ባነር

የትምህርት ቦርድ ወቅታዊ መረጃ ሜይ 17, 2024

የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ ለሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ አመራር ይሰጣል እና ክትትል ያደርጋል። የዚህ ሳምንት የትምህርት ቦርድ ዘገባ አዲስ ሱፐርኢንተንደንት ፍለጋን በሚመለከት ስለ ማህበረሰብ ተሳትፎ፣ የቦርዱ አዲስ የመሰብሰቢያ ቦታ፣ እና ስለ መጪዎቹ ስብሰባዎች ያካትታል።

የሱፐርኢንተንደንት ፍለጋው በሞንትጎመሪ ካውንቲ ድምጾች እየተመራ ነው

ለቀጣዩ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የትምህርት ቤቶች ሱፐርኢንተንደንትነት ውድድር የቀረቡ ማመልከቻዎች በትምህርት ቦርድ የግምገማ ሂደት ላይ ነው። በፍለጋው ሂደት የእጩዎችን የግላዊነት መብት ለመጠበቅ ሲባል፣ ለኃላፊነት ቦታው ስላመለከቱት ወይም ግምት ስለሚሰጣቸው ግለሰቦች ዝርዝር አይገለጽም። 

ቦርዱ አመልካቾችን ግምት ውስጥ የሚያስገባው፣ ከትኩረት ቡድኖች፣ ከማህበረሰብ የውይይት መድረኮች የተሰጡ አስተያየቶች፣ እና በኦንላይን ዳሰሳ ከአካባቢው ማህበረሰብ በተገኘ ግብአት ላይ ተመሥርቶ ነው። የእነዚህ የተሳትፎ እድሎች ውጤት ስለ ማህበረሰባችን ፍላጎቶች፣ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ነገሮች፣ እና ምኞቶች የጋራ ግንዛቤን ያስጨበጠን ነው። 

ከቀጣዩ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) መሪ በሚፈለጉት ባህሪያት ዙሪያ ሶስት ዋና ዋና ጭብጦች በግልጽ ተቀምጠዋል።

  • ግልጽነት እና ተጠያቂነት

  • እውነተኛነት ፣ ታማኝነት፣ እና ተአማኒነት

  • ግንኙነት እና ተሳታፊነት

ስለ አዲሱ ሱፐርኢንተንደንት ሥራ አራት ቅድሚያ የሚሰጣቸው ቦታዎችም ተለይተዋል፦

  • የተማሪዎች አካዳሚክ ስኬት እና የፕሮግራሞች እና የሪሶርሶች በእኩልነት ተደራሽ እንዲሆን ማድረግ

  • ደህንነት እና አስተማማኝ የት/ቤቶች ሠላም

  • የተማሪዎች እና የሰራተኞች ደህንነት

  • ምልመላ እና የሠራተኞች የሥራ አያያዝ 

ቦርዱ የማመልከቻዎችን ግምገማ የሚቀጥል ሲሆን በሚቀጥሉት ጥቂት ሳምንታት ውስጥ የመጀመሪያ ዙር ቃለመጠይቆችን እንደሚጀምር ይጠበቃል። 

የMCPS ሱፐርኢንቴንደንት ፍለጋ ድረ-ገጽን በመጎብኘት ህዝቡ መረጃ እንዲሰጥ እና እንዲሳተፍ ይበረታታል።

የትምህርት ቦርድ ወደ አዲስ የመሰብሰቢያ ቦታ ተዛውሯል

የትምህርት ቦርድ ከሜይ 23 ጀምሮ የቢዝነስ ስብሰባውን በአዲሱ የመሰብሰቢያ ቦታ 15 W Gude Drive፣ Rockville ማድረግ ይጀምራል። በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ ለሕዝባዊ ስብሰባዎች ክፍት የሆነ እና ተደራሽነት ያለው ቦታ የማዘጋጀት ሥራ ተጀምሮ ነበር።

አዲሱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ሰፊ ቦታ፣ የተመጣጠነ አየር የሚያስገባ እና ብዙ ብርሃን ያለው ክፍል ነው። ለተሰብሳቢዎች በቂ የመቀመጫ ቦታ፣ግልፅ እይታ፣ እና በርካታ የቪዲዮ ስክሪኖች ስላሉት ደስተኞች ይሆናሉ። በኦንላይን መከታተል ለሚመርጡ ሰዎች የቴክኖሎጂ አጠቃቀሙ ስብሰባዎችን በተሻለ ሁኔታ ለመመልከት ያስችላል።  

በአጀንዳው ውስጥ ብዙ ቁጥር ያላቸው አዳዲስ የሰው ኃይል ምደባዎች ስለሚኖሩ በአዲሱ ቦታ የሚደረገው የመጀመሪያው ስብሰባ በተለይ በጣም አስፈላጊ ነው። ቦርዱ የሚያካሄደውን ስብሰባ ህዝቡ በአካል በመገኘት ወይም በኦንላይን እንዲከታተል ይጋብዛል፣ ዝርዝሮቹ በቦርዱ ድረ ገጽ ላይ ይገኛሉ።

የተሳትፎ እድሎች

ህብረተሰቡ ከቦርዱ ጋር እንዲሳተፍና እንዲተባበር እናበረታታለን። በእኛ ድረ ገጽ ላይ መሳተፍ ስለሚችሉባቸው መንገዶች ያንብቡ።

ቀጣይ ስብሰባዎች

  • ማክሰኞ፥ ሜይ 21 - የኮሙዩኒኬሽን እና የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ኮሚቴ

  • ሐሙስ፥ ሜይ 23 - የትምህርት ቦርድ መደበኛ ስብሰባበ (15 W. Gude Drive)

አጀንዳዎችን ለማየት እና የቀጥታ ስርጭት ለመመልከት የኛን ድረ-ገጽ ይጎብኙ።

ግንኙነትዎ ይቀጥል

ፌስቡክ እና X  ላይ ይከታተሉ

ኢሜል ያድርጉልን፦ boe@mcpsmd.org 


ኢሜል ይላኩልን፦ boe@mcpsmd.org