ለተከበራችሁ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ማህበረሰብ፦
ይህንን የምጽፈው የዘገዩ እና የተሰረዙ የአውቶቡስ መስመሮችን በተመለከተ ችግሮችን ለመፍታት የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ ስለሚወስዳቸው አስቸኳይ እና ቀጣይነት ያለው አስፈላጊ እርምጃዎች ለማሳወቅ ነው። የትምህርት ቤት አውቶቡስ ኦፕሬተሮችን ጨምሮ የአውቶቡስ ኦፕሬተሮችን የመመልመል አገራዊ ፈተና አሁንም እንደቀጠለ ነው። ነገር ግን፣ ተማሪዎቻችን በየእለቱ በደህና ወደ ትምህርት ቤት እንዲገቡ እና እንዲመለሱ ለማድረግ ቆርጠኝነት አለን። ተጨማሪ መስመሮችን ለሚነዱ የትምህርት ቤት አውቶቡስ ሹፌሮች $25 ዶላር ክፍያ ቦነስ ወደነበረበት መመለሱን ሳሳውቅ ደስታ ይሰማኛል። ይህንን የደመወዝ ጥቅማጥቅም በፍጥነት ወደነበረበት ለመመለስ ከእኛ ጋር የሰሩትን "Ms. Pia Morrison, president of the Service Employees International Union, Local 500" ፕሬዝዳንት ያለኝን አድናቆት መግለጽ እፈልጋለሁ።
የበለጠ መረጃ:
ያልተጠበቁ የት/ቤት አውቶቡስ ሹፌሮች መቅረት የ MCPS ን የትራንስፖርት መምሪያ በየቀኑ እያንዳንዱን የአውቶቡስ መስመር ሙሉ በሙሉ ተሸፍኖ እንዲሰራ ለማድረግ ተግዳሮት ፈጥሮብናል። ይህም ሆኖ ትምህርት ቤት ክፍት በሆኑባቸው 48 ቀናት ውስጥ አሽከርካሪዎቻችን 59,040 መስመሮችን ያጠናቀቁ ሲሆን 114 ብቻ ተሠርዝዋል። የትራንስፖርት ሰራተኞቻችን ለተማሪ ተጓዦች ላሳዩት ቁርጠኝነት አመሰግናለሁ።
ችግሩን ለማቃለል እና ለተማሪዎች ከፍተኛ የደህንነት ደረጃን ለማረጋገጥ እንዲረዳ የሚከተሉትን እርምጃዎች በፍጥነት እየተገበርን መሆኑን ለማሳወቅ እወዳለሁ።
የቡድኑ ቁልፍ አባላት
አሽከርካሪዎቻችን ከተማሪ ተጓዦቻቸው ጋር ጠቃሚ ግንኙነትን የሚያዳብሩ በማህበረሰባችን ዋጋ ያላቸው አባላት ናቸው። የትምህርት ቦርድ አባላት፣ የእኔ አመራር ቡድን እና እኔ ለተማሪዎቻችን ያላቸውን ቁርጠኝነት ያሳዩትን አሽከርካሪዎቻችንን አነጋግረናል።
ሌላም ተጨማሪ እየመጣ ነው
ለተማሪዎቻችን አስፈላጊ የደህንነት እርምጃዎችን ለመተግበር እና የትራንስፖርት ሰራተኞችን ለመደገፍ ሌሎች አዳዲስ የፈጠራ ሀሳቦች በእቅድ ደረጃ ላይ ናቸው። እነዚህ ሃሳቦች የተሻሻለ የመንገድ እቅድ ማውጣት፣ ሙያ ማዳበር እና የወላጅ እና የማህበረሰብ አጋሮችን የሚያሳትፍ "Walking School Bus" ፕሮግራም መተግበርን ያካትታሉ። ዲስትሪክቱ በዲሴምበር 2022 በመላው ዲስትሪክቱ 150 መስመሮች ላይ የአውቶቡስ መተግበሪያ "bus app" በሙከራ ሥራ ላይ እንዲውል ያደርጋል። መተግበሪያው ወላጆች አውቶብሳቸውን በስማርትፎን በቅጽበት እንዲያዩ ያስችላቸዋል። በሙከራ ፕሮግራሙ ውስጥ የተካተቱት የአውቶቡስ መስመሮች በሙከራ መርሃ ግብር ውስጥ ስላላቸው ልምድ አስተያየት/ግብረመልስ ይሰጣሉ።
የምልመላ ጥረቱ ይቀጥላል
ሁሉንም ክፍት የአውቶቡስ ሾፌትነት ቦታዎች ለመሙላት የምልመላ ጥረቱ ይቀጥላል፣ እና 37 አዳዲስ አሽከርካሪዎች በስልጠና ላይ በማግኘታችን ደስታ ይሰማናል። በቅርቡ ኖቬምበር 3 እና ኖቬምበር 7 የተደረጉት የቅጥር ዝግጅቶች ይህን ስራ ለመስራት የበለጠ ፍላጎት ማሳደራቸውን ተመልክተናል። (MCPS በዩናይትድ ስቴትስ 14ኛው ትልቁ የትምህርት ቤቶች ዲስትሪክት ሲሆን፣ በዩናይትድ ስቴትስ በትልቅነቱ 6ኛ የትምህርት ቤት አውቶቡስ መጓጓዣዎች አሉት።) የትምህርት ቤቶች ሲስተማችን ወደ 25,000 የሚጠጉ ሰራተኞች ያሉት ሲሆን ይህም 1,195 የአውቶቡስ አሽከርካሪዎችን እና 580 የአውቶቡስ አተንዳንቶችን ያካትታል። ጀግኖች የአውቶቡስ ሹፌሮቻችን 210 ትምህርት ቤቶችን፣እና 20 የህዝብ ት/ቤት ያልሆኑ የግል ትምህርት ቤቶችን በሙሉ ያገለግላሉ። በተጨማሪም፥ በትምህርት አመቱ ሙሉ ለትምህርት ቤት የመስክ ጉዞዎች እና ከመደበኛ ትምህርት ውጭ እንደ አትሌቲክስ ያሉ እንቅስቃሴዎች የትራንስፖርት አገልግሎት ይሰጣሉ።
"ሁሉም በአንድ ላይ፣ ሁሉንም ለተማሪዎቻችን" መርኆአችን መሠረት እነዚህን ወሳኝ የመጀመሪያ እርምጃዎች እና የወደፊቱን እቅድ በትብብር አዘጋጅተናል። ለትምህርት ስርዓታችን፣ ለሰራተኞቻችን እና ለተማሪዎቻችን የላቀ ብቃትን ለመደገፍ አብረን በምንሰራው ታላቅ ስራ በጣም ደስተኛ መሆኔን ለመግለጽ ፈልጋለሁ።
ከአክብሮት ጋር
Monifa B. McKnight, Ed.D.
Superintendent of Schools
Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org