መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች

ሐሙስ፥ ጁን 13፣ 2024

ስለተጠናቀቀው አስደናቂ 2023-2024 የትምህርት አመት እንኳን ደስ አላችሁ!

ሁላችሁም እንኳን ደስ አላችሁ፣ አደረግነው! ዛሬ 2023-2024 የትምህርት አመት የመጨረሻው የትምህርት ቀን ነው። አሁን ወደ ጁን ወር መጨረሻ እየተቃረብን ስለሆነ፣ በዚህ የስፕሪንግ ወቅት በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ከእናንተ ጋር ስላሳለፍኩት ጊዜ ጥቂት ለማንፀባረቅ እፈልጋለሁ። ከጊዜያዊ ሱፐር ኢንተንደንት ዶ/ር ፌልደር የተላለፈ ሙሉውን መልእክት ያንብቡ።


የምረቃ ጉዞ፦ 2024 የተመራቂዎች ታሪክ 

  • የዊንስተን ቸርችል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመራቂ ካሮላይን በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመጀመሪያዎቹ ሁለት ዓመታት ከአእምሮ ጤንነቷ ጋር ስትታገል አሳልፋለች። ለማደግ የምትፈልገውን ድጋፍ ለመስጠት የትምህርት ቤቷ ማህበረሰብ እና ቤተሰቧ እንዴት እንደተረባረቡላት ካሮሊን ትናገራለች።
    የካሮሊንን ታሪክ ይመልከቱ

  • የዋትኪንስ ሚል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመራቂ ሚሼል ለመመረቅ ጉዞዋን የጀመረችው12 ዓመቷ ላይ ዩ.ኤ.ስ እንደደረሰች ነበር። አዲስ ቋንቋ፣ አዲስ ባህል፣ እና አዲስ የትምህርት ሥርዓት ስትማር እና ስትለማመድ ብዙ ተግዳሮቶች አጋጥሟታል።
    የሚሼልን ታሪክ ይመልከቱ

  • ኤድና የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ዲፕሎማዋን ያገኘችው በአካባቢዋ ከሚገኘው ከደማስከስ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ነው፣ በጌትስበርግ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ጥብቅ የሶስት አመት የኮስሞቶሎጂ መርሃ ግብር እና ከሞንትጎመሪ ኮሌጅ በባህሪ ጤና ላይ አሶሽየት ዲግሪ ለማግኘት የሚያስፈልጉትን መስፈርቶች በሙሉ በተሳካ ሁኔታ አጠናቃለች።
    የኤድናን ታሪክ ይመልከቱ


የትምህርት ቦርድ ለ2025 የበጀት ዓመት 3.32 ቢሊዮን ዶላር የሥራ ማስኬጃ በጀት አፅድቋል።

የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ ጁን 11 ባደረገው ስብሰባ ለ 2025 የበጀት ዓመት $3.32 ቢሊየን ዶላር የስራ ማስኬጃ በጀት በሥራ ላይ እንዲውል አፅድቋል። ይህም ካለፈው አመት የሥራ ማስኬጃ ባጀት $147 ሚሊዮን ዶላር ወይም 4.6 በመቶ ጭማሪ ያሳያል። ምንም እንኳን የጸደቀው በጀት ለሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ከፍተኛ ጥራት ያለው የመማር ማስተማር ክንውን ከፍተኛ ብቃት ያላቸው ሰራተኞችን ይዞ ለመቀጠል የሚብቃቃ ቢሆንም፤ 2024 ለተመሳሳይ አገልግሎት በሥራ ላይ ከዋለው በጀት $30 ሚሊዮን ዶላር ቅናሽ ያሳያል። ይበልጥ ያንብቡ

  • በመማሪያ ክፍል የተማሪዎች ቁጥር መጨመርን መረዳት - ለቀጣዩ የትምህርት አመት በብዙ ክፍሎች ውስጥ የመማሪያ ክፍል በአንድ ተማሪ ይጨምራል። ይበልጥ ያንብቡ.

  • በ 2025 የቅድመ መዋዕለ ሕጻናት መስፋፋት እንደሚዘገይ መረዳት - MCPS በቅድመ-መዋእለ ህጻናት ፕሮግራም 520 መቀመጫዎችን ከትርፍ ሰዓት ወደ ሙሉ ቀን ለመቀየር የነበረውን እቅድ ያዘገያል። እዚህ ይበልጥ ያንብቡ.


በዚህ ሠመር ለልምምድ፣ለመዘጋጀት እና ለክለሳ ነፃ የኦንላይን ሪሶርሶች/መርጃዎች አሉ።

ነጻ የኦንላይን መርጃዎች/ሪሶርሶች በሠመር ትምህርት የማስጠናት ፕሮግራም ወይም በሠመር ትምህርት ቤት ለማይሳተፉ ተማሪዎች ድጋፍ ይሰጣል። ይህ ሰነድ 2024–2025 የትምህርት አመት ነፃ የትምህርት መርጃዎችን እና የአንደኛ ደረጃ፣ መካከለኛ ደረጃ እና ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች የትምህርት ይዘታቸውን ለመገምገም፣ ችሎታቸውን ለማዳበር መለማመድ እና ለ 2023–2024 የትምህርት ዘመን የሚያዘጋጁ ተግባሮችን ያካትታል።


ሁለት የሠመር ትምህርት ክፍል ምዝገባ ጁን 30 ያበቃል 

ሁለተኛው ክፍለ ጊዜ ሪጅናል የሠመር ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ፕሮግራም (በአካል) እና ሴንትራል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሠመር ፕሮግራም (ቨርቹዋል) ከጁላይ 18–ኦገስት 6 የሚካሄድ ሲሆን፥ የሁለተኛው ፈረቃ ምዝገባ እሑድ፣ ጁን 30 ይዘጋል። ወላጆች ተማሪዎቻቸውን ParentVue አካውንታቸው ላይ ማስመዝገብ ይችላሉ። ለሠመር ትምህርት ከተመዘገቡ በኋላ የክፍያ መጠየቂያው ሠነድ ካልደረሰዎት፣ እባክዎ የተማሪዎን ካውንስለር ያነጋግሩ። እዚህ ይበልጥ ያንብቡ


ለዓመታዊው ወደ ትምህርት ቤት የመመለስ ትርዒት የቀን መቁጠሪያዎን ምልክት ያድርጉ

MCPS ዓመታዊውን ወደ ትምህርት ቤት የመመለስ ትርዒት ቅዳሜ፣ ኦገስት 24 ቀን 10፡00 a.m. እስከ 1 p.m. በዊተን ዌስትፊልድ የገበያ ማዕከል/Westfield Wheaton mall ያስተናግዳል። ዝግጅቱ ቤተሰቦች ስለ ትምህርት ቤት ስርዓት እና ስለ ካውንቲ ፕሮግራሞችና አገልግሎቶች እንዲያውቁ ጥሩ አጋጣሚ ነው። በቤተሰብ እንቅስቃሴዎች፣ በሙዚቃ፣ በመዝናኛ ዝግጅቶች ይደሰታሉ፤ስጦታዎችን ያገኛሉ። ክትባት የሚሰጥበትም ክሊኒክ ይኖራል ነፃ የመጓጓዣ አውቶቡስ ይኖራል።

አድራሻ፦ Westfield Wheaton is located at 11160 Veirs Mill Road. በሠመር ወቅት በሙሉ ወቅታዊ ጉዳዮችን ለማግኘት ድረ-ገጻችንን ጋር ይከታተሉ።


በሠመር ወቅት ግንኙነትዎን ይቀጥሉ!


"GIVE Backpacks" ዘመቻ እየተካሄደ ስለሆነ ዛሬውኑ ይለግሱ

13ኛው አመታዊ GIVE BACKpacks ዘመቻ በመካሄድ ላይ ስለሆነ፥ ለሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች በጀርባ የሚያዝ የደብተር/የመጻህፍት ቦርሳዎችን እና የት/ቤት ቁሳቁሶችን በመግዛት የተቸገሩ ተማሪዎችን እርዷቸው። እስከ $20 ዶላር ቢለግሱ፣ ወረቀት፣ እርሳሶች፣ ከለሮች/ እስክሪብቶዎች፣ የእርሳስ መቅረጫ፣ የወረቀት መያዣ ባይንደሮችን፣ ፎልደሮችን፣ እና ሌሎችንም አስፈላጊ የትምህርት እቃዎችን ጨምሮ የታጨቀ ቦርሳ ለሚያስፈልጋቸው ተማሪዎች መስጠት ይችላሉ።


የኢኖቬቲቭ ትምህርት ቤቶች የመጀመሪያ የትምህርት ቀን 

በሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) አንዱ የአርኮላ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አንድ ኢኖቬቲቭ የቀን መቁጠሪያ የሚከተል ትምህርት ቤት የትምህርት መጀመሪያ ቀን ሰኞ፣ ጁላይ 10, 2024 ይሆናል። 

ለጥያቄ ትምህርት ቤቱን በቀጥታ ያነጋግሩ፦ 

አርኮላ ኤለመንተሪ ት/ቤት = Arcola ES: 301-287-8585


መልካም ዜና

ባለፈው ሳምንት በተካሄደው የሴቶች ፍላግ ፉትቦል ክህሎት ክሊኒኮች ላይ በመቶዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች ተገኝተዋል። MCPS በመጪው ፎል 2024 የውድድር ወቅት በሁሉም 25 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ከባልቲሞር ሬቨንስ እና አንደር አርመር ጋር በመተባበር የልጃገረዶች ፍላግ ፉት ቦል ልምምድ ያደርጋል። 


ፋውንዴሽን በጃክሰን ሮድ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አዲስ የልጆች ቁጠባ ፕሮግራም ጀምሯል

የጃክሰን ሮድ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በሜሪላንድ ውስጥ የግሬተር ዋሽንግተን ማህበረሰብ ፋውንዴሽን "ብሪሊየንት ፊውቸርስ ፕሮግራም" ለማካሄድ የመጀመሪያው ትምህርት ቤት ነው። "Brilliant Futures" የልጆች ቁጠባ ፓይለት ፕሮግራም ሲሆን ለመዋዕለ ሕፃናት ተማሪዎች በየዓመቱ ከመዋዕለ ሕፃናት እስከ 12ኛ ክፍል እስከ $1,000 ተቀማጭ ያደርጋል። ይበልጥ ያንብቡ 


የደማስከስ ተማሪዎች፣ATF፣በቤተሰብ-ባለቤትነት የሚመራ ኩባንያ ለአካባቢው ቤተሰብ መኪና ለግሰዋል

የደማስከስ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች፣ የአውቶሞቲቭ ትሬድ ፋውንዴሽን (ATF)፣ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ (MCPS) ሰራተኞች፣ እና የማህበረሰብ አባላት 2020 Kia Soul በመለገስ የተቸገረን ቤተሰብ ለመደገፍ ተሰብስበው ነበር። ይበልጥ ያንብቡ 


በሠመር ወቅት በካውንቲው ውስጥ ያሉ እድሎች 

  • የሞንትጎመሪ ካውንቲ የህዝብ ቤተ መፃህፍት የሠመር የማንበብ ፉክክር ልጆች እና ታዳጊ ወጣቶች የሠመር እረፍት ጊዜያቸውን ምርጥ መጽሃፎችን በማንበብ እና አዝናኝ እንቅስቃሴዎችን እያዘወተሩ እንዲያሳልፉ እድል ይሰጣል። ከ 0 ክፍል እስከ 12ኛ ክፍል ያሉ ልጆች በሠመር ወቅት በሙሉ የሚጠቀሙበት ኢ-ባጅ ( e-badges) ማግኘት ይችላሉ። የዋሽንግተን ናሽናልስ MCPL ለሠመር ምንባብ ፉክክር ባጅ 2 ያገኙ ተሳታፊዎች በመደበኛ የጨዋታ ወቅት ላይ መጠቀም የሚችሉት ለሁለት የሚሆን ቫውቸር ይሰጣል። አቅርቦቶቹ እስካሉ ደረስ ቫውቸሮች ይገኛሉ። ተጨማሪ መረጃ


መታወስ ያለባቸዉ ቀኖች፦

  • ጁን 14 ውጤት መስጫ እና የተርም ማብቂያ እቅድ ዝግጅት
  • ጁን 19 ስርዓት አቀፍ ት/ቤቶች ዝግ የሚሆኑበት ቀን—ትምህርት ቤቶች እና ቢሮዎች ዝግ ይሆናሉ
  • ጁን 24 ሪፖርት ካርዶች ወደ ቤት ይላካሉ


ኢሜል ይላኩልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS)