መልካም የምስጋና በዓል ይሁንላችሁ!

ለሁሉም የምስጋና እና የደስታ መልካም ምኞት መልእክት

ኖቬምበር 21, 2023

የተወደዳችሁ ተማሪዎች፣ ሰራተኞች እና ቤተሰቦች 

ይህን በዓል ለማክበር እና ለማመስገን ከጓደኞቻችን እና ቤተሰቦቻችን ጋር በምንሰባሰብበት ወቅት፣ የማመሰግንበትን ነገር ሳሰላሰል ለእያንዳንዳችሁ ያለኝን ምስጋና እና አድናቆት መግለጽ እፈልጋለሁ። 

ተማሪዎች፦ ላደረጋችሁት ትጋት፣ ጥረት፣ እና የመማር ፍላጎት እናመሰግናችኋለን። አስተዳዳሪዎቻችን፣ መምህራኖች እና ሙያዊ ድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች በየቀኑ ምርጡን እንዲሰጧችሁ አድርጋችኋል። በትምህርት ጉዟችሁ ላይ እናንተን ለመደገፍ እድሉን ስላገኘን እናመሰግናለን።

ሰራተኞቻችን የላቀ የመማር ማስተማር ስራ ለመሥራት ያላሰለሰ ጥረት እና ቁርጠኝነት ስላሳያችሁ እናመሰግናችኋለን። ለተማሪዎቻችን ያሳያችሁት ቁርጠኝነት እጅግ አበረታች ነው፣ እና እናንተን በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ቡድን ውስጥ በማግኘታችን እድለኞች ነን። 

ቤተሰቦች በእኛ ላይ ስላሳደራችሁት እምነት፣ስላደረጋችሁልን ድጋፍ እና አጋርነት እናመሰግናለን። ትምህርት በቡድን የሚከናወን የጋራ ጥረት ነው፣ እና ተማሪዎቻችን ስኬታማ እንዲሆኑ ለመርዳት አብረን ለመስራት ለተሰጠን እድል አመስጋኞች ነን። 

በግል ማስታወስ የምፈልገው፥ በቅርብ ጊዜ ባጋጠመኝ ከባድ የጤና መታወክ ወቅት ለሰጣችሁኝ በርካታ የመልካም ጤንነት ምኞቶች እና የማበረታታት መልእክቶቻችሁ ምስጋናዬን ማቅረብ እፈልጋለሁ። ድጋፋችሁ ለብዙ ሌሎች ሰዎች እንክብካቤ እንደምናደርግ ሁሉ ጤናን መጠበቅ እና እራሳችንን ስለመንከባከብ አስፈላጊነት እና ጠቀሜታ አዲስ ብርሃን ፈንጥቆብኝ በፈታኝ የጤና መቃወስ ወቅት የጥንካሬ ምንጭ ሆኖኛል። 

ዕድሎችን ለመጠቀም እና ከፊታችን ያሉትን ፈተናዎች እየተጋፈጥን ወደፊት ለመጓዝ ቁርጠኞች ነን። የእያንዳንዳችንን እምቅ አቅም አሟጠን መጠቀም እንዳለብን የሚያስተምረን እና እውቀትና ጥበብን የሚያጎለብት የትምህርት ስርዓት ለመገንባት በጋራ መስራታችንን እንቀጥል። በጋራ ጥረት የምናከናውነው የማሻሻል ሂደት፣ ሁችን በአንድ ላይ - ለደህንነት፣ ለፍትሃዊነት እና የላቀ ደረጃ ለመቀዳጀት ያለን ቁርጠኝነት ይበልጥ ብሩህ ወደሆነ አቅጣጫ ይመራናል።

መልካም እና ጤናማ የምስጋና በዓል እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ። 

ከመልካም ወዳጅነት ጋር

Dr. Monifa B. McKnight Superintendent of Schools

ዶ/ር ሞኒፋ ቢ. ማክናይት የትምህርት ቤቶች ሱፐርኢንተንደንት



ኢሜል ይላኩልን: ASKMCPS@mcpsmd.org

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS)