Bells Mill የBlue Ribbon Awardን ያከብራል
በU.S. የትምህርት ዲፓርትመንት የሚሰጠው The National Blue Ribbon Award/ሽልማት ትምህርት ቤቶች ላሳዩት የላቀ የአካደሚክ አፈጻጸም እውቅና ይሰጣል። የBells Mill አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሽልማቱን ያገኘው በሁሉም የተማሪ ቡድኖች ውስጥ ጠንካራ ስኬት ያላቸውን ተቋማት አጉልቶ በሚያሳየው በExemplary High-Performing Schools ምድብ/ጎራ ነው። የWoodfield አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤትም የክብር እውቅናን አግኝቷል እና የእውቅና ስነ-ስርዓቱን በጃንዋሪ 2025 ያካሂዳል።
BOE የ2026 ዓ.ም ካፒታል በጀትን አጽድቋል
የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ ኖቬምበር 21 በተደረገው ስብሰባ ላይ በበላይ ተቆጣጣሪው የተመከሩ የበጀት ዓመት (FY) 2026 ካፒታል በጀትን እና በFY 2025-2030 የካፒታል ማሻሻያዎች ፕሮግራም (CIP) ላይ የተደረጉ ማሻሻያዎችን አጽድቋል።
CIP አዳዲስ ፋሲሊቲዎችን እና መሰረተ ልማቶችን የመገንባት ወይም ነባሮቹን የማሻሻል ፕሮጀክቶችን ይዘረዝራል።
ከሱፐርኢንተንደንቱ የቀረበው FY2026 ካፒታል በጀት በድምሩ $1.853 ቢሊዮን ዶላር ነው። የበጀት ድምሩ ባይጨምርም፣ የገቢ እጥረቶችን ለመፍታት ዲስትሪክቱ ከMontgomery County 21.6 ሚሊዮን ዶላር እየጠየቀ ነው።
CIP webpageየታንክስጊቪንግ ሳምንት መርሀ ግብር እና በትምህርት ገብታ ላይ መገኘት
ትምህርት ቤቶችሰኞ፣ ኖቬምበር 25, እና ማክሰኞ ኖቬምበር 26 ተማሪዎችን ቀደም ብለው እንደሚለቁ ያስታውሱ። በእነዚህ ቀናቶች ተማሪዎች ትምህርት መማር እና ከበዓል እረፍት በፊት ወደኋል እንዳይቀሩ ስራቸውን ማጠናቀቃቸው አስፈላጊ ነው።
ለታንክስጊቪንግ በዓል ትምህርት ቤቶች እና መስሪያ ቤቶች ከረቡዕ፣ ኖቬምበር 27, እስከ አርብ፣ ኖቬምበር 29 ዝግ ይሆናሉ።
ጠቃሚ/አስፈላጊ የሆኑ ቀኖችን ለማግኘት እና የትምህርት ቤቱን ካላንደር በተመለከተ ወቅታዊ መረጃ ለማግኘትMCPS School Calendarን ይጎብኙ።
አዲሱን የስራ ማስኬጃ በጀት ዳሽቦርድ ይመርምሩ
MCPS ለ2025 የፊስካል አመት (የአሁኑ የትምህርት አመት) አዲስ የበጀት ዳሽቦርድ ጀምሯል፣ ይህም የ3.3 ቢሊዮን ዶላር የስራ ማስኬጃ በጀቱን ለመመርመር የሚያስችል ለተጠቃሚ ምቹ እና ግልጽነት ያለው መንገድን ያቀርባል።
በዚያ ላይ የሚያዩት ነገር
መሣሪያው የፍለጋ ተግባራትን እና ሊያወርዱት የሚችሉት የ Excel ፋይሎችን ያካትታል፣ ይህም የበጀት ትንታኔን ቀላል ያደርገዋል።
ተጠቃሚዎች ሶስቱን የበጀት ደረጃዎች ማወዳደር ይችላሉ፡
ዲሴምበር ላይ በበላይ ተቆጣጣሪው የተመከረ በጀት።
የትምህርት ቦርዱ ፌብርዋሪ ላይ በጊዜያዊነት ያጸደቀው በጀት።
ጁን ላይ የጸደቀው በጀት።
ስለ በጀቱ የበለጠ ይወቁ፡
የስፓኒሽኛ የበጀት ፎረሙን በ Pregúntale a MCPS Live ይመልከቱ
ዛሬ ማታ የሚካሄደው የበጀት ፎረም እንዳያመልጥዎት፡ ኖቬምበር 21, ከ6:30–8 p.m., Clarksburg ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ 22500 Wims Road in Clarksburg.
የMCPS የፎል ስፖርት የካውንቲ ሻምፒዮናዎች
በ2024 Fall Sports County Championships ላይ የላቀ አፈጻጸም ላሳዩት ለሚከተሉት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ቡድኖች እንኳን ደስ አላችሁ ማለት እንወዳለን፡
የወንዶች አገር አቋራጭ/Boys’ Cross Country- Montgomery Blair ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
የሴቶች አገር አቋራጭGirls’ Cross Country- Bethesda-Chevy Chase ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
የቺርሊዲንግ ዲቪዥን I- Winston Churchill ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
የቺርሊዲንግ ዲቪዥን II- Bethesda-Chevy Chase ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
የቺርሊዲንግ ዲቪዥንIII -John F. Kennedy ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
የመስክ ሆኪ - Walt Whitman ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
Golf 3A/4A - Walt Whitman ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
Golf 2A/1A - Damascus ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
Pickleball Co-Champions - Damascus ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት & Walter Johnson ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
የወንዶች እግር ኳስ - Walt Whitman ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
የሴቶች እግር ኳስ - Walt Whitman ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
የመረብ ኳስ - Richard Montgomery ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
የሴቶች Flag Football - Clarksburg ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት
እነዚህ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ቡድኖች ሲዝኑን በሙሉ ልዩ ክህሎትን፣ ትጋትን እና ስፖርታዊ ጨዋነትን አሳይተዋል። የአንዳንዶቹን አሸናፊዎች ፎቶዎች ለማየት ድህረ ገፃችንን ይጎብኙ።
የተማሪ እድሎች
በቦታው ላይ/ወዲያውኑ የሚደረጉ ምዝገባዎች፡በርካታ የአካባቢ እና የክልል ኮሌጆች እና ዩኒቨርሲቲዎች ማክሰኞ ዲሴምበር 3, ከ 3–6 p.m በRichard Montgomery ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለMCPS ሲኒየር ተማሪዎች በቦታው ላይ/ወዲያውኑ የሚደረጉ ምዝገባዎችን ያቀርባሉ። ተሰብሳቢዎች/ተሳታፊዎች የFAFSA ድጋፍንም ያገኛሉ እና ስለ Montgomery College የማመልከቻ ሂደትም ይማራሉ። Richard Montgomery የሚገኘው በ250 Richard Montgomery Drive Rockville ነው።
Vision Zero Youth Ambassador Programየሞንትጎመሪ ካውንቲ የትራንስፖርት ዲፓርትመንት (MCDOT) ለ2024 Vision Zero Youth Ambassador Programን የሚቀላቀሉ እስከ 35 የሚደርሱ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎችን ይፈልጋል። ፕሮግራሙ ተማሪዎች በመንገድ ደህንነት ፖሊሲዎች እና በመሠረተ ልማት ላይ ተጽእኖ እንዲፈጥሩ እድል ይሰጣል፣ እና የተመረጡ አምባሳደሮች ከጃንዋሪ ጀምሮ በአካል በመገኘት መሳተፍ ይጠበቅባቸዋል። ለበለጠ መረጃ ወይም ለማመልከት የMCDOT ድረ-ገጽን ይጎብኙ።
መከባበርን ይምረጡ/Choose Respect 2025፡የመካከለኛ እና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች እስከ $1,000 የማሸነፍ እድልን ለማግኘት መከባበርን ይምረጡ/Choose Respect ውድድር ላይ እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል። በውድድሩ ለመሳተፍ፣ ተማሪዎች ስለ ስሜታዊ ጥቃት፣ ፈቃድ መስጠት፣ ወይም አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ያለ ጓደኛን እንዴት መደገፍ እንደሚችሉ ግንዛቤ የሚፈጥር መልእክት ያለው የ60 ሰከንድ ቪዲዮ መስራት አለባቸው። ተሳታፊዎች የSSL ሰዓቶችን ማግኘት ይችላሉ፣ እና አሸናፊ ቪዲዮዎች በRespectFest 2025 ላይ ይታያሉ። ቪዲዮዎችን የማስገቢያ የመጨረሻው ቀን እሑድ፣ ፌብሩዋሪ 16 ነው። የበለጠ ለመረዳት/ለማወቅ፣ ድረ-ገጹን ይጎብኙ።
KID Museum Programming፡ የKID Museum የመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት Maker Nightን ዲሴምበር 6, ከ5፡30-8 p.m በ3 Bethesda Metro Centerያስተናግዳል። እዚህይመዝገቡ።ጥያቄ ከቀረበ ስኮላርሺፖች ይኖራሉ።
ግንኙነትዎን ይቀጥሉ
ይህን ድረገጽ ይጎብኙ፦ MCPS homepage.
240-740-3000 ይደውሉ፦ ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 7:30 a.m. እስከ 5 p.m. ሠራተኞች በእንግሊዝኛ እና በስፓንሽኛ ጥሪዎችን ስለሚቀበሉ (240-740-2845) ይደውሉ።
የኢሜይል እና የጽሁፍ መልዕክቶችን እና ስለ MCPS የሚተላለፉ ዘገባዎችን ያንብቡ።
MCPS የማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችንን፦ Twitter፣ Facebook እና Instagram በእንግሊዝኛ እና በስፓንሽኛ ይከታተሉ።
http://twitter.com/mcps
https://www.facebook.com/mcpsmd
https://www.instagram.com/mcps_md
https://www.facebook.com/mcpsespanol
https://twitter.com/MCPSEspanol
https://www.instagram.com/mcpsenespanol/
ኢሜሎች እና የጽሑፍ ማሳሰቢያዎች እንዲደርስዎት ይመዝገቡ እና የእርስዎ ParentVue ወቅታዊ መሆኑን ያረጋግጡ
MCPS ኬብል ቻነሎችን ይከታተሉ፦ Comcast 34 (1071 HD)፣ Verizon 36 ወይም RCN 89
በመካሄድ ላይ ያሉ ክፍት ምዝገባዎች
ተጨማሪ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) መረጃዎች
ኢሜል ይላኩልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org