የ MCPS ሱፐር ኢንተንደንት እንዲሆኑ አዲስ ከተሰየሙት ከዶ/ር ሞኒፋ ቢ መክናይት (Dr. Monifa B. McKnight,) የተጻፈ ደብዳቤ።

February 8, 2022

ለተከበራችሁ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ማህበረሰብ፦

የሞንትጎመሪ ካውንቲ የህዝብ ትምህርት ቤቶች ሱፐርኢንተንደንት በመሆኔ ትህትና እና ክብር ይሰማኛል። ለ 20 ዓመታት ከብዙ ወላጆች፣ ተማሪዎች፣ አስተማሪዎች እና አስተዳዳሪዎች ጋር በመተባበር ሠርቻለሁ። በዚህ የትምህርት ስርዓት ውስት እንደ መምህር፣ መሪ መምህር፣ ርዕሰ መምህር፣ የዋና ጽ/ቤት አስተዳዳሪ እና ምክትል ሱፐርኢንተንደንት ሆኜ የማደግ እድል አግኝቻለሁ። ከዛሬ በኋላ የሚቀጥለው የጋራ ጉዟችን ጅምር ነው።

ልክ እንደ እናንተም፣ እኔም በጥልቀት ስለልጆቻችን ይሰማኛል። አዳራሹን፣ ኮሌጅ፣ እና ማህበረሰባችንን ዝግጁ ለማድረግ እያንዳንዳቸው ጤናማ፣ደህንነታቸው የተጠበቀ፣ሥራቸው ላይ የሚያተኩሩ እና ተፈታታኝ ሁኔታዎችን መቋቋም የሚችሉ መሆናቸውን ለማረጋገጥ በገባነው ቃል መሠረት ማወላወል እንደሌለብን አውቃለሁ። ያንን ለማድረግ መተማመን እና እውነተኛ አጋርነት፣ የማያቋርጥ ጥረት እና ሁላችንም እጅግ በጣም ውድ- ልጆቻችንን ለማገልገል አንድ ላይ ስንቆም የምንፈጥረው ተአምር ያስፈልጋል። አንዳንድ ጊዜ ባንስማማ እና በእኔም በኩል ሁልጊዜ ትክክል ባልሆን፣ ከፍተኛ ደረጃዎችን ለመድረስ የምንችለውን ሁሉ ለማድረግ ቆርጠናል። ልጆቻችን ከዚያ ያነሰ አይፈልጉም ሁላችንም - አስተማሪዎች፣ አስተዳዳሪዎች፣ ወላጆች እና የማህበረሰብ አባላት - በአላማ እና በታማኝነት ሚናችንን ሙሉ በሙሉ መደገፍ አለብን።

ለሁላችሁም ቃል እገባላችኋለሁ። ይህ በአብዛኛው እዚህ በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ ያሳለፍኩት በጠቅላላ ሙያዊ ህይወቴ የተዘጋጀሁበት ወቅት ነው። በአንድነት ከቆምን ለማከናወን የማንችለው ነገር የለም።

ትምህርት ቤቶቻችንን የላቀ ደረጃ ላይ ለማድረስ መግፋታችንን እየቀጠልን ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ የህዝብ ጤና ቀውስ ስንታገል ያለፉት ሁለት ዓመታት በእኛ ላይ ያደረሱብንን ጫናዎች አስታውሳለሁ። እናም ልጆቻችሁን እና የትምህርት ስርዓቱን ለመደገፍ ያደረጋችሁትን ሁሉ አውቃለሁ። ወረርሽኙ ያስከተለውን ግራ የሚያጋባ እርግጠኛ መሆን አለመቻል፣ ማግለል/መገለል እና ፍርሃት ገጥሞናል፥ ይህም በመላው ማህበረሰባችን ውስጥ የተለያዩ ማህበራዊ፣ ስሜታዊ፣ አካዳሚያዊ እና የአእምሮ ጤና ፍላጎቶችን አስከትሏል።

በወረርሽኙ እንዳንገደብ በቁርጠኝነት ተጋፍጠናል፤ ይልቁንስ በጋራ ተግዳሮቶችን ለመቋቋም ቆርጠን ተነስተናል። ትምህርት ቤቶቻችንን ለልጆቻችን የሚገባቸውን ጤናማ እና አስተማማኝ ቦታዎች እናደርጋለን እና በአካል የመማር እድሎችን እናስከብራለን። በዚህ ፈታኝ ወቅት የእርስዎ አጋርነት፣ እርጋታ እና ትዕግስት ለመላው የትምህርት ቤት ማህበረሰብ ትምህርት ከመሆኑም በላይ እድገት አስገኝቷል። ይህ ቀላል ሁኔታ አልነበረም፥ ነገር ግን አንድ ላይ ሆነን ጸንተናል እናም ለዚህ ከፍተኛ ጥረት ላደረጋችሁት ጠቃሚ አስተዋፅዖ አመሰግናለሁ።

በዚህ የጋራ ሃላፊነት መንፈስ፣ ለልጆቻችን የጋራ ስኬት እድሎችን ለመስጠት ለት/ቤቶቻችን እና ለማህበረሰባችን የጋራ እድል በመፍጠር እንቀጥል። የእኛ ጥምር ጥረት፣ እንክብካቤ እና ቁርጠኝነት ኃይል ወደፊት ያራምደናል። በተማሪዎቻችን ስኬት ዙሪያ ባለን የጋራ ጥቅም በአንድነት ስንቆም ልንወድቅ አንችልም።

በሚቀጥሉት ሳምንታት እናንተን ለማግኘት አቅጃለሁ፣ ለዲስትሪክታችን ያላችሁን ምኞት እንዴት ማበርከት እንደምትፈልጉ እና እኔ ምን ማድረግ እንደምችል ከእናንተ ለመስማት ቦታ ለመፍጠር እና ብዙ ልዩ ልዩ የማህበረሰብ ድምጾችን የበለጠ ለመስማት እና ዋጋ ለመስጠት እቅድ አለኝ። በተማሪዎቻችን እና በትምህርት ስርአታችን ስም ማህበረሰቡን የማሰባሰብ እቅዳችንን የበለጠ እገልጽላችኋለሁ።

ከፊት ለፊት ብዙ ስራዎች አሉብን፥ እና ከፊታችን ያሉትን እድሎች ለመጠቀም ከዚህ የተሻሉ አጋሮችን ማሰብ አልችልም። በእኔ ላይ እምነት ስለተጣለብኝ አመሰግናለሁ፣ አጋርነታችሁን ከፍ አድርጌ እመለከተዋለሁ፣ ከእናንተ ጋር ወደፊት ለትምህርት ቤቶቻችን ማህበረሰቦች ብሩህ ተስፋን እጠባበቃለሁ። እንግፋበት

ከአክብሮት ጋር

Monifa B. McKnight, Ed.D.
Interim Superintendent of Schools
ሞኒፋ ቢ. ማክነይት ዶ/ር
ተጠባባቂ የትምህርት ቤቶች ሱፐርኢንተንደንትEmail us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools