ይህ ኢሜይል በሚገባ አይታይም ወይ? በአሳሻችሁ/browser ተመልከቱት ቀን: ጁን 21, 2023

ከበላይ ተቆጣጣሪ ዶ/ር ሞኒፋ ማክናይት (Dr. Monifa B. McKnight) ቢሮ

ለተከበራችሁ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ማህበረሰብ፦

ሌላ አንድ የትምህርት አመት ስናጠናቅቅ በጉዟችን የተወጣናቸውን ስኬቶቻችንን፣ እድገቶቻችንን፣ እና አይበገሬ መንፈሳችንን ማክበር አለብን። በእነዚህ ዘጠኝ ወራት ውስጥ አንድ ሶስተኛውን  ትምህርት ቤቶች በጎበኘሁበት ወቅት፣ ተማሪዎቻችን በጥልቅ ሲሳተፉ እና ሲማሩ አይቻለሁ፣ ስለዚህ በቀጣይነት ከተጠበቀው በላይ ከፍተኛ ጥራት ያለው ትምህርት እና ድጋፍ የሰጡትን ልዩ መምህራን ላመሰግናቸው እፈልጋለሁ።

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ ከአሁን በኋላ የስኬት መንገዳቸውን የሚቀጥሉ 12,000 የሚጠጉ ተማሪዎችን የምርቃ ሥነ ሥርአት በቅርቡ አክብረዋል። ለተመራቂዎቻችን፥ ለዚህ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ በመድረሳችሁ እንኳን ደስ አላችሁ! በለውጥ ውስጥ የመጓዝ ጽናትን፣ብቃትን እና መላመድን አሳይታችኋል። በስኬቶቻችሁ ኩራት ይሰማናል፥ እናም የወደፊት ዕጣችሁ ወዴት እንደሚመራችሁ ለማየት እንጓጓለን። 

ወደ ኋላ መለስ ብለን ስናስብ በተለያዩ ዘርፎች ከፍተኛ መሻሻል አሳይተናል። እኛስለ ተማሪዎች አፈጻጸም ሪፖርት ስናደርግ ሁሉም ተማሪዎች ሙሉ አካዳሚያዊ አቅማቸው ላይ እንዲደርሱ ለመደገፍ ያለንን እቅድ ደጋግመን ገልፀናል። የሜሪላንድ ስቴት የኮከብ ደረጃ ውጤት ያወጣ ሲሆን፣ በዚህ ውጤት መሠረት 92% የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ትምህርት ቤቶች ሶስት እና ከዚያ በላይ ኮከቦችን አግኝተዋል። እንዲሁም በኮሌጅ፣ በስራ እና በማህበረሰብ አገልግሎት ተማሪዎችን ወደ ስኬት መንገድ የሚመራቸውን መነቃቃት አሳይተናል። የተማሪዎች የደህንነት ጉዳዮች እና ዘረኝነትን እና አድሏዊነትን ለመቅረፍ ወሳኝ ስራ መሥራት እንዳለብን ለት/ቤቶች እና ለትምህርት ስርዓቱ መሪዎች ትኩረት የምንሰጠው ተግባር ሆኗል። 

በየትምህርት ቤቶቹ የደህንነት ጉዳዮችን መርምረናል፣ በየካምፓሱ አጠቃላይ አካላዊ ለደህንነት ጥበቃ የሚያስፈልጉ ነገሮችን ለመጨመር አዳዲስ እቅዶችን አውጥተናል፣ ከዚህ በተጨማሪ ዘረኝነት እና ጥላቻ የሚያስከትለውን ፈረጀ ብዙ ጉዳትና ተጽእኖ በሚመለከት በግልጽ ተነጋግረናል። የትምህርት ቦርዳችን የላቀ የአካዳሚክ እና የተግባር እቅዳችንን የሚወክል 2024 የበጀት ዓመት የሥራ ማስኬጃ በጀት በሙሉ ድምፅ አጽድቋል። 

የተማሪዎቻችንን እና የመምህራኖቻችንን አስደናቂ ስኬቶችን ከመመረቅ እስከ ስኮላርሺፕ እና የአካዳሚክ ሽልማቶችን መጎናጸፋቸውንስናከብር ትልቅ ደስታ ይሰማናል። የወደፊቱን ጊዜ ስናስብ፣ ኦገስት 28 ላይ የሚጀመረውን የትምህርት ቀን በጉጉት እንጠባበቃለን፥ እንደገና አንድ ላይ የምንሰበሰብበት፣ ለአዲሱ የትምህርት፣ የእድገት እና የስኬት አመት እንዲሆንልን ተዘጋጅተን እንጠብቃለን። 

ከአድማስ ባሻገር ፀሐያማ የሠመር ቀናት፡ ሠመር በተለያዩ እንቅስቃሴዎች ላይ በመሳተፍ፣ አዳዲስ የትርፍ ጊዜ ማሳለፊያዎችን በማሰስ እና የጀብድ ተግባራት ላይ በመሳተፍ፣ ከቤተሰብ እና ከጓደኞች ጋር ጥሩ ጊዜ በማሳለፍ እውቀት የምትሸምቱበት ጊዜ ነው። ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ የኛ ቁርጠኛ አስተማሪዎች እና አስተዳዳሪዎች ለሚቀጥለው የትምህርት አመት በዝግጅት ላይ ይቆያሉ። ትምህርት በሚጀመርበት ቀን ሁላችሁንም እስክንገናኝ በጉጉት እንጠብቃለን! 

ቅዳሜ፣ ኦገስት 26 በዌስትፊልድ ዊተን የገበያ ማዕከል ለ2023-2024 ወደ ትምህርት ቤት የመመለስ አውደ ርእይ የቀን መቁጠሪያዎ ላይ ምልክት ማድረግዎን ያስታውሱ። ከማናቸውም ጊዜ የበለጠ ትልቅ እና የተሻለ ይሆናል። እኛ ሥራችንን እንወዳለን እናም ከእርስዎ ጋር አንድ ላይ ተባብረን እንሠራለን።

ከመልካም ወዳጅነት ጋር

Dr. Monifa B. McKnight ዶ/ር ሞኒፋ ቢ. ማክናይት
Superintendent of Schools የትምህርት ቤቶች ሱፐርኢንተንደንት

ማሳሰቢያ፡ የሠመሩን ወቅት በአዝናኝ እድሎች እና እንቅስቃሴዎች ለማሳለፍ የሚያግዙ አንዳንድ ግብዓቶችን እዚህ ያገኛሉ።

የተቸገሩ ተማሪዎችን ይደግፉ / "BaCKPacks" ዘመቻ ዛሬውኑ ይለግሱ

ቀኑን ይቆጥቡ፡ 2023-2024 ወደ ትምህርት ቤት የመመለስ አውደ ርእይ ቅዳሜ፥ ኦገስት 26 ዳግም በዌስትፊልድ የገበያ ማዕከል/Westfield Wheaton mall ይካሄዳል። ከመቼውም ጊዜ ይበልጥ ትልቅ እና የተሻለ ይሆናል።