የብሌር ሁለተኛ አመት ተማሪ በ "StudentCam" ዶክመንተሪ ውድድር ታላቁን (ግራንድ) ሽልማት አሸንፏል
በሞንትጎመሪ ብሌር ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሁለተኛ አመት ተማሪ የሆነው ዴርሞት ፎሌይ/Dermott Foley፣ በ 2025 የትምህርት አመት C-SPAN StudentCam ለፊልም/ለቴሌቪዥን የተዘጋጀ ቅንብር ውድድር ታላቁን ሽልማት አሸንፏል። ፎሌ ላዘጋጀው "ታዳጊዎች፣ ማህበራዊ ሚዲያ፣ እና ፌንታንይል ከመጠን በላይ መመጠቀም የሚያስከትለው ቀውስ" ዘጋቢ ፊልም $5,000 ዶላር አሸንፏል። ይህ ዘጋቢ ፊልም ሰኞ፣ ኤፕሪል 21 ከጠዋቱ 6:50 a.m. ጀምሮ C-SPAN አየር ላይ የሚውል ሲሆን ቀኑን ሙሉ ይተላለፋል።
አመታዊ ውድድሩ በመላ ሀገሪቱ ለሚገኙ የመካከለኛ እና የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ክፍት ነው። ከ—ቤተዝዳ-ቼቪ ቼዝ፣ ሞንትጎመሪ ብሌር፣ ዊንስተን ቸርችል፣ ፑልስቪል፣ ሪቻርድ ሞንትጎመሪ፣ ሮክቪል፣ እና ዊተን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች፣ እና ኢስተርን፣ ጁሊየስ ዌስት እና ዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ ጁኒየር፥ ከ 10 የመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ ተማሪዎች — በውድድሩ ተሳትፈዋል። የአሸናፊዎችን ሙሉ ዝርዝር ይመልከቱ።
ስለ ትምህርት ቤቶች የድንበር ጥናቶች የህዝብ መረጃ ልውውጥ ስብሰባዎች ላይ ይቀላቀሉን።
በድንበር ጥናቶች ላይ በቅርቡ የሚደረጉ የህዝብ መረጃ ልውውጥ ስብሰባዎች ቻርለስ ደብሊው ውድዋርድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ ክራውን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና ደማስከስ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን እንደገና ለመክፈት የተዘጋጁ ናቸው። በነዚህ ክፍለ-ጊዜዎች ስለ ድንበር የወሰን ጥናት ሂደት እና የወደፊት ተሳትፎ እድሎች ላይ ጠቃሚ ዝርዝሮች ይቀርባሉ። ተጨማሪ መረጃ
የቻርለስ W. ውድዋርድ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን እንደገና ስለመክፈት የሚደረግ የድንበር ጥናት
የክራወን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መክፈቻ እና የደማስከስ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ማስፋፊያ የወሰን ጥናት
ምዝገባ የማያስፈልግ ቢሆንም፣ ዲስትሪክቱ እንዲዘጋጅ ለማገዝ ተሰብሳቢዎች RSVP እንዲመዘገቡ MCPS ይጠይቃል።
MCPS ስለ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) አጠቃቀም መመሪያዎችን እያዘጋጀ ስለሆነ ሀሳብዎን ይንገሩን!
አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) የተለያዩ ኢንዱስትሪዎችን እየቀየረ ስለሚገኝ በትምህርት ላይም ያለው ሚና በፍጥነት እየሰፋ ነው። AI የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል እና ለሰራተኞች ቅልጥፍናን ለመጨመር ጉልህ እድሎች ይኖሩታል። ነገር ግን፣ ከነዚህ እድገቶች ጋር ተያይዘው የሚከሰቱ ተግዳሮቶችም ይኖራሉ፥ የአጠቃቀም ስነምግባር፣ የውሂብ ግላዊነትን መጠበቅ፣ እና ፍትሃዊ ተደራሽነትን ጨምሮ የጥንቃቄ ትኩረት መሰጠት አለባቸው። እያደገ ከመጣው የክፍል እና የአስተዳደራዊ ሂደቶች አንጻር፣ MCPS ስለ AI አጠቃቀም መመሪያዎችን ማዘጋጀት አስፈላጊ ነው።
MCPS በትምህርት ቤቶች ስለ AI አጠቃቀም ደንቦችን እና መመሪያዎችን በማዘጋጀት ላይ ስለሆነ የአስተያየቶችን ግብአት ይፈልጋል። እርስዎ ወላጅ/አሳዳጊ፣ ወይም የማህበረሰብ አባል፣ የአሁን ወይም የቀድሞ ተማሪ፣ መምህር ወይም ሰራተኛ በመሆንዎ AI በብቃት፣ በኃላፊነት፣ እና አግባብነት ባለው ሥነ ምግባር መማርና ማስተማርን ለመደገፍ አስፈላጊ በመሆኑ በዚህ ረገድ የእርስዎን አመለካከት ማወቅ አስፈላጊ ነው። ስለ AI አጠቃላይ መግለጫ አጭር ቪዲዮ እዚህ ይገኛል። የዳሰሳ ጥናቱን ይሙሉ።
መገልገያዎች/ሪሶርሶች፦
ሠመር ራይዝ መጀመር እና ደማቅ የጎልፍ ውድድር "Inaugural Summer RISE & Shine Golf Tournament" ይቀላቀሉን።
ሠመር ራይዝ እና ደማቅ የጎልፍ ውድድር "Summer RISE & SHINE Golf Tournament"ሰኞ፣ሜይ 5 የሚካሄድ ስለሆነ MCPS እና የአጋርነት ማስተባበሪያ መምሪያን በዚህ አድራሻ ይቀላቀሉ፥ አድራሻ፦ Montgomery Country Club in Laytonsville። በዚህ ዝግጅት ለሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ጁንየር እና ሲንየር ተማሪዎች በሙያ ላይ የተመሰረተ የሠመር ትምህርት እድል ለመስጠት ለሠመር ራይዝ ፕሮግራም ገንዘብ ይሰበሰባል። የጎልፍ ውድድሩ ከካውንቲ መሪዎች ጋር፣ ከአካባቢው የንግድ ማህበረሰብ ጋር፣ ከ MCPS ሰራተኞች፣ እና ከተሳታፊ ድርጅቶች ጋር አስደሳች የሆነ የጎልፍ ጨዋታ ለመጫወት እና መስተጋብር ለማድረግ አመቺ እድል ይፈጥራል።
የቲኬት ግዢው ጎልፍ በዙር መጫወት እና ለሠመር ራይዝ ፕሮግራም ልገሳ፣ እንዲሁም የአረንጓዴ እና ክልል ጊዜን መለማመድ፣ ጎልፍ የሚጫወቱበትን ተርታ፣ የቁርስ ምግቦችን፣ ምሳ እና ከጨዋታ በኋላ የሚደረግ የሽልማት አሰጣጥ ዝግጅት ላይ መሳተፍን ያካትታል። በጎልፍ ሜዳው ላይ ተጨማሪ ጨዋታዎችም ይኖራሉ፣የሱፐርኢንተንደንት የውድድር ዝግጅት፣ Pin ርቀት እና ቅርበት። ዛሬውኑ ይመዝገቡ።
ድጋፍ/ስፖንሰርሽፕ ይኖራል። የበለጠ መረጃ ለማግኘት የአጋርነት ማስተባበሪያ ክፍልን በስልክ ቁጥር 240-740-5599 ደውለው ይጠይቁ ወይም ለኬቪን ብራንክ/Kevin Brunk ኢሜይል ያድርጉ።
በጣም የተጠየቀ መረጃ አንድ ጊዜ ጠቅ አድርገው ያገኙታል።
“ለምሳ ምን አለ?”፣ “ቅጹ የት ነው?”፣ “ለልጄ ምን አይነት እንቅስቃሴዎች አሉ?” በማለት እራስዎን ጠይቀው ያውቃሉ? MCPS ይሸፍናል! ከ AskMCPS፣ Google analytics እና ከሌሎች ቻናሎች የተሰበሰበ፥ አዲሱ ብዙ የተጠየቀ መረጃ ገጽ የጥያቄዎን መልስ ለማግኘት አይነተኛ ቦታ ነው።
ፈጣን ዕድል— ወደ እርስዎ እየመጣ ነው!
MCPS የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) የፈጣን የሥራ እድሎችን ተንቀሳቃሽ የምልመላ ሪባን የመቁረጥ ስነ-ስርዓት እና የቅጥር ክፍለጊዜ ረቡዕ፣ ኤፕሪል 2 10 a.m. ላይ ይጀምራል። የምልመላ ጉዞው የሚጀምረው በዊተን ውድስ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ነው። "Opportunity Express"/ኦፖርቹኒቲ ኤክስፕረስ በካውንቲው ውስጥ የሚገኙ ትምህርት ቤቶችን እና ሌሎች ቦታዎችን ይጎበኛል። ዲስትሪክቱ ለፓራኢጁኬተሮች ክፍት የስራ ቦታዎች አሉት፣ እንዲሁም በመጓጓዣ ሥራ፣ በምግብ ዝግጅት አገልግሎት፣ እና በጥገና እና ኦፕሬሽኖች የሥራ እድሎች አሉ። ማስታወቂያውን ለጓደኞችዎ እና ለጎረቤቶችዎ ያሰራጩ፣ እና ለአዲስ የስራ እድል ኤፕሪል 2 ይቀላቀሉን። ወደፊት ኦፖርቹኒቲ ኤክስፕረስ የሚከናወኑባቸው የማህበረሰብ ተሳትፎ ዝግጅቶችን ይጠብቁ።
2025 የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ፈጣን ዕድል
መጋረጃ እየተሰቀለ ነው!
በፀደይ/ስፕሪንግ ወቅት ለሚካሄዱ የመካከለኛ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ቲያትር እና የዳንስ ዝግጅቶች ቲኬቶችን አሁኑኑ ያግኙ። እነዚህ ምርጥ ትርኢቶች እስከ ሜይ ወር ይካሄዳሉ። “Mean Girls” and “Shrek the Musical” to “Antigone” and “A Midsummer Night’s Dream,” ከመሳሰሉት ትእይንቶች ለሁሉም ሰው ፍላጎት የሚስማማ ነገር ይኖራል።
ማሳሰቢያ
"RespectFest" ከማርች 30 እስከ ኤፕሪል 6 ይካሄዳል።
የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች እና ወላጆች፡ ስለ ጤናማ ግንኙነት፣ የፍቅር ጓደኝነት ጥቃትን መከላከል፣ እና ስለ ስምምነት እና የማህበረሰብ መገልገያዎችን ለማወቅ ከማርች 30 እስከ ኤፕሪል 5 ቀን በሚካሄድ ፕሮግራም ለመሳተፍ ቀን መቁጠሪያዎ ላይ ያስታውሱ። RespectFest ከማርች 30 እስከ ኤፕሪል 5 ቨርቹዋል ወርክሾፖችን እና በአካል የሚሳተፉበት ፌስቲቫል እሁድ፣ ኤፕሪል 6 ከቀኑ 1-4 p.m. በዊተን የማህበረሰብ መዝናኛ ማዕከል ያካሄዳል። አድራሻው፦ Wheaton Community Recreation Center፣ 11701 Georgia Avenue፣ Silver Spring። እዚህ ተጨማሪ ግንዛቤ ያግኙ
የሠመር ትምህርት ቤት ምዝገባ ሐሙስ፣ ኤፕሪል 3 ይከፈታል። ክፍለ ጊዜዎቹ፦ ጁን 30 እስከ ጁላይ 18 እና ጁላይ 22 እስከ ኦገስት 8 በጌትስበርግ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ይካሄዳሉ። ቨርቹዋል አማራጮችም ይኖራሉ። ተጨማሪ መረጃ በድረገጻችን እና በዚህ በራሪ ወረቀት ላይ ይገኛል።
ስለ ማዝለቅ/ማስቀጠል የፖስተር ውድድር፡ ይህ አመታዊ ውድድር ስለ ተፈጥሮ አካባቢ ጥበቃ ዘላቂነት፣ የሃይል አጠቃቀም፣ ቆሻሻ ቅነሳ፣ እና በኃላፊነት ስሜት እንደገና ጥቅም ላይ ስለማዋል አስፈላጊነት ግንዛቤ ይሰጣል። ሁሉም የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች እና ሰራተኞች እንዲሳተፉ እና አሸናፊዎቹን ለመወሰን በኦንላይን እንዲመርጡ ተጋብዘዋል። የመጨረሻው ቀነ ገደብ አርብ፣ ኤፕሪል 4 ነው። 2025 ስለ ማዝለቅ/ማስቀጠል የፖስተር ውድድር መግቢያ ቅጽ እና የውድድር መመሪያ.
MCPS ለመካከለኛ ደረጃ ት/ቤት እና ለሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች 4ኛውን ዓመታዊ የወጣቶች የአየር ንብረት ጥበቃ ጉባኤ ቅዳሜ፣ ኤፕሪል 5ከጠዋቱ 8:30 a.m. እስከ 3:30 p.m. በጁሊየስ ዌስት መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ያካሄዳል። አድራሻ፦ Julius West Middle School, 651 Great Falls Road in Rockville. የሚሳተፉ ተማሪዎች ስድስት SSL ሰዓቶች ያገኛሉ። ምሳ ይቀርባል፤ እና ከአማካይ ቦታ መጓጓዣ ይኖራል። መገኘት የሚፈልጉ ተማሪዎች የተማሪ ምዝገባ ቅጽ መሙላት አለባቸው። ተጨማሪ መረጃ
ጨዋታ ቀያሪ ኮንፈረንስከ 4-12 የሚማሩ ወጣት ወንድ ተማሪዎችን ወላጆች/ተንከባካቢዎች ለፀደይ/ለስፕሪንግ ጨዋታ ቀያሪ ኮንፈረንስ እና የስኬት መንገዳቸውን ለማጎልበት እና ለማቀጣጠል እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል። ኮንፈረንሱ ቅዳሜ፣ ኤፕሪል 5ከጠዋቱ 8 a.m. እስከ ቀትር በሞንትጎመሪ ኮሌጅ፣ ጀርመንታውን ካምፓስ ይካሄዳል።at Montgomery College, Germantown campus from 8 a.m.–noon. ይመዝገቡ/Register.
COSA የሚያመለክቱበት ጊዜ ሊያበቃ ተቋርቧል፦የትምህርት ቤት ምደባ ለውጥ የማድረግ (COSA) ሂደትን በተመለከተ ወላጆች/አሳዳጊዎች ልጃቸው በተለየ ሁኔታ ምክንያት ከአካባቢ ትምህርት ቤት ወደ ሌላ ት/ቤት ተመድቦ(ባ) እንዲማር/እንድትማር መጠየቅ ይችላሉ። 2025–2026 የትምህርት አመት COSA ጥያቄ የሚቀርብበት ወቅት ማክሰኞ፣ ኤፕሪል 1 ላይ ያበቃል። ከኤፕሪል 1, 2025 በኋላ የሚቀርቡ ጥያቄዎች በቅርብ ያጋጠመ ምክንያት ወይም ከኤፕሪል 1 በፊት ሊተነበይ የማይቻል አጋጣሚ ሁኔታ ካልተከሰተ በስተቀር ተቀባይነት አይኖራቸውም። COSA ጥያቄዎች በሙሉ በ ParentVue Synergy በኦንላይን መቅረብ አለባቸው። የበለጠ መረጃ ለማግኘት ለተማሪ ፐርሶኔል እና ትምህርት ቤት መገኘትን የሚቆጣጠር ክፍልን በስልክ ቁጥር 240-740-5620 ያነጋግሩ ወይም ድረገጹን ይጎብኙ።
ካውንቲው የራይድ ኦን "Ride On" 50ኛ አመት ለማክበር አርት ውድድር ጀምሯል
የመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች በሞንትጎመሪ ካውንቲ የራይድ ኦን አውቶብስ "Ride On bus" 50ኛ ዓመት አገልግሎት የሚያከብሩ የስነጥበብ ስራዎችን እንዲያቀርቡ ተጋብዘዋል። የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትራንስፖርት ዲፓርትመንት ተማሪዎች ስለ "Ride On" አውቶቡስ ጥራት ያለው የመጓጓዣ አገልግሎት በህይወት ተሞክሮ ላይ ስለሚያሳድረው ተፅእኖ ለማስተማር እና የህዝብ መጓጓዣ መጠቀምን ለማበረታታት ውድድር እያዘጋጀ ነው። የስነጥበብ ስራው "ለውድድር የሚቀርበው አርት" አንድ ወይም ከዚያ በላይ የራይድ ኦን/Ride On አውቶቡስ አገልግሎቶችን ማሳየት እና Ride On ለማህበረሰቡ ያመጣውን እሴቶች የሚያስገነዝብ መሆን አለበት።
ተሳታፊ ተማሪዎች አምስት የተማሪ አገልግሎት ትምህርት ሰዓት ያገኛሉ።
ሶስት ከፍተኛ ነጥብ ያገኙ አሸናፊዎች $100 ዶላር፣ $75 ዶላር እና $50 ዶላር የስጦታ ካርዶችን ያገኛሉ። በአንደኛ ደረጃ ያሸነፈው የስነጥበብ ሥራ በሁሉም ራይድ ኦን አውቶቡሶች መግቢያ ላይ እንዲታይ ይደረጋል። ብዙ ተወዳዳሪዎችን ያቀረበ መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት $500 ዶላር የስጦታ ካርድ ያገኛል። ተጨማሪ ግንዛቤ ያግኙ። መወዳደሪያ አርት መቅረብ ያለበት ቀነ ገደብማክሰኞ፣ ኤፕሪል 15እስከ 11:59 p.m. ነው።
ምናልባት አምልጥዎት ከሆነ…
የቅርብ ጊዜውን MCPS የዜና ገጾቻችንን ያንብቡ፡
12 የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች ለ "National Association for Music Education 2025 All-Eastern Honors Ensembles" ተመርጠዋል። ሙዚቀኞቹን ይመልከቱ።
የቀጣዩ ትውልድ የአመራር ቀን "Next Generation Leadership Day" በትምህርት ቤቶቻቸው የተመረጡ 4ኛ እና 5ኛ ክፍል ተማሪዎች ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አማካሪዎች ስለ አመራር ክህሎት ይማራሉ። በጉባኤ ከተማሪ መሪዎች ጋር ያስተዋውቃቸዋል፣ እና ቀኑን ሙሉ የሚደረጉ አውደ ጥናቶች የፈጠራ ችሎታቸውን እና ክህሎታቸውን የመጠቀም እድል ይፈጥርላቸዋል። የተማሩትን ይመልከቱ።
ማርች ብሄራዊ የአትሌቲክስ ማሰልጠኛ ወር ሲሆን የአትሌቲክስ አሰልጣኞች አትሌቶችን ደህንነታቸው የተጠበቀ እና ጤናማ እንዲሆኑ የሚጫወቱትን ወሳኝ ሚና የሚያንፀባርቁበት ጊዜ ነው። የአትሌቲክስ አሰልጣኞች ጉዳቶችን ከመከላከል እስከ ድንገተኛ አደጋ እንክብካቤ ድረስ ለስፖርት ቡድኖች እና ለተሳታፊ ግለሰቦች ደህንነት አስፈላጊ ናቸው። የአትሌቶችን ጠንካራ አቅም በመገንባት የሚጠብቋቸውን ታታሪ ባለሙያዎች ለማክበር ይቀላቀሉን!
ከእኛ ጋር ግንኙነትዎን ይቀጥሉ
ይህን ድረገጽ ይጎብኙ፦ MCPS homepage.
240-740-3000 ይደውሉ፦ ከሰኞ እስከ አርብ 7:30 a.m. እስከ 5 p.m. ሠራተኞች በእንግሊዝኛ እና በስፓንሽኛ ጥሪዎችን ስለሚቀበሉ (240-740-2845) ይደውሉ።
የኢሜይል እና የጽሁፍ መልዕክቶችን እና ስለ MCPS የሚተላለፉ ዘገባዎችን ያንብቡ።
በማህበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ላይ በእንግሊዝኛ እና በስፓንሽኛ ቋንቋዎች የሚተላለፉ ዘገባዎችን MCPS Twitter፣ Facebook እና Instagram ላይ ይከታተሉ።
http://twitter.com/mcps
https://www.facebook.com/mcpsmd
https://www.instagram.com/mcps_md
https://www.facebook.com/mcpsespanol
https://twitter.com/MCPSEspanol
https://www.instagram.com/mcpsenespanol/
ኢሜሎች እና የጽሑፍ ማሳሰቢያዎች እንዲደርስዎት ይመዝገቡ፤ የእርስዎ ParentVue ወቅታዊ መሆኑን ያረጋግጡ
MCPS ኬብል ቻነሎችን ይከታተሉ፦ Comcast 34 (1071 HD)፣ Verizon 36 ወይም RCN 89
ተጨማሪ የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) መረጃዎች
ኢሜል ይላኩልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org