ሐሙስ፣ ሴፕቴምበር 29 መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች

ሐሙስ ሴፕቴምበር 29 ማወቅ የሚገባችሁ ስምንት ጉዳዮችን እነሆ! ዶክተር ማክኒት የአትሌቲክስ ደህንነትን በተመለከተ የላኩትን የክትትል ደብዳቤ፣ ስለ ቤተሰብ የአካል ማጎልመሻ ትምህርት ሳምንት ማሳሰቢያ፣ ስለሚቀጥለው አመት የትምህርት ቤት የቀን መቁጠሪያ ጥናት፣ የአእምሮ ጤና መረጃ እና ሌሎችንም ያካትታሉ።

 • በዚህ ቅዳሜና እሁድ ሊከሰት ለሚችለው ከባድ የአየር ሁኔታ መከታተል
  የሳምንት መጨረሻ የአየር ሁኔታዎችን በቅርበት እየተከታተልን ነው። የቅዳሜ እና እሁድ እንቅስቃሴዎችን ለመሰረዝ ማንኛውም ውሳኔ ኦክቶበር 1 ቅዳሜ 6 a.m., ላይ በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የአደጋ ጊዜ የመገናኛ አውታሮች ላይ ይገለጻል።
 • MCPS ዋናው ድረገጽ www.montgomeryschoolsmd.org
 • MCPS Cable Channel 34
 • MCPS ማህበራዊ ሚድያ (Twitter, Facebook እና Instagram)
 • MCPS ዜናዎች እና መረጃዎች የሚተላለፉበት ክፍት መሥመር 301-279-3673
 • Alert MCPS
 • ConnectED
 • athleticsMCPS የአትሌቲክስ ደህንነት እቅድ—ተግባራዊ ተደርጓል እና በመስራት ላይ ነው።
  ትናንት በማህበረሰብ ደብዳቤ ላይ፣ ሱፐርኢንቴንደንት ዶ/ር ሞኒፋ ማክኒት አዲሱ የአትሌቲክስ ደህንነት እቅድ ባለፈው ሳምንት ተግባራዊ ሲደረግ ለተሰጠው አዎንታዊ የማህበረሰብ ድጋፍ አድናቆታቸውን አጋርተዋል። ከእርሳቸው ደብዳቤ የተወሰደ፦
  “ባለፈው አርብ፣ ጥሩ የአስተዋይነት ስሜት ያላቸው፣ ከፍተኛ አቅምና ጉልበት ያላቸው፣ ተማሪ-አትሌቶች በከፍተኛ ደረጃ የተወዳደሩበት እና ተመልካቾች ሲመለከቷቸው የተደሰቱባቸውን ጨዋታዎች አይቻለሁ። ይህ አዎንታዊ ውጤት በአጋጣሚ የተከሰተ አይደለም። ተማሪዎቻችን እኩዮቻቸው ጥሩ ስፖርታዊ ጨዋነትን እና መከባበርን እንዲጠብቁ ጥሪ አድርገዋል፣ ሰራተኞች፣ ወላጆች እና በጎ ፈቃደኞች የመልካም ባህሪ ሞዴል አሳይተዋል፣ ሁሉም ሰው አስተማማኝ እና አስደሳች ተከታታይ የአትሌቲክስ ዝግጅቶች ላይ ያለምንም ስጋት ተዝናንቷል፣ እነዚህ የት/ቤቶቻችን ባህሎች አስፈላጊ አካል ናቸው።”
  ሙሉውን መልእክት ያንብቡ

  አንዳንድ የምግብ ምርቶችን አደገኛነት ይረዱ
  የሞንትጎመሪ ካውንቲን ጨምሮ በብዙ አካባቢ ማህበረሰቦች ውስጥ ወላጆች እና ተማሪዎች በሚበሉት ምግብ በተከታታይ አሳሳቢ አደጋዎች መከሰታቸውን መረዳት አስፈላጊ ነው። እነዚህ የሚበሉ ነገሮች ከማሪዋና ጋር የተዋሃዱ የምግብ ምርቶች ናቸው። ብዙውን ጊዜ ከረሜላ እንዲመስሉ ተደርገው የሚዘጋጁ ናቸው፥ ነገር ግን በማሪዋና ውስጥ ያለውን ንጥረ ነገር THC ጨምሮ አደገኛ ንጥረ ነገሮች ይኖሩበታል። ሆን ብለው ወይም ሳያውቁ ወደ ውስጥ ሲያስገቡ በህጻናት ላይ ከባድ የጤና ችግር ሊያስከትሉ ይችላሉ። የአሜሪካ የሕፃናት ሕክምና አካዳሚ እንደገለጸው፣ ሕፃናት THC በመውሰዳቸው ከፍተኛ ተጽዕኖ ሊያሳድርባቸው ይችላል፣ ከእነዚህም መካከል ስካር፣ ጭንቀት/ድንጋጤ፣ ማዞር፣ ደካማ ራስን የቆጣጠር የሰውነት ቅንጅት እና ከመጠን ያለፈ እንቅልፍ። አንድ ሰው በጭንቀት ውስጥ ከሆነ(ች)፣ ወዲያውኑ 911 ይደውሉ። ልጅዎ ንጥረ ነገሮችን ሊጠቀም እንደሚችል/ልትጠቀም እንደምትችል ከተጠራጠሩ የሞንትጎመሪ ካውንቲ SASCA ክፍልን ያነጋግሩ ወይም 988 ይደውሉ፣ ቴክስት ያድርጉ ወይም ስለኔታው ተነጋገሩ።
  በዚህ የዩ ኤስ ድረ ገጽ ላይ የበለጠ ግንዛቤ ማግኘት ይችላሉ Just Think Twice

 • pe weekኦክቶበር 3-7 የቤተሰብ የአካላዊ ትምህርት ሳምንት ነው።
  ኦክቶበር የጤና ትምህርት ወር ነው፣ ስለሆነም ኦክቶበር 3-7 የቤተሰብ አካላዊ ትምህርት ሳምንት ይካሄዳል። በየቀኑ የሚደረግ አካላዊ እንቅስቃሴ ብዙ ጥቅሞች አሉት፥ ጉልበትን፣ ትኩረትን እና ለመማር ዝግጁነትን ይጨምራል፥ እና ጭንቀትን እና ውጥረትን ይቀንሳል። የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ሁላችንንም ይጠቅማል፣ ስለዚህ የተማሪዎች ቤተሰቦች አብረው በንቃት መንቀሳቀስ እንዲችሉ መርዳት MCPS ካሉት የአካል ማጎልመሻ ግቦች አንዱ ነው።
  በኦክቶበር የአካል እንቅስቃሴ ቀን መቁጠሪያ መሠረት ቤተሰብ በአንድ ላይ ተሳተፉ (የቀን መቁጠሪያውን እንግሊዝኛ እና ስፓኒሽኛ ይመልከቱ)።

 

 • calendar2023–2024 የትምህርት ቤት የቀን መቁጠሪያ ላይ የእርስዎን ሃሳብ/አስተያየት ይስጡ
  ለሚቀጥለው ዓመት የትምህርት ቤት የቀን መቁጠሪያ የማህበረሰብ ግብአት ሂደት የሚጀምረው አሁን የእርስዎን ሃሳብ/አስተያየት እንዲሰጡን በመጠየቅ ነው። 2023-2024 የትምህርት ዓመት የቀን መቁጠሪያ ሁኔታዎች ሲዘጋጁ በዚህ የዳሰሳ ጥናት የማህበረሰቡን ፍላጎት ለማወቅ እንፈልጋለን። ሰራተኞች ማክሰኞ ኦክቶበር 25 በትምህርት ቦርድ ስብሰባ ላይ ሁኔታዎችን ያቀርባሉ።
  የእርስዎን ፍላጎቶች እስከ ሐሙስ፣ ኦክቶበር 13 ያጋሩን። የዳሰሳ ጥናቱን እነሆ

 • mental health weekከኦክቶበር 10–15 የአእምሮ ጤና ግንዛቤ ሳምንትን እንደሚከታተሉ እርግጠኛ ይሁኑ
  MCPS እና የሞንትጎመሪ ካውንቲ ትምህርት ቤት ሳይኮሎጂስቶች ማህበር ከኦክቶበር 10-15 ወጣቶች እና ቤተሰቦች ከአእምሮ ጤና ባለሙያዎች ጠቃሚ የሆኑ ጉዳዮችን የማዳመጥ እድል ለመስጠት ነፃ ቨርቹወል ዝግጅቶችን ያስተናግዳሉ። ይህ የአንድ ሳምንት ርዝመት ያለው ኤክስፖ ዕለታዊ ጭብጦችን፣ በሙያ የተካኑ ተናጋሪዎች እና መረጃ ሰጪ ቪዲዮዎችን እንዲሁም ሁለት የቀጥታ ስርጭት ዝግጅቶችን ያቀርባል። የተማሪዎች የአእምሮ ጤንነት ላይ በተለየ መንገድ መስራት፣ እና የተለያዩ ሪሶርሶች አውደ ርእይ እና የጥያቄና መልስ ክፍለ ጊዜ ቅዳሜ ኦክቶበር 15 በበርካታ ቋንቋዎች ይካሄዳሉ።
  ስለ አእምሮ ጤንነት የግንዛቤ ሳምንት የበለጠ ይወቁ።
  ስለ አእምሮ ጤንነት መረጃ እና ግብዓቶችን ይመልከቱ

 • የሊተርሲ ካውንስል ለ MCPS ወላጆች ነፃ የ ESL ትምህርት ይሰጣል
  ከ MCPS ጋር በመተባበር የሞንትጎመሪ ካውንቲ (LCMC) የሊተርሲ ካውንስል (LCMC) እንግሊዝኛ ሁለተኛ ቋንቋ ለሆነ የ MCPS ወላጆች በነፃ የእንግሊዝኛ ትምህርት ይሰጣል። ክፍል እንደሚገኝ እና የምዝገባ ሂደትን በተመለከተ ጥያቄዎች ያሏቸው ወላጆች ለኬቨን ራልፍ (Kevin Ralph) LCMC kevin@lcmcmd.org ኢሜይል ማድረግ ወይም 240-665-0471 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

 • በምርጫ ቀን ተማሪዎች SSL ሰዓቶችን ማግኘት ይችላሉ
  MCPS ተማሪዎች በምርጫው ሂደት እንዲሳተፉ ለማበረታታት የሞንትጎመሪ ካውንቲ ምርጫ ቦርድን ይደግፋል። ተማሪዎች ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መመረቂያ መስፈርታቸው ወይም (እንደ ስራው ሁኔታ) ስታይፐንድ ለማግኘት የተማሪ አገልግሎት ትምህርት (SSL) ሰዓቶችን ለማግኘት ብቃት ይኖራቸዋል።
  ስለ ምርጫ ቀን የአገልግሎት እድሎች የበለጠ ይወቁ።
  የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ
  Montgomery County Public Schools 


Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org

Montgomery County Public Schools