ጉዞ ወደ ምረቃ 2024፡ ጠንክሮ መስራት ዋጋ ያስከብራል
ኤድና ሬይስ/Edna Reyes የተባለች የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪ ባደረገችው ትምህርታዊ ጉዞ ወደ ፍጻሜው ስትደርስ በአንድ ጊዜ ሶስት ፕሮግራሞችን በተሳካ ሁኔታ አጠናቃለች። ሬየስ/Reyes በቅርቡ የሁለተኛ ደረጃ ዲፕሎማዋን ከአካባቢዋ የደማስከስ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ያገኘች የሳልቫዶርያን ዝርያ የመጀመሪያ ትውልድ ተማሪ ነች። በተጨማሪ በጌትስበርግ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ጥብቅ የሶስት አመት የኮስሞቶሎጂ መርሃ ግብር በተሳካ ሁኔታ አጠናቃለች፣ ከሞንትጎመሪ ኮሌጅ የአሶሺየት ዲግሪ ለማግኘት የሚያስፈልጉትን በሁለት የምዝገባ መርሃ ግብሮች አጠናቃለች፣ እንዲሁም በታዋቂው የሜሪላንድ የብዝሃ ቋንቋ ፕሮግራም ተመርቃለች። ይበልጥ ያንብቡ
ሬየስ/Reyes በዚህ የምረቃ ሰሞን የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ዲፕሎማቸውን ከሚቀበሉ ከ12,000 በላይ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች አንዷ ናት።
በሚቀጥለው ዌቢናር ስለ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ፕሮግራሞች ግንዛቤ እንዲያገኙ ለሁሉም የመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ያሏቸው ቤተሰቦች ጥሪ እናደርጋለን።
በቅርቡ ወደ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ለሚቀላቀለው (ለምትቀላቀለው) ተማሪዎ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ፕሮግራም አማራጮች የበለጠ ለማወቅ ፍላጎት አለዎት? እነዚህን ፕሮግራሞች የት እና እንዴት ማግኘት እንደሚችሉ ጥያቄዎች አሉዎት? ረቡዕ፣ ጁን 12 ቀን 6 p.m. MCPS የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ፕሮግራም ዌብናራ/Webinar ይቀላቀሉን። የላቀ ምደባ/ዓለም አቀፍ ባካሎሬት፣ የሙያ እና የቴክኒክ ትምህርት (CTE)፣ ጣምራ ምዝገባ፣ የሙያ ምክር፣ በሥራ ላይ የተመሰረተ ትምህርትና ልምድ እና ሪጅናል/ካውንቲ አቀፍ ፕሮግራሞችን በሚመለከት ከፕሮግራም ሱፐርቫይዘሮች ያዳምጡ።
በተቻለ ፍጥነት መረጃ ማግኘት የተማሪዎን የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ሽግግር ለማዘጋጀት ምርጡ የመጀመሪያ እርምጃ ነው። ለዌቢናር እዚህ ይመዝገቡ። የዌቢናር ማገናኛ ዝግጅቱ ከሚካሄድበት ቀን በፊት እናጋራለን።
የሠመር ትምህርት ቤት ክፍያ እና የሁለተኛ ፈረቃ ምዝገባ ማሳሰቢያ
ለአንደኛ ፈረቃ ሪጅናል የሠመር ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ፕሮግራም (በአካል) እና የሴንትራል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሠመር ፕሮግራም (ቨርቹዋል) ክፍያዎች መፈፀም መጠናቀቅ ያለባቸው ጁን 16 ነው። እስከ ጁን 16 ድረስ ክፍያ ካልተጠናቀቀ ተማሪ ከትምህርቱ ይቋረጣል። የመጀመሪያው ዙር ከጁን 26 እስከ ጁላይ 16 ይካሄዳል (ጁላይ 4 ትምህርት የለም)፣ ሁለተኛው ዙር ከጁላይ 18 እስከ ኦገስት 6 የሚካሄድ ሲሆን 6. የሚካሄድ ሲሆን የሁለተኛው ክፍለጊዜ ምዝገባ እሁድ፣ ጁን 30 ይዘጋል። ወላጆች ተማሪዎቻቸውን ParentVue አካውንታቸው ላይ ማስመዝገብ ይችላሉ። ለሠመር ትምህርት ከተመዘገቡ በኋላ የክፍያ መጠየቂያው ሠነድ ካልደረሰዎት፣ እባክዎ የተማሪዎን ካውንስለር ያነጋግሩ። እዚህ ይበልጥ ያንብቡ.
ለዓመታዊው ወደ ትምህርት ቤት የመመለስ ትርዒት የቀን መቁጠሪያዎን ምልክት ያድርጉ
MCPS ዓመታዊውን ወደ ትምህርት ቤት የመመለስ ትርዒት ቅዳሜ፣ ኦገስት 24 ቀን 10፡00 a.m. እስከ 1 p.m. በዊተን ዌስትፊልድ የገበያ ማዕከል/Westfield Wheaton mall ያስተናግዳል። ዝግጅቱ ቤተሰቦች ስለ ትምህርት ቤቶች ስርዓትአቀፍ መረጃ እና የካውንቲ ፕሮግራሞችን እና አገልግሎቶችን እንዲያውቁ ጥሩ አጋጣሚ ነው። በሙዚቃ፣ በመዝናኛ ፕሮግራሞች፣ በስጦታ እና በቤተሰብ እንቅስቃሴዎች ይደሰቱ። ክትባት የሚሰጥበትም ክሊኒክ ይኖራል ነፃ የመጓጓዣ አውቶቡስ ይኖራል።
አድራሻ፦ Westfield Wheaton is located at 11160 Veirs Mill Road. በሠመር ወቅት በሙሉ ወቅታዊ ጉዳዮችን ለማግኘት ድረ-ገጻችንን ጋር ይከታተሉ።
ሃያ ሁለት የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች የኮሌጅ ብሄራዊ የብቃት ስኮላርሺፕ አግኝተዋል።
22 የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች ከብሔራዊ የሜሬት ስኮላርሺፕ ኮርፖሬሽን በመጨረሻው ዙር ሽልማቶች የኮሌጅ እና የዩኒቨርሲቲ ብሄራዊ የብቃት ስኮላርሺፕ አግኝተዋል። እነዚህ ሽልማቶች ስኮላርሺፕ በሚሰጥ ተቋም ውስጥ እስከ አራት ዓመት ለሚደርስ የቅድመ ምረቃ ጥናት በየዓመቱ $500 እና $2,000 መካከል ይሰጣሉ።
አሸናፊዎችን፣ ስፖንሰር የሚያደርጉትን ዩኒቨርሲቲ ወይም ኮሌጅ፣ እና የታቀዱትን የስራ መስኮች ይመልከቱ።
"GIVE Backpacks" ዘመቻ እየተካሄደ ስለሆነ ዛሬውኑ ይለግሱ
13ኛው አመታዊ GIVE BACKpacks ዘመቻ በመካሄድ ላይ ስለሆነ፥ ለሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች በጀርባ የሚያዝ የደብተር/የመጻህፍት ቦርሳዎችን እና የት/ቤት ቁሳቁሶችን በመግዛት የተቸገሩ ተማሪዎችን እርዷቸው። እስከ $20 ድረስ ወጪ በማድረግ ወረቀቶችን፣ እርሳሶችን፣ ከለሮች/ እስክሪብቶዎች፣ የእርሳስ መቅረጫ፣ መያዣዎች እና የትምህርት መጻፍት ማህደሮችን ጨምሮ በትምህርት ቁሳቁሶች የታጨቀ ቦርሳ ለተማሪ ማበርከት ይችላሉ።
በቀጥታ ወደ ዋናው ነጥብ፡ የከባቢ ትምህርት
ስለ MCPS የካባቢ ትምህርት ፕሮግራም የበለጠ ለማወቅ እና ከፕሮግራሙ መምህራን እና የእንስሳት መብት አምባሳደሮች ጋር ለመገናኘት በቅርቡ የተዘጋጀውን "To the Point" ይመልከቱ።
የስፖርት ውድድሮች ግንዛቤ ክፍል 33 - የካውንቲ ሻምፒዮናዎች
የስፖርታዊ ጨዋነት የቅርብ ጊዜ ትዕይንት በካውንቲ ሻምፒዮና ጨዋታዎች ተመልካቾችን እና የተለያዩ ድምጾችን ያደምቃል፣ እና ከተጫዋቾች እና ከአሰልጣኞች ጋር በመደበኛው የውድድር አመት እና በሌሎች የድህረ ውድድር ጨዋታዎች መካከል ስላለው ተጨማሪ ጨዋታ ምን እንደሚያስቡ ያሳያል።
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ዘገባዎች
NBC 4 የዋሽንግተን የሴቶች "flag football" እግር ኳስ በሚቀጥለው አመት ወደ MCPS ይመጣል
መታወስ ያለባቸዉ ቀኖች፦
ተጨማሪ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) መረጃዎች
ኢሜል ይላኩልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org