አበይት ጉዳዮች
ኖቨምበር 13, 2025
|
|
አትዘግዩ፤ የዳሰሳ ጥናቱን ዛሬውኑ ይፈጽሙ!
MCPS በትምህርት፣ በኮሙኒኬሽን፣ እና በትምህርት ቤት እና በዲስትሪክቱ ስላላቸው አጠቃላይ እርካታ ልምዳቸውን እና ሀሳባቸውን እንዲያካፍሉ ወላጆችን/ተንከባካቢዎችን ይጋብዛል። የትምህርት አሰጣታችንን በማሻሻል እና ትምህርት ቤቶቻችን እና ዲስትሪክታችን ለሁሉም ተማሪዎች፣ ለሰራተኞች እና ለቤተሰቦች የበለጠ ተቀባይነት ያለው ቦታ እንዲሆን ማድረግ እንፈልጋለን።
የዳሰሳ ጥናቶች አሁን በስምንት ቋንቋዎች ይገኛሉ።
የዳሰሳ ጥናቱ የልጅዎን የተማሪ መታወቂያ ቁጥር ይጠይቃል። የልጅዎን መታወቂያ ቁጥር ParentVue ከፍተው የተማሪ መረጃ ላይ ጠቅ በማድረግ ማግኘት ይችላሉ። የሚሰጡት ምላሽ በሚስጥራዊነት ይጠበቃል፤የተማሪ መታወቂያው የሚያስፈልግበት ምክንያት ምላሾቹን ከትክክለኛው ትምህርት ቤት ጋር የሚገናኙ መሆናቸውን ለማረጋገጥ ይረዳናል።
|
|
|
የፕሮግራሞች ትንተና እና የሪጅን ሞዴሎች - ይህ ሥራ ለምን አስፈላጊ ሆነ - እና ለምን ማቆየት አልተቻለም
MCPS በእያንዳንዱ ማህበረሰብ ውስጥ ያለ እያንዳንዱ ተማሪ የርቀት ወይም የዕድል እንቅፋቶች ሳይገድቡት ከፍላጎቱ እና ከዓላማው ጋር የሚጣጣሙ ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን የትምህርት ፕሮግራሞች ማግኘት እንዲችል ለማድረግ ቁርጠኛ ነው። እየተካሄደ ያለው የሁለተኛ ደረጃ ፕሮግራሞች ትንተና እና የታቀዱት የሪጅን ሞዴሎች ወደ ፍትሃዊ ስርዓት የሚያመሩ አስፈላጊ እርምጃዎች ናቸው። ይህ በተማሪዎች፣ በሠራተኞች፣ እና በቤተሰቦች ተሳትፎ እና በግልፅ ውይይቶች እና የማህበረሰብ አስተያየቶች ታክለውበት የተገነባ የጋራ ጥረት ነው። ይበልጥ ያንብቡ
|
|
|
|
|
MCPS በፌዴራል ከምሳ እና ከሙያ ግንኙነቶች ታግደው የነበሩትን ቤተሰቦችን ተቀብሏል።
ባለፈው ሳምንት፣ በዲስትሪክቱ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች በፌዴራል መንግሥት ከሥራ የተባረሩ ሠራተኞች ወላጆችን እና አሳዳጊዎችን ከተማሪዎቻቸው ጋር ምሳ እንዲበሉ ጋብዘዋል። ወደ 1,600 የሚጠጉ ሰዎች ምላሽ የሰጡ ሲሆን ወደ 1,900 የሚጠጉ ወላጆች እና አሳዳጊዎች ከልጆቻቸው ጋር ምሳ ለመብላት ተገኝተዋል። በተመሳሳይ ጊዜ፣ በዲስትሪክቱ ውስጥ የሥራ ዕድሎችን ለመፈለግ 120 በላይ እንግዶች በማዕከላዊ ቢሮ የሥራ አውደ ርዕይ ላይ ተገኝተዋል።
ፎተግራፎችን እና ቪዲዮውን ይመልከቱ።
|
|
|
የምረቃ ሂደትን መከታተል
ለመጀመሪያው የማርክ መስጫ ወቅት ወላጆች የተማሪ ሪፖርት ካርዶች ይደርሳቸዋል። ወላጆች የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎቻቸው ወደ ምረቃ የሚያደርጉትን ግስጋሴ ለመከታተል እንዲረዳቸው የተማሪ ውጤት እና የመመረቂያ ክሬዲት ሪፖርት ወደ ቤት መላክ እንዲችሉ ወደ ትምህርት ቤቶች ደርሰዋል። ይህ ሪፖርት፣ ከ10ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ላሉ ወላጆች የተላከ ሲሆን፣ Grade Point Average እና Weighted Grade Point Average፣ የኮርስ ውጤቶች እና ክሬዲቶች እንዲሁም የተማሪ አገልግሎት ትምህርት ሰዓቶችን ማጠቃለያ ውጤት ያካትታል። ይበልጥ ያንብቡ።
|
|
|
የታንክስጊቪንግ ሳምንት መርሀ ግብር እና በትምህርት ገብታ ላይ መገኘት
ትምህርት ቤቶች ሰኞ፣ ኖቨምበር 24 እና ማክሰኞ፣ ኖቨምበር 25 ተማሪዎችን ቀደም ብለው እንደሚለቁ የተሰጠ ማሳሰቢያ። ተማሪዎች ከበዓል ዕረፍት በፊት በእነዚህ ቀናት ትምህርት ቤት ተገኝተው በትክክለኛው መንገድ ስራቸውን ማጠናቀቅ ይጠበቅባቸዋል።
ለታንክስጊቪንግ በዓል ትምህርት ቤቶች እና መስሪያ ቤቶች ከረቡዕ፣ ኖቬምበር 26, እስከ አርብ፣ ኖቬምበር 28 ዝግ ይሆናሉ።
አስፈላጊ የሆኑ ቀኖችን ለማግኘት እና የትምህርት ቤት ካላንደርን በተመለከተ ወቅታዊ መረጃ ለማግኘት የሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ የትምህርት ቤት ካለንደር"MCPS School Calendar" ይመልከቱ።
|
|
|
ስለ 2026-2027 የትምህርት ቤት የቀን መቁጠሪያ (ካለንደር) አስተያየትዎን ያጋሩን።
MCPS የትምህርት ቤት የቀን መቁጠሪያ 2026-2027 (ካለንደር) እያዘጋጀ ስለሆነ፣ ዲስትሪክቱ ከእርስዎ ተጨማሪ አስተያየት ግብዓት ማግኘት ይፈልጋል!
እባክዎ ለትምህርት አመት 2026-2027 በታቀደው መደበኛ የቀን መቁጠሪያ ላይ ያለዎትን አስተያየት ለማጋራት ይህንን ሁለተኛ የዳሰሳ ጥናት ይሙሉ።
የካላንደር ዝግጅቱን ሂደት ለማዳበር የእርስዎ ግብረመልስ አስፈላጊ ነው። MCPS የትምህርት ፍላጎቶችን፣ ለአሠራር አመቺ ሁኔታዎችን፣ በስቴት ህግ የተደነገጉ ትምህርት ቤቶች መዘጋት ያለባቸውን ጊዜያት፣ ዝቅተኛውን የትምህርት ቀናት እና የክሬዲት ሰዓት መስፈርቶችን ማሟላት፣ ከባድ የአየር ሁኔታ እና ሌሎች ድንገተኛ አደጋዎችን፣ የሰራተኞች የሙያ ማዳበር ቀናትን፣ እና ተማሪዎች ቀደም ብሎ የሚለቀቁባቸውን ቀናት ከግምገማ መርሃ ግብሮች ጋር በተሣለጠ ሁኔታ ይዘጋጃል።
የዳሰሳ ጥናቱን ይሙሉ።
|
|
|
የትምህርት ቦርድ BOE ስለ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች አጠቃቀም ከማህበረሰቡ አስተያየት ማግኘት ይፈልጋል።
የሞንትጎመሪ ካውንቲ የትምህርት ቦርድ በቦርድ ፖሊሲ IGS፣ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ከትምህርት አሰጣጥ ጋር ለማዋሃድ የሚረዱ መመሪያዎችን ለማዘመን በቀረቡት ማሻሻያዎች ላይ የማህበረሰብ አስተያየት እንዲሰጥበት እየጠየቀ ነው። ፖሊሲው ከኦክቶበር 27, 2025 ጀምሮ አስተያየት እንዲሰጥበት ቀርቧል። የሕዝብ አስተያየት እስከ ሰኞ፣ ጃንዋሪ 26, 2026 ድረስ መቅረብ አለበት።
ረቂቅ ፖሊሲውን ይገምግሙ እና አስተያየት ይስጡ።
|
|
|
SNAP ላይ የተደረጉ ለውጦች የትምህርት ቤት ምግቦችን የሚነካው እንዴት ነው?
"Supplemental Nutrition Assistance Program (SNAP)" ስር በቀጥታ ነፃ ምግብ እንዲያገኙ የተፈቀደላቸው ተማሪዎች 2025-2026 የትምህርት አመት ለቀሪው ጊዜ የምግብ ጥቅማጥቅሞችን ማግኘታቸውን ይቀጥላሉ። አዲስ SNAP ጥቅማጥቅሞችን የማግኘት መብት ያላቸው ተማሪዎች ማመልከቻዎቻቸው ሲጠናቀቁ በዚህ የትምህርት ዓመት ለነፃ የትምህርት ቤት ምግቦች ብቁ ይሆናሉ። ከሥራ የተባረሩ ወላጆች/አሳዳጊዎች ልጆቻቸው ነፃ እና ቅናሽ ዋጋ ያለው ምግብ እንዲያገኙ እዚህ ማመልከት ይችላሉ። ይበልጥ ያንብቡ።
|
|
|
|
|
ለተማሪዎች የተዘጋጁ እድሎች
-
በግልጽ ይናገሩ፤ ሕይወት ያድኑ፦ በአሥራዎቹ ዕድሜ ላይ የሚገኙ ወጣቶች የኦፒዮይድ/ፌንታኒል አላግባብ መጠቀምን እና ከመጠን በላይ የመውሰድን አደጋዎች ግንዛቤ ለማስጨበጥ ኦሪጅናል ቪዲዮ በመፍጠር ሕይወት አድን ትምህርት ሰጪ የሆነ ማስገንዘቢያ ያቅርቡ። የመጨረሻው ቀን እሑድ፣ ዲሰምበር 7 ነው።
-
BOLT Leadership Academy ቦልት የአመራር አካዳሚ፦ ይህ ፕሮግራም የአመራር አቅማቸውን በማዳበር እና የአስተዳደር ክህሎት ለማጠናከር ለሚፈልጉ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመጀመሪያ አመት ተማሪዎች እና ሶፎሞር ተማሪዎች ክፍት ነው።
-
C-SPAN StudentCam Competition: 6ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች C-SPAN ዓመታዊ ብሔራዊ የቪዲዮ ዶክመንተሪ StudentCam ውድድር ላይ እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል። ተማሪዎች “Exploring the American Story through the Declaration of Independence.” በተሰኘ ርዕስ ላይ የቪዲዮ ዘጋቢ ፊልም አዘጋጅተው ለውድድር እንዲያቀርቡ ተጠይቀዋል። ከፍተኛው ሽልማት $5,000 ነው። የመጨረሻው ቀነገደብ ማክሰኞ፣ ጃኑዋሪ 20, 2026 ነው።
-
"Choose Respect Video Contest"/አክብሮትን መምረጥ የቪዲዮ ውድድር ለሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ክፍት ነው፣ ይህ ውድድር ታዳጊዎች በወጣቶች መካከል ስለ ፍቅር ጓደኝነት ጥቃት ግንዛቤ ለማዳበር የሚረዳ ኦሪጅናል ቪዲዮ እንዲፈጥሩ ያበረታታል። ቪዲዎችን የሚያዘጋጁት በእንግሊዝኛ ወይም በስፓንሽኛ ቋንቋ ሊሆን ይችላል። ከፍተኛው ሽልማት $1,000 ያስገኛል። የመጨረሻው ቀነገደብ እሁድ፣ ፌብሩዋሪ 15, 2026 ነው።
-
"America’s Field Trip"የአሜሪካ ጉዞ፡ ይህ ውድድር 3ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች አሜሪካ ለእነሱ ምን ማለት እንደሆነ ያላቸውን አመለካከት ለማካፈል ጽሑፍ ወይም የስነጥበብ ስራ እንዲያቀርቡ ይጋብዛል — እና በአገሪቱ ውስጥ ባሉ እጅግ ታዋቂ ታሪካዊ እና ባህላዊ ወደሆኑ ቦታዎች የመስክ ጉዞ ልምዶችን እንዲያገኙ የመጓዝ እድል ያገኛሉ። ቀነ ገደቡ ማርች 30, 2026 ነው።
-
የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች በምርጫ ሰራተኝነት እንዲሳተፉ ይፈለጋል፦ ይህ የሞንትጎመሪ ካውንቲ የምርጫ ቦርድ ፕሮግራም ተማሪዎች ጁን 2026 በሚካሄደው "Gubernatorial Elections" ወቅት የሞንትጎመሪ ካውንቲ መራጮችን የማገልገል እድል ይሰጣቸዋል። ድምጽ ለመስጠት የተመዘገቡ ተማሪዎች ማመልከቻ ማቅረብ ይችላሉ። ድምጽ ለመስጠት ያልተመዘገቡ ተማሪዎች እነዚህን ሶስት ቅጾች ማውረድ፣ መሙላት እና በፖስታ መላክ አለባቸው፡ የሜሪላንድ የመራጮች ምዝገባ፣ የምርጫ ሰራተኛ ማመልከቻ እና የፈቃድ ወረቀት (ከ18 ዓመት እድሜ በታች ለሆኑ ሰራተኞች)።
|
|
|
ለትምህርት ቤቶቻችን ደህንነት ቅድሚያ መስጠት
ባለፈው ሳምንት፣ የሞንትጎሞሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ (MCPS) ቡድኖች የሪቻርድ ሞንትጎመሪ እና የኖርዝውድ ትምህርት ቤቶችን ክለስተር ጎብኝተዋል፣ ዲስትሪክቱ እስከ ዲሰምበር አጋማሽ ድረስ የሠራተኞችን የበፊት ታሪካቸውን ማጣራት፣ የጣት አሻራ መውሰድ፣ እና አዲስ ባጅ የመስጠት ሂደት ለማጠናቀቅ በትክክለኛው መንገድ ላይ መሆኑን አረጋግጠዋል። ከዚህ በታች እስካሁን ድረስ ስለተከናወነው ሂደት ወቅታዊ መረጃ ይገኛል፣ ይህም እንደገና ማጣሪያ ያጠናቀቁ ሠራተኞችን ቁጥር የሚያንፀባርቅ ነው።
ሜትሪክ/Metric |
ቫልዩ/Value |
እስከ ዛሬ እንደገና ማጣራት የተደረገላቸው ጠቅላላ ሠራተኞ ብዛት |
6,612 |
% የተጠናቀቀ የትምህርት ቤት ሠራተኞች |
56% |
# የተጠናቀቀ የትምህርት ቤቶች ብዛት |
145/211 |
|
|
|
ማሳሰቢያ
-
የስራ ቅጥር አውደ ርዕይ፡ የአውቶቡስ ሹፌር ወይም የአውቶቡስ አስተናጋጅ ለመሆን ፍላጎት ያለው ሰው ያውቃሉ? ሐሙስ፣ ኖቨምበር 13 ከጠዋቱ 10:30 a.m.-12:30 p.m. ድረስ ይምጡና ይጎብኙን። አውደ ርዕዩ የሚካሄደው ሮክቪል በሚገኘው የመጓጓዣ አገልግሎት ዲቪዥን (DOTS) መሥሪያ ቤት ነው።
አድራሻ፦ Division of Transportation Services (DOTS), 16651 Crabbs Branch Way in Rockville ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፦ 240-740-6080 ይደውሉ።
-
የትምህርት ማበልጸጊያ እድሎች፦ የተፋጠነ እና የበለፀገ ትምህርት ቢሮ ቤተሰቦች ከመዋእለ ህጻናት እስከ 12ኛ ክፍል ድረስ (K-12ኛ ክፍል) ላሉ ተማሪዎች የትምህርት ማበልጸጊያ እንዲማሩ የሚያግዙ ሁለት ተጨማሪ የበይነመረብ ዌቢናሮች አሉት።
-
የመታሰቢያ እና የእርቅ ወር፦ ተማሪዎች ሰኞ፣ ኖቨምበር 24 ከቀኑ 7:30-8:30 p.m. ስለ ሞንትጎመሪ ካውንቲ " Montgomery County’s Urban Renewal Programs on African American Communities" በሚደረገው የዌቢናር ውይይት ላይ በመሳተፍ አንድ SSL ሰዓት ማግኘት ይችላሉ። ተጨማሪ ግንዛቤ ያግኙ እና ይመዝገቡ።
-
"Financial Aid Workshops"/የፋይናንስ እርዳታ አውደ ጥናቶች፦ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች ለኮሌጅ ክፍያቸው የሚያግዙ አማራጮችን ለማወቅ እንዲችሉ እና ቤተሰቦች እነዚህን አውደ ጥናቶች እንዲከታተሉ አዘጋጅተዋል። ወላጆች በማንኛውም ትምህርት ቤት በመገኘት በፋይናንስ አውደ ጥናት ላይ መሳተፍ ይችላሉ። ተጨማሪ ግንዛቤ ያግኙ.
|
|
|
"Montgomery County Thanksgiving Parade" የሞንትጎመሪ ካውንቲ የምስጋና በዓል የሰልፍ ትርኢት በጎ ፈቃደኞችን እየፈለገ ነው!
የሠልፍ ትእይንትን የማይወድ ማነው?
አመታዊው የሞንትጎመሪ ካውንቲ የምስጋና በዓል የሰልፍ ትርኢት "Montgomery County Thanksgiving Parade" ቅዳሜ፣ ኖቨምበር 22 ከጠዋቱ 10 a.m. ጀምሮ ይካሄዳል። ሰልፉ የማርሽ ባንዶችን፣ የዳንስ ትርኢቶችን፣ በእሳት አደጋ መኪናዎች የሚቀርቡ እና አዝናኝ ተንሳፋፊ ባሉኖችን ያካትታል። መስመሩ የሚጀምረው ከ Ellsworth Drive እና Fenton Street በ downtown Silver Spring ሲሆን፣ በ Georgia Avenue ወደ ደቡብ አቅጣጫ ይሄድና Silver Spring Avenue ላይ ይቆማል። ዝናብ ቢኖርም ባይኖርም የሰልፍ ትርኢቱ ይካሄዳል።
ሰልፉ የሚካሄደው የተለየ አይነት አለባበስ ኖሯቸው፣ እንደ ቡድን መሪዎች ሆነው የሚያገለግሉ፣ እና ባሉኖችን ተቆጣጣሪዎች የሚሆኑ በጎ ፈቃደኞችን ይፈልጋል። የበጎ ፈቃደኞች የአገልግሎት ሰአት ከጠዋቱ 7:30 a.m. እስከ 1:30 p.m. ነው። (በጎ ፈቃደኞች ሙሉውን ስድስት ሰዓት መገኘት አለባቸው)። ከ13 ዓመት በላይ የሆናቸው ተማሪዎች ለተሳትፏቸው የተማሪ አገልግሎት ትምህርት (SSL) ሰዓት ማግኘት ይችላሉ። ለሰልፍ ትርኢት በጎ ፈቃደኛነት እዚህ ይመዝገቡ።
|
|
|
በዜና ገጾቻችን ላይ የቅርብ ጊዜ ዘገባዎችን ይመልከቱ
-
ብሔራዊ የትምህርት ቤቶች የስነ-ልቦና አገልግሎት ሳምንት፡ ኖቬምበር 3-7 ባለው ሳምንት፣ MCPS የተማሪዎችን ትምህርት፣ ጤና፣ እና ደህንነት የሚደግፉ የትምህርት ቤት የስነ-ልቦና ባለሙያዎችን እውቅና ሰጥቷል። ስማቸው የተዘረዘሩት አራቱ ባለሙያዎች ንባብ፣ ጥያቄዎችን እና መልሶችን አስተናግደዋል፦ Dr. Trellis Jones, Dr. Sharon Huang, Nicole Rodriguez-Caraballo, Harriet Kuhn እና Dr. Kenneth Reimer.
-
ወታደራዊ አገልግሎት የሚሰጡ ቤተሰቦችን ማክበር፦ ግሌን ሄቨን አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለሁለተኛው አመታዊ "Purple Star Breakfast Bunch" ወታደራዊ አገልግሎት የሚሰጡ ዜጎች ጋር ግንኙነት ያላቸውን ቤተሰቦች አስተናግዷል። በዝግጅቱ ወቅት ተማሪዎች፣ ቤተሰቦች እና ሰራተኞች አንድ ላይ በመሆን ወታደራዊ አገልግሎትን ማክበር፣ ግንኙነቶችን ማጠናከር፣ እና አብረው ምግብ እንዲበሉ ተስተናግደዋል።
-
ከፍ፣ ከፍ፣ እና ወደላይ ከፍ፦ ሮቤርቶ ክለመንቴ የመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት “whole child” ለመደገፍ እና በትምህርት ቀን የበለጠ ማህበራዊ-ስሜታዊ ጊዜን ለመገንባት፣እና ተማሪዎች ስሜታቸው ወደላይ ከፍ እንዲል ይሠራል።
|
|
ከእኛ ጋር ያለዎትን ግንኙነት ይቀጥሉ
|
|
|
|
በመካሄድ ላይ ያሉ ክፍት ምዝገባዎች
|
MCPS የበለጠ መረጃ ያግኙ
|
|
|
በዚህ አድራሻ ኢሜል ያድርጉልን፦ ASKMCPS@mcpsmd.org
|
የሞንትጎመሪ ካውንቲ ፐብሊክ ስኩልስ
|
|
©1995–2025 Montgomery County Public Schools
|
|