መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች

ሀሙስ ሜይ 2/2024

የጌትስበርግ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህርት የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የአመቱን ምርጥ መምህርነት አሸናፊ ሆነዋል 

ሜሊሳ ፖርተር ፓርክስ/Melissa Porter Parks፣ በጌትስበርግ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የእንግሊዘኛ ቋንቋ ማዳበር ሪሶርስ መምህርት፣ 2024–2025 የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የአመቱን የምርጥ መምህርነት ስያሜ ያገኙት ሜይ 1 ቀን 2010 ዓ.ም ነው። ከዚህ በመቀጠል ለሜሪላንድ የአመቱ ምርጥ መምህርነት ይወዳደራሉ። በተጨማሪም በዓመታዊው የህፃናት ሻምፒዮንሺፕ ዝግጅት ወቅት፣በሚል ክሪክ ታወን አንደኛ ደረጃ ት/ቤት የህንፃ አገልግሎት ስራ አስኪያጅ ብሩኖ ስሚዝ/Bruno Smith፣የአመቱ ምርጥ የድጋፍ ሰጪ አገልግሎት ሰራተኛ ስያሜ አግኝተዋል። ይበልጥ ያንብቡ.

የዝግጅቱን ቀጥታ ስርጭት ይመልከቱ


ሜይ 6 እስከ 10 የመምህራን የምስጋና ሳምንት ነው!

MCPS በተማሪዎቻችን ህይወት ላይ አስደናቂ ተጽእኖ የፈጠሩትን አስተማሪዎች ማክበር ይፈልጋል። የአስተማሪ ሚና በጣም አስፈላጊ እና ፈታኝ ከሆኑ ስራዎች አንዱ ነው፥ እናም ታታሪነታቸው እና ትጉህነታቸው ሊደነቅ ይገባል። በሚቀጥለው ሳምንት አስተማሪዎቻችንን "እናመሰግናለን" ስለምንላቸው ከእኛ ጋር ይቀላቀሉን። ስለዚህ አመት የአመቱ ምርጥ መምህር አሸናፊ የበለጠ ለማወቅ ይህን ቪዲዮ ይመልከቱ። 


2024 የምረቃ መርሃ ግብር በይነመረብ ላይ ይገኛል 

የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመክፈቻ ስነስርዓቶች እሮብ፣ ሜይ 29 እና እሮብ፣ ጁን 12 መካከል ይከናወናሉ። በተናጠል የሚደረጉት የምረቃ ሥነ-ሥርዓቶች በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ካምፓሶች፣ በዋሽንግተን ዲሲ DAR ኮንስቲትዩሽን አዳራሽ፣ እና በማውንት ሴንት ሜሪ ዩንቨርስቲ ካምፓስ፣ እንዲሁም በዩንቨርስቲ ኦቭ ሜሪላንድ ባልቲሞር ካውንቲ ይካሄዳሉ።

ለእያንዳንዱ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የምረቃ ቀን፣ ቦታ፣እና ሰዓት ለማወቅ እዚህ ጠቅ ያድርጉ


በልዩ ትምህርት መርጃ/ሪሶርስ አውደ ርእይ ላይ ይሳተፉ 

ቅዳሜ፣ ሜይ 11 በሞንትጎመሪ ብሌየር ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የዚህ አመት የልዩ ትምህርት የቤተሰብ መገልገያ አውደ ርዕይ እንዳያመልጥዎት። የነጻ ዝግጅቱ የሚካሄደው ከጠዋቱ 10፡00 a.m. እስከ 1፡00 p.m., ሲሆን ለሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ወላጆች፣ ሰራተኞች እና የማህበረሰብ አባላት ክፍት ነው። አውደ ርዕዩ ከተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች እና አቅራቢዎች የተገኙ ጠቃሚ ግብአቶችን እና አዝናኝ የልጆች እንቅስቃሴዎችን፣ ጨረቃ ስትወጣ፣ ሙዚቃ፣ ኪነ ጥበብ፣ እና የትላልቅ ፊኛ/ባሉን አርቲስቶችን ያካትታል። 

ሞንትጎመሪ ብሌር በሚከተለው አድራሻ ይገኛል፦ Montgomery Blair is located at 51 University Blvd. ሲልቨር ስፕሪንግ በስተምስራቅ East in Silver Spring.

ስለ ልዩ ትምህርት የቤተሰብ መገልገያዎች/ሪሶርስ አውደ ርእይ 2024


ሜይ 14 ከትምህርት ቤት ውጭ በነፃ የሚካሄድ ክፍለጊዜ "Coed Football Clinic"

ከ1ኛ እስከ 8ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች ማክሰኞ፣ ሜይ 14 ከትምህርት ሲቀሩ ጠዋት 10፡30 a.m. እስከ 3፡30 p.m. ወደ "coed football clinic" ዝግጅት በነጻ እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል። ክሊኒኩ የሚስተናገደው 480 Club ከሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ጋር በመተባበር በተዘጋጀ ከትምህርት-ቀን-ውጭ በሚካሄድ ፕሮግራም በጌትስበርግ "Laytonia Turf Field" መስክ ላይ ነው። በዝግጅቱ ላይ ምግብ የሚያቀርቡ መኪናዎች፣ ዲጄ፣ ልዩ እንግዶች፣ የአውቶግራፍ ክፍለ ጊዜዎች እና የፎተግራፍ ስፍራዎች ይኖሩታል። 

በክፍል ደረጃ የተዘጋጁ ክፍለ-ጊዜዎች፦ 

1ኛ እስከ 5ኛ ክፍል: 10:30 a.m.-12:30 p.m.
6ኛ እስከ 8ኛ ክፍል: 1:30- 3:30 p.m.

ለአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች እዚህ ይመዝገቡ/RSVP here

ለመካከለኛ ደረጃ ተማሪዎች እዚህ ይመዝገቡ/RSVP here። 

ዝግጅቱ የሚካሄደው በሚከተለው አድራሻ ነው፦ Laytonia Turf Field is located at 7300 Airpark Road in Gaithersburg.


ለመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ነፃ የሠመር ኮዲንግ ትምህርት ይሰጣል።

ሞንትጎመሪ ካን ኮድ የሠመር ካምፕ "Montgomery Can Code’s summer camp" ለሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) 6ኛ፣7ኛ፣ እና 8ኛ ክፍል ተማሪዎች ለአንድ ሳምንት የሚካሄድ ካምፕ ነው። በካምፑ ውስጥ የሚቆዩ ተሳታፊዎች ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ መተግበሪያዎችን ለመፍጠር ፕሮፌሽናል አልሚዎች በሚጠቀሙት ለመረዳት ቀላል በሆነው አፕል ስዊፍት ኮድ ማድረግን ይማራሉ። 

እዚህ ይመዝገቡ ወይም ተማሪዎች የትምህርት ቤታቸውን ካውንስለር ማነጋገር ይችላሉ።


የትምህርት ቤት የምግብ ሰራተኞች አድናቆት ሳምንት 

MCPS ለትምህርት ቤቶች የምግብ ዝግጅት ሰራተኞች አድናቆት ኤፕሪል 29 ጀምሮ እስከ ሜይ 3 ድረስ፣ በ 211 ትምህርት ቤቶች በየቀኑ ከ 90,000 በላይ ምግብ ለሚያቀርቡ ከ 800 በላይ የምግብ እና የተመጣጠነ አመጋገብ አገልግሎት ሰራተኞችን በማመስገን እውቅና ይሰጣል። በተጨማሪ ግንዛቤ ያግኙ. 


ተማሪዎችን ለኮሌጅ እና ለስራ ማዘጋጀት

የአልበርት አንስታይን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በዚህ ስፕሪንግ መጀመሪያ ላይ ሁለተኛውን ዓመታዊ የስራ ቀን አካሄዷል። ይህ ዝግጅት ለኮሌጅ እና ለስራ ዝግጁ ለመሆን ተማሪዎች ከተሳተፉባቸው እና ከስራ ባለሙያዎች መማር ከሚችሉባቸው በርካታ መንገዶች አንዱ ነው። እነዚህ እድሎች MCPS ስልታዊ/ስትራቴጄክ እቅድብቻ ሳይሆን የሜሪላንድ የወደፊት ብሉፕሪንት ድንጋጌንም ይደግፋሉ። የበለጠ ለማወቅ የሜሪላንድ ብሉፕሪንት ድረ ገጽ ይጎብኙ። 


የስፕሪንግ ወቅት የወላጅ አካዳሚ መርሃ ግብር 

"Parent Academy TO GO" ቤተሰቦች በትምህርት ዓመቱ በሙሉ በተሳትፎ መቀጠል ይችላሉ። የወላጅ አካዳሚ ቱ ጎ "Parent Academy " የተነደፈው ቤተሰቦች በልጆቻቸው ትምህርት እንደ ደጋፊ እና አጋሮች መሆናቸውን ለማሳወቅ እና ለማበረታታት ነው። ይበልጥ ያንብቡ 

ቀጣይ ርዕሶች፦ ንቁ ወላጅነት አሁን! (ተከታታይ)፣ አዎንታዊ ዲስፕሊን፣ ናርካን/Narcan ምንድን ነው? እና ሌሎች ጉዳዮችንም ያካትታል።

ቀኖቹን ለማወቅ የወላጅ አካዳሚ ድረ ገጽ ይጎብኙ። 

ለመመዝገብ እዚህ ይክፈቱ።


የቤተሰብ መዝናኛ፣ እና የትራፊክ እና የእግረኛ ደህንነት መረጃ የሚናኝበት የደህንነት ቀን 

ቅዳሜ፣ ሜይ 11 -- Carver Educational Services Center (CESC) parking lot at 850 Hungerford Drive in Rockville -- በሚካሄደው የደህንነት ቀን ላይ እንዲገኙ ሁሉም ቤተሰቦች ተጋብዘዋል። "በደህንነት ቀን" ህብረተሰቡ በመዝናናት እና በበዓል ቀናት ስለ ትራፊክ ደህንነት የበለጠ ጥንቃቄ ስለማድረግ ለማወቅና መረጃ ለማሠራጨት በአንድ ላይ ይሰበሰባል። ይበልጥ ያንብቡ 


የጌትስበርግ መፅሀፍት ፌስቲቫል/አውደርዕይ ሜይ 18 እንዳያመልጥዎት ያስታውሱ

የጌትስበርግ መፅሀፍት ፌስቲቫል/አውደርዕይ ፣ የመፅሀፍት፣ የፀሀፊዎች እና የስነ-ፅሁፍ ልህቀት ክብረ በአል፣ቅዳሜ፣ ሜይ 18 ከጠዋት 10 a.m. እስከ ከሰአት 6 p.m. ይካሄዳል። አድራሻው፦ Bohrer Park, 506 S. Frederick Avenue, Gaithersburg በዚህ አመት ከሚገኙት ደራሲያን መካከል የዋትኪንስ ሚል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አስተማሪ ሳራ ጉድማን ኮንፊኖን/Sara Goodman Confino ይገኙበታል። ይበልጥ ያንብቡ


MCPS የፈረንሳይኛ ኢመርሽን ፕሮግራም 50 አመት ሞልቶታል

MCPS የፈረንሳይኛ ኢመርሽን ፕሮግራም ኤፕሪል 27 በዋልት ዊትማን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በተደረገ ዝግጅት 50ኛ አመቱን አክብሯል። የፈረንሣይኛ ኢመርሽን ፕሮግራም በቀድሞው ፎርኮርነር አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተጀመረ ሲሆን ከዚያ ጊዜ ጀምሮ እያደገ መጥቷል። አሁን MCPS ውስጥ አንደኛ ደረጃ—ሜሪቫሌ እና ስላይጎ ክሪክ ሁለት ትምህርት ቤቶች፣ እና ሁለት በመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች—ጌትስበርግ እና ሲልቨር ስፕሪንግ ኢንተርናሽናል የሚካሄዱ ፕሮግራሞች አሉ። MCPS የሚያካሄደው ፕሮግራም በመላ አገሪቱ ላሉ የኢመርሽን ፕሮግራሞች እንደ ሞዴል ማነቃቂነት ያገለግላል። የፎተግራፎችን ክምችት ይመልከቱ


መታወስ ያለባቸዉ ቀኖች፦



ኢሜል ይላኩልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS)