ለማስታወቂያ ወይም ለማሸብረቅ የሚያገለግል ረዥም ጨርቅ ወይም ወረቀት፣ ሰንደቅ ዓላማ/ባነር

የትምህርት ቦርድ ወቅታዊ መረጃ፦ ኤፕሪል 26, 2024

የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ ለሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ አመራር ይሰጣል እና ክትትል ያደርጋል። የዚህ ሳምንት ከትምህርት ቦርድ የተሰጡ ዘገባዎች፦ ኤፕሪል 25 ከተካሄደው የቦርድ ስብሰባ የተገኙ ቁልፍ ጉዳዮችን፣ የትምህርት ቤቶች ሱፐርኢንተንደንት ፍለጋን የሚመለከት ወቅታዊ መረጃ፣ እና ለማህበረሰብ ተሳትፎ ያሉትን እድሎች ይመለከታል።

የቦርድ ስብሰባ፤ ኤፕሪል 25

የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ ሐሙስ፣ ኤፕሪል 25 ስብሰባ አካሂዷል። ቦርዱ ስለ ትምህርት ቤት ካውንስሊንግ ፕሮግራሞች እና አገልግሎቶች ፖሊሲ IJA ማሻሻያዎችን አጽድቋል። በማሻሻያዎቹ ላይ የሚከተሉት ተካተዋል፦

  • በተለያዩ ደረጃዎች ለሚሰጡ የተማሪ አገልግሎቶች የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የትምህርት ተልእኮ ጋር የተሣለጠ/ የሚደግፍ ማዕቀፍ ማብጀት።
  • ስያሜውን የቦርድ ፖሊሲ IJA፣ የተማሪዎች ማህበራዊ-ስሜታዊ እና የአእምሮ ጤና አገልግሎቶች ፕሮግራም ወደሚለው መለወጥ።

ስለ ት/ቤቶች ሱፐርኢንተንደንት ፍለጋ

ለሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) አዲስ ሱፐርኢንተንደንት ፍለጋው በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተካሄደ ነው። የቅርብ ጊዜው ማስታወቂያ የሚከተሉትን ያካትታል፦

  • የሱፐርኢንተንደንት ፍለጋ ዳሰሳ ዛሬ ይዘጋል - ይህ ስለ ሱፐርኢንተንደንት አስፈላጊ ነው ብለው የሚያምኑትን ባህሪያት እና የአመራር ብቃት እንዲሁም ቅድሚያ መሰጠት ያለባቸው ጉዳዮችን በተመለከተ የትኞቹ የመጪው ሱፐርኢንተንደንት ትኩረት መሆን እንዳለባቸው ሀሳብዎን ለማካፈል የመጨረሻ እድልዎ ነው።
  • ቦርዱ ባለፈው ወር የተሰበሰቡትን ሁሉንም አስተያየቶች ከግምት ውስጥ በማስገባት እጩዎችን በሚያነጋግርበት ጊዜ ከማህበረሰቡ የቀረቡትን ግብአቶች የአመራር መገለጫ በማድረግ ይጠቀማል።
  • የፍለጋ ድርጅቱ "Greenwood Asher & Associates, LLC" የስራ መደቡን ማስተዋወቅ እና እጩዎችን በንቃት መመልመል ጀምሯል።

የተሳትፎ እድሎች

ማህበረሰቡ እስከ ሜይ 6 ድረስ የፖሊሲ IOD ረቂቅ ማሻሻያዎችን እንዲገመግም እና አስተያየት እንዲያካፍል የትምህርት ቦርድ ያበረታታል። ፖሊሲ IOD የተነደፈው እንግሊዝኛ የሚማሩ ተማሪዎችን ስለማስተማር ነው። ማሻሻያዎቹ፦

  • ፖሊሲ IOD ስያሜውን እያደገ የመጣ የመድብለ ቋንቋ ተማሪዎች ትምህርት በሚለው ተለውጧል።
  • ተማሪዎች ብዝሃ ቋንቋ ተናጋሪ በሚሆኑበት ጊዜ ጠቃሚ የቋንቋ ችሎታ እንዳላቸው በማየት አወንታዊ ትኩረት በመስጠት ያበረታታል።

ቀጣይ ስብሰባዎች

  • ሰኞ፣ ሜይ 6 - የልዩ ማህበረሰብ ኮሚቴ
  • ሰኞ፣ ሜይ 6 - የስትራቴጂክ ዕቅድ ኮሚቴ
  • ሐሙስ፣ ሜይ 9 - መደበኛ (ቢዝነስ) ስብሰባ

አጀንዳዎችን ለማየት እና የቀጥታ ስርጭት ለመመልከት የኛን ድረ-ገጽ ይጎብኙ።

ግንኙነትዎ ይቀጥል

ፌስቡክ እና X  ላይ ይከታተሉ

በዚህ ኢሜል ያድርጉልን፦ boe@mcpsmd.org 


በዚህ ኢሜል ይላኩልን፦ boe@mcpsmd.org