ውድ የሞንትጎመሪ ካውንቲ የህዝብ ትምህርት ቤቶች ማህበረሰብ፣

በቅርብ ጊዜ የወጡትን የስራ አስፈጻሚ መመሪያዎችን በተመለክተ የወጣው ዜና ለMontgomery County ተማሪዎች የሚሰጠውን የህዝብ ትምህርት አስመልክቶ አንዳንድ ስጋቶችን እና ጥያቄዎችን እንደሚያስነሳ እናውቃለን።

ሁሉም ልጆቻችን ዘርን፣ ጎሳን፣ ጾታዊ ዝንባሌን፣ ፆታን፣ የኢሚግሬሽን ደረጃን/ሁኔታን፣ የአካል ጉዳትን/እክልን፣ ሀይማኖትን ወይም ሌላ መለያ ባህሪን ሳይለይ ሁለቱንም አካዳሚያዊ ልህቀት እና ደህንነትን የሚያበረታታ/የሚያጎለብት ከፍተኛ ጥራት ያለው ትምህርት ይገባቸዋል።  

መማርን፣ ግንኙነቶችን፣ መከባበርን፣ ልህቀትን እና ፍትሃዊነትን የሚያካትቱ የማህበረሰባችን እና የት/ቤታችን ስርዓት እሴቶችን እንደግፋልን። በየእለቱ ይመሩናል እና በአስቸጋሪ ጊዜያት ውስጥ ስንጓዝ አጥብቀው ይይዙናል። እነሱን ለማስቀጠል ሁሉንም ህጋዊ መንገዶች እንጠቀማለን። 

በስርዓተ ትምህርታችን፣ በማስተማር እና በመማር ላይ የአካባቢ ባለስልጣንን ለማስቀጠል ቆርጠን ተነስተናል። እና መምህራኖቻችን እና ሰራተኞቻችን ስርአተ ትምህርታችንን እና ፖሊሲያችንን ተግባራዊ ሲያደርጉ አጥብቀን እንደግፋልን። 

ትምህርት ለሁሉም ልጆች የተሰጠ እና ለህብረተሰባችን መሰረታዊ የሆነ መብት ነው። ጠንካራ እና የበለጸገ የህዝብ ትምህርት ቤት ስርዓት ለህብረተሰባችን፣ ለስቴቶቻችን እና ለሀገር ስኬት፣ ብልጽግና እና የወደፊት ህይወት አስፈላጊ ነው። 

MCPS እና የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ ለእያንዳንዱ ተማሪ ከሁሉም የላቀ ትምህርትን ለመስጠት በተልዕኳችን ላይ ማተኮሩን ይቀጥላል።
 

Julie Yang
የትምህርት ቦርድ ፕሬዚደንት

Thomas W. Taylor, Ed.D., MBA 
Superintendent


ኢሜል ይላኩልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org