ሀሙስ ኖቬምበር 17 መታወቅ ያለባቸው ስምንት ጉዳዮች ከዚህ የሚከተሉት ናቸው፦ የት/ቤቶቻችንን የአውቶቡስ መስመሮችን ለመደገፍ ስለተወሰዱ ወሳኝ እርምጃዎች መረጃ፣ ስለ በጀት ሂደቱ ሌላ የውይይት እድል፣ 2022-2023 የዊንተር አትሌቲክስ ደህንነት እቅድ፣ ድምጽዎ ተሰሚነት ያለው መሆኑን እንዴት ማረጋገጥ እንደሚችሉ የሚገልጽ መረጃ፥ ስለ መጪው የትምህርት ዓመት አቆጣጠር/ካለንደር፣ ለወላጆች ESL ትምህርቶች፣ ተጨማሪ የመንገድ ማቋረጫ ጠባቂዎች ጥሪ፣ የተማሪዎቻችን በስፖርት እና በሙዚቃ አስደሳች ድሎች እና ስለ መጪው ትምህርት ቤቶች የሚዘጉባቸው ቀናት ማሳሰቢያዎች ይቀርባሉ።
MCPS እንግሊዝኛ ሁለተኛ ቋንቋቸው ለሆኑ አዋቂዎች የእንግሊዝኛ ትምህርት ስለሚሊሰጥበት ሁኔታ ከሞንትጎመሪ ካውንቲ (LCMC) የሊተርሲ ካውንስል ጋር ተከታታይ ቨርቹወል ውይይቶች ያደርጋል። ውይይቶቹ በእንግሊዝኛ፣ በቻይንኛ እና በስፓኒሽኛ ቋንቋዎች ይስተናገዳሉ። LCMC እንግሊዘኛን እንደ ሁለተኛ ቋንቋ ለ MCPS ወላጆች እና አሳዳጊዎች በነጻ ይሰጣል። ለሁሉም ደረጃ የእንግሊዝኛ ተናጋሪዎች የቨርቹወል እና በአካል የመማር አማራጮች ይኖራሉ። እንግሊዝኛ የመጀመሪያ ቋንቋቸው ላልሆነ ወላጅ ሁሉ ይሰጣል። ስለ ESL ትምህርቶች የፍላጎት መግለጫ ቅጽ
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ
Montgomery County Public Schools
Email us: ASKMCPS@mcpsmd.org