የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ መለያ አርማ

አበይት ጉዳዮች

ኦክቶበር 16, 2025

English / español / 中文 / français / Português / 한국어 / tiếng Việt / አማርኛ

ያለውን ነባራዊ ሁኔታ መገንዘብ እና የወደፊቱን ሂደት ማዘጋጀት

የበጀት ዓመት (FY) 2027 የካፒታል በጀት እና 2027-2032 የካፒታል ማሻሻያ ፕሮግራም (CIP)፣ ኦክቶበር 14 በተካሄደው የትምህርት ቦርድ ስብሰባ ወቅት በሱፐርኢንቴንደንት ቶማስ ቴይለር የቀረበው ሀሳብ፣ በስድስት ዓመታት ውስጥ $2.7 ቢሊዮን ዶላር ይጠይቃል። ሆኖም ግን፣ የተጠየቀው የበጀት መጠን የዲስትሪክቱ መገልገያዎች ከሚፈልጉት ወጪ ውስጥ ግማሽ ያህሉን ብቻ ይሸፍናል። ይበልጥ ያንብቡ።

ከሱፐርኢንተንደንቱ የቀረበውን ለመስማት ኦክቶበር 21 በዚህ አድራሻ በአካል ተገኝተው፦ (DCPS Warehouse፣ 580 N. Stone Street Ave፣ Rockville፣ MD) እና ኦክቶበር 22 (ቨርቹዋል)በሚደረግ ውይይት ላይ ይሳተፉ።

ሙሉ 2027-2032 የቀረበ የካፒታል ማሻሻያ እቅድ

የሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ሰራተኞች ስለ ሁለተኛ ደረጃ የፕሮግራም ትንተና እና የሪጅኖችን ሞዴል ወቅታዊ መረጃ አጋርተዋል።

የሞንትጎመሪ ካውንቲ የህዝብ ትምህርት ቤቶች ማንኛውም ለውጥ እርግጠኛ እንደማይሆን ስሜት ሊኖር እንደሚችል እንገነዘባለን። ዛሬ፣ስለ ሁለተኛ ደረጃ የአካዳሚክ ፕሮግራሞች ትንተና፣ ምንም ነገር ሳይወስድ እድሎችን በመጨመር ላይ ያተኮረ፣ ስራን በተመለከተ ወቅታዊ መረጃ MCPS ለትምህርት ቦርድ አቅርቧል። ይህ ተነሳሽነት ፍትሃዊነትን ከማረጋገጥ አንፃር፣ ማንኛውም ተማሪ ዚፕ ኮዱ ምንም ይሁን ምን፣ ጠንካራ ትምህርት እና አሳታፊ ፕሮግራሞችን ማግኘት እንደሚችል በማረጋገጥ ረገድ ወደ መሰረታዊ ሽግግርን ይወስደናል። ተጨማሪ ግንዛቤ ያግኙ

የተማሪዎን አሁናዊ የትምህርት ይዘት ሪፖርት ካርዱን እንዴት መመልከት እንዳለብዎት እነሆ፣ ኖቨምበር 7 የሪፖርት ካርዶች ይወጣሉ።

ወቅታዊ የትምህርት ይዘት ሪፖርቶች በእያንዳንዱ የማርክ መስጫ ወቅት አጋማሽ ላይ በዓመት አራት ጊዜ ይዘጋጃሉ፡- ኦክቶበር 3፣ ዲሴምበር 19፣ ማርች 6, 2026፣ ሜይ 12, 2026 (ለሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች) እና ሜይ 22, 2026 (ሌሎች ተማሪዎች በሙሉ) ይወጣሉ። እነዚህን ሪፖርቶች ወላጆች/ተንከባካቢዎችParentVue ላይ ማየት ይችላሉ። እነዚህን ሪፖርቶች ParentVue ላይ ለማየት ደረጃ በደረጃ መከተል ያለብዎት መመሪያ እነሆ።

ለመጀመሪያዎቹ ሶስት የማርክ መስጫ ወቅቶች የሪፖርት ካርዶች ከሁሉም ተማሪዎች ጋር ወደ ቤት ይላካሉ። የዓመቱ የመጨረሻ ሪፖርት ካርድ በፖስታ ወደ ተማሪዎች ቤት ይላካል። 

ParentVue አካውንት ለሌላቸው ቤተሰቦች የሪፖርት ካርዶች በፖስታ ወደ ቤት ይላካሉ።

የሁለተኛ ሩብ አመት የትምህርት ቁሳቁሶችን በተመለከተ የሂሳብ ትምህርት ፖሊሲ የቅድመ ግምገማ ስብሰባዎች ተዘጋጅተዋል።

MCPS በሚቀጥለው ሳምንት ወላጆች/አሳዳጊዎች ስለ ሁለተኛው ሩብ አመት የማስተማሪያ ቁሳቁሶች ቅድመ ምልከታ ለማድረግ ሶስት የማህበረሰብ ስብሰባዎችን ያስተናግዳል። በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ፣ MCPS ሥርዓተ ትምህርቱን የበለጠ ግልጽ እና ለቤተሰብ ተስማሚ ለማድረግ ያለውን ቁርጠኝነት እና ተነሳሽነቱን አሳውቋል። “Refrigerator Curriculum” ተማሪዎች እያንዳንዱን የማርክ መስጫ ጊዜ የሚያጠኗቸውን ዋና ዋና ጭብጦች እና ፅሁፎችን በአንድ-ገጽ አሳጥሮ ያቀርባል።  

  • የሁለተኛ ደረጃ ሥርዓተ ትምህርት ሐሙስ፣ ኦክቶበር 23 ከሠዓት በኋላ 7-8:30 p.m. ይታያል። አድራሻው፦ Tilden Middle School, 6300 Tilden Lane, Rockville

  • የአንደኛ ደረጃ (ኤለመንተሪ) ሥርዓተ ትምህርት ሐሙስ፣ ኦክቶበር 23፣ ከሠዓት በኋላ 7-8:30 p.m. ቅድመ-እይታ ይካሄዳል። አድራሻው፦ Farmland Elementary School, 7000 Old Gate Road, Rockville

  • MSDE የሂሳብ ትምህርት ፖሊሲ ማክሰኞ፣ ኦክቶበር 21፣ ከሠዓት በኋላ 6:30-8 p.m. ቅድመ-እይታ ይካሄዳል። አድራሻው፦ Gaithersburg High School, 101 Education Blvd., Gaithersburg

ደንብ IFD-RA፣ የስርአተ ትምህርት ግልፅነት እና የተወሰነ የትምህርት ምዕራፍ/ክፍል እንዳይማሩ ይቅርታ እንዲደረግላቸው ስለሚቀርቡ ጥያቄዎች

ጨዋታ ቀያሪ ኮንፈረንስ ለኦክቶበር 25 ተዘጋጅቷል።

4ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያሉ ወንድ ተማሪዎች 2025 ፎል ወቅት የወጣት ወንዶች ጨዋታ ቀያሪ ኮንፈረንስ ላይ እንዲገኙ ተጋብዘዋል። ይህ ዝግጅት ቅዳሜ፣ ኦክቶበር 25 ከጠዋቱ 8 a.m. እስከ ቀትር ድረስ በሞንትጎመሪ ኮሌጅ ጀርመንታውን ካምፓስ ይካሄዳል። ይመዝገቡ/Register.

የኮንፈረንሱ አላማ የወጣት ወንዶችን ማህበራዊ-ስሜታዊ ደህንነት፣ በራስ መተማመንን እና እሴቶችን የሚገነባ እና የሚያንፅ ልምድ ለመፍጠር ነው። አንዳንዶቹ ክፍለ-ጊዜዎች የህይወት ክህሎት ተሞክሮዎችን፣ የፓነል ውይይቶችን፣ STEM ተሳትፎ፣ የፅሁፍ ውድድር እና የወላጅ አቀንቃኝነት አውደ ጥናትን ያካትታሉ። ተጨማሪ መረጃ

ትምህርት ቤቶቻችንን ማጠናከር፦ የበፊት ዳራ መፈተሽ እና የመለያ ባጅ ማሻሻል

MCPS ለሁሉም ተማሪዎች እና ሰራተኞች ደህንነት ቅድሚያ መስጠቱን ሲቀጥል የዳራ ፍተሻ፣ የጣት አሻራ፣ እና ባጅ በማጣራት ረገድ ወደፊት እየገሰገሰ ነው። ባለፈው ሳምንት ቡድናችን የኬኔዲ ክለስተር ትምህርት ቤቶችን የጎበኘን ሲሆን MCPS ሂደቱን በዲሴምበር አጋማሽ ለማጠናቀቅ ያላሰለሰ ጥረት ያደርጋል። ከዚህ በታች በድጋሚ ማጣራት የተደረገላቸውን ሰራተኞች ብዛት የሚያመለክት የእስካሁን አፈጻጸማችንን ይመለከቷል።

ሜትሪክ/Metric

ቫልዩ/Value

እስከ ዛሬ እንደገና ማጣራት የተደረገላቸው ጠቅላላ ሠራተኞ ብዛት

3,891

% የተጠናቀቀ የትምህርት ቤት ሠራተኞች

37%

# የተጠናቀቀ የትምህርት ቤቶች ብዛት

88/211

ኤይንስታይን/Einstein የትርኢት ባንድ ኦክቶበር 25 ትርኢቶችን ያቀርባል።

ቅዳሜ፣ ኦክቶበር 25 ከቀኑ 11:30 a.m.–3 p.m. በአልበርት አንስታይን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በሚካሄደው የዚህ አመት የማርሽ ባንድ ትርኢት ላይ አስራ ሁለት የሙዚቃ ባንዶች ይሳተፋሉ። የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሙዚቃ ባንዶቹ፦ ሞንትጎመሪ ብሌር፣ ጄምስ ሁበርት ብሌክ፣ ደማስከስ፣ ጆን ኤፍ ኬኔዲ፣ ኖርዝውድ፣ፔይንት ብራንች፣ ኩዊንስ ኦርቻርድ፣ ሮክቪል፣ ሴኔካ ቫሊ፣ ስፕሪንግብሩክ፣ ዋትኪንስ ሚል፣ እና አንስታይን ናቸው። ብሄራዊ መዝሙሩ የሚቀርበው MCPS የመካከለኛ ደረጃ ት/ቤት Massed ባንድ ሲሆን የአመቱ ምርጥ መምህር ሜጋን ካምቤል "Teacher of the Year Megan Campbell" ትመራዋለች። ከሜሪላንድ ዩኒቨርሲቲ ማርሽ ባንድ፣የሜሪላንድ አስደናቂ ድምፅ የእንግዶች ትርኢትም ይኖራል።

ይህ ዝግጅት ነፃ እና ለህዝብ ክፍት ነው። አድራሻ፦ 11135 Newport Mill Road in Kensington. በአስቸጋሪ የአየር ሁኔታ ምክንያት የሚደረጉ ለውጦች "Fine Arts X feed @MCPSArts" ላይ ይለጠፋሉ።

መታሰቢያ እና እርቅ የሚዘከርበት ወር

የሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ተማሪዎች ስለአካባቢው አፍሪካን አሜሪካን ታሪክ እንዲያውቁ እና የአካባቢውን የነጻነት ቀን በዓል እንዲደግፉ እድል ለመስጠት የአራተኛው ዓመት የመታሰቢያ እና የእርቅ ወር ይከበራል።

የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ሐሙስ፣ ኖቨምበር 6 ከሠዓት በኋላ 6:30-8:30 p.m. በሚካሄድ በማህበረሰብዎ ላይ ለውጥ ለማምጣት የሚያስችልኦንላይን የለውጥ ሐዋርያነት አውደ ጥናት ላይ በመሳተፍ ሁለት የተማሪ አገልግሎት ትምህርት (SSL) ሰአት ማግኘት ይችላሉ። ዋና ተናጋሪው Maryland Delegate Greg Wims/የሜሪላንድ ተወካይ ግሬግ ዊምስ ናቸው። ተጨማሪ ግንዛቤ ያግኙ።

በተጨማሪም ተማሪዎች ቅዳሜ፣ ኦክቶበር 26 ከቀትር እስከ 3 p.m. በሚካሄደው የነጻነት ቀን በዓል ላይ ተገኝተው በነጻ እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል። አድራሻው፦ Button Farm’s Living History Center, 16820 Black Rock Road in Germantown. ተማሪዎች እስከ ሶስት SSL ሰዓት ማግኘት ይችላሉ።

የዊንተር (የክረምት) ጃኬት እርዳታ በመሰብሰብ ላይ ነው

የቅድመ መዋዕለ ሕፃናት እና ሄድ ስታርት ቢሮዎች ለተቸገሩ ተማሪዎች አዳዲስ ጃኬቶችን እንዲለግሱ እየጠየቁ ነው። ለትናንሽ ልጆች ኮፍያ፣ ጓንት፣ እና ቦት ጫማዎች ያስፈልጋቸዋል። መጠናቸው 4፣ 5፣ እና 6 የሆነ የወንዶች እና የሴቶች ጃኬት ልብስ ልገሳ በጣም ያስፈልጋል። የተጠቆሙ ጃኬት ልብሶች Head Start/Pre-K Amazon wish list ላይ ሊገኙ ይችላሉ።

የጃኬት ልብሶቹን በዚህ አድራሻ መላክ ይቻላል፦ Rocking Horse Road Center, 4910 Macon Road, Room 141 in Rockville. ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 9 a.m.–5 p.m., ድረስ በአካል ተገኝተው ወይም በኦንላይን የታዘዘውን በቀጥታ Rocking Horse Road Center፣ ለሊሳ ኮንሎን/Lisa Conlon. ማስረከብ ይችላሉ።

ጥያቄ ካለዎት በስልክ ቁጥር 240-550-2615 ደውለው Lisa Conlonያነጋግሩ።

የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ውድድር ወቅት ተቃርቧል!

የፎል ወቅት ውድድር እና የአትሌቲክስ ዝግጅቶች ቅዳሜ፣ ኦክቶበር 18 ይጀምራሉ። ስለ ፕሮግራሙ ለማወቅ እና ትኬቶችን ለመግዛት GoFanከፍተው MCPS የሚለው ላይ ይፈልጉ።

ስለ ትምህርት ቤት ምግብ ማወቅ ያለብዎት

ለተማሪ ስኬት የተመጣጠነ ምግብ ወሳኝ ነው! MCPS የምግብ እና የተመጣጠነ አልሚ ምግብ አገልግሎት ክፍል በየዓመቱ 18 ሚሊዮን በላይ ምግቦችን ያቀርባል። ለቁርስ ወይም ለምሳ የሚዘጋጀው ምንድነው ብለው ያስባሉ? montgomeryschoolsmd.org ከፍተው “menus” የሚለው ላይ ይመልከቱ። እዚያ ላይ የእያንዳንዱን ትምህርት ቤት የምግብ ዝርዝር ከነስዕሉ የምግቦቹን አይነት መረጃ ማግኘት ይችላሉ። እዚህ ይበልጥ ያንብቡ

Watch in Spanish | French | Chinese | Vietnamese | አማርኛ/Amharic | Korean | Portuguese

በዲጂታል አለም ውስጥ የቤተሰብዎን ደህንነት ይጠብቁ

የትምህርት ቴክኖሎጂ ዲፓርትመንት በኦክቶበር እና በኖቬምበር መጀመሪያ ላይ ሀሙስ፣ 6-7 ፒ.ኤም ነፃ የሳይበር ደህንነት ግንዛቤ ዌቢናር ተከታታይ ፕሮግራም ያቀርባል። በዲጂታል አለም የቤተሰብዎን ደህንነት ለመጠበቅ ቀላል እና ጠቃሚ ስልቶችን ይማሩ። ተጨማሪ ግንዛቤ ያግኙ

ምናልባት አምልጥዎት ከሆነ…

"EdTalk" የቅርብ ጊዜ አምድ ወጥቷል፣ እና በትምህርት ላይ ስላለው ስነጥበብ/አርትስ ውይይት ያደርጋል። ይመልከቱት።

2026 የዜጎች የክብር ሽልማት እጩዎችን ለመጠቆም አሁን ክፍት ነው።

"Congressional Medal of Honor Society" ለ 2026 ሽልማቶች እጩዎች እንዲጠቆሙ ይፈልጋል—ሁለቱ ለወጣቶች የተዘጋጁ ሽልማቶች ናቸው።

  • የወጣት ጀግና ሽልማት የሚሰጠው እድሜያቸው 8 እስከ 17 አመት የሆኑ አሜሪካውያን በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ላሳዩት ቆራጥነት እና ድፍረት እውቅና የሚሰጥበት ሽልማት ነው።

  • የወጣት አገልግሎት ሽልማቱ 8-17 አመት እድሜ ያላቸው አሜሪካውያን የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሲሰጡ ከራሳቸው በፊት ሌሎችን በማስቀደማቸው አክብሮት ለመስጠት የተዘጋጀ ሽልማት ነው።

ለማመልከት ቀነ-ገደቡ ሰኞ፣ ዲሴምበር 1 ነው፣ የሽልማት ሥነ-ሥርዓት ረቡዕ፣ ማርች 25, 2025 በዋሽንግተን ዲሲ ይካሄዳል።

በዜና ገጾቻችን ላይ የቅርብ ጊዜ ዘገባዎችን ይመልከቱ

ከእኛ ጋር ያለዎትን ግንኙነት ይቀጥሉ

ግንኙነትዎ ይቀጥል

በመካሄድ ላይ ያሉ ክፍት ምዝገባዎች

MCPS የበለጠ መረጃ ያግኙ

Facebook Twitter Instagram YouTube Flickr LinkedIn
በዚህ አድራሻ ኢሜል ያድርጉልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org
Montgomery County Public Schools የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ
©1995–2025 Montgomery County Public Schools