የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ መለያ አርማ

አበይት ጉዳዮች

ኦክቶበር 23, 2025

English / español / 中文 / français / Português / 한국어 / tiếng Việt / አማርኛ

የካፒታል በጀት የማህበረሰብ ውይይት መድረኮች እና የስራ ክፍለ ጊዜዎች ተዘጋጅተዋል።

ለበጀት ዓመት (FY) 2027 የካፒታል በጀት እና FY 2027-2032 የካፒታል ማሻሻያ ፕሮግራም (CIP) በስድስት ዓመታት ውስጥ $2.7 ቢሊዮን ዶላር ተጠይቋል። ሆኖም ግን፣ የተጠየቀው የበጀት መጠን የዲስትሪክቱ መገልገያዎች ከሚፈልጉት ወጪ ውስጥ ግማሽ ያህሉን ብቻ ይሸፍናል። ተጨማሪ ያንብቡ እና መጪዎቹን የማህበረሰብ ውይይት መድረኮች እና የስራ ክፍለ ጊዜዎች ይቀላቀሉ።

መጪው ስለ ድንበር ጥናት ውይይት እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ፕሮግራሞች ትንታኔ ክፍለ ጊዜ እንዳያመልጥዎት ይሳተፉ።

በሚቀጥሉት ጥቂት ሳምንታት ውስጥ፣ MCPS በወሰን ጥናቶች እና የአካዳሚክ መርሃ ግብሮች ትንተና ጥረቶች ላይ በተከታታይ የጥያቄ እና መልስ ክፍለ ጊዜዎች ላይ እንዲሳተፉ ማህበረሰቡን እየጋበዘ ነው። መቼ እና የት እንደሚካሄዱ ይመልከቱ። 

በተጨማሪም እሮብ፣ ኖቨምበር 5 ከቀኑ 6:30 p.m. የስፓንሽኛ ተናጋሪ ቤተሰቦች ቨርቹዋል “Pregúntale a MCPS” በፌስቡክ ላይ በቀጥታ መሣተፍ ይችላሉ። ይህ ክፍለ ጊዜ በወሰን ጥናት አማራጮች እና በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አዲስ የአካዳሚክ ፕሮግራሞች ላይ ያተኩራል። 

የትምህርት ቤት ማሻሻያ እቅዶች አሁን በኦንላይን ይገኛሉ።

ስለ ሁሉም የሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ት/ቤቶች የትምህርት ቤት ማሻሻያ እቅዶች (SIPs) አሁን በኦንላይን በሦስት ዘርፎች ይገኛሉ፦

  •  SIP webpage/በይነመረብ ላይ

  •  በእያንዳንዱ ትምህርት ቤት ድረ ገጽ ላይ ባለው የትምህርት ቤት መረጃ በይነመረብ ላይ– ለምሳሌ፦ Arcola ES

  •  በትምህርት ቤትSchool-Odex ገጾች (በእያንዳንዱ ትምህርት ቤት) –ለምሳሌ፦Arcola School-Odex በሪፖርት ትር ስር።

SIP ጥንካሬዎችን ለመለየት፣ ተግዳሮቶችን ለመፍታት፣ እና የተማሪዎችን ውጤት ለማሳደግ እና አጠቃላይ የት/ቤት አፈጻጸምን ለማሻሻል የስኬት ስትራቴጂዎችን ለማዘጋጀት መረጃን የሚጠቀሙ የማስተማሪያ እቅዶች ናቸው።

የአእምሮ ጤና ግንዛቤ ሳምንት ኖቨምበር 3-8 ይካሄዳል።

የልዩ ድጋፍ አገልግሎቶች ክፍል እና የሞንትጎመሪ ካውንቲ ትምህርት ቤት ሳይኮሎጂስቶች ማህበር 2025 የአእምሮ ጤና ግንዛቤ ሳምንት (MHAW) ኖቨምበር 3-8 በጋራ ያስተናግዳሉ። የአእምሮ ጤና እና ደህንነት ትርዒት ቅዳሜ፣ ኖቨምበር 8 ከቀኑ 10 a.m.-2 p.m. በጌትስበርግ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ይካሄዳል። አድራሻ፦ Gaithersburg High School 101 Education Blvd. /in Gaithersburg። ይህ የነፃ ዝግጅት ለሰራተኞች፣ ለተማሪዎች፣እና ለቤተሰቦች ክፍት ነው፣ አውደ ጥናቶችን፣ የማህበረሰብ አጋሮች ስለአይምሮ ጤና እና ደህንነት የሚያጋሩትን መረጃዎች፣ የተማሪዎች መድረክ፣ እና ዳንስ፣ ዙምባ እና ዮጋ ያካትታል። RSVP/ለመሳተፍ ይመዝገቡ

የሪፍሪጅሬተር ከሪኩለም "Refrigerator Curriculum" የሁለተኛ ሩብ አመት ሰነዶች አሁን ይገኛሉ።

የሪፍሪጅሬተር ከሪኩለም "Refrigerator Curriculum" — የሁለተኛው ሩብ ዓመት መማሪያ ቁሳቁሶች ከኖቨምበር 4 ጀምሮ - በኦንላይን ማግኘት ይቻላል። ይህ ሥርዓተ ትምህርት ተማሪዎች በእያንዳንዱ የማርክ መስጫ ጊዜ ምን እንደሚማሩ የሚያመላክት ባለ አንድ ገጽ አጠቃላይ መግለጫ ነው። እነዚህ መመሪያዎች ቤተሰቦች ስለ ቁልፍ የትምህርት ጭብጦች እና ጽሑፎች እንዲያውቁ፣ በተማሪዎቻቸው ትምህርት ላይ ተሳትፎ እንዲኖራቸው እና ካስፈለገም ጽሑፉ ከሃይማኖታዊ አመለካከቶች ጋር የሚጋጭ ከሆነ አማራጭ የትምህርት ስራዎችን እንዲጠይቁ ይረዷቸዋል።

በተጨማሪም፣ ቤተሰቦች ቁሳቁሶችን አስቀድመው ለማየት ዛሬ ማታበማህበረሰብ የውይይት ስብሰባ ላይ መገኘት ይችላሉ። እዚህ ይበልጥ ያንብቡ

የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች "Financial Aid" የገንዘብ ድጋፍ ወርክሾፖችን ያካሄዳሉ።

የሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች ለኮሌጅ ክፍያ ስላሉት አማራጮች እንዲያውቁ ለመርዳት"financial aid" የፋይናንስ እርዳታ አውደ ጥናቶችን እያካሄዱ ነው። ወላጆች በማንኛውም ትምህርት ቤት በመገኘት በፋይናንስ አውደ ጥናት ላይ መሳተፍ ይችላሉ። 

"Financial aid" የፋይናንስ እርዳታ ለኮሌጅ እና ለስራ ስልጠና ለመክፈል ለተማሪዎች የሚሰጥ ገንዘብ ሲሆን በብድር፣ በእርዳታ፣ በስኮላርሺፕ ወይም ለስራ ጥናት ፕሮግራሞች የሚከፋፈል ነው። ሁለት ሦስተኛ ያህሉ የሙሉ ጊዜ ተማሪዎች ኮሌጅ የሚገቡት በፋይናንሺያል እርዳታ ነው። ተጨማሪ ግንዛቤ ያግኙ

 

ትምህርት ቤቶቻችንን ማጠናከር፦ የበፊት ዳራ መፈተሽ እና የመለያ ባጅ ማሻሻል

MCPS ለሁሉም ተማሪዎች እና ሰራተኞች ደህንነት ቅድሚያ መስጠቱን ሲቀጥል የዳራ ፍተሻ፣ የጣት አሻራ፣ እና ባጅ በማጣራት ረገድ ወደፊት እየገሰገሰ ነው። ባለፈው ሳምንት ቡድናችን የብሌክ እና የውተን ትምህርት ቤቶችን ክለስተር የጎበኘ ሲሆን MCPS ሂደቱን እስከ ዲሴምበር አጋማሽ ድረስ ለማጠናቀቅ ጥረት ማድረግ ይቀጥላል። ከዚህ በታች በድጋሚ ማጣራት የተደረገላቸውን ሰራተኞች ብዛት የሚያመለክት የእስካሁን አፈጻጸማችንን ይመለከቷል።

ሜትሪክ/Metric

ቫልዩ/Value

እስከ ዛሬ እንደገና ማጣራት የተደረገላቸው ጠቅላላ ሠራተኞ ብዛት

4,221

% የተጠናቀቀ የትምህርት ቤት ሠራተኞች

40%

# የተጠናቀቀ የትምህርት ቤቶች ብዛት

97/211

የዊንተር/የክረምት አትሌቲክስ ምዝገባ አሁን ተከፍቷል

ለመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለክረምት/ዊንተር አትሌቲክስ ምዝገባ ሰኞ፣ ኦክቶበር 27 እኩለ ቀን ላይ ParentVue ምዝገባ ይጀመራል። የመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ስፖርት የወንዶች እና የሴቶች ቅርጫት ኳስ ያካትታል። ተጨማሪ መረጃ

ስለ ትምህርት ቤት አውቶቡስ ደህንነት ማወቅ ያለብዎት ጉዳይ

በአውቶቡስ መጓዝ ልዩ ድጋፍ ነው፣ ስለዚህ ህጎቹን በማክበር መጓዝ አስፈላጊ ነው — አውቶቡስ ውስጥ ከገባችሁ በኋላ መቀመጫችሁ ላይ ተቀምጣችሁ ቆዩ፣ አውቶቡስ ውስጥ የመተላለፊያ መንገዱን አትዝጉ፣ እና የአውቶቡስ ነጂው(ዋ)ን ሁል ጊዜ አዳምጡ። አስታውሱ፣ አውቶቡስ ልክ እንደ ተንቀሳቃሽ መማሪያ ክፍል ነው፣ ስለዚህ ጥሩ ስነምግባር የሁሉንም ሰው ደህንነት ለመጠበቅ ይረዳል። ወላጆች፣ እባካችሁ እነዚህን ደንቦች በቤት ውስጥ ከልጆቻችሁ ጋር ተነጋግራችሁ በማጠናከር እርዷቸው፣ እና ጧት እና ከሰዓት በኋላ አምስት ደቂቃ ቀደም ብላችሁ ወደ አውቶቡስ ፌርማታው ለመድረስ ሞክሩ። ይበልጥ ያንብቡ።

Watch in Spanish | French | Chinese | Vietnamese | አማርኛ/Amharic | Korean | Portuguese

እንዲሁም፣ የረዥም ጊዜየአውቶቡስ ሹፌር ሁጎ ካሪዮን/Hugo Carrion ለተማሪዎች በየቀኑ የሚያሳየውን እንክብካቤ እና ቁርጠኝነት የሚገልፅ አጭር ቪዲዮ ይመልከቱ።

ለተማሪዎች እና ለማህበረሰብ የቀረቡ እድሎች

C-SPAN StudentCam Competition: 6ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች C-SPAN ዓመታዊ ብሔራዊ የቪዲዮ ዶክመንተሪ StudentCam ውድድር ላይ እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል። በዚህ አመት ተማሪዎች “Exploring the American Story through the Declaration of Independence” ርዕስ ላይ በመመርኮዝ 5 እስከ 6 ደቂቃ የሚፈጅ የቪዲዮ ዶክመንተሪ እንዲሰሩ ተጋብዘዋል። ከፍተኛው ሽልማት $5,000 ነው። የመጨረሻው ቀነገደብ ማክሰኞ፣ ጃኑዋሪ 20, 2026 ነው።

"Choose Respect Video Contest"/አክብሮትን መምረጥ የቪዲዮ ውድድር ለሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ክፍት ነው፣ ይህ ውድድር ታዳጊዎች በወጣቶች መካከል ስለ ፍቅር ጓደኝነት ጥቃት ግንዛቤ ለማዳበር የሚረዳ ኦሪጅናል ቪዲዮ እንዲፈጥሩ ያበረታታል። ቪዲዮዎቹ በእንግሊዝኛ ወይም በስፓንሽኛ ሊሆኑ ይችላሉ፤ እና 50-70 ሰከንድ ርዝመት ሊኖራቸው ይገባል። ከፍተኛው ሽልማት $1,000 ያስገኛል። የመጨረሻው ቀነገደብ እሁድ፣ ፌብሩዋሪ 15, 2026 ነው።

የመታሰቢያ እና የእርቅ ወር

  • ተማሪዎች ቅዳሜ፣ ኦክቶበር 25 ከቀትር እስከ 3 p.m. የነጻነት ቀን ላይ የሚዘከርበት ዝግጅት ላይ በመሳተፍ እስከ ሶስት SSL ሰዓቶችን ያግኙ። አድራሻ፦ Button Farm’s Living History Center, 16820 Black Rock Road in Germantown

  • ቅዳሜ፣ ኖቨምበር 1 ከቀኑ 11 a.m.-4 p.m. "Sandy Spring Slave Museum and African Art Gallery" ኦፕን ሀውስ እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል። ሙዚየሙ የሚገኝበት አድራሻ፦ The museum is at 18524 Brooke Road in Sandy Spring ተጨማሪ ግንዛቤ ያግኙ።

  • ሐሙስ፣ ኖቨምበር 6 ከቀኑ 6:30-8:30 p.m. በማህበረሰብህ ውስጥ ለውጥ ስለ ማምጣት በኦንላይን ጨዋታ ቀያሪ አውደ ጥናት ላይ በመገኘት ሁለት የተማሪ አገልግሎት ትምህርት (SSL) ሰዓት ያግኙ።የበለጠ ግንዛቤ ያግኙ።

ቅዳሜ፣ ኦክቶበር 25 ከቀኑ 10 a.m.-2 p.m."Walking for a Good Cause: The 21st annual Step UP for Down Syndrome Walk and Celebration"ዝግጅት ከዚህ ቀጥሎ ባለው አድራሻ ይካሄዳል። አድራሻ፦ Falls Road Local Park, 12600 Falls Road in Potomac ይህ ዝግጅት ማካተትን ለማበረታታት እና ለሞንትጎሞሪ ካውንቲ ዳውን ሲንድሮም ኔትወርክ ገንዘብ ለማሰባሰብ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ያሰባስባል።

"KID Museum" ኪድ ሙዚየም አለልዎት

KID ሙዚየም ትምህርት ቤቶች በሚዘጉበት ቀናት ካምፖች አሉት። በቀን የሚካሄዱ ካምፖች ከመዋዕለ ህጻናት እስከ 5ኛ ክፍል ለሚገኙ ተማሪዎች ሰኞ፣ ኖቨምበር 3 ከጠዋቱ 9 am.-4 p.m ክፍት ናቸው። አድራሻ፦ KID Museum is located at 3 Bethesda Metro Center in Bethesda ለመሳተፍ ክፍያ ይኖራል።

በተጨማሪም፣ በሙዚየሙ በመላው ኖቨምበር ወር " Native American Heritage Month" ይከበራል። እሑድ፣ ኖቨምበር 2 ከጠዋት 10:30 a.m.-12:30 p.m ሞንትጎሞሪ ብሌር ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ማያ ክለብ "Montgomery Blair High School's Club Maya" የሚያቀርበውን ስለ ማያ ቋንቋ እና ዳንስ ለማወቅ እንድትሳተፉ ተጋብዛችኋል። 

ማሳሰቢያ

  • በኦንላይን አጠቃቀም የቤተሰብዎን ደህንነት ስለመጠበቅ የበለጠ ለመረዳት ኦክቶበር 23፣ 30፣ እና ኖቨምበር 6 ስለ ከቀኑ 6-7 p.m. በሚካሄዱ የሳይበርሴፍቲ ዌብናርስይቀላቀሉን።

  • ቅዳሜ፣ ኦክቶበር 25 ከቀኑ 11:30 a.m.–3 p.m.የማርቺንግ የሙዚቃ ባንድ ትርኢት12 የሙዚቃ ባንዶች በዚህ አመት ነጻ ዝግጅት ላይ ይሳተፋሉ። አድራሻ፦ አልበርት አንስታይን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት Albert Einstein High School, 11135 Newport Mill Road in Kensington. በአስቸጋሪ የአየር ሁኔታ ምክንያት የሚደረጉ ለውጦች "Fine Arts X feed @MCPSArts" ላይ ይለጠፋሉ።

  • ቅዳሜ፣ኦክቶበር 25 ከቀኑ 8 a.m. ጀምሮ ቀትር ድረስ 4ኛ እስከ 12ኛ ክፍል የሚማሩ ወንድ ተማሪዎችን የሚመለከትጨዋታ ቀያሪ ኮንፈረንስበሞንትጎሞሪ ኮሌጅ ጀርመንታወን ካምፓስ ይካሄዳል። አድራሻ፦ Montgomery College, Germantown Campus

በዜና ገጾቻችን ላይ የቅርብ ጊዜ ዘገባዎችን ይመልከቱ

  • 50 ዓመታትን በመንገድ ላይ፡ የአውቶቡስ ሹፌር ቪኪ ኦውንስ/Vickie Owens MCPS በምታሽከረክረው በእያንዳንዱ ማይል ጉዞ ደስታ እንደሚሰማት ትገልጻለች፣ይህንን ሥራ ስታከናውን የቆየችው ከ 1975 ጀምሮ ነው።

  • ከደወል ባሻገር ተማሪዎችን መምራት፡ ኤ.ማሪዮ ሎደርማን መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት A. Mario Loiederman Middle School "Excel Beyond the Bell" initiative ዳይሬክተር እንደመሆኗ፣ ራሞን ፓዝሚኖ/Ramon Pazmino ከትምህርት በኋላ ፕሮግራሞች ለላቲኖ ተማሪዎች ምን ያህል ጠቀሜታ እንዳለው በድጋሚ ገልጻለች።

ከእኛ ጋር ያለዎትን ግንኙነት ይቀጥሉ

ግንኙነትዎ ይቀጥል

በመካሄድ ላይ ያሉ ክፍት ምዝገባዎች

MCPS የበለጠ መረጃ ያግኙ

Facebook Twitter Instagram YouTube Flickr LinkedIn
በዚህ አድራሻ ኢሜል ያድርጉልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org
Montgomery County Public Schools የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ
©1995–2025 Montgomery County Public Schools