ወደ ኮሌጅ፣ ስራ እና የማህበረሰብ አገልግሎት የዝግጅት መንገድ
MCPS ቤተሰቦች፣ ተማሪዎች እና አስተማሪዎች የተማሪን ስኬት ለማረጋገጥ አብረው እንዲሰሩ ለመርዳት አዲስ መመሪያ አዘጋጅቷል።
እንዴት እንደሚሰራ እነሆ!
ተማሪዎች ወደ አዲስ የክፍል ደረጃ፣ ኮሌጅ ወይም የስራ ግብረሃይል ከመሸጋገራቸው በፊት የሚወስዷቸው የአካዳሚክ ማሻሻያዎች ማንኛውንም የመማር ክፍተቶችን ለማሟላት ይጠቅማሉ።
ወላጆች ልጆቻቸው እነዚህን ልዩ መመዘኛዎች እያሟሉ ስለመሆኑ መረጃ ይደርሳቸዋል።
የት/ቤት ሰራተኞች፣ ተማሪዎች እና ቤተሰቦች ለተማሪው(ዋ) እንዲሳካ ለመርዳት የተሻለውን መንገድ ለመወሰን ተገናኝተው ይወያያሉ።
ከአካዳሚክ መመዘኛዎች በተጨማሪ፣ ትምህርት ቤቶች ለተማሪዎች ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት በኋላ ለሚኖራቸው ህይወት ለማዘጋጀት ዋና ብቃቶችን እና ክህሎቶችን እንዲያዳብሩ እድሎችን እና ልምዶችን ይሰጣሉ።
ስለ ዋና ዋና ጉዳዮች ለማወቅ ከዚህ በታች ያሉትን አገናኝ ሊንኮች ይጎብኙ።
አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች (እንግሊዝኛ)
español / 中文 / français / tiếng Việt / 한국어 / አማርኛ / Portuguese
መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት (እንግሊዝኛ)
español / 中文 / français / tiếng Việt / 한국어 / አማርኛ / Portuguese
ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት (እንግሊዝኛ)
español / 中文 / français / tiếng Việt / 한국어 / አማርኛ / Portuguese
ስለ ኮቪድ-19 ወረርሽኝ አዲስ መረጃ
አዳዲስ የኮቪድ-19 ተጠቂዎች በአገር ውስጥ እየጨረ ሲሄድ፣ በካውንቲያችን ውስጥ ባሉ በርካታ ትምህርት ቤቶች ወረርሽኙ ሲከሰት አይተናል። ኮቪድ-19 በፍጥነት እየተስፋፋ ባለባቸው የመማሪያ ክፍሎች የሚወሰደው ጊዜያዊ የመከላከል እና የጥንቃቄ እርምጃ ለወረርሽኝ ተጋላጭ ለሆኑ ግለሰቦች እና ለተቀረው የትምህርት ቤት ህብረተሰብ እንዳይሰራጭ ይረዳል። ወረርሽኙን እንዴት መከላከል እንደሚቻል የበለጠ መረጃ ለማግኘትFAQ ገጽ ይመልከቱ። አዲስ የጸደቀው የኮቪድ-19 የተሻሻለ ክትባት በሚቀጥሉት ጥቂት ሳምንታት ውስጥ በአካባቢያችን ይደርሳል። ስለ ኮቪድ-19፣ የኢንፍሉዌንዛ እና የመተንፈሻ አካልን የሚያጠቃ ህዋስ/RSV ክትባት መኖሩን መረጃ ለማግኘት Vaccines.Gov ይመልከቱ።
MCPS የሴቶች ልጃገረዶች ስብሰባ ያስተናግዳል
ዲስትሪክቱ ሁሉንም የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ቤተሰቦች ቅዳሜ፥ ኦክቶበር 21 በክላርክስበርግ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በሴቶች ልጃገረዶች ስብሰባ ላይ እንዲሳተፉ ይጋብዛል። ይህ ዝግጅት ለመካከለኛ እና ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ልጃገረዶች በተለያዩ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ መረጃ ሰጭ አውደ ጥናቶችን ያቀርባል። የኝኙነት መረብ የመዘርጋት ዕድል ለማግኘት ከእኛ ጋር ይቀላቀሉ፥ አዝናኝ እንቅስቃሴዎች ላይ ለመሳተፍ፣ ጠቃሚ ክህሎቶችን ለመማር እና ለተለያዩ የሰውነት ዓይነቶች የተዘጋጁ በዋይት ሀውስ ጥቁር ገበያ በሚቀርበውን የፋሽን ትርኢት በመመልከት ይደሰታሉ!
ክፍለ-ጊዜዎቹ በእንግሊዝኛ እና በስፓኒሽኛ የሚካሄዱ ሲሆን፣ በየክፍል ደረጃዎቻቸው የተቀናበሩ ናቸው። ለተማሪዎች የተማሪ አገልግሎት ትምህርት (SSL) ሰዓቶችን ያገኛሉ። ርዕሰ ጉዳዮቹ እና እንቅስቃሴዎቹ የሚከተሉትን ያካትታሉ፦
ስለ ጤናማ ግንኙነቶች/በፍቅር ጓደኝነት የሚፈፀሙ ጥቃቶች
የሳይበር ጥቃቶችን ጨምሮ የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም እና የአእምሮ ጤንነት
በራስ መተማመን
የጭንቀት እና የመንፈስ መረበሽ ምልክቶችን መለየት
ጤናማ አመጋገብ እና የሰውነት ቅርጽ
የሙዚቃ ቴራፒ፣ ዙምባ እና ካይዘር ፐርማንቴ ስፒን ብስክሌቶችን ለአርት ሕክምና መጠቀም
የናርካን ኪትስ ይሰራጫል፥ እና የአጠቃቀም ስልጠናም ይሰጣል።
ይመዝገቡ/RSVP
2024–2025 የትምህርት ዘመን አቆጣጠር ላይ አስተያየትዎን አጋሩን
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) 2024–2025 የትምህርት ካለንደር ለማጠናቀቅ እየሠራ ስለሆነ የማህበረሰብ አስተያየት እንዲሰጥበት ይፈልጋል። እባክዎ ሀሳብዎን ለማጋራት ይህን የዳሰሳ ጥናት ሞልተው ያቅርቡ።
የእርስዎ አስተያየት በማዳበር ሂደቱ አስፈላጊ አካል ነው። MCPS የትምህርት ፍላጎቶችን፣ የአሠራር ፍላጎቶችን፣ በስቴት ህግ የታዘዘ የትምህርት ቤት መዘጋትን፣ አነስተኛውን የትምህርት ቀናት እና የክሬዲት ሰዓት መስፈርቶችን ማክበርን፣ መጥፎ የአየር ሁኔታን እና ሌሎች ድንገተኛ ሁኔታዎችን፣ የሰራተኞችን የሙያ ማዳበር ቀናት እና ተማሪዎች በቅድሚያ የሚለቀቁበትን ቀናት፣ ከግምገማ መርሃ ግብሮች ጋር ማጣጣምን እና ሌሎችንም ይመለከታል።
የዳሰሳ ጥናቱን ይሙሉ.
በሌሎች ቋንቋዎች የተዘጋጀ የዳሰሳ ጥናት፡-
Calendario escolar de MCPS 2024 - 2025 Comentarios
MCPS 校歷 2024 - 2025 年反饋
MCPS 학교 일정 2024 - 2025 피드백
Calendrier scolaire de MCPS 2024-2025
Calendário Escolar MCPS 2024 - 2025
Phản hồi về Lịch học MCPS 2024 - 2025
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ትምህርት ቤት የቀን መቁጠሪያ 2024 - 2025 ግብረመልስ
ቦርዱ በሶስት ፖሊሲዎች ላይ የህዝብ አስተያየት ይፈልጋል
የትምህርት ቦርድ በሶስት ፖሊሲዎች ላይ በቀረቡት የማሻሻያ ሃሳቦች አስተያየት እንዲሰጥባቸው ይፈልጋል፦
ፖሊሲ ABC፣ የወላጅ እና የቤተሰብ ተሳትፎ
ፖሊሲ BLB፣ በይግባኝ የችሎት ሂደት ላይ ያሉ የአሰራር ህጎች
ፖሊሲ IJA፣ በትምህርት ቤቶች የካውንስሊንግ/የምክር አገልግሎት ፕሮግራሞች እና አገልግሎቶች
የቋንቋ ትርጉም ይኖራል።
የፖሊሲ ABC ረቂቅ ማሻሻያዎች ከፌብሩዋሪ 9, 2023 ጀምሮ ለአስተያየት የቀረበ ሲሆን የአስተያየት መስጫው ጊዜ ሴፕቴምበር 18 ይዘጋል። የቦርዱ የፖሊሲ አስተዳደር ኮሚቴ ኦክቶበር 10, 2023 በሚያካሂደው ስብሰባ ላይ የህዝብ አስተያየቶችን ለመገምገም የጊዜ ቀጠሮ ተይዞለታል።
የፖሊሲ BLB ረቂቅ ማሻሻያዎች ከጁላይ 7, 2023 ጀምሮ አስተያየት እንዲሰጥበት ቀርቧል፥ እና የአስተያየት መስጫው ጊዜ ሴፕቴምበር 18, 2023 ይዘጋል። የቦርዱ የፖሊሲ አስተዳደር ኮሚቴ ኦክቶበር 10, 2023 በሚያካሂደው ስብሰባ ላይ የህዝብ አስተያየቶችን ለመገምገም የጊዜ ቀጠሮ ተይዞለታል።
የፖሊሲ IJA ረቂቅ ማሻሻያዎች ከአፕሪል 26, 2023 ጀምሮ ለአስተያየት ይቀርባል፣ እና የአስተያየት መስጫው ጊዜ ኖቬምበር 6, 2023 ላይ ይዘጋል። የቦርዱ የፖሊሲ አስተዳደር ኮሚቴ ዲሴምበር 14, 2023 ስብሰባ ላይ የሕዝብ አስተያየቶችን ለመገምገም የጊዜ ቀጠሮ ተይዞለታል።
የማሻሻያዎቹ መግለጫ፣ ረቂቅ ማሻሻያዎች እና የህዝብ አስተያየት መጠይቆች ይፋዊ አስተያየት መስጫ ገጽ ላይ ይገኛሉ።
መልካም ዜና
የአመራር ማሰልጠኛ ተቋም 30ኛ አመት ሞላው!
በጆን ኤፍ ኬኔዲ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የአመራር ማሰልጠኛ ተቋም (LTI) ተማሪዎችን በተሞክሮ ትምህርት፣ በማህበረሰብ አገልግሎት ፕሮጀክቶች እና በአመራር ፅንሰ-ሀሳብ እና አተገባበር ላይ አፅንዖት በመስጠት በጠንካራ የዲሲፕሊን ትምህርት ተማሪዎችን ያቀዳጃል። LTI የቀድሞ ተማሪዎች እና ጓደኞች ስለ LTI ትዝታዎቻቸውን እንዲያካፍሉ እና የፕሮግራሙን 30ኛ-ዓመት በዓል ለማክበር ለኦክቶበር 6 ተጋብዘዋል። ዝግጅቱ በሞንትጎመሪ ካንትሪ ክለብ/Montgomery Country Club 6–8:30 p.m. ይካሄዳል።
ለበለጠ መረጃ የዝግጅት ገጹን ይመልከቱ።
የብሪግስ ቼኒ መለስተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በትምህርት አመቱ በአስደሳች ጅምር እየተደሰተ ይገኛል
ተማሪዎች በዚህ አመት ወደ ትምህርት ቤት የመመለስ ምሽት ላይ MCPS የምግብ እና ስነ-አመጋገብ አገልግሎት መምሪያ (DFNS) ያዘጋጃቸው ምግቦችን የመቅመስ እድል አግኝተዋል። የምግብ ዝርዝር ለውጥ ለማድረግ DFNS የምግብ ቅምሻ ግብረ መልሶችን ይጠቀማል።
የተማሪ አትሌቶች የትምህርት ዓመቱን ከዲስትሪክት መሪዎች ጋር ጀምረዋል
አመታዊ የተማሪ-አትሌት አመራር ካውንስል (SLC) የማስጀመር ስብሰባ ሴፕቴምበር 12 በሮክቪል ካርቨር የትምህርት አገልግሎት ማዕከል ተካሄዷል። SALC ከሁሉም MCPS ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በተወጣጡ አባላት እና ሰባት ትላልቅ አባላትን ያቀፈ ሲሆን በየሁለት ወሩ በሚሰበሰቡ በኢንተር-ስኮላስቲክ የአትሌቲክስ መርሃ ግብር ላይ ሃሳቦችን ይለዋወጣሉ።
ኢሜል ይላኩልን: ASKMCPS@mcpsmd.org