የማህበረሰብ መልእክት:

ስለ ሠመር የጤና አጠባበቅ ማሳሰቢያ

ኦገስት 2, 2023

የተወደዳችሁ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ማህበረሰቦች

ፎል ወቅቱ ተቃርቧል! ቤተሰቦች ወደ ትምህርት ቤት ለመመለስ እየተዘጋጁ ሳለ፣ ከሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) እና ከትምህርት ቤቶች የጤና አገልግሎት ክፍል የተሰጡ ጥቂት የጤና አጠባበቅ ጥንቃቄ ማሳሰቢያዎችን እነሆ፦

  1. የትምህርት ቤት ክትባቶች—የሜሪላንድ የጤና ዲፓርትመንት 2023-2024 የትምህርት አመት የተሻሻለ የትምህርት ቤት ክትባቶችን መስፈርት አውጥቷል። መጪዎቹ የመዋለ ሕጻናት ተማሪዎች ቤተሰቦች፣ አዲስ ተማሪዎች እና 7ኛ እና 8ኛ ክፍል ተማሪዎች የትምህርት ዓመቱን ለመጀመር ተጨማሪ ክትባቶች ሊያስፈልጋቸው ይችላል። የሚያስፈልጋቸው ክትባቶች ያላሟሉ ተማሪዎች፣ ወቅታዊ የክትባት ማስረጃቸውን በመጀመሪያ የትምህርት ቀን ማቅረብ አለባቸው። ከክትባት ነፃ የመሆን ማረጋገጫ ወይም ለክትባት ጉብኝት የተደረገበት ማስረጃ 20 ቀናት ውስጥ መቅረብ አለበት። የትምህርት ቤት ሰራተኞች ያልተሟሉ የክትባት ማስረጃ ያላቸውን ተማሪዎች ቤተሰቦቻቸውን በማነጋገር ላይ ናቸው። የተማሪዎ የክትባት ማስረጃ ወቅታዊ መሆኑን እርግጠኛ አይደሉም? የልጅዎን የጤና እንክብካቤ ሰጭ ያነጋግሩ ወይም የክትባት ማስረጃዎቻቸውን ሪከርድበኦንላይን ይመልከቱ። ዕድሜያቸው 18 እና ከዚያ በታች ብቁ የሆኑ ተማሪዎች በካውንቲው "የልጆች ክትባት ፕሮግራም/Vaccines for Children program" የክትባት ፕሮግራም ነፃ ክትባቶችን ሊያገኙ ይችላሉ።

  1. የትምህርት ቤት የጤና አጠባበቅ ቅጾች—ተመላሽ ተማሪዎች መድሀኒት የሚያስፈልጋቸው የጤና እክል ካለባቸው፣ ሌላ የጤና ድጋፍ ወይም አኮሞዴሽን፣ ወይም በትምህርት ቤት የድንገተኛ የጤና እቅድ (ለምሳሌ፦ አስም፣ የምግብ አለርጂ ወይም የሚጥል ህመም) ካለባቸው ሌሎች ቅጾችን መሙላት ሊያስፈልግ ይችላል)። የተለመዱት ቅጾች የሚከተሉትን ያካትታሉ፦

  1. አትሌቲክስ—የስፖርት ቡድን ሙከራዎች ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ኦገስት 9፣ እና ሴፕቴምበር 12 ለመካከለኛ ደረጃ ት/ቤቶች ይጀመራሉ። ተማሪ-አትሌቶች ለመጀመሪያ ጊዜ የሚመዘገቡ ከሆነ፣ ወይም የመጨረሻ ፈተናቸውን ከወሰዱበት ቀን ጀምሮ 13 ወራት (ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት) ወይም ሁለት ዓመት (መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት) ካለፉ አካላዊ/ፊዚካል ስፖርት ያስፈልጋቸዋል። ወላጆች/አሳዳጊዎች በኦንላይን የምዝገባ ሂደት የተማሪው(ዋ)ን አካላዊ/ፊዚካል ቅጽ ማቅረብ አለባቸው። ስለ ምዝገባ የሚያስፈልጉ ቅጾች ወይም ሌሎች የስፖርት ፊዚካል ግብአቶች/ሪሶርሶች የበለጠ መረጃ ለማግኘት MCPS የአትሌቲክስ ድረ ገጽን ይጎብኙ።

  1. ስለ ትምህርት ቤት የጤና አገልግሎት የበለጠ መረጃ ለማግኘት በጤና እና ሰብአዊ አገልግሎት መምሪያ (DHHS) ድረ ገጽ ላይ ያለውን የፕሮግራም መረጃ ይመልከቱ። ስለ አእምሮ ጤና አገልግሎቶች እና ድጋፎች አጠቃላይ መረጃ ለማግኘት፣ MCPS Stronger Student App ይጫኑ ወይም MCPS ድረገጽ ላይ የአእምሮ ጤና ድጋፍ “Mental Health Support” የሚለውን ከፍተው ይመልከቱ።

ቅዳሜ፣ ኦገስት 26 በዌስትፊልድ ዊተን ሞል 2023 MCPS ወደ ትምህርት ቤት የመመለስ ትርኢት / Ferio de Comenzar el Ciclo Escolar 2023-2024 ሁሉም ሰው እንደሚገኝ ለማየት በጉጉት እንጠብቃለን! አውደ ርዕዩ ስለ ትምህርት ቤት እና የካውንቲ አገልግሎቶች ለማወቅ፣ እንዲሁም ነጻ የክትባት ክሊኒክ ለማግኘት ጥሩ እድል ይሰጣል።

ደህና እና ጤናማ ሠመር ይሁንልዎት!

ከልብ

Patricia Kapunan፡ M.D., MPH
Medical Officer, MCPS

Mark Hodge, MS, B.S.N., RN
Sr. Administrator, School Health Services, DHHS



ኢሜል ይላኩልን: ASKMCPS@mcpsmd.org

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS)