አበይት ጉዳዮች
ኦገስት 14, 2025
|

|
የተማሪ ሽግግር ቀን | የተማሪ ስነምግባር ደንብ | ውጤት መስጠት እና ሪፖርት ማድረግ | ሞባይል ስልክ በት/ቤት | ለአደጋ ጊዜ ዝግጁነት | ስለ ዳራ ማጣራት ወቅታዊ መረጃ | እደ ት/ቤት የመመለስ አውደ ርዕይ | FARMS ማመልከቻዎች | AskMCPS የውይይት መድረክ/AskMCPS Chatbot | ሠራተኞችን እየቀጠርን ነው! | አትሌቲክስ
|
|
ስለ ሽግግር ቀን ጥያቄዎች አሉ? መልስ ለመስጠት ተዘጋጅተናል!
ሰኞ፣ ኦገስት 25 ቀን MCPS በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ የተማሪ የሽግግር ቀን ያካሂዳል፣ ቀኑን ሙሉ፣በክፍል ትምህርት የማይሰጥበት የትምህርት ቤት ልምድ የሚያገኙበት፣ ወደ አዲስ የት/ቤት ደረጃ የተሸጋገሩ ወይም ወደ አዳዲስ ህንፃዎች የሚገቡትን ተማሪዎች ሽግግር ለማቃለል የታለመ ነው። ለሁሉም ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት ከመመለሳቸው በፊት የትምህርት ቤት ውሎን ለመሞከር እና ለመዘጋጀት ጥሩ ቀን ይሆናቸዋል። ይህን ቪዲዮ ይመልከቱ
ተጨማሪ ግንዛቤ ያግኙ
|
|
|
ተማሪዎች በት/ቤት ደህንነት እንዲሰማቸው፣ የት/ቤት አካል እንደሆኑ እና በትምህርት ቤት እንደሚደገፉ ማረጋገጥ፣
2025–2026 የትምህርት አመት MCPS የተማሪ የስነምግባር ደንብ ክለሳ እየተደረገ ነው። ለውጦቹ፦ ለተማሪዎች የስነምግባር ደንቡን ለመረዳት ቀላል ማድረግ እና በዲስትሪክቱ ውስጥ የሚፈጠሩ ደንብ የመጣስ ክስተቶችን መደበኛ የምርመራ እና እርምጃ የመውሰድ አፈጻጸም ሂደት ማቋቋምን ያካትታሉ። ይህ ሰነድ ከተማሪ ባህሪ የሚጠበቁ ነገሮችን እና የተለያዩ ፖሊሲዎችን፣ ደንቦችን እና ደንቦችን መጣስ የሚያስከትለውን መዘዝ ይዘረዝራል። ትኩረቱ ተማሪዎች ከስህተቶቻቸው እንዲማሩ፣ የደረሰ ጉዳትን እንዲጠግኑ፣ እና እምነት እንዲገነቡ ለመርዳት ነው። በተጨማሪ ግንዛቤ ያግኙ።
2025–2026 የስነምግባር ደንብ ማክበር
|
|
|
በትምህርት ውጤት አሰጣጥ የስሌት አሠራር ለውጦች ይደረጋሉ።
በሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶችየትምህርት ውጤት አሰጣጥ ስሌት እና ሪፖርት አሰጣጥ ላይ አስፈላጊ ክለሳዎች የተደረጉ ስለሆነ በዚህ የትምህርት አመት ተፈጻሚ ይደረጋሉ። ከ 6ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች የማጠናቀቂያ ውጤቶች ስሌት የሚሠራው በአራቱ የማርክ መስጫ ወቅት አማካይ ውጤት ላይ ተሞርኩዞ ይሆናል። ይህ ለውጥ፣ ከሌሎች ሁኔታዎች ጋር፣ ወጥነት ያለው አሠራር ለማዳበር፣ ተማሪዎች በትምህርታቸው ላይ የሚጠበቅባቸውን ውጤት ማምጣት እንዳለባቸው ለማጠናከር እና በትምህርት ቤት ውስጥ ትክክለኛ የተማሪዎችን የትምህርት ችሎታ ለመለካት የተነደፈ ነው።
በተጨማሪ ግንዛቤ ያግኙ.
|
|
 |
አነስተኛ የስልክ ጊዜ = ተጨማሪ የመማሪያ ጊዜ
2025–2026 የትምህርት አመት፣ MCPS በትምህርት ቀን እንዴት የግል ሞባይል ስልኮችን/መሳሪያዎችን መጠቀም እንደሚቻል ገደብ አስቀምጧል። ትምህርት በሚሰጥበት ክፍለጊዜ የስልክ አጠቃቀምን መገደብ ተማሪዎች በትኩረት ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ፣ እንዲሳተፉ እና መረጃዎችን በተሻለ ሁኔታ እንዲገነዘቡ ይረዳቸዋል።
ተጨማሪ ግንዛቤ ያግኙ.
|
|
|
የአደጋ ጊዜ ዝግጁነት
ሁሉም የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ትምህርት ቤቶች ተከታታይ የአደጋ ጊዜ ዝግጁነት ልምምድ በኦክቶበር መጨረሻ ላይ ማጠናቀቅ ይጠበቅባቸዋል። ትምህርት ቤቶችም ለምሳሌ፦ ቤተሰቦች ከአደጋ በኋላ እንዴት እንደሚገናኙ እና ከባድ ስጋት በሚፈጠርበት ጊዜ ሰራተኞች እና ተማሪዎች እንዴት ምላሽ ሊሰጡ እንደሚችሉ በአደጋ ጊዜ ዝግጁነት ልምምድ ወቅት የደህንነት አጠባበቅ ሂደቶችን ይገመግማሉ። እነዚህ ልምምዶች እና ንግግሮች ከእድሜ ጋር የሚመጥኑ፣ በተረጋጋ መንፈስ እና በመደጋገፍ በራስ መተማመን እና ዝግጁነት ላይ ያተኮሩ ናቸው። መደበኛ የአደጋ ጊዜ ምላሽ ዝግጁነት ፕሮቶኮል ያንብቡ።
ተጨማሪ ግንዛቤ ያግኙ
|
|
|
የተማሪዎች ደኅንነት ቅድሚያ ትኩረት የምንሰጠው ጉዳይ ነው፡ እያደረግን ያለነውን ይመልከቱ።
ከሞንትጎመሪ ካውንቲ የዋና ኢንስፔክተር ፅህፈት ቤት የቅርብ ጊዜ ግኝቶች፦ የት/ቤት ሰራተኞች፣ የስራ ተቋራጮች እና በጎ ፈቃደኞች የበፊት ዳራ እንዴት እንደሚጣራ እና ክትትል እንደሚደረግ መሻሻል ያለባቸውን ሁኔታዎች በነቂስ አሳይተዋል። ልጆችዎ በትምህርት ቤት ደህንነታቸው የተጠበቀ ነው፣ እና በዚያው ሁኔታ መቆየቱን ለማረጋገጥ አፋጣኝ እና ቀጣይነት ያለው እርምጃ እየወሰድን ነው።
እዚህ ይበልጥ ያንብቡ.
|
|
|
ወደ ትምህርት ቤት መመለሻ አውደርዕይ የሚካሄደው ኦገስት 23 ስለሆነ —እንዳያመልጥዎት!
MCPS ቅዳሜ፣ ኦገስት 23 ከጠዋቱ 10፡00 a.m እስከ 1 p.m. አመታዊውን ወደ ትምህርት ቤት የመመለስ አውደ ርዕይ በሚከተለው አድራሻ ያስተናግዳል፦
Westfield Wheaton mall (11160 Veirs Mill Road in Wheaton) ስለ ትምህርት ቤት ስርዓት፣ በካውንቲው ስለሚገኙ ፕሮግራሞች እና አገልግሎቶች ይወቁ፣ ስጦታዎችን ይውሰዱ፣ እና ህጻናት ክትባቶችን ያግኙ። በሙዚቃ የታጀበ መዝናኛ ይኖራል፤እንደ ብስክሌት ሮዲዮ የመሳሰሉ ለልጆች አስፈላጊ የብስክሌት ደህንነት ክህሎቶችን ለማስተማር የተዘጋጁ አስደሳች እንቅስቃሴዎች ስለሚኖሩ ተገኝተው ይደሰቱ።
ተጨማሪ ግንዛቤ ያግኙ
|
|
|
ለነጻ እና የዋጋ ቅናሽ ምግብ (FARMS) ዛሬውኑ ያመልክቱ
የምግብ ጥቅማጥቅሞችን ለማግኘት ዛሬውኑ በኦንላይን ያመልክቱ! ምንም እንኳን ልጆቻችሁ ባለፈው አመት ብቁ ቢሆኑም በየትምህርት አመቱ አዲስ FAARMS ማመልከቻ መቅረብ አለበት። የፌደራል የገቢ ደረጃዎችን የሚያሟሉ ቤተሰቦች ለነጻ የትምህርት ቤት ምግብ ብቁ ናቸው፣ ነገር ግን ይህንን ጥቅማጥቅም ለማግኘት ማመልከት አለባቸው። በአንድ ቤተሰብ ለሚገኙ ሁሉም ተማሪዎች የሚያስፈልገው አንድ ማመልከቻ ብቻ ነው።
ተጨማሪ ግንዛቤ ያግኙ.
|
|
|
እርስዎ ጥያቄዎች አሉዎት፣ እኛ መልሶች አሉን!
Just Ask MCPS! ይጠይቁ ተሻሽሎ የቀረበው የዲስትሪክቱ ድረ-ገጽ በተሻለ ሁኔታ መረጃ ይሰጣል። በብዛት የሚጠየቅ ድረ-ገጽ ላይ (በቀላሉ "በጣም የሚጠየቅ" MCPS ድረ ገጽ ላይ መረጃ ሰጪ AskMCPS chatbot (MCPS ጋር የተያያዙ ጥያቄዎችን በማንኛውም ቋንቋ ሊመልስ ይችላል)፣ ጥያቄዎን እንመልሳለን!
|
|
|
ሥራ ፈላጊዎችን እንቀጥራለን! የእርስዎ የወደፊት እጣ ፈንታ ከ MCPS ጋር ነው።
MCPS ጥልቅ ፍላጎት ያላቸው ለመልካም ዓላማ ጊዜና ጉልበታቸውን አሳልፈው የሚሰጡ ግለሰቦችቡድናችንን እንዲቀላቀሉ ይፈልጋል ልምድ ያካበቱ አስተማሪም ይሁኑ ወይም አዲስ የስራ መስክ ፈላጊም ቢሆኑ ለእርስዎ የሚሆን ቦታ አለን። ከችሎታዎ እና ከፍላጎቶችዎ ጋር የሚዛመዱ እና በተማሪዎች ህይወት ላይ ትርጉም ያለው ተጽእኖ የሚፈጥሩ የልዩ ትምህርት አስተማሪነት፣ ፓራኢጁኬተርነት፣ የደህንነት ጥበቃ እና የመጓጓዣ/የትራንስፖርት ክፍት የሥራ ቦታዎችን ጨምሮ በርካታ የሥራ እድሎችን ይቃኙ።
|
|
|
ጨዋታ ይግቡ! በዚህ ሳምንት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የማጣሪያ ሙከራ እና የመካከለኛ ደረጃ ት/ቤት አትሌቲክስ ምዝገባ ተጀምሯል።
የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የፎል/በልግ ስፖርቶች የማጣሪያ ሙከራዎች በዚህ ሳምንት በመካሄድ ላይ ናቸው። ለስፖርት-ተኮር መረጃ በትምህርት ቤትዎ የሚገኘውን የአትሌቲክስ ዳይሬክተር ያነጋግሩ።
የሁሉም የመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የፎል/የበልግ ስፖርቶች ምዝገባ አሁን ParentVue ላይ ተከፍቷል። ከስፖርት ጋር የተያያዙ ማናቸውንም ጥያቄዎች የትምህርት ቤትዎን የአትሌቲክስ አስተባባሪ ያነጋግሩ።
|
|

|
ከእኛ ጋር ያለዎትን ግንኙነት ይቀጥሉ
|
|
|
|
በመካሄድ ላይ ያሉ ክፍት ምዝገባዎች
|
MCPS የበለጠ መረጃ ያግኙ
|
|
በዚህ አድራሻ ኢሜል ያድርጉልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org
|
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ
|
©1995–2025 Montgomery County Public Schools
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ
|
|