ለተከበራችሁ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ማህበረሰብ
ስለ ቻርለስ W. ውድዋርድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እንደገና መከፈት፣ የክራውን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መከፈት እና የደማስከስ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መስፋፋት ላይ ያተኮረ የድንበር ጥናት ተሳትፎ ክፍለ ጊዜዎች ላይ የተገኙትን ሁሉ እናመሰግናለን። እነዚህን ተጨማሪ አዳዲስ ቦታዎችን ማስፋት ማለት ዲስትሪክቱ በርካታ የትምህርት ቤት ድንበሮችን ማዘመን/ማሻሻል ያስፈልገዋል ማለት ነው። እነዚህ ለውጦች መደረግ ያለባቸው አዲሶቹን የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተመጣጣኝ ተማሪዎች እንዲኖራቸው ያደርጋሉ፣ አሁን ባሉት የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ያለውን የተማሪዎች መጨናነቅ ያቃልላሉ፣ እና በወሰን ጥናት ውስጥ በተካተቱት የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች እና መለስተኛ ደረጃ ት/ቤቶች የተሻለ ሚዛናዊ የተማሪዎች ምዝገባ ስለሚኖር — ሁሉም ተማሪዎች የተቻለውን ያክል ተመጣጣኝና ፍትኃዊ የመማር ልምድ እንዲያገኙ ይደረጋል።
በተሳትፎ ክፍለ ጊዜዎቹ ስለ 2027-2028 የትምህርት አመት የታቀዱ የትምህርት ቤት ድንበሮችን በቅድሚያ እንዲያውቁ ግንዛቤ ተሰጥቷል። በእነዚህ ክፍለ-ጊዜዎች ላይ የመጨረሻው የድንበሮች ውሳኔ እንዳልቀረበ ማወቅ አስፈላጊ ነው፤ በዚህ ሂደት ውስጥ የቀረቡት አማራጮች የመጀመሪያው እርምጃ ነው። የድንበር ጥናት ሂደት የሚመራው በቦርድ ፖሊሲ FAA መሠረት በትምህርት ተቋማት እቅድ ነው። ስለ ድንበር ጥናት አማራጭ ምክረሃሳቦች ሲዘጋጁ በዚህ የቦርድ ፖሊሲ ውስጥ የተዘረዘሩት አራት ምክንያቶች ግምት ውስጥ ይገባሉ። እነዚህ አራት ምክንያቶች የሚከተሉትን ያካትታሉ፦
የተማሪ ማህበረሰብ ስብጥር ባህርያት
ጂኦግራፊ
የትምህርት ቤት ምደባዎች የሚቆዩበት ጊዜ
የፋሲሊቲ አጠቃቀም
እነዚህ ስለ ትምህርት ቤት ድንበሮች የሚደረጉ ውይይቶች በብዙ ቤተሰቦች ላይ ተጽእኖ ሊኖራቸው ይችላል። ለዚህም ነው ይህ ሂደት የማህበረሰብን ተሳትፎ ማካተት ያለበት። በጥንቃቄ የታሰበበት፣ በመረጃ ላይ የተመሰረተ ውሳኔዎችን እንድናደርግ እንዲያግዘን የእርስዎ አስተያየት አስፈላጊ—ስለሆነ ከእርስዎ መስማት እንፈልጋለን። በዚህ የበልግ ወቅት (ፎል)፣ በዚህ የማጣሪያ ውይይት ወቅት በሚቀርቡት አማራጮች ላይ ተጨማሪ ግብረመልስ ማግኘት የሚያስፈልገን ክለሳ የተደረገባቸው የድንበር አማራጮች ይቀርባሉ።
እባክዎን ሀሳብዎን ለማጋራት ይህንን የዳሰሳ ጥናት ሞልተው ይመልሱ (ውድዋርድ/Woodward፣ ክራወን እና ደማስከስ/Crown and Damascus)
የሚደረጉት ለውጦች የእርስዎን ተማሪ እንዴት ሊነኩ እንደሚችሉ አሁንም ጥያቄ ወይም ስጋት ሊኖርዎት እንደሚችል እናውቃለን። እናበረታታዎታለን፦
ቨርቹዋል የሚካሄዱበት ሠአቶች:እስከ ጁላይ አጋማሽ ድረስ በየሣምንቱ ማክሰኞ 8-9 A.M፣ ሐሙስ 6-7 P.M፣ እና አርብ 12-1 P.M (በዙም አገናኝ መረብ/ZOOM LINK የስብሰባ መለያ ቁጥር/Meeting ID: 812 8216 እና የመግቢያ ኮድ/Passcode፡ MCPS 3918 and) በመጠቀም ቨርቹዋል ይሳተፉ።
የመጀመሪያዎቹን አማራጮች ይገምግሙ፦ የቻርልስ W. ውድዋርድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የድንበር ጥናት እና የክራውን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መክፈቻ እና የደማስከስ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የድንበር ጥናት፣ የመረጃ ሠንጠረዦችን፣ ካርታዎችን፣ በሥዕል የተዘጋጁ ንድፎችን እና ለእያንዳንዱ አማራጭ ግላጭ የሆነ ካርታ ጭምር የቀረቡትን አማራጮች ይቃኙ።
ይህንን መግለጫ ሰጪ ካርታ ይጠቀሙ፦የድንበር አማራጮቹ በትምህርት ቤትዎ ስራ ላይ ምን አይነት ተጽዕኖ እንደሚኖራቸው ለማየት የቤትዎን አድራሻ አስገብተው ይመልከቱ። (ፈጣን የቪድኦ መመሪያ ውድዋርድ፣ ክራወን እና ደማስከስ)።
ድረገጻችንን ይጎብኙ፦ ዝርዝሩን ይመልከቱ፣የጊዜ ሠሌዳ፣ እና ሪሶርሶች mcpsmd.info/BoundaryStudy የእርስዎ ግብረመልስ በቅርብ ጊዜ የድንበር ጥናት ድረ ገጽ ላይ በሚለጠፍ የተሻሻለ ተደጋጋሚ ጥያቄዎች (FAQs) ውስጥ ይካተታል።
የዳሰሳ ጥናቱን ሞልተው ይመልሱ፦ የዳሰሳ ጥናቶቹ የሚመለከቱት የቻርልስ W. ውድዋርድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የድንበር ጥናት እና የክራውን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መክፈት፣ እና የደማስከስ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የድንበር ጥናት የዳሰሳ ጥናቶቹን የመጀመሪያ አማራጮች ለመገምገም እና ጠቃሚ ግብዓቶችን ለመቃኘት ጊዜ እንዲኖሮት እስከ ጁላይ አጋማሽ ድረስ ክፍት ይሆናል።
ከእርስዎ የምናገኘው ግብአት አስፈላጊ ነው። አለበለዚያ ቁልፍ የሆኑ አስተያየቶች ሊቀሩብን ይችላሉ። የማህበረሰባችን ንቁ ተሳታፊ ስለሆኑ እና የትምህርት ቤቶቻችንን የወደፊት ዕጣ ፈንታ ለማስተካከል ስለሚያደርጉት ትብብር እናመሰግናለን.
በዚህ አድራሻ ኢሜል ያድርጉልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org