MCPD የፖሊስ አዛዥ ማርከስ ጆንስ እና MCPS የደህንነት ሀላፊ ፓሜላ ዊለር-ቴይለር የጋራ መግለጫ

የቅርብ ጊዜ የቦምብ ዛቻ/ማስፈራራት እና ለትምህርት ቤት ደህንነት ያለን ቁርጠኝነት

 

የተወደዳችሁ ወላጆች፣ ሞግዚቶች፣ ተማሪዎች እና የማህበረሰብ አባላት


ይህ መልእክት በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) በቅርብ ጊዜ ስለደረሰው የቦምብ ማስፈራራት/ዛቻ ወቅታዊ መረጃ ልንሰጣችሁ እና የት/ቤቶችን ደህንነት ለማረጋገጥ ያለንን የጋራ ቁርጠኝነት ደግመን ለመግለጽ የተጻፈ ነው።


በኦክቶበር ወር፣ በበርካታ ሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ትምህርት ቤቶች አስር የሚረብሹ የቦምብ ማስፈራሪያዎች ገጥመውናል ። እንደ MCPS የፖሊስ መምሪያ እና የደህንነት ቡድን፣ ደህንነትን ለማረጋገጥ እና ትምህርት ቤቶችን በፍጥነት ወደ መማር ማስተማር ለመመለስ እያንዳንዱን ክስተት መርምረናል፣ ለትምህርት ቤቶች ፈጣን ድጋፍና ምላሽ ሰጥተናል። 


በእያንዳንዱ ሁኔታ በምርመራ ቡድኖች የተገኙ ቦምቦች ወይም አደገኛ መሳሪያዎች እንዳልነበሩ ልብ ሊባል ይገባል። የቦምብ ማስፈራራትና ዛቻዎች እንደ ቀልድ ወይም ማታለል ከሚፈልጉ ግለሰቦች ሊሰነዘሩ ቢችሉም ሁልጊዜ በትኩረት ይታያሉ። የቦምብ ማስፈራራትና ዛቻ እና ሌሎች የጥቃት ዛቻዎች ለብዙዎች ጭንቀት ይፈጥራሉ እናም የሁሉንም የመማር ማስተማር ሂደት ያደናቅፋሉ። የማስመሰል ማስፈራራትና ዛቻ ህገወጥ ከመሆኑም በላይ MCPS የተማሪ ስነምግባር ደንብ ጋራ የሚጻረር ተግባር ነው። በማህበረሰባችን ላይ ከፍተኛ ጉዳት ስለሚያደርስ፣ ደህንነትን ለማረጋገጥ የተጠያቂነት አስፈላጊነትን እንገነዘባለን።


መታወቅ ያለባቸው ጠቃሚ ነገሮች፦

  • የምርመራ መረጃ፦ የፖሊስ ዲፓርትመንት በሞንትጎመሪ ብሌር ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት፣ ሲልቨር ስፕሪንግ ኢንተርናሽናል መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት እና ኦክ ቪው አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ላይ ለበርካታ የቦምብ ማስፈራሪያዎች ተጠያቂ የሆነውን የ12 አመት ወጣት በፍጥነት ምርመራ በማድረግ ደርሶበታል። ምንም እንኳን የሜሪላንድ የወጣቶች ፍትህ ህግ በዚህ ጉዳይ ላይ የወንጀል ክስ እንዲመሠረት የማይፈቅድ ቢሆንም የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች የስነ ምግባር ደንብ ተገቢ የዲሲፕሊን እርምጃ እንደሚወሰድ የተደነገገ ነው። 

  • ማስፈራራት/ዛቻ ሲፈጠር ምን ይደረጋል፡
    • ትምህርት ቤቶች እና ፖሊሶች ስጋቱን በአንክሮ ይመለከቱታል። 
    • ከቦታው የመልቀቅ ወይም ወደ መጠለያ የመሸሽ ውሳኔ የሚወሰነው በተወሰኑ ሁኔታዎች እና መረጃዎች ላይ በመመርኮዝ እና ከህግ አስከባሪ አካላት ጋር በመቀናጀት ነው።
    • አደጋው በሚከሰትበት ጊዜ ቤተሰቦች ፈጣን እና ቀጣይነት ያለው ግንኙነት ይደርሳቸዋል።
    • የህግ አስከባሪ አካላት የአደጋውን ተአማኒነት ለመገምገም ጥልቅ ምርመራ ያደርጋሉ።
    • የህግ አስከባሪ አካላት ትምህርት ቤቱ ደህንነቱ የተጠበቀ መሆኑን ካረጋገጡ እና ግልጽ የሆነ ምልክት ከተሰጠ፣ ት/ቤቶች ወደ መማር ማስተማር ተግባር እንዲመለሱ ወይም ወላጆች/ልጆችን እንዲወስዱ የማድረግ እቅድ ይኖራቸዋል። 
    • የትምህርት ቤት እና የማህበረሰብ አጋሮች በክስተቱ ስሜታቸው ለተጎዱ ተማሪዎች፣ ሰራተኞች እና ወላጆች የምክር እና የድጋፍ አገልግሎቶችን ይሰጣሉ።

  • እንዴት መርዳት እንደሚችሉ፡ እንደ ማህበረሰብ፣ የደህንነት ስጋት የሚፈጥሩ ማንኛውንም መረጃ ካወቁ ወይም የፖሊስን ምርመራ ሊደግፉ የሚችሉ ከሆኑ እባክዎን ወዲያውኑ ለአካባቢው ህግ አስከባሪዎች ይጠቁሙ። አስቸኳይ ያልሆነ ጊዜ የፖሊስ ስልክ ቁጥር 301-279-8000 በኦንላይን የሜሪላንድ ደህንነቱ የተጠበቀ ትምህርት ቤት ጠቃሚ ምክር፦ በኢሜል እና በስልክ እና ማንነታቸው ሳይገለጽ ምክሮችን ይሰጣሉ። እዚህ ተጨማሪ መረጃ ያግኙ። ሁላችንም በደህንነት አጠባበቅ ላይ ወሳኝ ሚና እንጫወታለን እና MCPS እና የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፖሊስ ዲፓርትመንት ደህንነትን የሚመለከቱ ጥርጣሪዎችን ሪፖርት እንድታደርጉ እናበረታታችኋለን፣ እንዲሁም “አጠራጣሪ ነገር ከተመለከቱ አንድ ነገር ይበሉ/ይጠቁሙ።” ማንኛውንም መረጃ ወይም ስጋቶችን ማጋራት ሁከት ከመከሰቱ በፊት ለማስቆም አስፈላጊና ጠቃሚ ነው። በራሪ ወረቀቱን ይመልከቱ


ወላጆች እና ተንከባካቢዎች ስለ ኦንላይን ደህንነትን እና ባህሪ ጭምር ከተማሪዎች ጋር መወያየት አለባቸው። የልጆቻችንን የኦንላይን ግንኙነት ለደህንነታቸው አስጊ የሆኑ ነገሮች ሊያጋጥሟቸው ስለሚችሉ ማናቸውም ጎጂ የኦንላይን ግንኙነቶች እና ማስፈራሪያዎች ላይ እንዳይሳተፉ ለማድረግ በጋራ እንስራ።


  • የድጋፍ አገልግሎቶች፡በቅርብ ጊዜ ክስተቶች ሊጎዱ የሚችሉ ተማሪዎችን እና ሰራተኞችን ለመርዳት የምክር አገልግሎቶች በሁሉም ትምህርት ቤቶች ይሰጣሉ። ዛሬ በረፋዱ፣ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩል (MCPS) ዋና የህክምና ኦፊሰር፣ ዶ/ር ፓትሪሺያ ካፑናን፣ በእነዚህ ርዕሶች ላይ ቤተሰቦች እንዲወያዩበት መረጃ እና ግብዓቶችን የሚሰጥ መልእክት ያስተላልፋሉ።

ለሁሉም ተማሪዎች ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ምቹ የመማሪያ አካባቢ እንዲኖር የማድረግ ቁርጠኝነታችንን እናረጋግጣለን። በየእለቱ በት/ቤቶቻችን እና በማህበረሰባችን ከፍተኛ የደህንነት ደረጃ መኖሩን ለማረጋገጥ ትብብራችንን እንቀጥላለን።


Marcus Jones
ሥራ አስኪያጅ Chief
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፖሊስ መምሪያ Montgomery County Department of Police

Pamela Wheeler-Taylor
Chief Safety Officer
ሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ Montgomery County Public Schools







ኢሜል ይላኩልን: ASKMCPS@mcpsmd.org

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS)