኑ ቦታዎች ለምግብ አገልግሎት ወደ ተከፈቱ ቦታዎች መሄድ ይችላሉ። ሁሉም ምግብ ፍራፍሬ፣ አትክልት እና የእህል ምርጫን ጨምሮ አምስት አይነት ምግብ የሚሰጥ ስለሆነ እዚያው በቦታው መመገብ አለባቸው። ክፍት የሆኑ ቦታዎችን ጨምሮ የቦታዎቹ ዝርዝር በሚቀጥለው ሳምንት ይገለጻል።
 2. ፖዚቲቭ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ መጠን ቁጥሩ እየቀነሰ ነው
  በዚህ ሳምንት፣ የካውንቲው የጤና ጥበቃ እና የሰብአዊ አገልግሎት ዲፓርትመንት (DHHS) የመረጃ ሠሌዳ (ዳሽቦርድ) የኮቪድ ሁሙማን ቁጥር እየቀነሰ መሆኑን ያሳያል። ይህም የሆነበት ምክንያት ጭምብል በመጠቀም፣ እጅ በመታጠብ እና በምርመራ ረገድ በተደረጉት ጥንቃቄዎች መላው ህብረተሰብ ባደረገው ጠቃሚ ጥረት ነው። እባክዎን እነዚህን ጠቃሚ ጥረቶች ይቀጥሉ! የትምህርት አመቱን መጨረሻ ስናከብር ኮቪድ አሁንም በመካከላችን መኖሩ መታወቅ አለበት። የኮቪድ ስርጭት መጠን እየቀነሰ ቢሆንም በጤና ጥበቃ መረጃ መሠረት አሁንም የሞንትጎመሪ ካውንቲ መጠነኛ የወረርሽኝ ስርጭት መኖሩን ያሳያል፣ ስለዚህ ለጥንቃቄ የምናደርገው ጥረት አሁንም አስፈላጊ ነው። ኮቪድ-19 ለመከላከል በምናደርገው የጋራ ጥረት እንቀጥል!
  MCPS የሰመር ፕሮግራም ውስጥ ልጅ ካለዎት፣ በኮቪድ የመያዝ ሁኔታዎችን በዚህ ቅጽ ሪፖርት ማድረግ ይቀጥሉ፡
  የኮቪድ-19 Google ሪፖርት ማቅረቢያ ቅጽ
  የኮቪድ-19 ክትባቶች በነጻ የሚሰጡ ናቸው። እዚህ ቀጠሮ ያድርጉ።

 

 1. ለዓመታዊ የትምህርት እቃ መያዣ ቦርሳዎች የእርዳታ ዘመቻ በመለገስ የተቸገረን ተማሪ ይርዱ
  በ MCPS ትምህርት ቤቶች ላሉ ተማሪዎች የትምህርት እቃ መያዣ ቦርሳዎችን እና የት/ቤት አቅርቦቶችን ለማከፋፈል ለ11ኛው አመታዊ "GIVE Backpacks" ዘመቻ ለመለገስ ያስቡበት። በአቅርቦት ሰንሰለት መስተጓጎል እና በዋጋ ንረት ምክንያት ለአንድ ቦርሳ የሚከፈለው ወጪ ወደ $15 በማደጉ እና በዚህ ፎል ወቅት የትምህርት ቁሳቁስ ለማግኘት እርዳታ የሚፈልጉ በርካታ ተማሪዎች ስላሉን ድጋፍዎን ከመቼውም ጊዜ በላይ አሁን እንፈልጋለን። MCPS በሠመር ወራት ቦርሳዎችን ለግዢ በማዘዝ በተቻለ መጠን ብዙ ተማሪዎችን በትምህርት አመቱ መጀመሪያ ላይ ከት/ቤት አቅርቦቶች ጋር ቦርሳዎችን የማቅረብ ግብ አለው።
  የበለጠ ግንዛቤ ያግኙ እና ልገሳ ያድርጉ
 2. ተማሪዎች ከትምህርት ቤት ውጭ የሚያሳልፉበትን ጊዜ በተመለከተ የዳሰሳ ጥናት እስከ ጁን 30 ድረስ ክፍት ነው።
  ተማሪዎች በትምህርት ላይ ባልሆኑ ቀናት አስደሳች እንቅስቃሴዎች እና እድሎች እንዳሉ ያውቃሉ? MCPS ከዚህ በፊት ከተሳተፉት እና ተሳትፈው ከማያውቁት ምን አይነት ልምድ እንዳላቸው እና የትኞቹን እድሎችን እንደተጠቀሙ ማወቅ ይፈልጋል። ከ 4ኛ እስከ 11ኛ ክፍል ተማሪ ያላቸው ወላጆች እና አሳዳጊዎች የሚቀጥለውን አመት ፕሮግራም ለማሻሻል እንዲረዳን ይህን የዳሰሳ ጥናት ሞልተው እንዲመልሱ ተጋብዘዋል። ጥናቱ እስከ ጁን 30 ድረስ ክፍት ነው።

MCPS ትምህርት በሌላቸው ቀናት ተማሪዎችን እና ቤተሰቦችን የሚያሳትፉ አማራጮችን ለመስጠት ከትምህርት ውጭ በሆኑ ጊዜያት ፕሮግራሞችን ያዘጋጃል። እነዚህ በአካል እና/ወይም ቨርቹወል የሚከናወኑ እንቅስቃሴዎች አካዴሚያዊ ክህሎትን፣ አካላዊ እና ስሜታዊ ደህንነትን፣ የስነ ጥበብ እና ዲጂታል የመማር ችሎታን ያዳብራሉ።
ከትምህርት ቤት ውጪ በሚሆኑበት ጊዜ ስላለው ፕሮግራም ይበልጥ ይወቁ

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ
Montgomery County Public Schools Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools