January 27, 2023

የተከበራችሁ የ MCPS ማህበረሰብ፦

ዛሬ፣ በተባበሩት መንግስታት አለም አቀፍ የሆሎኮስት መታሰቢያ ቀን ላይ፣ በሆሎኮስት ወቅት በስድስት ሚሊዮን የአይሁድ ህዝቦች ላይ ስለደረሰው የዘር ማጥፋት ለተማሪዎቻችን የሚያስተምሩ ትምህርታዊ ፕሮግራሞችን ለማጠናከር በምናደርገው ከልብ የመነጨ ትውስታ/ጥሞና እና ቁርጠኝነታችን ላይ እንድትተባበሩኝ እጠይቃለሁ።

በአገራችን እና በአካባቢያችን ማህበረሰብ ውስጥ እየጨመረ ያለው ፀረ-ሴማዊነት ማዕበል ውስጥ ሆነን፣ ትምህርት ለዚህ የምንሰጠው ምላሽ ትልቅ አካል መሆኑን እራሳችንን እናስታውሳለን። በ MCPS ውስጥ፣ ሥርዓተ ትምህርታችን ተማሪዎችን ስለ ፀረ-ሴማዊነት ስር መሰረቶች፣ በመንግስት የሚደገፉ ሁከት እና የዘር ማጥፋት ታሪክን፣ እና ዩናይትድ ስቴትስን ጨምሮ ከዓለም አቀፍ መንግሥታት የሚሰጡትን የተለያዩ ምላሾች ያስተምራል። በተጨማሪም፣ በሁሉም የእንግሊዝኛ ቋንቋ የስነ ጥበባት ክፍሎች፣ ተማሪዎች ከሆሎኮስት ጋር የተገናኙ ከእድሜ ጋር የሚስማሙ ጽሑፎችን ያነባሉ፣ እነዚህንም ጨምሮ፦

  • 8ተኛ ክፍል፦ የአና ማስታወሻ / The Diary of a Young Girl በ አና ፍራንክ
  • 10ኛ ክፍል፦ ናይት / Night   ኤሊ ቪሰል
  • 12ተኛ ክፍል (ተጨማሪ ፅሁፍ)፦  Out of the Whirlwind: A Reader of Holocaust Literature (የሆሎኮስት ስነ-ፅሁፍ አንባቢ)

እንዲሁም እንደ ባለፈው ማክሰኞ በዌቢናር ከ500 በላይ ተማሪዎች፣ ቤተሰቦች እና የማህበረሰብ አባላት ስለ ሆሎኮስት ከተረፉት መካከል አንዱ ከሆነው ከዶ/ር ማኒ ማንዴል (Dr. Manny Mandel) የተማሩበት አይነት አጋጣሚዎችን በመጠቀም፣ ለተማሪዎች እና ሰራተኞች ለተከሰቱት አሰቃቂ ድርጊቶች ጥልቅ ግንዛቤ እንዲያገኙ ተጨማሪ እድሎችን እናቀርባለን።

በቅርቡ በሀገሪቱ እና በአካባቢያችን የተከሰቱ ፀረ-ሴማዊ ክስተቶች፣ ፀረ-ሴማዊነት እና ጥላቻ ሲያጋጥሙን በፍጥነት፣ በቆራጥነት እና በማያዳግም ሁኔታ ምላሽ መስጠት እንዳለብን እና እነሱን ለማጥፋት የምናደርገውን ጥረት አጠናክረን እንድንቀጥል ያስታውሱናል። በሁሉም የማህበረሰባችን ክፍሎች መካከል ግንዛቤ መፍጠር በጣም አስፈላጊ ነው። የበለጠ ስናውቅ፣ የተሻለ ስራ እንሰራለን። በዚህ ሥራ የአይሁድ ማህበረሰብ ግንኙነት ምክር ቤት፣ የፀረ-ስም ማጥፋት ሊግ እና ከሁሉም በላይ ደግሞ የMCPS ቤተሰቦቻችንን ጨምሮ ብዙ አጋሮች በማግኘታችን እድለኞች ነን፣ የምጠይቃቸውም ሃብቶችን/ግብዓቶችን መጠቀም በመቀጠል (እዚህ ልያገኟቸው የሚችሉትን አይነት) ዛሬ —እና በየቀኑ ስለ አስቸጋሪ ታሪኮች ግልጽ እና እውነተኛ ውይይቶችን እንዲያደርጉ ነው።

መቼም ቢሆን አትርሱ።

ከአክብሮት ጋር

Dr. Monifa B. McKnight ዶ/ር ሞኒፋ ቢ. ማክናይት
Superintendent of School



Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools