ርዕሰ ጉዳዩ፡ "አሁን ሁላችን አንድ ላይ ተማሪዎቻችንን ማስቀደም" - የጊዜያዊ ሱፐር ኢንተንደንት ዶ/ር ሞኒፋ ቢ. ማክከኒት መልእክት

ርዕስ፡አሁን ሁላችንም አንድ ላይ ተማሪዎቻችንን ማስቀደም

last day of school

ውድ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ቤተሰቦች

ቅርብ ጊዜ በተካሄዱት በርካታ የማህበረሰብ እና የ MCPS ሰራተኞች የተሳተፉባቸው ዝግጅቶች ከብዙዎቻችሁ ለመስማት እድል በማግኘቴ በጣም ደስተኛ ነኝ። ከሁሉም የካውንቲ እና የዲስትሪክቱ አካባቢዎች ዝግጅቶቻችን ላይ የተገኙ ሰዎች ስለ ጥንካሬዎቻችን እና ተግዳሮቶቻችን እንዲሁም ከትምህርት ስርዓታችን ወደፊት ስላሉት እድሎች ያላቸውን ሀሳብ አካፍለዋል። የተሳተፉት ተማሪዎች፣ ሰራተኞች፣ ወላጆች እና የማህበረሰብ አባላት ነበሩ። በመጀመሪያው የማህበረሰብ ዝግጅት ላይ ከ 360 በላይ የተገኙ ሲሆን በተለይም ተማሪዎች ለመምጣት ጊዜ መስጠታቸውና በትምህርት ቤቶቻችን ልምዳቸውን በማካፈላቸው በጣም ተደስቻለሁ። የእርስዎ መሣተፍ ስለ ተሳትፎ ባህል ያለኝን እምነት በእውነት ይደግፋል፣ እና ለወደፊቱ በርካታ የመሣተፍ እድሎች እንደሚኖሩን እተማመናለሁ።

ከሦስቱ ዋና ዋና ጉዳዮች አንዱ በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ላይ የማህበረሰብ እምነትን መልሶ መገንባት መሆኑን ገልጫለሁ። የግንኙነት ግንባታ የሁለትዮሽ ጥረት ነው፣ እነዚህ ዝግጅቶች በአክብሮት የምናገለግላቸውን ድንቅ ተማሪዎች በመወከል በጋራ ስንሰራ ለጠንካራ ታማኝ ግንኙነት ያለንን ቁርጠኝነት ለማረጋገጥ ጠቃሚ እርምጃ ነው። ይህን ስናደርግ፣ እርስበርስ ከተተዋወቅንና –ለማኅበረሰባችን በጣም አስፈላጊ የሆኑትን ጉዳዮች ለይተን ካወቅን እና ከተረዳን የተሻለ አገልግሎት መስጠት እችላለሁ። ችግሮቻችንን ለመፍታት እና ብዙ ጥንካሬዎቻችንን ለማዳበር በምንሰራበት ጊዜ ግልፅነት እና ምላሽ ሰጪነት ቁርጠኝነቴ ነው። ተማሪዎቻችንን፣ ቤተሰቦቻቸውን እና የ MCPS ሰራተኞቻችን ለማገልገል ዝግጁ ነኝ። ባደረግናቸው ውይይቶች ተደንቄአለሁ። ወደፊት ስለምናደርጋቸውም ውይይቶች በጉጉት እጠብቃለሁ።

ከእናንተ የሰማሁትን፦

በቅርብ ጊዜ በነበሩን የተሳትፎ ክፍለ ጊዜዎች የወሰድነውን ግብረመልስ በዚህ ሰነድ ላይ ተንፀባርቆ ማየት ይችላሉ። የእርስዎ አስተያየት የተለያዩ ፍላጎቶችን ይሸፍናል እና እያንዳንዱ ንጥል ነገር ተማሪዎችን እና ሰራተኞችን የሚያገለግል አስፈላጊ ማሻሻያ ወይም ማስተካከያ ማድረግ የምንችልባቸውን ቦታዎች መለየት እንዳለብን ያመለክታል። ስለ አእምሮ ጤና፣ የትምህርት ቤት ደህንነት፣ የሰራተኞች መሟላት ጉዳይ፣ የስራ ማስኬጃ በጀት፣ የልዩ ትምህርት ተማሪ አገልግሎቶች እና ሌሎችንም ተነጋግረናል። የማህበረሰቡ አስተያየት ስራችንን ለማሳወቅ የእኔ ቁርጠኝነት አካል ቢሆንም፣ ማንኛውም የሚወሰድ እርምጃ ወይም ውሳኔ ውጤቱ MCPS ውስጥ ተማሪዎችን፣ ሰራተኞችን እና የላቀ የአገልግሎት አሰጣጥን እንደሚደግፍ ማረጋገጥ አለብን። ተማሪዎችን ማስቀደም ያልነው በዲስትሪክቱ ውስጥ ላለው እያንዳንዱ ቤተሰብ ያለን ቁርጠኝነት ይቀጥላል።

እያደረግን ያለነው

በተሳትፎ ክፍለ-ጊዜዎች ስለሰማኋቸው ብዙ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ነገሮች በማየቴ በጣም ተደስቻለሁ። የትምህርት ቦርድ ስትራቴጂካዊ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን እና የእኔን ስትራቴጂ ሁለቱንም የተጣጣሙ አድርገን ቅድሚያ የሚሰጧቸውን ጉዳዮች ለመደገፍ አስፈላጊ ለውጦችን እያደረግን ነው። ቅድሚያ የሚሰጣቸው ነገሮች በ MCPS ውስጥ የትምህርት ቤቶችን እና የተማሪዎችን ቀጥተኛ ፍላጎቶች በሚያሟሉ የአመራር መዋቅር እና የተለያዩ የስራ መደቦች ላይ ለውጦችን አድርጌያለሁ። ለምሳሌ፡-

  1. የትምህርት ስርአቱን አመራር በትክክል ለመጠቀም እና ከትምህርት ቦርድ እና ከውጪ ባለድርሻ አካላት ጋር ግንኙነት ለማድረግ የሚረዳኝን ሚስተር ብሪያን ስቶክተንን (Mr. Brian Stockton) Chief of Staff/ቺፍ ኦቭ ስታፍ አድርገን ቀጥረናል።
  2. በእኛ ማህበረሰብ ውስጥ ካሉ አጋሮች፣ ባለድርሻ አካላት እና መሪዎች ጋር እንዲያስተባብሩ ወይዘሮ ኤልባ ጋርሲያን (Ms. Elba Garcia) የማህበረሰብ ከፍተኛ አማካሪ እንዲሆኑ ቀጥረናል።
  3. ሚስስ ሴሊያ ፊሸር (Ms. Celia Fischer) የኮሚዩኒኬሽን ረዳት ዋና ዳይሬክተር በመሆናቸው የተሻሻለ፣ ንቁ፣ እና ውጤታማ ግንኙነቶችን እንጠባበቃለን።
  4. የአካል ጉዳተኛ ከሆኑት የተማሪዎቻችን ቤተሰቦች ጋር በቀጥታ የሚሳተፍ የልዩ ትምህርት ግንኙነትን የሚመራ እንቀጥራለን፥ በዚህም የተማሪዎቹን ፍላጎቶች የበለጠ ለመረዳት እና ለፍላጎታቸው የበለጠ ምላሽ መስጠት የምንችልበትን መንገድ እናዳብራለን።
  5. አዲስ ምክትል ሱፐርኢንቴንደንት፣ ዋና የአካዳሚክ ኦፊሰር እና ዋና የኦፕሬሽን ኦፊሰር ይኖረናል። ሁሉም የትምህርት ቤቶችን እና የተማሪዎችን፣የሰራተኞችን እና የሁላችንንም ተሳትፎ ከፍ ለማድረግ ቁልፍ ሚና ይኖራቸዋል።

ጥረቶቻችን እና ትኩረታችን በሌሎችም መንገዶች በተጨባጭ የሚገለጹ ናቸው፦

  1. የሰራተኞቻችን እና የተማሪዎቻችን ደህንነት ቅድሚያ የሚሰጣቸው ሲሆን በዚህ ሠመር በት/ቤት ደህንነት እና ሠላም ዙሪያ ለሰራተኞቻችን ሙያዊ ክህሎት እየሰጠን ነው።
  2. በሁሉም ደረጃዎች ጠንካራ የሠመር ትምህርት ፕሮግራም እናቀርባለን።
  3. ቨርቹወል አካዳሚችንን ለመቀጠል እና ለማሻሻል አቅደናል።
  4. የአዕምሮ ጤንነት እና ደህንነትን ፕሮግራም ወደ ብዙ ትምህርት ቤቶች ማስፋፋት እና በሚቀጥለው የትምህርት አመት ለተማሪዎች የቴሌ ጤና አገልግሎት ለመስጠት አቅራቢዎችን መለየት የመሳሰሉ ተጨማሪ የአእምሮ ጤና እና ደህንነት መርጃዎችን እናደራጃለን።
  5. ለተማሪዎቻችን አሁን እና ለወደፊቱ ጠንካራ እድሎችን ለማቅረብ ከማህበረሰቡ ውስጥ ካሉ አስፈላጊ የትምህርት እና የንግድ አጋሮች ጋር ያለንን አጋርነት ማጠናከር እና ማዳበር እንቀጥላለን።

ቀጥሎ የሚደረገው ምንድነው?

ለጠንካራ የሃሳብ ልውውጥ ቀጣይ ውይይቶች ላይ ለመሳተፍ እና በሚቀጥሉት ወራት የእናንተን ፍላጎትና አስተያየት ለመጠየቅና ለመስማት ቁርጠኛ ነኝ። ፈጣኑ እድል ይህ የዓመቱ መጨረሻ የዳሰሳ ጥናት ነው። ይህን የዳሰሳ ጥናት ለመሙላት ትንሽ ጊዜ ይውሰዱ - ለእርስዎ እንደሚመችዎት በሚቀጥሉት ቀናት በማንኛውም ጊዜ ሊከናወን ይችላል። የዳሰሳ ጥናቱ እስከ ሰኔ 30 ድረስ ክፍት ይሆናል። እርስዎ ቅድሚያ መሰጠት ያለበትን ነገር እንዲጠቁሙ ለማስቻል በቅርብ ጊዜ በተሳትፎ ክፍለ ጊዜ የሰማነውን በጥልቀት መመርመር እንፈልጋለን። እባክዎን የዳሰሳ ጥናቱን ይሙሉ፣ በቅርብ ጊዜ በተደረጉት የተሳትፎ እድሎች ላይ የተሳተፉ ወይም አንዱንም መሳተፍ ያልቻሉ ቢሆን እንኳ ሁሉም ድምጾች ዋጋ ስላላቸው ይቆጠራሉ። ከዚህ በታች ባለው ቪዲዮ ስለ ዳሰሳ ጥናቱ የበለጠ ማወቅ ይችላሉ።

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ከፍተኛ ጥራት ያለው የትምህርት ተቋም መሆኑን ለማረጋገጥ ቁርጠኛ የሆነ ማህበረሰብ በማግኘቱ እድለኛ ነው፥ ስለሆነም ከእናንተ ጋር በዚህ ስራ አጋር በመሆኔ ኩራት ይሰማኛል።
ከልብ

Monifa B. McKnight Ed.D.
Interim Superintendent of Schools
last day of school


Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools