መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች

MCPS መታወቅ ያለባቸው ጉዳዮች

ሐሙስ፣ ዲሴምበር 12 ቀን 2024

በአየር ሁኔታ ምክንያት የሚደረጉ ለውጦችን መረጃ ማወቅ አለብዎት 

የክረምት አየር ሁኔታ እየመጣ ስለሆነ አንዳንድ ጊዜ የትምህርት ቤት መርሃ ግብሮችን እና ስራዎችን ለውጥ ማድረግ ሊያስፈልግ ይችላል። በከባድ የአየር ፀባይ ምክንያት ት/ቤቶች ዘግይተው የሚጀምሩ ከሆነ፣ ወይም ት/ቤቶችን መዝጋት አስፈላጊ ከሆነ፣ የአሠራር ለውጦች ስለሚደረጉ ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት ያለዎትን ግንኙነት መቀጠልእና Alert MCPSአገልግሎት ለማግኘት ተመዝግበው በቀለም ኮድ የምናስተላልፈውን የመረጃ ስርጭት ይከታተሉ።

እርስዎን ማግኘት የምንችልበት መረጃ ወቅታዊ መሆኑን ያረጋግጡ

ወቅታዊ መረጃዎች እንደሚደርሰዎት ለማረጋገጥ እባክዎ ParentVUE link በመጠቀም MCPS Community Tech Support ድረገጽ ላይ የእርስዎን ወቅታዊ መረጃ ያስገቡ።

ስለቀለም ኮዶች ይበልጥ ይወቁ
2024-2025 የትምህርት አመት ከባድ የአየር ሁኔታ በሚከሰትበት ወቅት ስለ MCPS የአሠራር ሁኔታ፣አማርኛ


አዲስ የምግብ ዝርዝር መመልከቻ "New MealViewer" በየትምህርት ቤቱ-ስለሚዘጋጅ የምግብ አይነት፣ ስለ አልሚ ምግቦች፣ እና ስለ ምግብ አለርጂ መረጃ ይሰጣል

የምግብ እና አልሚ ምግብ አገልግሎት ክፍል (DFNS) በየትምህርት ቤቱ ስለሚዘጋጅ የምግብ አይነት በዝርዝር ለማየት ቀላል አድርጎታል። የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች፣ ወላጆች፣ እና የማህበረሰብ አባላት ከዚህ በኋላ "MealViewer" በመጠቀም የትምህርት ቤት የምግብ አይነቶችን በዝርዝር ማየት ይችላሉ፣ ይህም የሚከተሉትን ተጨማሪ መረጃዎች ይሰጣል፦

በኮምፒውተር የመረጃ ቋት በመዳሰስ በአንድሮይድ እና በአይፎን ወይም በማንኛውም ስማርትፎን ላይ MealViewer መተግበሪያ በመጠቀም ተደራሽነት ሊኖረው ይችላል። የምግብ አይነት ዝርዝር ለማየት ምንም የመክፈቻ ወይም የይለፍ ቃል አያስፈልግም። እንዲሁም የምግብ አይነቶችን፣ በተለይ የሚወዱትን ምግብ የኮከብ ምልክት በማድረግ የንጥረ ምግብ ማሳያ መጠቀም እና መግለጫ መፍጠር ይቻላል።(ነገር ግን ላያስፈልግ ይችላል) ዛሬውኑ የትምህርት ቤትዎን የምግብ ዝርዝር ይመልከቱ። በዚህ ቪዲዮ (በእንግሊዝኛ) እና (በስፓንሽኛ/en Español) መመልከት ይችላሉ።

ቪዲዎችን፣ አጫጭር ፍንጭ እና ተጨማሪ መገልገያዎችን/ሪሶርሶችን ለማግኘት የምግብ እና የአልሚ ምግብ አገልግሎት ክፍልድረገጽ ይጎብኙ።

MealViewer Infographic


ዲሴምበር 18 ከሱፐርኢንተንደንት የሚቀርበውን የበጀት እቅድ የቀጥታ ስርጭት ይከታተሉ 

ሱፐርኢንቴንደንት ቶማስ ቴይለር ስለ 2026 የበጀት ዓመት የስራ ማስኬጃ በጀት እቅድ እሮብ፣ ዲሴምበር 18 ከቀኑ 6 p.m. ላይ ያቀርባሉ። ሱፐርኢንተንደንቱ የሚያቀርቡትን የባጀት እቅድ ማህበረሰቡ MCPS ድረ ገጽ ወይም MCPS-TV YouTube channel ላይ የሚተላለፈውን የቀጥታ ስርጭት እንዲመለከት ተጋብዟል።

በሚከተለው መርኃግብር መሠረት የህዝብ ውይይት እና አስተያየት የሚሰጥባቸው መድረኮች ይካሄዳሉ።


93.6% ትምህርት ቤቶች 3 ነጥብ እና ከዚያ በላይ ውጤት ማግኘታቸውን በሜሪላንድ የሪፖርት ካርድ ሪፖርት ላይ ተገልጿል።

በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ፣ የሜሪላንድ ስቴት የትምህርት ዲፓርትመንት (MSDE) 2024 የሜሪላንድ ሪፖርት ካርድ ሪፖርት አውጥቷል፣ይህም የትምህርት ቤቶችን ስኬት የሚለካ እና በሜሪላንድ ስቴት፣ በዲስትሪክት፣ እና በት/ቤቶች ደረጃ የተገኙ ውጤቶችን እና መሻሻል ያለባቸውን ክፍተቶች ለይቶ ያሳያል።

2023-2024 የትምህርት አመት MSDE የአፈጻጸም ግምገማ ላይ 202 የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ትምህርት ቤቶችን አካቷል። ከተገመገሙት የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ትምህርት ቤቶች 50% የሚሆኑት ባለ 5-ኮከብ ወይም ባለ 4-ኮከብ ደረጃ አግኝተዋል፣ ይህም 2022-2023 የትምህርት አመት ላይ ከነበረው 1.8% እድገት ያሳያል። ከ 93% በላይ የሚሆኑት የ MCPS ት/ቤቶች ሶስት ወይም ከዚያ በላይ ኮከቦችን አግኝተዋል፣ይህም በስቴቱ ካለው 83% አማካይ ውጤት የሚበልጥ ነው።

ይበልጥ ያንብቡ።


ለመሳተፍ ቀኖቹን ይመዝግቡ — የልዩ ትምህርት መገልገያ/ሪሶርስ አውደ ርዕይ ጃንዋሪ 15 ይካሄዳል፣እና HBCU አውደ ርዕይ ፌብሩዋሪ 14 ይደረጋል።

MCPS ለተማሪዎች እና ለቤተሰቦቻቸው በሚያቀርባቸው ዝግጅቶች ላይ ለመሳተፍ የቀን መቁጠሪያዎን ምልክት ያድርጉ፦

የልዩ ትምህርት መርጃ አውደ ርዕይእሮብ፣ ጃኑዋሪ 15 ቀን ከቀኑ 5:30–7:30 p.m. Carver Educational Services Center, 850 Hungerford Drive in Rockville. auditorium/አዳራሽ ውስጥ ይካሄዳል። ይህ ዝግጅት ግላዊ የትምህርት ፕሮግራም (IEPs) የሚሰጣቸው ልጆች ላሏቸው ወላጆች ሁሉ ክፍት ነው። የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ቤተሰቦች ከትምህርት ሠዓት በኋላ ስለሚደረጉ እንቅስቃሴዎች፣የሠመር ፕሮግራሞች፣ እና ተጓዳኝ ስልጠናዎች ከማህበረሰብ ድርጅቶች የበለጠ መማር ይችላሉ።

የጥቁሮች ኮሌጆች እና ዩኒቨርሲቲዎች ታሪክ (HBCU) አውደ ርዕይ አርብ፣ ፌብሩዋሪ 14 ከቀኑ 6–8፡30 p.m. በሼዲ ግሮቭ (USG) ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ይካሄዳል። ይህ ዝግጅት ከ 8ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች እና ለወላጆቻቸው/ለአሳዳጊዎቻቸው ከ 50 በላይ HBCU ተወካዮች ጋር እንዲገናኙ እና በአውደ ጥናቱ ላይ እንዲሳተፉ እድል ይሰጣቸዋል። ምዝገባው አርብ፣ዲሴምበር 13 ይከፈታል።ተጨማሪ መረጃ

በተጨማሪም FAFSA/MHEC አንድ ማመልከቻ የሚሞላበት/የሚጠናቀቅበት ዝግጅት፡ ፌብሩዋሪ 14 ከቀኑ 6–8፡30 p.m. በሼዲግሮቭ ዩንቨርስቲ (USG) ይካሄዳል፣ ይህ ዝግጅት ለሁሉም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሲንየር ተማሪዎች እና ለወላጆቻቸው ክፍት ነው። ተጨማሪ መረጃ


MCPS የሠመር ራይዝ ተማሪዎችን ተቀብለው ለማስተናገድ አሁን ያመልክቱ

ምዝገባው ምናልባት በጣም የቀደመ ሊመስል ይችላል፥ነገር ግን ክረምቱ በፍጥነት እየቀረበ ነው!

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የትብብር አገልግሎት ክፍል፥ የሞንትጎመሪ ካውንቲ የንግድ ማህበረሰቦች፣የመንግስት ኤጀንሲዎች፣ እና ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶች በ 2025 የሠመር ራይዝ ፕሮግራም ላይ ተማሪዎችን በመቀበል እንዲሳተፉ ይፈልጋል። ምዝገባ ከአሁን ጀምሮእስከ አርብ፣ ማርች 7 ድረስ ክፍት ነው።

ሠመር ራይዝ ለሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ጁንየር እና ሲንየር ተማሪዎች የሥራ-ሙያን መሠረት ያደረጉ ልምዶችን ይሰጣል፣ እንዲህም የሥራ ቀጣሪዎች ተሰጥኦ እና ዝንባሌ ያላቸውን ተማሪዎች ለመመልመል ይረዳቸዋል። ተማሪዎች ከሚፈልጉት የሥራ መስክ ጋር የተያያዙ ሙያዎችን እየሰሩ የመማር እድል ይሰጣቸዋል። ፕሮግራሙ ከጁን 23 እስከ ጁላይ 25 ድረስ ለአምስት ሳምንታት የሚቆይ ሲሆን ቢያንስ 50 ሰዓታት በአካል በመገኘት፣ ቨርቹዋል ወይም ሁለቱንም አጣምሮ የመማር እድል አላቸው።

ስለ ሠመር ራይዝ ፕሮግራም የበለጠ መረጃ እዚህይገኛል።


20 አመት የስትራትሞር ምትሀታዊ ድምቀት

ቪዲዮ ይመልከቱ

ላለፉት 20 አመታት ከ 240,000 በላይ የሁለተኛ ክፍል ተማሪዎች በብሄራዊ የፊልሃርሞኒክ ኦርኬስትራ የሚቀርቡ ነጻ ኮንሰርቶች ላይ ለመሳተፍ እና ለማየት በስትራትሞር የሚገኘውን የሙዚቃ ማእከል ጎብኝተዋል። በዚህ የቪዲዮ ትረካ፣የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የቀድሞ ተማሪዎች ኮንሰርቶቹ በህይወታቸው እና በሙያቸው ላይ ያሳደሩትን አዎንታዊ ተፅእኖ ያንፀባርቃሉ። 


የብሌክ ተማሪዎች ከሁሉም የሜሪላንድ ስቴት ምርጥ ዳንሰኞች በመሆን ተመርጠዋል

የጄምስ ሁበርት ብሌክ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች Neive Carr እና Niambi Mills ከሁሉም የሜሪላንድ ስቴት ምርጥ ዳንሰኞች በመሆን ተቀባይነት አግኝተዋል። እነርሱ የተመረጡት በሜሪላንድ ዩኒቨርሲቲ፣ ባልቲሞር ካውንቲ (UMBC) ተገኝተው የችሎታ ውድድር ካደረጉት 108 ዳንሰኞች መካከል ነው። 

ጥንዶቹ ለመጀመሪያ ጊዜ በሜሪላንድ ስቴት የዳንስ ፌስቲቫል እና ትርኢት ያሳያሉ። እዚህ ይበልጥ ያንብቡ።


ከእኛ ጋር ግንኙነትዎን ይቀጥሉ



ኢሜል ይላኩልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org

የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS)